በሳውዲው ባለሃብት ሼህ ሀምዛ የተመራ ልዑክ ቡድን ለይፈዊ የስራ ጉብኝት ጅግጅጋ ገቡ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በሳውዲው ባለሃብት ሼህ ሀምዛ የተመራ ልዑክ ቡድን ለይፈዊ የስራ ጉብኝት ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በገራድ ዊል ዋል አየር ማረፊያ በመገኘት ለባለሀብቶቹ አቀባበል አድርገዋል።
የነዳጅ ካምፓኒ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሼህ ሀምዛ አብዲአዚዝ አል ሱኬሪያ ከክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ጋር በክልሉ ስላለው ምቹ ኢንቨስትመንት ሁኔታ መክረዋል፡፡
ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሉኡካን ቡድኑ በክልሉ ለሚያከናውናቸው የኢንቨስትመንት ስራዎች የክልሉ ህዝብና መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም አረጋግጠዋል።
ባለሀብቱ ወደ ክልሉ የመጡበት ዋነኛ አላማ በክልሉ የኢንቨስትመንት መስክ ተሳትፎ ለማድረግ ሲሆን በቤቶች ግንባታ፣ በፀሀይ የሚሰራ የሶላር መገጣጠሚያ፣ በመኪና መገጣጠሚያ ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ነው፡፡
በክልሉ በሪል እስቴት መስክ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የባለሃብቱ ድርሻ የጎላ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የመገጣጠሚያ ካምፓኒዎቹ መገንባትም በኢኮኖሚው ረገድ ያለው ሚና የጎላ እንደሆነም ከክልሉ መገናኛ ቡዙሃን አጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሰበር ዜና ‼️
የጁንታው ከፍተኛ አመራር የነበሩት ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሀይ አስመላሽ ወልደሥላሴ መደምሰሳቸው ተገለጸ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመካለከያ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈጸም ጥቃት እንዲሰነዘር ያደረጉ ቁልፍ የጁንታው አመራር የነበሩት ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሀይ፣ አስመላሽ ወልደሥላሴ እና ኮሮኔል ኪሮስ ሀጎሥ መደምሰሳቸው ተገለጸ።
የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ ተደብቀው የነበሩት አነዚህ የጁንታ አመራሮች ከእነጠባቂዎቻቸው እና ከወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር ተደምስሰዋል።
በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች
1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዳ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር
አዛዥ የነበረ
5. መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች
ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ
በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ ያስታወቁት።
በራስወርቅ ሙሉጌታ

በ25 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የይስማ ንጉስ ሙዝየም በዛሬው ዕለት ይመረቃል
******************************
(ኢ ፕ ድ)
ለዓድዋ ጦርነት ምክንያት የሆነው የውጫሌ ውል በተፈረመበት ታሪካዊ ቦታ ላይ በ25 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የይስማ ንጉስ ሙዝየም በዛሬው ዕለት የፌዴራልና የክልል የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት እንደሚመረቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በ25 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ሙዚየም ፣ካፌና የመግቢያ በር የኢትዮጵያ ቁጥር ፲፯ (17) አምሳል የተገነባ ነው፡፡
የባህል ማዕከሉ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያሳዩ መረጃዎችን ያካተተ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

"ሱዳን ከጥቅሟ ይልቅ ለግብፅ ፖለቲካዊ ጥምረት ትኩረት ሰጥታለች"
- ዶክተር ይልማ ስለሽ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ሱዳን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደሚጠቅማት ብታውቅም ከግብፅ ጋር በፈጠረችው ጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥምረት ምክንያት ከወዳጅ አገር የማይጠበቅ ተግባር በኢትዮጵያ ላይ እየፈፀመች መሆኑን ዶክተር ይልማ ስለሽ አስታወቁ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህድስና መምህር ዶክተር ይልማ ስለሽ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሱዳን የህዳሴውን ግድብ ጎርፍ በመከላከላከልና ኤሌክትሪክ ኃይል በአነስተኛ ዋጋ እንድታገኝ በማድረግ ረገድ እንደሚጠቅማት ብታውቅም ከግብፅ ጋር በፈጠረችው ፖለቲካዊ ትብብር ምክንያት በድርድሩና በድንበር አካባቢ ከወዳጅ አገር የማይጠበቅ ተግባር እየፈፀመች ነው።
ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሆነ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ እየሠራች ያለችው ሥራ ከወዳጅ አገር የሚጠበቅ አይደለም ያሉት ዶክተር ይልማ በግድቡ ድርድር ላይ ሱዳንና ግብፅ የሚያሳዩት ተለዋዋጭ ባህሪ በአጋጣሚ ሳይሆን በፈጠሩት ፖለቲካዊ ትብብር መሆኑን አመልክተዋል።
ሁለቱም አገራት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገውን ድርድር ሰበብ አድርገው በአባይ ወንዝ የውሃ ድርሻቸውን ለማስጠበቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው፣ በተለይ ሱዳን የህዳሴው ግድብ ከጎርፍ አደጋ እንደሚታደጋትና ኤሌክትሪክ ኃይል በርካሽ ዋጋ እንድታገኝ በማድረግ ረገድ እንደሚጠቅማት ብታውቅም ከግብፅ ጋር በፈጠረችው ጊዜያዊ የፖለቲካ ትብብር ምክንያት ድርድሩ እንዲስተጓጎል እየሠራች ነው ብለዋል።
ድርድሩ የሚካሄደው በግብፅና በሱዳን ጥያቄ መሰረት በታችኛው አገራት መተማመን ለመፍጠር ሲባል እንጂ ኢትዮጵያ ፈልጋው አለመሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ድርድሩን እነሱ ካልፈለጉት ይቀጥል ብላ የምትጠይቀው ምክንያት አይኖርም፤ በህግም የመደራደር ግዴታ የለባትም፣ ግድቡንም ውሃ ስንሞላና ስናስተዳድር ተቀባይነት ባለው ዓለም አቀፍ ህግ መሰረት እንደሆነም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን የታችኛዎቹን የአባይ ተፋሰስ አገራት ለመጉዳት አስባ አታውቅም፤ በጋራ እንልማ ነው የምትለው ያሉት ዶክተር ይልማ ፤ይህን የማይቀበሉ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ኢትዮጵያም በአባይ ውሃ ፍትሐዊ የመልማት መብቷንም አሳልፋ እንደማትሰጥ መታወቅ አለበት ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39434

“የሀገራችን ፖለቲካ ማንም ዘው ብሎ ከሚገባበት አካሄድ መውጣት ይኖርበታል”
-አቶ አቡበከር ያሲን
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር
************************
(ኢ ፕ ድ)
“የሀገራችን ፖለቲካ ማንም ዘው ብሎ ከሚገባበት አካሄድ መውጣት እንደሚኖርበት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር እና የማህበራዊ ሳይንስ መምህር የሆኑት አቶ አቡበከር ያሲን አስታወቁ። አሁን በሃገራችን እየታየ ያለው ምስቅልቅልም ፖለቲካና ፖለቲከኞች ባለመለያየታቸው እንደሆነም አመለከቱ።
አቶ አቡበከር ያሲን በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፣ የአገራችን ፖለቲካ ማንም ሰው ዘው ብሎ ከሚገባበት አካሄድ መውጣት ይኖርበታል።
የአገራችን ፖለቲካ በፖለቲከኞች ቅኝ ግዛት ስር ወድቋል የሚሉት አቶ አቡበከር፤ ፖለቲካ ራሱ ከፖለቲከኞች ነፃ ካልወጣ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አዳጋች እንደሚሆን አመልክተዋል።
ፖለቲካ ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ማበልፀጊያ እየዋለ ነው፣. ይህ በሆነበት ሁኔታም የህዝብን ችግር መረዳትና ለችግሩ መፍትሔ ማምጣም አይቻልም ብለዋል።
እንደ አቶ አቡበከር ገለጻ፣ እንደ ሃገር የፖለቲካን “ሀ - ሁ” የተረዳንበት መንገድ የተሳሳተ ነው። ፖለቲካ ህዝብን የምናገለግልበት፣ የህዝብ ጥቅም የሚከበርበት፣ እንዴት፣ መቼ እና በምን መንገድ እንደምናስተዳድር የምንማርበት የሙያ ዘርፍ ሆኖ እያለ ፖለቲከኞች ከሙያው ስነምግባር ውጪ ፖለቲካን የሀብት ማከማቻ እና የስልጣን ጥም መወጣጫ አድርገውታል።
በሃገራችን እየታየ ያለው ምስቅልቅልም ፖለቲካና ፖለቲከኞች ባለመለያየታቸው የመጣ በመሆኑ ፖለቲካው ከፖለቲከኞች ነፃ ወጥቶ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ ብሎም እንደ ህዝብ ማስተዳደሪያ መሳርያነቱ ማወቅና መረዳት ይገባል ብለዋል።
በአገራችን ያለው ለውጥ በርካታ ለውጦች የታዩበትና እንደ አገርም ብዙ ተስፋን ያጫረ ነው ያሉት አቶ አቡበከር፤ ሆኖም አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ቡድንተኝነት፣ ጎሰኝነት፣ በኔት ወርክ መደራጀት እንደሚታይ ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39450

በኩዌት የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት ኢትዮጵያዊት በምህረት ተለቀቀች
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ከ8 አመታት በፊት በኩዌት አገር በወንጀል ተከሳ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት ሉባባ ኑረዲን የተባለች ኢትዮጵያዊት በምህረት እንዲትፈታ መደረጉን በኪዌት የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ፡፡
ኤምባሲው ላለፉት ዓመታት ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የኩዌት የፍትህ ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት ምህረት እንደተደረገላት ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ሉባባ ኑረዲንን ወደ ሀገር ቤት እንድትመለስ የጉዞ ሂደቱን በማስጨረስ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በሰላም እንድትሳፈር አድርጓል።
ኤምባሲው በኩዌት የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበርን ጨምሮ በሂደቱ ለተባበሩ ሁሉ ምሥጋና ማቅረቡን ከኢምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

"በመዲናዋ ወንጀል እየተፈጸመ ነው፤ በሚል የውጭ ሃገራት ዜጎች ጉዞ እንዳያደርጉ" በሚል የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያለገናዘበ ነው – ፖሊስ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ወንጀል በስፋት እየተፈፀመ ስለሆነ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ተጠቀሱት ስፍራዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና የከተማችን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ስድስት ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ቢወሰዱባቸውም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ስፍራው በጣም ሰፊ እና ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ መሆኑን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስለ አካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ከኮሚሽኑ በቂ መረጃ ሳይጠይቁ በስማ በለው ያገኙትን መረጃ መነሻ በመድረግ የከተማችን ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ በተለይ ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ መንቀሳቀስ ስጋት እንደሆነ አድርገው መዘገባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብሏል፡፡
በቅርቡ የተከበረው የገና በዓል በሰላም መከበሩንና ከ12ሺህ በላይ ሰዎች የታደሙበት ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁ የከተማዋን ሰላማዊነት ማሳያ ስለመሆኑ ኮሚሽኑ አስታውሶ፤ በተጠቀሱት ስፍራዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ ሰዎች በጋራም ሆነ በግል ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከኦነግ ሸኔ ጋር ያበሩ ከ1000 በላይ ፖሊሶች እርምጃ ተወሰደባቸው
-1 ሺ100 በላይ የኦነግ ሸኔ አባላት ተደምስሰዋል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በፀጥታ እና ፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ሰዎችን አደራጅቶ በመያዝ ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚሰሩ አካላትን ጨምሮ ከ1000 በላይ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መውሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ከኦነግ ሸኔ ስልት ውስጥ አንዱ የሽምቅ ኃይል ነው። ሌላኛው በተለያየ ሁኔታ ህዝብ ውስጥ መደበቅ ነው። መረጃ ለማግኘት ደግሞ መዋቅር ውስጥ በተለይም ደግሞ የፀጥታና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ መግባትና ሰዎችን አደራጅቶ መያዝ ነው።
የቡድኑን ይህን መሰል አካሄድ በማጥናትና ሰፊ ግምገማ በማድረግ ከ1000 በላይ በሚሆኑ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ የማጽዳት ስራዎች መሰራታቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፣ እርምጃው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በቡድኑ የጥፋት ተልእኮ አልፎ አልፎ የሚሳተፉ፣ የሚጠረጠሩ፣ መረጃ የሚሠጡ፣ ከእነርሱ ጋር የሚያብሩ፣ ከጎሰኝት፤ ከከባቢነትም ተነስተው ከፀጥታ መዋቅርና አመራር ጋር በሚመሳጠሩት ላይ በየወቅቱ ግምገማዎች እየተካሄደ እርምጃ እንደሚወሰድ ያስታወቁት ኮሚሽነሩ ፣ ኃላፊነት ኖሯቸው ኦነግ ሸኔን አምርረው በማይተጋሉት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39495

የሰረቀው ገመድ ጠልፎ የጣለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አምቼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሰረቀው ገመድ ጠልፎ የጣለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ቡድን ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አሰፋ እንደገለጹት፣ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ/ም ምሽት ወደ ግንባታው ስፍራው ሰራተኛ መስሎ በመግባት ነው ወንጀሉን የፈጸመው፡፡
ተጠርጣሪው ከንጋቱ 12 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ገደማ ለህንፃው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ከተቀመጠ ገመድ ላይ 40 ሜትር ያህል ቆርጦ በመውሰድ በወገቡ ጠምጥሞ በላዩ ላይ ጃኬት በመደረብ ከግቢው መውጣቱን ገልጸዋል፡፡
የጥበቃ ሰራተኞችም ሰራተኛ መስሎ የገባው ተጠርጣሪ ሲወጣም ትኩረት እንዳላደረጉ የገለፁት ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን ግለሰቡ ገመዱን ሰርቆ በመንገድ ላይ ሲጓዝ አረማመዱን ተመልክተው ጥርጣሬ ያደረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያስቆሙት ለማምለጥ ሲሮጥ፤ ሰርቆ በወገቡ ላይ የጠመጠመው የኤሌክትሪክ ገመድ ጠልፎ እንደጣለውና በህብረተሰቡ ትብብር ተይዞ ወደ ፖሊስ እንደቀረበ ተናግረዋል፡፡
የጥበቃ ሰራተኞች ተገቢውን የፍተሻ ተግባር ቢያከናውኑ መሰል ወንጀሎችን መከላከል እንደሚቻል ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አሰፋ ማሳሰባቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሰቬኒ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸው ተገለጸ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሰቬኒ የአገሪቱን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን የአገሪቷ የምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ቦቢ ዋይን ከአጠቃላይ ድምጽ 35 በመቶ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ደግሞ 59 በመቶ ማግኘታቸውን የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን መግለጹን ቢቢሲ በሰበር ዜናው ዘግቧል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ2005 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ በትግራይ ክልል ከ113 ሚሊዮን ብር በላይ የበጎ አድራጎትና የልማት ስራ ማከናወኑን ገለጸ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ2005 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ በትግራይ ክልል ከ113 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የበጎ አድራጎትና የልማት ስራ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡
የሰሜን እዝ የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ ለ21 ዓመታት በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ የሃገሩን ህዝብ ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ ሲል በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና በትግራይ ክልል ውስጥ የክልሉን ህዝብ ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ የበጎ አድራጎት እና የመሰረተ ልማት ስራዎችን አከናውኗል፡፡
በዚህም ባለፉት ስምንት ዓመታት 113 ሚሊዮን 102 ሺህ 426 ብር ግምት ያለው የበጎ አድራጎትና የልማት ስራ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መረጃ ያመላክታል።
ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሃገር ጥቅም የሚለውን ቁልፍ እሴቱን ተግባራዊ በማድረግ ከወር ደመወዙ በማዋጣት ሞልቶ ስለተረፈው ሳይሆን ፣ ያለውን ከወገኖቹ ጋር በፍቅር ተካፍሎ የሚበላ ህዝባዊ ሰራዊት ነው፡፡
ለሰው ሰው በሚያስፈልግበት በዚያ ቀውጢ ሰዓት በወር ከሚከፈለው ትንሽ ደመወዝ በመቀነስ የሚወደውን ህዝብ በሞት ላለማጣት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ሃይል ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የጥምቀት በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የጥምቀት በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሁሉም በመከባበር ፣ በመደማመጥ እና በአብሮነት እንዲያከበር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የታቦት ማደሪያ ስፍራን አጽድተዋል፡፡
በጽዳት ዘመቻው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር ማህበራዊ ጥቅሙም ትልቅ ነው ብለዋል፡፡
የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያዊያን ህብር የሚገለፅበት ልዩ ድምቀት መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ የተካሄደው የፅዳት መርሃግብር ኢትዮጵያዊያን የተለያየ ሃይማኖት፣ ብሄርና ማንነት ቢኖራቸውም አንድ መሆናቸውን የሚያመላከት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።
በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በተለመደው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በመከባበር ፣በመደማመጥ እና በአብሮነት እንዲከበር ሁሉም አካላት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት መልዕከት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባዋ የበዓሉ ታዳሚ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳይጋለጡ የጥንቃቄ መንገዶችን በአግባቡ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡
ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች በበኩላቸው ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም ሁሉም በጋራ መሰለፍ የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ከሁሉም ሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች ፣ወጣቶች፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ምንጭ- የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት

ሽግግሩ ከባድ ፈተናዎች የበዙበት በመሆኑ በጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባ ተጠቆመ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች የበዙባት በመሆኑ የጀመረችው የዴሞክራሲ ሽግግር በጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባ በምስራቅ አፍሪካ የደህንነት ተቋም ምክትል ዳሬክተር ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ አሳሰቡ፡፡ በባህርዳር ለሁለት ቀናት የተካሄደው ብሄራዊ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ።
ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ በባህር ዳር ከተማ ትናንት ቀጥሎ በዋለው ብሄራዊ የምክክር መድረክ ላይ ‹‹የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግርና ተሃድሶ ችግሮች›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ እንዳመለከቱት ፤ አገራት ከአምባገነናዊ መንግስት ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመሸጋገር ሙሉ ለሙሉ መለወጥ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነገሮችን ማቻቻል አሊያም ደግሞ በኃይል አንዱ ሌላውን ማስወገድ የሚለውን መርህ ይከተላሉ።
ኢትዮጵያም ይህ ልምምድ እንደነበራት፡፡ ይሁንና በአገሪቱ በብዛት የተለመደው ለውጥ ኃይል እና ነውጥ የተቀላቀለበት በመሆኑ ዋጋ ሲያስከፍላት መኖሩን ያመለከቱት ዶክተር ብርሃኑ ፣ በዚህም ለዓመታት የቆየው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር የሚፈለገውን ውጤት አላስገኘም ብለዋል፡፡
በልጅ እያሱ ዘመን ከሃይማኖትና ከብሄር ክፍፍል የፀዳ ማህበረሰብ ለመገንባት ጥረት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ጥረቱ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውድቀት እንደገጠመው ያመለከቱት ዶክተር ብርሃኑ ፣ 1966 ዓ.ም የንጉሱ ሥርዓት በሃይል ከስልጣን የተወገደ ቢሆንም የተፈለገው ለውጥ እንዳልመጣ አመልክተዋል ።
https://www.press.et/Ama/?p=39620

www.press.et
ሽግግሩ ከባድ ፈተናዎች የበዙበት በመሆኑ በጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባ ተጠቆመ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ ሚኒስቴሩ አስታወቀ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ የሚታየውን የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አመለከተ።
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የብረታ ብረትና ኬሚካል ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ዱጋሳ ዶንሳ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት ፣ሚኒስቴሩ ከስድስት ወር በፊት በምርትና በአቅርቦት በኩል የተፈጠረውን የሲሚንቶ እጥረት መንስኤ ለማጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም በሀገሪቱ ያሉ ፋብሪካዎች ለረጅም ጊዜ የሚቆሙ፣ ገሚሶቹም ያረጁና መለዋወጫ የሚፈልጉ፣ የገበያ ፍላጎታቸውም በሶስት ኢንዱስትሪዎች ላይ መሰረት ያደረጉ መሆናቸውንና አብዛኛዎቹ ግንባታዎችም በተመሳሳይ ወቅት መከናወናቸው ችግሩ እንዲጎላ ማድረጉን ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የሲሚንቶ ምርት ፍላጎትና አቅርቦት ልዩነት እንደነበር መረጋገጡን አመልክተዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39629

በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለዘለቄታው ለማስቆም በምክንያት የሚያምን ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። በአገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች በአገር ጉዳይ ምክንያታዊ የሆነ አስተሳሰብን መፍጠር የሚስችላቸው የሙግትና የንግግር መድረክ በአዲስ አበባ ተጀመረ።
የብልጽግና ወጣት ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አክሊሉ ታደሰ ትናንት መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳስታወቁት ፤ በአገሪቱ በእምነት እና በፖለቲካ ልዩነት እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ወደ ግጭት እየተገባ ነው። ይህን ለመቀነስና ለማስቆም ምክንያታዊ የሆነ ወጣት መፍጠርና በንግግር የሚያምን ትውልድ መቅረጽ ያስፈልጋል ፤ ለዚህም መድረኩ ተመቻችቷል።
የጋራ ባህል፣ እሴት፣ ታሪክ እንዲሁም መተሳስሮች ባይኖሩ ባለፉት ጊዜያት የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር የተሰራጩት የታዘቡ መረጃዎች ሀገርና ህዝብን ከሆነው በላይ ሀገርና ህዝብን ዋጋ ያስከፍሉ እንደነበር አመልክተዋል። በቀጣይም ተመሳሳይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ ምክንታዊ የሆነ ወጣት ለመፍጠር የንግግር መድረኮች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቁሟል።
https://www.press.et/Ama/?p=39630

በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ- ሥርዓት ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በጎንደር ከተማ የሚከበረውን የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ። በከተማዋ በሚደረገው ክብረ በዓልም የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን መምሪያው ገልጿል።
በጎንደር ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ኃላፊ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ባህላዊና ሐይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል።
የጥምቀት በዓል በሰላምና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው እየሰሩ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አደባባይ በጸጥታ፣ በእንግዳ አቀባበል፣ በባህልና ቅርስ ትውውቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ከበዓሉ ዝግጅት ስራዎች ቀዳሚው ስራ የጥምቀተ ባህሩን ቦታ የማስተካከል ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አደባባይ፤ ከዚህ አንጻር የቦታው የእድሳት ስራ መቶ በመቶ ተከናውኖ ውኃ የመሙላት ስራው ዛሬ እንደሚጠናቀቅና ለበዓሉ ዝግጁ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
እንደ አቶ አደባባይ ገለጻ፣ በበአሉ እለት የሚፈጠረውን መጨናነቅ ለመቀነስና ታዳሚው በጥምቀተ ባህሩ ዙሪያ ሳይጨናነቅ መስተናገድ እንዲችል የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮች ተግባራዊ ተደርገዋል። ከእነዚህ መካከልም ታዳሚው ከአጥር ውጪ ሆኖ የበዓሉን ክዋኔ መከታተል እንዲችል በአራት አቅጣጫዎች ሰፋፊ ማሳያ ስክሪኖች ተዘጋጅተዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39628

”አቶ ስብሃትና ጓደኞቻቸው በመረጡት የተሳሳተ መንገድ ራሳቸውን ለውርደት ዳርገዋል‘
– አቶ ቀጄላ መርዳሳ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ለበርካታ ዓመታት በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ግዙፍ ተጽዕኖ የነበራቸው የህውሓት ቡድን አባላት በመረጡት የተሳሳተ መንገድ ራሳቸውን ለውርደት መዳረጋቸውን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ አስታወቁ።
አቶ ቀጄላ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የህውሓት ቡድን በህዝብ አመጽ መቀሌ ከገባ ጀምሮ ሰላማዊ አማራጮችን ከመጠቀም ይልቅ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ትርክቶችን በማሰራጨትና ሁከቶችን በመቀስቀስ ሀገሪቱን ሲያተራምስ ቆይቷል።
ቡድኑ በሰላማዊ ፖለቲካ ለማራመድ ወይም ተግባብቶ ሀገሪቱን ለማሻገር ፍላጎት ስላልነበረው በየጊዜው ትንኮሳዎችን ሲያደርግ ቆይቶ በመጨረሻም በመከላከያ ሠራዊት ላይ በፈጸመው አሳፋሪ ተግባር መንግሥት ወደ ህግ ማስከበር ተግባር መግባቱን የጠቆሙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው፣ የመከላከያ ኃይሉ በህዝብ በመታገዝ ባደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ በሁለንተናዊ መልኩ ተጽዕኖ የነበረው ኃይል ላይመለስ መሰናበቱን አስታውቀዋል።
አንዳንዶች ህውሓት የገንዘብ አቅምና የፖለቲካ የበላይነት አለው ብለው በድሮ ጉልበቱ ፤በድሮ ኃይሉ በመተማመን ጦርነቱን በበላይነት አሸንፎ ሀገሪቱን ዳግም ይቆጣጠራል የሚል እምነት ነበራቸው ያሉት አቶ ቀጄላ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተደረገው ቅንጅታዊ ሥራ ቡድኑ ተሸንፎ አባላቱም ባልተጠበቀ መልኩ እጃቸውን ለመንግሥት ለመስጠት መገደዳቸውን ጠቁመዋል።
በቡድኑ ላይ የደረሰው ውርደት ኃይልና ጉልበትን ተማምኖ ሀገርን ለዘላለም መግዛት እንደማይቻል ተጨባጭ ማስተማሪያ እንደሚሆኑ ያመለከቱት አቶ ቀጄላ ፣ ምንም ኃያል ነን ቢሉ በአንድ ታሪካዊ ወቅት ላይ ሁሉም ነገር እንደሚያበቃና ሁሉም ነገር እንደሚንኮታኮት የሚያሳይ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39615

”አቶ ስብሃትና ጓደኞቻቸው በመረጡት የተሳሳተ መንገድ ራሳቸውን ለውርደት ዳርገዋል‘ – አቶ ቀጄላ መርዳሳ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት