”አቶ ስብሃትና ጓደኞቻቸው በመረጡት የተሳሳተ መንገድ ራሳቸውን ለውርደት ዳርገዋል‘
– አቶ ቀጄላ መርዳሳ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ለበርካታ ዓመታት በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ግዙፍ ተጽዕኖ የነበራቸው የህውሓት ቡድን አባላት በመረጡት የተሳሳተ መንገድ ራሳቸውን ለውርደት መዳረጋቸውን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ አስታወቁ።
አቶ ቀጄላ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የህውሓት ቡድን በህዝብ አመጽ መቀሌ ከገባ ጀምሮ ሰላማዊ አማራጮችን ከመጠቀም ይልቅ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ትርክቶችን በማሰራጨትና ሁከቶችን በመቀስቀስ ሀገሪቱን ሲያተራምስ ቆይቷል።
ቡድኑ በሰላማዊ ፖለቲካ ለማራመድ ወይም ተግባብቶ ሀገሪቱን ለማሻገር ፍላጎት ስላልነበረው በየጊዜው ትንኮሳዎችን ሲያደርግ ቆይቶ በመጨረሻም በመከላከያ ሠራዊት ላይ በፈጸመው አሳፋሪ ተግባር መንግሥት ወደ ህግ ማስከበር ተግባር መግባቱን የጠቆሙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው፣ የመከላከያ ኃይሉ በህዝብ በመታገዝ ባደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ በሁለንተናዊ መልኩ ተጽዕኖ የነበረው ኃይል ላይመለስ መሰናበቱን አስታውቀዋል።
አንዳንዶች ህውሓት የገንዘብ አቅምና የፖለቲካ የበላይነት አለው ብለው በድሮ ጉልበቱ ፤በድሮ ኃይሉ በመተማመን ጦርነቱን በበላይነት አሸንፎ ሀገሪቱን ዳግም ይቆጣጠራል የሚል እምነት ነበራቸው ያሉት አቶ ቀጄላ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተደረገው ቅንጅታዊ ሥራ ቡድኑ ተሸንፎ አባላቱም ባልተጠበቀ መልኩ እጃቸውን ለመንግሥት ለመስጠት መገደዳቸውን ጠቁመዋል።
በቡድኑ ላይ የደረሰው ውርደት ኃይልና ጉልበትን ተማምኖ ሀገርን ለዘላለም መግዛት እንደማይቻል ተጨባጭ ማስተማሪያ እንደሚሆኑ ያመለከቱት አቶ ቀጄላ ፣ ምንም ኃያል ነን ቢሉ በአንድ ታሪካዊ ወቅት ላይ ሁሉም ነገር እንደሚያበቃና ሁሉም ነገር እንደሚንኮታኮት የሚያሳይ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39615

www.press.et
”አቶ ስብሃትና ጓደኞቻቸው በመረጡት የተሳሳተ መንገድ ራሳቸውን ለውርደት ዳርገዋል‘ – አቶ ቀጄላ መርዳሳ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
የዘይት ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት ከ100 ብር በላይ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የዘይት ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በላይ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተዘዋውረን ያነጋገርናቸው ቸርቻሪ ባለሱቆች አስታወቁ።
የጋዜጣው ሪፖርተር ያነጋገራቸው አራት ኪሎ አካባቢ የችርቻሮ ሱቅ ባለቤት የሆኑት አቶ ኑረዲን ጸሃ ፣ ዘይት ምክንያቱን ሳናውቀው ከነበረበት 330 ብር ወደ 450 ብር ከፍ ብሏል። የዘይት ጭማሪው ከማከፋፈያው በመሆኑ አስደንጋጭ ነው። አምስት ሊትር ዘይትን የምናመጣው ከ390 ብር እስከ 420 ብር ሲሆን የአውራጅና የታክሲ ክፍያን ከፍለን 500 ብር ካልሸጥን በስተቀር ትርፍ አይኖረውም።
አሁን የተስተዋለው የዘይቱ ዋጋ ከበርካታ ዜጎች የኑሮ ደረጃ ጋር የሚመጣጠን አይደለም ያሉት አቶ ኑረዲን ፣ ሸማቹ በተከሰተው ነገር ተደናግሮ የመግዛት ፍላጎት የለውም። እኛም እንደ ነጋዴ ሸጠን ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ አልችልንም ብለዋል ። መንግስት ለችግሩ በአፋጣኝ መፍትሄ ሊያበጅ እንደሚገባም አመልክተዋል።
ሌላኛው ያነጋገራቸው የችርቻሮ ሱቅ ባለቤት አቶ ሁነኛው በየነ በበኩላቸው ፤ የዘይት ውድነት በአልን ተከትሎ የመጣና በዓል ሲያልፍ እንደሚስተካከል ተስፋ አድርገን ነበር። የጅምላ አከፋፋይ በአምስት ሊትር ዘይት ላይ ከ90 እስከ 120 ብር ድረስ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ከአራት መቶ ብር በላይ መጥቶ ሱቅ እስኪደርስ ድረስ የተለያዩ ወጪዎች ተጨምረውበት ስንት መሸጥ እንዳለበት ግራ ተጋብተናል ያሉት አቶ ሁነኛው፣ ቀደም ሲል እንደነበረው አሁን ከዋጋው መወደድ ጋር ተያይዞ ገዥም የለም ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39613

ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ድሮን ማብረር እንደማይችሉ ተገለጸ
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታዉቋል።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫእንዳመለከተው ሁሉም የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ከከተራ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በድምቀት የሚከበረዉ የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርገዋል።
ከፀጥታ አጠባበቅ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከልም የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ከተገቢው አካል ፈቃድ ሳይኖራቸው ድሮኖችንም እንዳያበሩ ወይንም እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ድሮንን ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማዋልም ህጋዊ ስልጣን ካለዉ አካል ፈቃድ ማውጣት እንደሚቻል ተገልጿል።
በዚህ አጋጣሚ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆን ምኞቱን እየገለፀ ሕብረተሰቡ ከበዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ ሰላምን የሚያደፈርሱ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለጸጥታ አካላት የተለመደ ጥቆማውን እንዲሰጥ ጠይቋል።

በዓድዋ ከተማ በጁንታው ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ዛሬ ጀመረ
👉 በጁንታው ጉዳት የደረሰባቸው መሰረተ ልማቶች ጥገና በፍጥነት እየተከናወነ ነው
************************
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በጁንታው አባላት ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ተደርጎለት በዛሬው እለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።
በትግራይ ክልል በጁንታው አማካኝነት ጉዳት የደረሰባቸውን የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች በፍጥነት ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ በፌዴራል መንግስት እየተከናወነ መሆኑንም የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ ለኢትዮፕያ ፕሬስ ድርጅት አስታውቀዋል።
እንደ ዶክተር አብረሃም ገለጻ፤ የፌዴራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት በጁንታው አማካኝነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ በዛሬው እለ የአደዋ ከተማ የመብራት አገልገሎት አግኝታለች።
አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት አግኝተዋል ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ የተቀሩት ማለትም አክሱም፣ሽሬና ሑመራ በአጭር ግዜ የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት የህግ ማስከበር ዘመቻ ጁንታው በሽንፈት ከከተሞች ለቆ ሲወጣ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፤ በዋናነትም የከፍተኛ የአሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በጣጥሷል፤ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን አቋርጧል፤ የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን አውድሟል፤ በተለያዩ ከተሞች መንገዶችን ቆፋፍሯል፤ ድልድይ አፍርሷል፤ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አውድሟል፤ ዘርፏል፤ የህክምና አምቡላንሶችን ዘርፎ ወስዷል።
በተጨማሪም የህግ ታራሚዎችን በመፍታት በመቀሌ ከተማ ለቆ ለወንጀል አሰማርቷቸዋል።

የዋልድባው መነኩሴ ተሸለሙ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ከለውጡ በፊት የዋልድባ ገዳም በስኳር ልማት ሰበብ ፈተና ላይ በወደቀበትና ለችግር በተዳረገበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉት አባ ገብረየሱስ ኪዳነማርያ ሽልማትና እውቅና ተሰጣቸው።
የማዕከላዊ ጎንደር ሀገር ስብከት፤ አባ ገብረየሱስ ለከፈሉት መስዋዕትነት በወርቅ የተሰራ ማህተም፣ ምስክር ወረቀት አበርክቶላቸውል፤ ካባ አልብሷቸዋል።
የዋልድባን ገዳም ሲነካ ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉ መሆናቸው ተጋድሎውም ፍሬ ያፈራ መሆኑ በጎንደር ባህረ ጥምቀት ላይ በነበረው ሥነ ስርአት ላይ ተገልጿል።
አባ ገብረየሱስ በገዳሙ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ብሎም ህዝቡ እንዲረጋጋ ከፍተኛ መስዕዋት መክፈላቸው በመድረኩ ላይ ተወስቷል።

የጎንደር የጥምቀት በአል አከባበር ደማቅና ውብ እንደነበር ቱሪስቶች ገለፁ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጎንደር የጥምቀትና የከተራ በአል የተከበረበት መንገድ ደማቅና ውበትን የተላበሰ ነበር ሲሉ በአሉን የታደሙ ቱሪስቶች ገለጹ።
በአሉ ምቹና ጎብኚዎችን የመሳብ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያነጋገራቸው የውጭ አገር ጎብኝዎች ተናግረዋል።
ከአሜሪካ፣ ፖላንድና ፈረንሳይ የመጡ ቱሪስቶች እንደገለፁት፤ በከተራ እና በጥምቀት በዓል የነበራቸው ቆይታ አስደሳችና የማይረሳ ሆኖ አልፏል።
የበአል አከባበሩ በተለይም ደግሞ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ የቆየ ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው መሆኑ ከሌሎች አገራት የተለየ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ በበኩላቸው ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለፁት፤ በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኚዎችም በበዓሉ ወቅት መንገላታት እንዲቀንስ ከወጣቶች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ ሆቴል ባለቤቶች፣ ፀጥታ አካላት እና የከተማው አስተዳደር ጋር በተከናወነ ቅንጅታዊ ሥራ ስኬታማ በዓል መሆን ችሏል ብለዋል።

ኤጀንሲው ለሽሬ ቅርንጫፍ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሕይወት አድን መድኃኒቶችን እያጓጓዘ ነው
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለሽሬ ቅርንጫፍ ለሁለተኛ ዙር የሚሆን ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሕይወት አድን መድኃኒቶች እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ።
ከ3 ሚሊዮን 96 ሺህ 657 ብር ዋጋ ያላቸውን ሕይወት አድን መድኃኒቶች ከጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እያጓጓዘ መሆኑ የመ/ሕ/መ/ክምችትና መጋዘን አያያዝ እስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ገዳምነሽ አስፋው ገልጸዋል፡፡
ለቅርንጫፉ የተላኩት በዋናነት ለእናቶችና ህፃናት የሚዉሉ ህይወት አድን መድሀኒቶችና ህክምና ግብዓቶች እንድሁም ለፀረ ወባና ሳንባ ነቀርሳን ለማከም የሚረዱ መድሀኒቶች ናቸው ፡፡
መድኃኒቶች እና ሕክምና ግብዓቶቹም ሽሬ ቅርንጫፍ ሲደርሱ ለጤና ተቋማት እንደሚከፋፈሉ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዶክተር አብረሃም በላይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብረሃም በላይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቅራቢነት በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
ከዶክተር አብረሀም በተጨማሪ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ፣ ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ እና አቶ ጣሂር መሀመድ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባል ሆነው ሲሾሙ አቶ ሰይፈ ደርቤ ደግሞ የቦርዱ አባልና የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሹመዋል።
ተሿሚዎቹ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በ1935 ዓ.ም የተቋቋመ የዜና አገልግሎት የሚሰጥ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን መሆኑ ይታወቃል።

ዘመን መጽሔት ገበያ ላይ ናት!
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የጥር ወር የዘመን መጽሔት ጥልቅ ትንታኔዎችንና በሳል ጽሁፎችን ይዛ ገበያ ላይ ውላላች
ዘመን በዚህ ወር እትሟ -
👉በዐብይ ርዕሷ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ (ድል ቁርሱ) እንግዳ ናቸው፤
ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ “ዋነኛው የጁንታ ሀይል ላይ ተረባርበን አከርካሪው ስለተሰበረ ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ሀይሎች በሙሉ ይከሰማሉ” ይላሉ፤ እንዴት? ዘመን መጽሔት መልስ አላት፤
👉ዘመን በፖለቲካዊ ትኩሳት አምዷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ አባንግ ሜቶን ይዛ ቀርባለች፤ አቶ ኦባንግ “ስብዕናን እና ሀገርን የመውደድ አብዮት ያሰፈልጋል ሲሉ” ይናገራሉ
👉 በተመሳሳይ “ኢትዮጵያ የግፍና የጭካኔ ወንጀሎች መከላከያና መቀነሻ ስልት ነድፏ ስራ ላይ ማዋል አለባት” የሚሉት ደግሞ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ናቸው፤ እርሳቸውም በኢትዮጵያ ስላለው አጠቃላይ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ዙሪያ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን አካፍለዋል፤
👉ዘመን መጽሔት በማህበራዊ አምዷ የጡት ካንሰርን ምንነት መከላከያ መንገዶችና ተያያዥ ጉዳዮች ታስነብበናለች፤
👉 በተጨማሪም ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴን አነጋግራ፤ “ማህበራዊ እሴቶቻችን ከየት ወደየት” የሚል ጽሁፍ አቅርባለች፤
👉ዘመን በፈለግ አምዷ ደግሞ ስፖርተኛው ሐኪም፤ ሐኪሙ ስፖርተኛ በሚል ርዕስ የዶክተር ይሄይስ ፈለቀን የህይወት ተሞክሮና የስራ ታሪክ ታስነብባለች፤
👉ዘመን በዓለም አቀፍ አምዷም የሚዋዥቀው የሱዳን የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ስትል ወቅታዊውን የሱዳን አቋም ተንትና ይዛለች፤
እነዚህንና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮችን ይዛ ለንባብ የበቃችውን ዘመን መጽሄት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ኪዮስኮች ያጋኟታል፤
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

በትግራይ ክልል በሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በመንግስት የተወሰደውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ለሕዝቡ መረጃ ለማቅረብ ወደግንባር ተሰማርተው ረፍት አልባ ተግባራትን መፈጸም ለቻሉ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ፡
ወደ ግንባር የተላኩት የሚዲያ ባለሙያዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ በመመልከትና በመዘገብ የሐሰት መረጃዎችን በማጋለጥ ታላቅ ስራ መስራታቸውና ሕብረተሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይደናገር ማድረግ መቻላቸው ተገልጿል።
ከዚህ አንጻር የመገናኛ ብዙኀኑ ሚና ሕዝቡን ያረጋጋና የሰራዊቱን አንድነት ያጠናከረ ነው ተብሏል፡፡
ቦታው ላይ በአካል በመገኘት ዘመቻው ጽንፈኛውን ቡድን ብቻ እንደሚመለከት የመገናኛ ብዙኋን መዘገብ ችለዋል፡፡
በእውቅና መረሃ ግብሩ የተገኙት የኮማንድ ፖስቱ የመረጃ ፍሰት ሴክሬተሪያት ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የመገናኛ ብዙሃን የተናበበ አሰራር ፈተናዎችን ለማለፍ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው በመድረኩ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደሩ እንዳሉት በብዛት የሐሰት መረጃ በሚሰራጭበት ዘመን ላይ በመሆናችን የመገናኛ ብዙሃን እንዲህ አይነቱን ተግባር መፈጸማቸው ችግሩን ይቀርፋል ብለዋል፡፡
ቀጣዩ ስራም የትግራይን ሕዝብ መታደግ እንደሆነ ጠቅሰው በተለይም መገናኛ ብዙሃን ለዚህ ሃለፊነት በትጋትና በቁርጠኝነት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእውቅና መረሃ ግብሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ጥሪ የተደረገላቸው የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራን ተገኝተዋል፡፡

ለትግራይ ክልል እየተደረገ ካለው አጠቃላይ ድጋፍ የፌዴራል መንግሥት ድርሻ 65 ከመቶ እንደሚደርስ ተገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ለትግራይ ክልል እየተደረገ ካለው አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ የፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እስከ 65 በመቶውን እንደሚሸፍን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
በትግራይ ክልል አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎችን መመገብ የሚያችል 311 ሺህ 526 ኩንታል የእርዳታ እህል መዘጋጀቱን ጠቆመ።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከሚሽነር ምትኩ ካሳ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የፌዴራል መንግሥትም የድጋፍ አሰጣጡን በበላይነት እየመራው ነው።
በመቀሌ ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ በመክፈትም ለትግራይ ክልል የሚውሉ 92 የምግብ ማሰራጫ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችም በድጋፉ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ከአጠቃላይ ድጋፉ ውስጥ የፌዴራል መንግሥት እስከ 65 በመቶውን እንደሚሸፍን፣ ቀሪውን ደግሞ በተለያዩ አካላት በመሸፈን ላይ መሆኑን አመልክተው፣ በትግራይ ክልል ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎችን መመገብ የሚያስችል 311 ሺህ 526 ኩንታል የእርዳታ እህል እና የተለያዩ ቁሳቁሶች መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39926

"ዘመቻው ቢያልቅም ዘመቻው የፈጠራቸው ዕድሎችም፤ ዘመቻው ያስከተላቸው ጫናዎችም አላለቁም"
- ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
******************
(ኢ.ፕ. ድ)
በትግራይ ክልል የተከናወነው ህግን የማስከበር ዘመቻው ቢያልቅም፤ የፈጠራቸው ዕድሎችም ሆኑ ያስከተላቸው ጫናዎች እንዳላለቁ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተናገሩ፡፡
ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይህንን ያሉት በህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ግዳጃቸውን ለመወጣት የሚዲያውን ሥራ ለመስራት የተላኩ ልዑካን ትላንት እውቅና በተሰጠበት መድረክ ላይ ነው፡፡
ዘመቻው በአንድ በኩል መድኃኒትነት ያለውና አገሪቱን ከብዙ ቀውስ ያዳነ መሆኑን ገልጸው፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተካሄደው ጦርነት ስለሆነ ያስከተለው ጫናም እንዳለ በምሳሌ አስደግፈው ተናግረዋል፡፡
“አንድ ሰው ሆስፒታል ገብቶ ለጤናው ሲባል ኦፕሬሽን ቢደረግ፤ በአንድ በኩል የሚያመው ነገር ስለወጣለት ይሄ ሰውዬ ድኗል ደስ ይለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኦፕሬሽን ሲደረግ የተቀደደው ሆዱ ላይ ደግሞ የሚቀር ነገር አለ፡፡ በዚህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ ያመዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሰው 'ምነው እዛ ውስጥ ገብቼ ኦፕሬሽን ባልተደረግኩ' አይልም፡፡
"ተስፋ የሚያደርገው መዳኑን ስለሆነ የተወሰነ ጊዜ ህመሙን ይሸከመዋል፡፡ ይታገሰዋልም፡፡ ሰውም ደግሞ 'ኧረ እንኳን ተሻለህ ይህንን ቁስልህን የውሻ ቁስል ያድርግልህ' ይለዋል እንጂ አፕሬሽን መሆን አልነበረብህም አይለውም፡፡ አሁንም በህግ ማስከበር ዘምቻው የተከናወነው ነገር እንደዛው ነው፡፡” ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ልክ ኦፕሬሽን እንደተደረገው ሰውዬ ዘመቻው ያስከተለው ጫና እንደለ ጠቁመው፤ ችግሩን በመቀነስ ጥቅሙን በመጨመር የኢትዮጵያን ህብረ ብሄራዊ አንድነት በማጽናት መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የሚዲያው ሚና ሰፊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
"በዘመቻው ላይ እንዳሳየነው ህብረት፣ አንድነትና መተጋገዝ ለሌሎች ነገሮችም እንዲሁ ኢትዮጵያን ወደምንፈልጋትና ህዝቡ ወደሚጠይቀው ደረጃ እናደርሳለን" ብለዋል፡፡

በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ66 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ
- ከዳያሰፖራው በስድስት ወራት ብቻ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ከ66 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ።
በውጭ አገራት ከሚኖሩ ዳያሰፖራዎች ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል
የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ሃይሉ አብረሃም ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት 66 ሚሊዮን 933 ሺህ 969 ብር ገቢ ተገኝቷል።
እንደ አቶ ሃይሉ ገለጻ፤ በተመሳሳይ ባለፉት ስድስት ወራት በውጭ አገር ከሚገኙ ዳያስፖራዎች የቦንድ ሽያጭና ስጦታ 41 ሚሊዮን 595 ሺህ 885 ብር መሰብሰብ ተችሏል።
በአገር ውስጥ የቦንድ ሽያጭ ደግሞ 901 ሚሊዮን 915 ሺህ 738 ብር መሰብሰቡን የገለጹት አቶ ሃይሉ፤ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስጦታ አካውንተ ደግሞ 10 ሚሊዮን 450 ሺህ 690 ብረ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት ለግድቡ አንድ ቢሊዮን 21 ሚሊዮን 514 ኚህ 33 ብረ ገቢ መገኘቱን ነው አቶ ሀይሉ ያስታወቁት።
በ8100 አጭር የጽሁፍ መልጽክት ከተጀመረ ጊዜ አንሰቶ በሶስት ዙር 195 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ታውቋል።
በሃይማኖት ከበደ

“ሱዳን ምንጊዜም የሚቆጫትን ስህተት ሰርታለች”
-ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በአ.አ.ዩ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሀይል በመዝለቅ ምንጊዜም ቢሆን የሚቆጫትን ስህተት መስራቷን በአ.አ.ዩ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ አስታወቁ። እየሄደችበት ያለው መንገድ ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ እና ዘላቂ ጥቅሟን የሚያሳጣት እንደሆነም አመለከቱ።
ፕሮፌሰር ያእቆብ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ሱዳን በመንግስትነት ሳትቋቋም በፊት በኢትዮጵያ እና በቅኝ ገዥዎች መካከል የተጀመረ ነው።
ችግሩን ለመፍታት የጋራ ኮሚሽን ተቋቁሞ የተለያዩ ልዑካን እና ኤክስፐርቶች ሐሳብ እየተለዋወጡ እንደሆነ አመልክተው፣ ውይይቱ ድንበሩ የት ይሁን የሚለውን ሳይቋጩ ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ወስዳ የእኔ ነው ማለት ተቀባይነት የለውም ብለዋል። የሰራችው ስህተት ምንግዜም ቢሆን የሚቆጫት እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
ከብዙ አቅጣጫ ሲታይ እና ሲመዘን ሱዳን ዛሬ የድንበር ጉዳይ የምታነሳበት ወቅት እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕሮፌሰሩ፤ የድንበር ጉዳይ ቢነሳ እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት አለኝ ብላ በጉልበት ለመውሰድ የምትንቀሳቀስበትም ጊዜ አይደለም ብለዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=40070

“ሱዳን ምንጊዜም የሚቆጫትን ስህተት ሰርታለች”ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በአ.አ.ዩ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ሉዓላዊነትን ያገናዘበ ዲፕሎማሲን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ከሱዳን ጋር የተጠፈረውን የድንበር ውዝግብ እልባት ለማበጀት መንግሥት የአገርን ሉዓላዊነትንና ጥቅምን ከግምት ውስጥ ባገናዘበ መልኩ የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የፓርቲ አመራሮች አስታወቁ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለፁት፤ ሱዳን በአሁኑ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የመከላከያ ኃይሏን ከማስጠጋቷ በላይ በርካታ የኢትዮጵያ ግዛቶችን የራሴ ግዛት ነው በሚል ተቆጣጥራለች፡፡
ከዚህም በተጨማረ ንብረት የመዝረፍና ዜጎችን የማፈናቀል ተግባር መፈፀሟን የጠቆሙት ረዳት ፕሮፌሰር፣ ይህም ሁለቱ አገራት ላለፉት 100 ዓመታት ሲገለገሉበት የነበረውን ስምምነት የጣሰ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ሱዳን በወታደራዊ እና ሲቪል መንግሥት መካከል የተቃረኑ ሃሳቦች ይዛ እየተናጠች መሆኗን ጠቁመው፣ የወታደር ክንፉ ውስጣዊ ችግሮችን ወደ ውጭ በማድረግና ትኩረት ለማስቀየስ ብሎም በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሥልጣን ሽኩቻ ለማደላደል ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነው አካባቢ ድንበር ጥሶ መግባቱንና በድንበር አካባቢ ጦር ማስፈሩን አስታውቀዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=40067

የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ሉዓላዊነትን ያገናዘበ ዲፕሎማሲን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
‹‹ህወሓት ከፖለቲካው መድረክ እንዲሰረዝ መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው›› አቶ ቀጄላ መርዳሳ የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ህወሓት ከፖለቲካው መድረክ እንዲሰረዝ መደረጉ ከሕግም ሆነ ከፖለቲካ አንጻር ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አስታወቀ፡፡
የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ህወሓት ቀደም ሲል ጀምሮ ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ጦርነትና ግጭቶችን መሠረት ያደረገ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ 1162/2011 ላይ በግልጽ እንደሰፈረው አንድ የፖለቲካ ድርጅት አላማውን በትጥቅ ትግል ለማሳካት የሚሞክር ከሆነ በፖለቲካ ፓርቲነት ሊመዘገብ አይችልም ከተመዘገበም እንደሚሰረዝ በግልጽ ማስቀመጡን ጠቁመው፣ ከዚህ አንጻር የቦርዱ ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ህወሓት ማነው የሚለውን ስንመለከት ሕዝብና መንግሥት ላይ ጦርነት ካወጀ ከሁለት ዓመት በላይ የሞላው እና በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊትን ከኋላው በመውጋት አሳፋሪ ድርጊት የፈጸመ ድርጅት ነው ብለዋል።
የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለጹት፣ የህወሓት ቡድን በሕዝብ አመጽ መቀሌ ከገባ ጀምሮ ሰላማዊ አማራጮችን ከመጠቀም ይልቅ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ትርክቶችን በማሰራጨትና ሁከቶችን በመቀስቀስ ሀገሪቱን ሲያተራምስ ቆይቷል፡፡ https://www.press.et/Ama/?p=40065

‹‹ህወሓት ከፖለቲካው መድረክ እንዲሰረዝ መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው›› አቶ ቀጄላ መርዳሳ የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት