Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሰበር ዜና ‼️
አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ
👉"ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው" የምስራቅ ዕዝ 25ኛ
ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ሃላፊ
**************************
(ኢ.ፕ.ድ)
አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል
አቶ አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ
ዶክተር አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ
ዶክተር ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ
ዶክተር ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ
አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ
አቶ ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ
ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች
ንጋቱ አንገሶም
አምደማርያም ተሰማ
እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በሀገር መከላከያ ሰራዊት በፌዴራል ፓሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት አማካኝነት ተይዘው አዲስ አበባ ገብተዋል።
በተመሳሳይ እነዚህን የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች "ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው" ሲሉ የምስራቅ ዕዝ 25ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ሃላፊ መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ ተናግረዋል።
አሁን አዲስ አበባ የገቡትን ከፍተኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ለማዋል የትግራይ ህዝብ መረጃ በመስጠትና መንገድ በመምራት ከፍተኛ ትብብር በማድረጉ መቶ አለቃ ስዩም አመስግነዋል።
በእጸገነት አክሊሉ
"ስብሀት ነጋ በዚህ መልኩ በቁጥጥር ስር መዋል የኢትዮጵያን ህዝብ በድሎ በሰላም መተኛት እንደማይችል የሚያስተምር ነው "
አቶ ሊላይ ኃይለማርያም
የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራር
**************************
(ኢ ፕ ድ)
የጁንታው ቁንጮ ስብሀት ነጋ በዚህ መልክ በቁጥጥር ስር መዋሉ የኢትዮጵያን ህዝብ በድሎ በሰላም መተኛት እንደማይችል የሚያስተምር እንደሆነ አቶ ሊላይ ኃይለማርያም አስታወቁ፡፡
የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ የጁንታው ስብሐት ነጋ በዚህ መልኩ ተዋርዶ መያዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሠርቶ ማምለጥ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ በድሎ በሰላም መተኛት እንደማይችል ያሳየ ነው።
የህወሓት ጁንታ ቡድን ሲፈጠር ጀምሮ ከአንድ ቤተሰብ (ከስብሐት ነጋ ቤተሰብና አካባቢ) የወጣ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ሊላይ ፣የኢትዮጵያን ኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካ በዚህ የቤተሰብ ኔትዎርክ በመያዝ አገሪቷን ሲዘርፍ ኖሯል ብለዋል።
በቤተሰብና በአካባቢ ተደራጅቶ ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ሀብት ሲዘርፍ የቆየው የህወሓት ጁንታ አዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ሕንፃ ያላቸው ጄኔራሎችን መፍጠሩን አመልክተዋል።
የጁንታው አባላት እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ላይ በፈጸሙት ክፋት እና በደል ፤ አደህይተው ለመግዛት ባደረጉት ጥረት በጣም የተጠሉ ሆነዋል፤ ይህንን ደግሞ ልቦናቸው በሚገባ ያውቃል ያሉት አቶ ሊላይ ፣ የትግራይ ህዝብ እነሱን አጥቶ ለአንድ ሳምንት እንኳን መኖር እንደማይችል ሲያስወሩ ቢኖሩም ነገሩ ግን በፍጹም ከሚሉት ተቃራኒ ነው ብለዋል ።አሁንም በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ህዝቡን ከሚገባው በላይ እያስደሰተው መሆኑን አስታወቀዋል፡፡
አሁን ላይ የህግ ማስከበር ዘመቻው ተጠናቅቆ እነዚህ አካላት በመከላከያ ሠራዊት እየተያዙ መሆኑ ለመላው ኢትዮጵያውያን ደስታን የሚፈጥር ቢሆንም ለትግራይ ህዝብ ደግሞ የድል ድል ሆኖ ነው ያገኘነው ያሉት አቶ ሊላይ ፤ጁንታው ለትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጥላት ነው። ላለፉት 46 ዓመታት የትግራይን ህዝብ ሲያርዱ ፣ሲገድሉ በስሙ እየነገዱ እነሱ ሲበለጽጉ ኑሯቸውን በተቀናጣ ሁኔታ ሲመሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል።
እነዚህ ሰዎች ከዚህም አልፈው ኢትዮጵያውያንን በብሔር በቋንቋ ሲከፋፍሉ፣ ሲያራርቁና ደም ሲያቃቡ የኖሩ ሴረኞች መሆናቸውን አመልክተው ፣ አሁን ላይ መንግሥት ህግ በማስከበር ዘመቻው የወሰደው ዕርምጃ ከምንም በላይ ትግራይን ብሎም መላው ኢትዮጵያን ነፃ ያወጣ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ በእነዚህ ፋሽስቶች መማረሩንና ከላዩ ላይም እንዲነቀሉለት መፈለጉ የሚታወቀው መከላከያ ሠራዊትን እየደገፈ መውጫ መግቢያቸውን እያሳየ ከተደበቁበት ጎሬ ተፈንቅለው እንዲወጡ የራሱን ሚና እየተጫወተ መሆኑ ነው ያሉት አቶ ሊላይ ፣ በዘመቻው መቶ በመቶ በሚባል ሁኔታ ተሳትፎውን አሳይቷል በማሳየት ላይም ነው ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ ጁንታው በፍጥነት ከላዩ ላይ ተነቅለው ወደቀድሞ ሰላሙና ልማቱ የሚገባበትን ቀን እየናፈቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39323
ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ ጎሹ እንዳላማው የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ
2. አቶ ደሳለኝ አስራደ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ
3. አቶ መስፍን አበጀ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ
4. ወይዘሮ ከድጃ ሁሴን በምክትል ቢሮ ኀላፊ ማዕረግ የአደረጃጀት ምክትል ዘርፍ አማካሪ ሁነው ተሹመዋል፡፡
" የስብሀት ነጋ መያዝ ጁንታው ከአሉባልታ በዘለለ ትርጉም ያለው ኃይል እንዳልሆነ በተጨባጭ ያሳየ ነው"
- አታክልቲ ሀይለ ስላሴ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ
*******************************
(ኢ ፕ ድ)
የስብሀት ነጋ መያዝ ጁንታው ከአሉባልታ በዘለለ ትርጉም ያለው ኃይል እንዳልሆነ በተጨባጭ ያሳየ መሆኑን መቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሀይለ ስላሴ አስታወቁ። ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ወደ እለት ተእለት ህይወቱ እንዲመለስ ከፍ ያለ ፋይዳ እንደሚኖረው አመለከቱ።

አቶ አታክልቲ የስብሀት ነጋ መያዝን አስመልክቶ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፣ በከተማው ጁንታው በዚህ እየመጣ ነው ፣ እንዲህና እንዲያ እያደረገ ነው የሚል አሉባልታ በስፋት ይናፈስ ነበር። ይህም ህዝቡ ተረጋግቶ ወደ እለት ህይወቱ እንዳይመለስ ትልቅ ተግዳሮት ነበር።

ስብሀት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች መያዝ እንደሚወራው ጁንታው ከአሉባልታ በዘለለ ትርጉም ያለው ኃይል እንዳልሆነ በተጨባጭ ማሳየቱን ያመለከቱት ከንቲባው ፣ የቡድኑ መጨረሻ በአጭር ጊዜ የሚሰማ ፣ ህዝቡም በቅርቡ ወደነበረበት መረጋጋት እና የሰላም ህይወት ሊገባ እንደሚችል ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ህዝቡን ለማረጋጋት በሚሠራው ሥራ ትልቅ ተግዳሮት የነበረው በየቀኑ ይሰማ የነበረው ተመልሰው ይመጣሉ የሚሉ አሉባልታዎች እንደነበር አመልክተው ፣ አሁን ግን ተመልሰው መቀሌ ሊመጡ ይቅርና እራሳቸውን መከለላከል የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ህዝቡ መረዳት የቻለበት ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። አቦይ ስብሐት በተያዙበት እለት በከተማዋ የደስታ መግለጫ ከፍተኛ የሆነ ተኩስ እንደነበር ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ነዋሪው ስብሰባ በሚጠራበት ወቅት ከምንጠራው ማህበረሰብ በላይ በመሳተፍ ያለውን ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት እያሳየ ነው። በከተማው የሚታየው የማህበረሰቡ የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደመቀሌ ከተማ በመግባት ቤተሰቦቻቸውን እየጠየቁ ነው። ይህ አሉባልታው የቱን ያህል ተጽእኖ ፈጥሮበት እንደነበር በተጨባጭ ማሳየት ያስቻለ ነው ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39324
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባው የብርሐን ደባርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት 13 ነጥብ 8 ሚሊዩን ብር ወጪ የተገነባው የብርሐን ደባርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እና የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ትምህርት ቤቱ የተመረቀው።
ትምህርት ቤቱ በዉስጡ የአስተዳደር ህንጻ፤የመማሪያ ክፍሎች ፤ላብራቶሪ ፤የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ነው፡፡
ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በአንድ ፈረቃ 1 ሺህ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም ያለው መሆኑን ከቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳይል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማሳደግ በሚያደረገዉ ጥረት በጽሕፈት ቤቱ ግንባታቸዉ ተጠናቆ ከተመረቁት ስድስተኛው ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች ያስመርቃል፡፡
“ስብሃት ነጋና ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ስር መዋል ግፈኞች መጨረሻቸው ውርደት መሆኑን የሚያሳይ ነው”
- አርቲስት ደበበ እሸቱ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ከ30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የኖሩት አቶ ስብሃት ነጋና ግብረአበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋል ግፈኞች መጨረሻቸው ውርደት መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ አርቲስት ደበበ እሸቱ አስታወቀ።
አርቲስት ደበበ እሸቱ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቀው ፣ በ1997 ዓ.ም በመነበረው የፖለቲካ ተሳትፎ እና በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት በህውሓት ቡድን በርካታ መከራና ስቃይ ደርሶበታል።
እነዚህ ሰዎች በሰው ልጅ ላይ ያልፈጸሙት በደል የለም የሚለው አርቲስት ደበበ ፣በምድር ላይ ያሉ ክፉ ሥራዎችን በሙሉ ሠርተዋል፤ በእስር ላይ በነበርኩበት ጊዜ የሰው ልጅ ላይ ሊደርስ የማይገባው ፤ሰብዓዊነትን ሽረው ማንነትን አስረስተው ዕቃ አድርገው በደል ፈጽመውብኛል ሲል የከፋ በደል እንዳደረሱበት አመልክቷል።
አርቲስቱ እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ ሲፈጽሙ የነበረውን በደል ሲያብራራም ‹‹ ሲፈልጉ ያስተኙሃል፤ሲፈልጉ ይረማመዱብሃል፤ ሲፈልጉ ይደበድቡሃል፤ሲፈልጉ ይረግጡሃል፤ ሲፈልጉ በሰደፍ ይመቱሃል፤ ባዶ መሬት ላይ ያስተኙሃል፤ በአጠቃለይ ሰብዓዊነት የተባለ ነገር ያልፈጠረባቸው ናቸው” ብለዋል።
ሰው መሆንህን እንድትረሳና ምንም እንዳልሆንክ እንድትቆጥር ለማድረግ የማይሠሩት ግፍ እንደሌለ የሚናገረው አርቲስቱ ፣ በኢትዮጵያ ባህልና ወግ የተጠሉ ነገሮችን በዜጎች ላይ መፈጸማቸውንም ጠቁመዋል።
‹‹ነገሩን ማስታወስ ባልፈልግም ከቃሊቲ ወጥቼ ማዕከላዊ በገባሁበት ጊዜ የደረሰብኝን እስከመቼውም አልረሳውም። አሁን ሳስበው ይዘገንነኛል። እንደሰው ሳይሆን እንደከበት እየነዱ ነበር ማዕከላዊ ያጎሩን። የሐሰት ቃል ለማናዘዝም ቡና ውስጥ የዕንቅልፍ ኪኒን በመስጠት ሰው በቁሙ እንዲቃዥ ያደርጉ ነበር። መውጫ ቀዳዳ በሌሌው ጉድጓድ ውስጥ በማሰር እስረኛው ከሰው ጋር እንዳይገናኝና እዚያው እንዲጸዳዳ በማድረግ በመጥፎ ሽታ እንዲሰቃይ ያደርጉ ነበር ›› ብሏል።
https://www.press.et/Ama/?p=39378
በጅቡቲ ቆመው የነበሩ 179 የትራንስ ኢትዮጵያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ሊመለሱን ነው
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በጅቡቲ ቆመው የነበሩ 179 የትራንስ ኢትዮጵያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዲመለሱ አዲሱ የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሽከርካሪዎችን ቁልፎች ተረክበዋል።

የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባኒያ አመራሮች ከጅቡቲ ወደብ እቃዎችን ለማምጣት በሚል 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጅቡቲ ወስደው እንዲቆሙ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያለአግባብ ወደ ጅቡቲ የተወሰዱ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ባደረገው ጥረት አዲሱ የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የ179ኙን ተሽከርካሪዎች ቁልፎች መረከብ ችለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የትራንስ ኢትዮጵያ ሀብት እንዳይንቀሳቀሱ ማገዱን ተከትሎ የጅቡቲ መንግሥት ቁልፎቹን ከአሽከርካሪዎቹ በመረክ ማቆየቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሳውዲው ባለሃብት ሼህ ሀምዛ የተመራ ልዑክ ቡድን ለይፈዊ የስራ ጉብኝት ጅግጅጋ ገቡ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በሳውዲው ባለሃብት ሼህ ሀምዛ የተመራ ልዑክ ቡድን ለይፈዊ የስራ ጉብኝት ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በገራድ ዊል ዋል አየር ማረፊያ በመገኘት ለባለሀብቶቹ አቀባበል አድርገዋል።
የነዳጅ ካምፓኒ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሼህ ሀምዛ አብዲአዚዝ አል ሱኬሪያ ከክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ጋር በክልሉ ስላለው ምቹ ኢንቨስትመንት ሁኔታ መክረዋል፡፡
ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሉኡካን ቡድኑ በክልሉ ለሚያከናውናቸው የኢንቨስትመንት ስራዎች የክልሉ ህዝብና መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም አረጋግጠዋል።
ባለሀብቱ ወደ ክልሉ የመጡበት ዋነኛ አላማ በክልሉ የኢንቨስትመንት መስክ ተሳትፎ ለማድረግ ሲሆን በቤቶች ግንባታ፣ በፀሀይ የሚሰራ የሶላር መገጣጠሚያ፣ በመኪና መገጣጠሚያ ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ነው፡፡

በክልሉ በሪል እስቴት መስክ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የባለሃብቱ ድርሻ የጎላ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የመገጣጠሚያ ካምፓኒዎቹ መገንባትም በኢኮኖሚው ረገድ ያለው ሚና የጎላ እንደሆነም ከክልሉ መገናኛ ቡዙሃን አጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሰበር ዜና ‼️

የጁንታው ከፍተኛ አመራር የነበሩት ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሀይ አስመላሽ ወልደሥላሴ መደምሰሳቸው ተገለጸ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በመካለከያ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈጸም ጥቃት እንዲሰነዘር ያደረጉ ቁልፍ የጁንታው አመራር የነበሩት ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሀይ፣ አስመላሽ ወልደሥላሴ እና ኮሮኔል ኪሮስ ሀጎሥ መደምሰሳቸው ተገለጸ።

የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ ተደብቀው የነበሩት አነዚህ የጁንታ አመራሮች ከእነጠባቂዎቻቸው እና ከወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዳ

2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣

3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣

4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር
አዛዥ የነበረ
5. መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች
ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ

በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ ያስታወቁት።

በራስወርቅ ሙሉጌታ
በ25 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የይስማ ንጉስ ሙዝየም በዛሬው ዕለት ይመረቃል
******************************
(ኢ ፕ ድ)
ለዓድዋ ጦርነት ምክንያት የሆነው የውጫሌ ውል በተፈረመበት ታሪካዊ ቦታ ላይ በ25 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የይስማ ንጉስ ሙዝየም በዛሬው ዕለት የፌዴራልና የክልል የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት እንደሚመረቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ25 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ሙዚየም ፣ካፌና የመግቢያ በር የኢትዮጵያ ቁጥር ፲፯ (17) አምሳል የተገነባ ነው፡፡
የባህል ማዕከሉ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያሳዩ መረጃዎችን ያካተተ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
"ሱዳን ከጥቅሟ ይልቅ ለግብፅ ፖለቲካዊ ጥምረት ትኩረት ሰጥታለች"
- ዶክተር ይልማ ስለሽ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ሱዳን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደሚጠቅማት ብታውቅም ከግብፅ ጋር በፈጠረችው ጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥምረት ምክንያት ከወዳጅ አገር የማይጠበቅ ተግባር በኢትዮጵያ ላይ እየፈፀመች መሆኑን ዶክተር ይልማ ስለሽ አስታወቁ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህድስና መምህር ዶክተር ይልማ ስለሽ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሱዳን የህዳሴውን ግድብ ጎርፍ በመከላከላከልና ኤሌክትሪክ ኃይል በአነስተኛ ዋጋ እንድታገኝ በማድረግ ረገድ እንደሚጠቅማት ብታውቅም ከግብፅ ጋር በፈጠረችው ፖለቲካዊ ትብብር ምክንያት በድርድሩና በድንበር አካባቢ ከወዳጅ አገር የማይጠበቅ ተግባር እየፈፀመች ነው።
ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሆነ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ እየሠራች ያለችው ሥራ ከወዳጅ አገር የሚጠበቅ አይደለም ያሉት ዶክተር ይልማ በግድቡ ድርድር ላይ ሱዳንና ግብፅ የሚያሳዩት ተለዋዋጭ ባህሪ በአጋጣሚ ሳይሆን በፈጠሩት ፖለቲካዊ ትብብር መሆኑን አመልክተዋል።
ሁለቱም አገራት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገውን ድርድር ሰበብ አድርገው በአባይ ወንዝ የውሃ ድርሻቸውን ለማስጠበቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው፣ በተለይ ሱዳን የህዳሴው ግድብ ከጎርፍ አደጋ እንደሚታደጋትና ኤሌክትሪክ ኃይል በርካሽ ዋጋ እንድታገኝ በማድረግ ረገድ እንደሚጠቅማት ብታውቅም ከግብፅ ጋር በፈጠረችው ጊዜያዊ የፖለቲካ ትብብር ምክንያት ድርድሩ እንዲስተጓጎል እየሠራች ነው ብለዋል።
ድርድሩ የሚካሄደው በግብፅና በሱዳን ጥያቄ መሰረት በታችኛው አገራት መተማመን ለመፍጠር ሲባል እንጂ ኢትዮጵያ ፈልጋው አለመሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ድርድሩን እነሱ ካልፈለጉት ይቀጥል ብላ የምትጠይቀው ምክንያት አይኖርም፤ በህግም የመደራደር ግዴታ የለባትም፣ ግድቡንም ውሃ ስንሞላና ስናስተዳድር ተቀባይነት ባለው ዓለም አቀፍ ህግ መሰረት እንደሆነም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን የታችኛዎቹን የአባይ ተፋሰስ አገራት ለመጉዳት አስባ አታውቅም፤ በጋራ እንልማ ነው የምትለው ያሉት ዶክተር ይልማ ፤ይህን የማይቀበሉ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ኢትዮጵያም በአባይ ውሃ ፍትሐዊ የመልማት መብቷንም አሳልፋ እንደማትሰጥ መታወቅ አለበት ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39434
“የሀገራችን ፖለቲካ ማንም ዘው ብሎ ከሚገባበት አካሄድ መውጣት ይኖርበታል”
-አቶ አቡበከር ያሲን
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር
************************
(ኢ ፕ ድ)
“የሀገራችን ፖለቲካ ማንም ዘው ብሎ ከሚገባበት አካሄድ መውጣት እንደሚኖርበት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር እና የማህበራዊ ሳይንስ መምህር የሆኑት አቶ አቡበከር ያሲን አስታወቁ። አሁን በሃገራችን እየታየ ያለው ምስቅልቅልም ፖለቲካና ፖለቲከኞች ባለመለያየታቸው እንደሆነም አመለከቱ።
አቶ አቡበከር ያሲን በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፣ የአገራችን ፖለቲካ ማንም ሰው ዘው ብሎ ከሚገባበት አካሄድ መውጣት ይኖርበታል።
የአገራችን ፖለቲካ በፖለቲከኞች ቅኝ ግዛት ስር ወድቋል የሚሉት አቶ አቡበከር፤ ፖለቲካ ራሱ ከፖለቲከኞች ነፃ ካልወጣ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አዳጋች እንደሚሆን አመልክተዋል።
ፖለቲካ ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ማበልፀጊያ እየዋለ ነው፣. ይህ በሆነበት ሁኔታም የህዝብን ችግር መረዳትና ለችግሩ መፍትሔ ማምጣም አይቻልም ብለዋል።
እንደ አቶ አቡበከር ገለጻ፣ እንደ ሃገር የፖለቲካን “ሀ - ሁ” የተረዳንበት መንገድ የተሳሳተ ነው። ፖለቲካ ህዝብን የምናገለግልበት፣ የህዝብ ጥቅም የሚከበርበት፣ እንዴት፣ መቼ እና በምን መንገድ እንደምናስተዳድር የምንማርበት የሙያ ዘርፍ ሆኖ እያለ ፖለቲከኞች ከሙያው ስነምግባር ውጪ ፖለቲካን የሀብት ማከማቻ እና የስልጣን ጥም መወጣጫ አድርገውታል።
በሃገራችን እየታየ ያለው ምስቅልቅልም ፖለቲካና ፖለቲከኞች ባለመለያየታቸው የመጣ በመሆኑ ፖለቲካው ከፖለቲከኞች ነፃ ወጥቶ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ ብሎም እንደ ህዝብ ማስተዳደሪያ መሳርያነቱ ማወቅና መረዳት ይገባል ብለዋል።
በአገራችን ያለው ለውጥ በርካታ ለውጦች የታዩበትና እንደ አገርም ብዙ ተስፋን ያጫረ ነው ያሉት አቶ አቡበከር፤ ሆኖም አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ቡድንተኝነት፣ ጎሰኝነት፣ በኔት ወርክ መደራጀት እንደሚታይ ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39450
በኩዌት የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት ኢትዮጵያዊት በምህረት ተለቀቀች
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ከ8 አመታት በፊት በኩዌት አገር በወንጀል ተከሳ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት ሉባባ ኑረዲን የተባለች ኢትዮጵያዊት በምህረት እንዲትፈታ መደረጉን በኪዌት የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ፡፡
ኤምባሲው ላለፉት ዓመታት ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የኩዌት የፍትህ ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት ምህረት እንደተደረገላት ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ሉባባ ኑረዲንን ወደ ሀገር ቤት እንድትመለስ የጉዞ ሂደቱን በማስጨረስ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በሰላም እንድትሳፈር አድርጓል።
ኤምባሲው በኩዌት የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበርን ጨምሮ በሂደቱ ለተባበሩ ሁሉ ምሥጋና ማቅረቡን ከኢምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
"በመዲናዋ ወንጀል እየተፈጸመ ነው፤ በሚል የውጭ ሃገራት ዜጎች ጉዞ እንዳያደርጉ" በሚል የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያለገናዘበ ነው – ፖሊስ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

ወንጀል በስፋት እየተፈፀመ ስለሆነ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ተጠቀሱት ስፍራዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና የከተማችን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ስድስት ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ቢወሰዱባቸውም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ስፍራው በጣም ሰፊ እና ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ መሆኑን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስለ አካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ከኮሚሽኑ በቂ መረጃ ሳይጠይቁ በስማ በለው ያገኙትን መረጃ መነሻ በመድረግ የከተማችን ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ በተለይ ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ መንቀሳቀስ ስጋት እንደሆነ አድርገው መዘገባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብሏል፡፡

በቅርቡ የተከበረው የገና በዓል በሰላም መከበሩንና ከ12ሺህ በላይ ሰዎች የታደሙበት ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁ የከተማዋን ሰላማዊነት ማሳያ ስለመሆኑ ኮሚሽኑ አስታውሶ፤ በተጠቀሱት ስፍራዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ ሰዎች በጋራም ሆነ በግል ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ከኦነግ ሸኔ ጋር ያበሩ ከ1000 በላይ ፖሊሶች እርምጃ ተወሰደባቸው
-1 ሺ100 በላይ የኦነግ ሸኔ አባላት ተደምስሰዋል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በፀጥታ እና ፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ሰዎችን አደራጅቶ በመያዝ ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚሰሩ አካላትን ጨምሮ ከ1000 በላይ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መውሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ከኦነግ ሸኔ ስልት ውስጥ አንዱ የሽምቅ ኃይል ነው። ሌላኛው በተለያየ ሁኔታ ህዝብ ውስጥ መደበቅ ነው። መረጃ ለማግኘት ደግሞ መዋቅር ውስጥ በተለይም ደግሞ የፀጥታና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ መግባትና ሰዎችን አደራጅቶ መያዝ ነው።
የቡድኑን ይህን መሰል አካሄድ በማጥናትና ሰፊ ግምገማ በማድረግ ከ1000 በላይ በሚሆኑ የፖሊስ አባላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ የማጽዳት ስራዎች መሰራታቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፣ እርምጃው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በቡድኑ የጥፋት ተልእኮ አልፎ አልፎ የሚሳተፉ፣ የሚጠረጠሩ፣ መረጃ የሚሠጡ፣ ከእነርሱ ጋር የሚያብሩ፣ ከጎሰኝት፤ ከከባቢነትም ተነስተው ከፀጥታ መዋቅርና አመራር ጋር በሚመሳጠሩት ላይ በየወቅቱ ግምገማዎች እየተካሄደ እርምጃ እንደሚወሰድ ያስታወቁት ኮሚሽነሩ ፣ ኃላፊነት ኖሯቸው ኦነግ ሸኔን አምርረው በማይተጋሉት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39495