"ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
+++++++++++++
የከተማችንን እድሳት ለማፋጠንና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል።
በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል።
የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል።
የእውነተኛ ልማት ማዕከል ማህበረሰቡ ላይ መሆን አለበት! ይህ ፕሮጀክት ከላቀ የስፖርት አገልግሎት ባለፈ፣ በልማቱ ምክንያት ለተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ አቅም የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆችን እንዲሁም 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ ይዟል።
በአንዴ 300 መኪናዎችን የሚይዝ ባለ ሁለት ወለል የምድር ቤት መኪና ማቆሚያ ያለውና ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር የተሳሰረው ይህ ፓርክ፤ ንፁህና ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የጀመርነውን ቁርጠኝነት ጉልህ ማሳያ ነው።
ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን!
#አዲስ_ስፖርት_ፓርክ #ታላቋ_ኢትዮጵያ #የጀግኖች_ታሪክ #የከተማ_እድሳት #በተግባር

❤1😁1
"በሀገር ውስጥ መድኃኒትን የማምረት አቅም ወደ 44 በመቶ አድጓል”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በሀገር ውስጥ መድኃኒትን የማምረት አቅም ወደ 44 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባውን እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀውን የምርምር ማዕከል መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ እንደ መኪና እና አውሮፕላን ያሉ ቴክኖሎጂዎች ባይኖሩ ሀገር ልትቀጥል ትችላላች።
ምግብ፣ ልብስ እና መድኃኒት ግን የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች በመሆናቸው በእነዚህ ዘርፎች ራስን አለመቻል የሀገርን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከት አስገንዝበዋል።
የኮሮና ወረርሽኝ በወቅቱ ያስከተለው ተግዳሮት እና መድኃኒት ከውጭ ለማግኘት የነበረው አዳጋች ሁኔታ፣ ኢትዮጵያ በእነዚህ ሦስት ቁልፍ ዘርፎች ራሷን ለመቻል ቁርጠኛ አቋም እንድትይዝ ትልቅ መነሳሳት መፍጠሩን አስታውቀዋል።
በባለፉት ጥቂት ዓመታት በመድኃኒት ምርት ዘርፍ ለውጥ መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሀገር ውስጥ የሚመረተው መድኃኒት ከ8 በመቶ ወደ 44 በመቶ ማደጉን ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚመረቁ አዳዲስ ፋብሪካዎች ደግሞ ይህንን አቅም ከ50 እስከ 55 በመቶ እንደሚያደርሱት ጠቁመዋል።
አዲሱ የምርምር ማዕከል በላቀ የላብራቶሪ ምርምር የኢትዮጵያን የመድኃኒትና የክትባት ማምረት አቅም እንደሚያሳድገው እና ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በዘርፉ ያቀደችውን ራስን የመቻል ግብ ለማሳካት ትልቅ መሠረት እንደሚሆን አመላክተዋል።
የምርምር ማዕከሉ ያለው የቴክኖሎጂ ብቃት፣ የሰው ኃይል መነሳሳት እና የተቋሙ ውበት ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸው፣ ምርምሮች ወደ ገበያ ወጥተው የዜጎችን ሕይወት እንዲታደጉ አደራ ብለዋል።
በሄለን ወንድምነው
++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ጤና #ራስን_መቻል #ሉዓላዊነት

❤2
"በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በአዲስ ስፖርት ፓርክ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#የጀግኖቻችን_ታሪክ #OlympicLegacy #የኢትዮጵያ_ጀግኖች #ChampionsPark #አዲስ_ስፖርት_ፓርክ
#NextGenerationAthletes

❤8