Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በቡሬ ከተማ የተቋቋመው የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት መጀመሩ ተገለጸ
********************************
(ኢ ፕ ድ)
በቡሬ ከተማ የተቋቋመውንና ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት መጀመሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
አቶ መላኩ አለበል በቡሬ ከተማ የተቋቋመውን የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ምርት ለማምረት ላበቁት አካላት በትዊተር ገጻቸው ምስጋና አቅርበዋል::
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ ለተገነባው የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ስኬታማነት አስተዋጽዖ ለነበራቸውና ፕሮጀክቱ ሥራ እንዲጀምር ጥረት ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል” ብለዋል፡፡
የዘይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት መጀመሩን አቶ መላኩ በትዊተር ገጻቸው ጠቅሰዋል፡፡
ሚኒስትሩ ከዚህ በፊትም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 22 ሚሊዮን 500 ሺህ ሊትር ለገበያ እንደሚያቀርብ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሪችላንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አማካኝነት የተገነባው የአኩሪ አተር ፕሮቲንና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ወደ ሙከራ ምርት መግባቱን ገልጸው ነበር፡፡ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም 22 ሚሊዮን 500 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ለሀገር ውስጥ ገበያ ያቀርባል።
ለውጪ ገበያ ከሚያቀርበው የምግብ ዘይትም 61 ሚሊዮን 680 ሺህ ዶላር እንደሚያስገኝ ሚኒስትሩ መናገራቸው አብመድ ዘግቧል፡፡
“አዲሱ የትግራይ ክልል ካቢኔ ማህበራዊ መሠረታቸው ትግራይ ላይ የሆኑ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ ነው” አቶ ጊደና መድህን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ
******************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱ የትግራይ ክልል ካቢኔ ማህበራዊ መሰረታቸው ትግራይ ላይ የሆኑ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አስታወቁ።
ዋና ፀሐፊው አቶ ጊደና መድህን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም ማህበራዊ መሰረታችን ትግራይ ላይ የሆንን ተፎካካሪ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ታስረናል። ተመርዘናል። ተገርፈናል፤ አሁን ግን ኑ ሃሳብ አላችሁ ተብለን ወደ ሥራ ገብተናል። እኔ እንኳን በሙያዬ ክልሉን እንዳገለግል የውሃ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በመሆን ተሹሜያለሁ።
አዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሁሉንም ሃሳብ ያላቸውን የክልሉን ተወላጆች ወደ አመራርነት በማምጣት ፣ በሌላም መንገድ በልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ የበኩላቸውን እንዲሳተፉ በማስቻል በኩል ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አመልክተዋል።
ከዚህ ቀደም በትግራይ ውስጥ የተለየ ሃሳብ ያለው የሚታሰርበት ፣የሚገረፍበት እና የሚገደልበት እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጊደና ፤ አሁን ግን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ህዝቡ ችግር ውስጥ ነው ታስፈልጉታላችሁ፤ የዴሞክራሲ ምህዳሩንም እናሰፋለን በማለት ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ እንድንገባ ተደርጓል። ይህ ደግሞ ለትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን ለመላ አገሪቱ ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38804
ዞኑ ከሚታወቅበት የአብሮነት እሴት ባፈነገጠ መልኩ ንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ እጅግ እንዳሳዘናቸው የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
የመተከል ዞን ከሚታወቅበት የአብሮነት እሴት ባፈነገጠ መልኩ ንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ እጅግ እንዳሳዘናቸው የዞኑ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ
በፌዴራሉ መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል ከመተከል ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሄዷል።
መንግስት ወንጀለኞችን አድኖ ለሀግ ለማቅረብ እያከናወነ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል።
የመተከል ዞን በርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በጋራ የሚኖሩበት ሲሆን በማህበረሰቡ ዘንድ መተሳሰብና አብሮነት መኖሩንም የሀገር ሽማግሌዎቹ አንስተዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የጉሙዝን ብሔረሰብ የማይወክሉ ‘የተደራጁ ሽፍቶች’ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ እነዚህ ሽፍቶች ችግሩ እንዳይከሰት ሲጥሩ በነበሩ የሀገር ሽማግሌዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንም ተናግረዋል።
በጉሙዝ ማህበረሰብ ግጭትን በመፍታት ረገድ ትልቅ ሚና ባላቸው እናቶች ላይ ጭምር ጉዳት ማድረሳቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
በእርሻ ኢንቨስትመንት ስም በአካባቢው የተሰማሩ የጽንፈኛው የህወሃት ጁንታ አባላቶች ወጣቶችን ሰብስበው ለጥፋት ተልኮ ሲያሰለጥኑ እንደነበርም ነው የሀገር ሽማግሌዎቹ የተናገሩት።
ይህንን እያወቁ ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጡ አመራሮች መኖራቸውንም አንስተዋል። በመሆኑም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ አመራሮች ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድም ጠይቀዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለ4ሺ 520 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገና ስጦታ አበረከተ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለ4 ሽህ 520 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በዛሬው እለት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገና ስጦታ አበርክቷል::
በስጦታ መርሐ ግብሩ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ: የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌና ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ ኃላፊዎች እንዲሁም የሃይኖት ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል::
የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌ የስጦታ መርሐ ግብሩን በንግግር ሲከፍቱ በዛሬው እለትም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ኑሮ ከሚመሩ ነዋሪዎች ጋር በዓሉን ለማክበር ታቅዶ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በተሰራው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሐብት በ12ቱም ወረዳዎች በማሰባሰብ ለ4500 ወገኖች ተደራሽ ተደርጏል ብልዋል::
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች : አመራሮች : በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና በበጎ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሐብቶች ለዚህ ስራ ስኬታማነት ለተረባረቡ ሁሉ አቶ አስፋው ምስጋና አቅርበዋል::
በተናጠል ተጉዘን ከሰራናቸው ብዙ ተግባራት ይልቅ ህብረትን ፈጥረን በምክክርና በጋራ የተረባረብንባቸው ጥቂት ስራዎች ፍሬያማ ነበሩ ያሉት አቶ አስፋው፤ ድህነትን ለመቅረፍም ችግረኞችን ከማገዝ ባሻገር ዘላቂ ኑሯቸውን ለማሻሻል የተነደፉ የመንግስት ፕሮግራሞችን በመተግበር ሃገርንም ወገንንም ወደ ለውጥ ምህዋር ውስጥ ማስገባትና ለምናልመው ብልፅግና መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል ነው ያሉት።
በዓሉን በደስታና በፍቅር ከማክበሩ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ ለኮሮና ቫይረስ ትኩረት በመስጠትና የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ እንዲሁም ለተቸገሩ ስጦታ በማበርከት እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈዋል::
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው አስተዳደሩ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በማገዝ ያሳየውን ውጤታማ ተግባር አድንቀው ለዚህ በጎ ስራ የተባበሩና ያስተባበሩ አካላትን አመስግነዋል::
በዓሉን አስመልክቶም በእለቱ ለ149 ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የገንዘብና የበዓል መዋያ ስጦታ ተበርቷክል::
ከ40 በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶች ታድሰው የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት ተመርቀው ለተጠቃሚዎች የተላለፉ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች መሰል የስጦታ መርሐ ግብሮች እስከ በአሉ ዋዜማ ድረስ እንደሚቀጥል አስተዳደሩ አስታውቋል።
“አስዋንን በግል የሚያስተዳድር አካል ሕዳሴ ግድብን ካንተ ጋር ላስተዳድር ቢል አያስኬድም”አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
አስዋንን በግል የሚያስተዳድር አካል ሕዳሴ ግድብን ካንተ ጋር ላስተዳድር ቢል እንደማያስኬድ ዓለምአቀፍ ሕግም እንደማይፈቅድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።
አምባሳደር ዲና የሳምንቱን አበይት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የዲፕሎማቲክ ክንውኖች አስመል ክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የታላቁን ህዳሴ ግድብ አስመልክተው ፣አስዋንን በግል የሚያስተዳድር አካል ሕዳሴ ግድብን ካንተ ጋር ላስተዳድር ቢል አያስኬድም። ዓለምአቀፍ ሕጉም አይፈቅድም። እንዲህ አይነት ነገሮች ላይ ልዩነቶች አሉ ብለዋል።
የታችኛው ተፋሰስ አገራት በሕዳሴ ግድብ ላይ የሚያሳዩት የእግር መጎተት ግድቡ ስለሚጎዳቸው ሳይሆን ግድቡን የማስተጓጎል ወይም የማስቆም ዓላማ ስላላቸው እንደሆነም አስታወቀዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ከአንድ ወር መቋረጥ በኋላ ባለፈው እሁድ በሶስቱ አገራት የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች አማካኝነት ዳግም መጀመሩን ከሳምንቱ አበይት ዲፕሎማሲያዊ ክንውኖች መካከል አንዱ እንደ ነበርም ጠቁመዋል።
በድርድሩ በደቡብ አፍሪካ አስተባባሪነት በአፍሪካ ኅብረት በተሰየሙ የባለሙያዎች ቡድን የቀረበውን የድርድር ሰነድ ኢትዮጵያና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ እንዳልተቀበለችው አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38957
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የገናን በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ሙሳ ፋኪ በዚሁ መልዕክታቸው "ለሁሉም ወዳጆቻችን እና ጓደኞቻችን መልካም ገና፤ እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታችሁ" ብለዋል።

ሊቀመንበሩ የበአሉ አክባሪ ለሆኑ ምዕመናን በአሉ የደስታ እና የጤና እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡
ባንኩ በመግለጫው እንዳስታወቀወ አዲስ የብር ኖት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማሳተም ሥራ ላይ አውሏል። ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በመላ አገሪቱ የብር ኖት ቅያሪ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
በመሆኑም፣ የብር ኖቱ ረጅም ጊዜ እንዲያገለግል በማስብ፡
1) በብር ኖቱ ላይ መፃፍ፣ መቅደድና በቀለም ማበላሸት፣ የትኛውንም ዓይነት ጉዳት ማድረስና ምልክቶቹን ያለፈቃድ ማባዛት የተከለከለና በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን፣
2)ለማስታወቂያ ሥራ ከተፈለገ ግን ለማባዛት የባንኩን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን፣
3) በጣም የተጎዱ የብር ኖቶች ሲያጋጥሙ ከዝውውር ስለሚወጡበት ሁኔታ ዝርዝር መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን የገና በዓልን አስመልክተው ለክርስትና እምነት ተከታዮች የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ
*******************^
(ኢ.ፕ.ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የገና በዓልን አስመልክተው ለክርስትና እምነት ተከታዮች የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል፡፡

"በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" ሲሉ ነው አቶ ደመቀ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት የበአል መልዕክት ምኞታቸውን የገለጹት።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በቃሊቲ ጊዜያዊ ማቆያ ከሚገኙ ከጎዳና ከተነሱ ዜጎች ጋር የገና በዓልን አከበሩ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጋር በመሆ ን በቃሊቲ ጊዜያዊ ማቆያ ከሚገኙ ከጎዳና ከተነሱ ዜጎች ጋር ማዕድ በማጋራት የገና በዓልን አክብረዋል።

በመርሐግብሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፣ በተያዘዉ በጀት ዓመት 8 ሺህ 286 በጎዳና ይኖሩ የነበሩ ዜጎችን በማንሳት የሙያ ክህሎት እና የስነ-ልቦና ስልጠናዎች ተሰጥቷል።

በዚህም እስካሁን በሰባት ክፍለ ከተሞች እና በአቃቂ ጊዜያዊ ማቆሚያ ማዕከል 3 ሺህ 966 የሚሆኑት ወጣቶች ተገቢዉን የሙያ እና የስነ-ልቦና ስልጠና አጠናቀው በደረቅ ቆሻሻ፣ አረንጓዴ ልማት እና መንገድ ጥርጊያ ላይ የስራ እድል ለመፍጠር ወደ ተግባር መገባቱን ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።

ጎዳና ጊዜያዊ የህይወት ማቆያችሁ ሆኖ ቆይቷል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ አሁን ያ ጊዜ አልፎ በሌላ የህይወት ምዕራፍ ላይ ተገኝታችኋል ብለዋል።

አያይዘውም ፈተና ለእናንተ አዲስ አይደለም፤ በጎዳናም ብዙ ፈተና አልፋችሁ መጥታችኋል፤ ስለሆነም የወሰዳችሁትን ስልጠና ወደ ተግባር ቀይራችሁ ወደ ስራ አለም ስትገቡ ለሚገጥማችሁ ፈተና እጅ ሳትሰጡ ራሳችሁንና ሀገራችሁን እንድትለውጡ ሲሉ ወ/ሮ አዳነች የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በማዕከሉ የተሀድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙ ወጣቶች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ከአስከፊው የጎዳና ህይወት አንስቶ የህይወት ክህሎት ስልጠና በመሰጠት የስራ እድል ስለተፈጠረላቸው አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በአቃቂ ክፍለ ከተማ ለሚገኘው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ለገና በዓል ማክበሪያ የሚሆን የዕርድ ሰንጋ በስጦታ ማበርከቱን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የጀግኖች አምባ እና ህፃናት አምባ በተጠናከረ መልኩ እንዲቋቋሙ ይደረጋል - ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ

- የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የገና በአልን አከበሩ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

የጀግኖች አምባ እና ህፃናት አምባ በተጠናከረ መልኩ እንዲቋቋሙ የሚደረግ መሆኑን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ አስታወቁ፡፡

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የገና በአልን አክብረዋል።

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ "የጦር ጉዳተኞቹ ለአገርና ለህዝብ ሲሉ ህይወታቸውንና አካላቸውን የሰጡ በመሆናቸው ልናከብራቸው ይገባል" ብለዋል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ዘላቂ እንክብካቤ ያገኙበትና በስሙ ይኮሩበት የነበረው ጀግኖች አምባ “ከኛ በፊት ጀግንነትም ጀግናም የለም” ይሉ በነበሩ ጽንፈኞች መዘጋቱን አስታውሰው፤ በቀጣይ የጀግኖች አምባ እና ህፃናት አምባ በተጠናከረ መንገድ እንደገና እንዲቋቋሙ የሚደረግ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የትናንቱን የጀግንነት ተግባር መካድ የዛሬን ጀግንነት መካድና ለነገም የማይጠቅም ፍፁም የተሳሳተ ድርጊት መሆኑንም ጠቅሰው፤ እነዚህ ተቋማት ከወደቁበት ተነስተው አገልግሎት እንዲሰጡ መወሰኑን ገልጸዋል።

መንግሥት የአካል ጉዳተኞችን መብት፣ ክብር፣ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የአካል ጉዳተኞችን እንዲሁም የጦር አካል ጉዳተኛ ጀግኖችን ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው "ጀግንነት የትውልድ ቅብብሎሽ በመሆኑ በዚሁ ሂደት ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ተከብረው ዘልቀዋል" ብለዋል።

ለዚህ ክብር የጦር ጉዳተኞቹ ታላላቅ ጀብድ የሰሩና ለአገርና ለህዝብ ህይወታቸውንና አካላቸውን መስዋዕት ያደረጉ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

"በመሆኑም ከጦር ጉዳተኞች ጋር በዓል ማክበር ብቻ ሳይሆን ማዕከሉ ለትውልድ እንዲያገለግል ብዙዎች የሚማሩበትና የዜጎች ኩራት ሆኖ እንዲቀጥል ይደረጋል" ብለዋል።

በየመስኩ የትውልድ ጀግንነት እንደሚቀጥል አውስተው፤ "ጀግንነት ሊከበር፣ ሊወደስና ቦታ ሊሰጠው ይገባል" ብለዋል።

ምክትል ከንቲባዋ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለገሱትን 30 በጎችም በእለቱ አስረክበዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ በደቡብ ሱዳን ቆንስላ ጽህፈት ቤት የሚገኙ አንድ ኢትዮጵያዊም ለማህበሩ 300 ሺህ ብር መለገሳቸውን በፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንዲሁም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል።
የአሜሪካ ምክር ቤቶች የጆባይደንን የምርጫ ውጤት አረጋገጡ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)

የሁለቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች የተሰጡትን የውክልና ድምጾች (ኤሌክቶራል ቮት) በመቁጠር ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጧል።

ኮንግረስ ጆባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሀሪስን የቀጣዮቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ ያገኙትን ድምጽ አጽድቋል።

የተሰጡት የውክልና ድምጾች የጸደቁት የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች በፔንሰልቫንያ እና አሪዞና ግዛቶች የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በመተከል ዞን የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች በመተከል ዞን ህግ በማስከበር ስራ ላይ ለሚገኘው የፀጥታ ሃይል አባላት ሰንጋዎችን አበረከቱ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች በዞኑ ህግ በማስከበር ስራ ላይ ለሚገኘው የፀጥታ ሃይል አባላት ለገና በዓል 210 ሺህ ብር ወጪ የተደረገባቸው ስድስት የእርድ ሰንጋዎችን አበረከቱ።

በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ፀረ ሰላም ሃይሎችን በማደንና በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።

ግብረ ሃይሉ ከዞን እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር በተንኮልና ሴራ ውስጥ የገቡ አመራሮችን የማጥራት፣ ህዝባዊ አንድነትን የማጠናከርና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን የመፍታት ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በአካባቢው በዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሽፍቶችን በማደን ለህግ የማቅረብ ስራም በማከናወን ላይ ነው።

ግብረ ሃይሉ ባከናወነው ተግባር በርካታ አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማቸው እየተመለሱ ሲሆን ህዝባዊ የውይይት መድረኮችም በመካሄድ ላይ ናቸው።

በዚህም ደስተኞች ነን ሲሉ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ለፀጥታ ሃይሉ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት የበዓል መዋያውን ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

ግብረ ሃይሉ በአካባቢው ስላመጣው አንፃራዊ ሰላም ደስተኞች መሆናቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በዳንጉር ወረዳ ህዝቡ ባደረገው ውይይት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨትና ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ አካላት ተለይተው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ ማንኛውንም በዓል በጋራ የማክበርና የአብሮነት ልምድ እንዳለው የገለጹት የአካባቢቅው ሽማግሌዎች "የገና በዓልን በለመድነው አብሮነት እያከበርን ነው" ብለዋል።

ማህበረሰቡ የለገሰውን ስጦታ የተረከቡት ሻለቃ ፍቃዱ ጃፍራ ለተደረገው ድጋፍ ሁሉ በሰራዊቱ ስም አመስግነዋል።
"የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት እስካሁን ውጤታማ ሆኗል። ባገኘናቸው ውጤቶች ላይ፣ ፈጠራ የታከለባቸውን ጥረቶች በማከል ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሕልማችንን እውን እናደርጋለን"

-የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
“የኢትዮ -ሱዳን የድንበር ግጭት የአገሪቱን ልማትና ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች ሴራ ነው” ዶክተር ደመቀ አጭሶበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፖሊቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ሱዳን ለዘመናት አብረው በሰላም የኖሩና ሰፊ ድንበር የሚጋሩ ጎረቤት አገራት ቢሆኑም በቅርብ ጊዜ በድንበር አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከድንበር በዘለለ የኢትዮጵያን ልማትና ሰላም የማይፈልጉ ሃይሎች አገሪቱን የማተራመስ ሴራ መሆኑ ተገለፀ::
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፖሊቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ደመቀ አጭሶ የድንበር ግጭቱን አስመልክቶ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያና ሱዳን ሰፊ ድንበር የሚጋሩ፣ ለዘመናት በሰላም አብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው።
በአገራችን እየተካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር ሂደት ተከትሎ ሱዳን በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት መክፈቷ ያልተለመደ ክስተት መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደመቀ፤ ከግጭቱ በስተጀርባ የአገራችንን ሰላም የማይፈልጉ ግብጾችና የኛው አኩራፊ ሃይሎች መኖራቸው ቅንጣት አያጠራጥርም ብለዋል::
ኢትዮጵያ ከግብጽ ይልቅ የሱዳን ታሪካዊ ወዳጅና አጋር መሆኗን ያመለከቱት ዶክተሩ፤ እ.ኤ.አ በ1973 እስከ 1983 በኮሎኔል ኒሜሪ ዘመን በታሪክ ተረጋግታ የማታውቀው ሀገር ሱዳን ለአስር ዓመታት ያህል በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ እገዛ ሰላም ሰፍኖባት እንደነበር አስታውቀዋል:: በወቅቱ አንፃራዊ ሰላም የሰፈነው ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ኮርድ አማካይነት ለደቡብ ሱዳኖች እውቅና ሰጥታ ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲካተቱ በማገዟ እንደሆነም አመልክተዋል::
እ.ኤ.አ በ1989 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን በያዙት በኮሎኔል ኦማር አልበሽር ዘመንም በደቡብ ሱዳንና በሱዳን መካከል በተፈጠረው ግጭት፣ በተለይ በዳርፉር ግጭት አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይፈጠር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ድርሻ ጉልህ መሆኑንም ጠቁመዋል::
https://www.press.et/Ama/?p=39077
ቦይንግ ስለ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ተስማማ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ቦይንግ ስለ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ከአሜሪካ የደኅንነት እና ጥንቃቄ ባለሙያዎች መረጃዎችን በመደበቅ ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ተስማማ።
የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳለው ከሆነ ኩባንያው "ከግልጽነት ይልቅ ትርፍን" አስቀድሟል።
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በኢትዮጵያ እና በኢዶኔዢያ ተከስክሶ የ346 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ቦይንግ ለመክፈል ከተስማማው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ በአውሮፕላኑ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ የሚከፋፈል ይሆናል።
ቦይንግ እንዳለው ይህ ስምምነት ኩባንያው "ያለበት ጉድለት" ምን ያህል መሆኑን ያሳያል።
የቦይንግ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ዴቪድ ካልሁን እንዳሉት "ወደ እዚህ ስምምነት መግባታችን ትክክለኛው ነገር እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፤ ይህም ከእሴቶቻችን እና ከሚጠበቅብን ምን ያህል ወደ ኋላ መቅረታችንን ያሳያል።"
"ይህ ስምምነት ሁላችንንም የሚያስታውሰን ለግልጽነት የገባነው ግዴታ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ፤ እንዲሁም አንዳችንም እንኳን እርሱን ሳናሟላ ብንቀር መዘዙ የከፋ መሆኑን ነው።"
የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳለው ከሆነ የቦይንግ ባለስልጣናት በኢንዶኔዢያ እና በኢትዮጵያ ለአውሮፕላኑ መከስከስ ምክንያት ስለሆነው ኤምካስ የተባለው አውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ላይ ስላለ ለውጥ መረጃ ደብቀዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ ይህ ውሳኔ የሚያሳው የአውሮፕላን አብራሪው ስልጠና መመሪያ ስለሥርዓቱ በቂ መረጃ አለመያዙን፣ ይህም በተሳሳተ መረጃ የአውቶማቲክ ሥርዓቱ የአብራሪውን ውሳኔ እንደሚሽረውና፣ ይህም አውሮፕላኑ ከማኮብኮቢያው በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አፍንጫውን አዘቅዝቆ ቁልቁል እንዲምዘገዘግ እንደሚያደርገው ነው።
“የትግራይ ሕዝብ የገጠመውን ፈተና ከፌደራል መንግሥት ጎን በመቆም ሊሻገረው ይገባል” ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ
************************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና ከፌደራል መንግሥት ጎን በመቆም ሊሻገረው እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ጥሪ አቀረቡ ::
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በዓሉን አስመልክተው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሕግ ማስከበር ከተጀመረ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው:: በተለይም ሰላምና መረጋጋትን ከማምጣት አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴ አለ፡፡
በዓሉን ለማክበር መሰረታዊው ነገር ሰላም ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ ውጤታማ ሥራዎች በመሥራት ላይ ናቸው ያሉት ዶክተር ሙሉ፣ በዓሉን ተመርኩዞ ዋና አስፈላጊ የሆኑት አስቸኳይ ዕርዳታ የሚፈልጉ አካላትን ማገዝ ነው:: ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወነ ነው ብለዋል ::
ብዙ የትግራይ አካባቢዎችም ከመብራትና ስልክ ጀምሮ ችግር የገጠማቸው በመሆናቸው ይህንንም ለማስተካከል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፣ በክልሉ ባንኮች እንዲከፈቱ መደረጉም የዚህ ትኩረት አካል እንደሆነ ጠቁመዋል::
መብራትና ስልክ እንዲሁም ውሃ ያላገኙ አካባቢዎች በዓሉን በጭለማ እንዳያሳልፉ እየተሠራ መሆኑን የሚጠቁሙት ዶክተር ሙሉ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በመሰረተ ልማት ችግር ምክንያት በተለይም በመንገድ ችግር የዕለት ደራሽ ዕርዳታውን ለማድረስ ችግር ገጥሟል:: ችግሩን በተቻለው ሁሉ በመፍታት ህዝቡ በዓልን በተረጋጋ መንፈስ እንዲያከብር እየተሞከረ ነው ብለዋል::
https://www.press.et/Ama/?p=39072
የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።
በአኢትዮጵያ ላለፉት 27 አመታት የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ ያስተባበረና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሰራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሰራዊቱን ያስጨፈጨፈው የጁንታው ቁንጮ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስታውቀዋል።
ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ዛሬ እንደገለፁት፤ የጁንታው ቁንጮ አመራር ስብሃት ነጋ ከተደበቀበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የጁንታውን ቁንጮ ስብሀት፣ የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀውት እንደነበር ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ገልፀው፤ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ስር አውለውታል።
በተጨማሪም ከመከላከያ የከዱ ሌሎች ከሃዲ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከጁንታው መሪ ስብሃት ነጋ ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
እነዚሁ ከመከላከያ የከዱ የጁንታው ቡድን አመራሮች የጁንታውን ታጣቂ ሀይል በማዋጋትና በማሰልጠን እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፣ በመጨረሻም የጁንታውን አመራር ዙሪያ ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።
እነዚህኑ የጁንታው አመራሮች ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የጁንታው ታጣቂ ሀይልም መደምሰሱን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ተናግረዋል።
በዚሁ መሰረት በቁጥጥር ስር የዋሉት
1. የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት ስብሃት ነጋ
2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር
ሃይሎች ሆስፒታል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች፤
3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ
4. ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመለካከያ የከዳ
5. አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው
ሃላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ
6. አምደማርያም ተሰማ ተወልደ፣ የክልሉ የቅሬታ ሰሚ ፅ/ቤት ኃላፊ
የነበረ
7. ኮማንደር በርሄ ግርማ፣ የክልሉ ልዩ ሀይል ሎጀስቲክ ሀላፊ የነበረ
በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን
8. የሜጀር ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል በመግባት ህይወቷ ማለፉን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልፀዋል።
ሌሎች የጁንታው አመራሮችንም የማደኑ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አስታወቀዋል።
የጁንታው ቃል አቀባይ የነበረው ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረው ዘርአይ አስገዶም፣ የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበረው
አበበ አስገዶም እና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበረው ዳንኤል አሰፋ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር መደምሰሳቸው መገለጹ ይታወሳል።
በተመሳሳይ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ 9 የጁንታው ቁልፍ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ትናንት ተገልጿል።
የገዳ ስርአት ለአለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ አመት የመታሰቢያ በአል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
መርሃግብሩ የተጀመረው በገዳ አባቶች ምርቃት ሲሆን፣ በመርህግብሩ የተገኝኙት የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የምእራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫላ ዋታን ጨምሮ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች እና የተለያዩ እንግዶች ናቸው።
በዝግጅቱ ላይ የገዳ ስርአትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
መርሃግብሩን ያዘጋጀው የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ እና ከምእራብ ጉጂ ዞን ጋር በጋራ በመሆን ነው።
ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ነገም የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል።
‹‹ለሱዳን ትንኮሳ ቸኩለን ምላሽ መስጠት አይገባንም››
-ዶ/ር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ
በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የካርታ ምህንድስና መምህር
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ሱዳን በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ላደረገችው የመሬት ወረራ ትንኮሳ ፈጥኖ የኃይል ምላሽ መሥጠት እንደማይገባ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ አስታወቁ፡፡
ዶ/ር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ለፈፀመው የመሬት ወረራ ቸኩሎ የኃይል ምላሽ መሥጠት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። በተለይም ውስጣዊውን ችግር በተሟላ ሁኔታ መፍታት ባልተቻለበት በዚህ ወቅት ወደ ኃይል ምላሹ መግባት አገሪቱን ያላሰበችው አደጋ ውስጥ ሊጥላት ይችላል፡፡
እንደእርሳቸው ገለፃ፤ ሱዳንም ሆነች ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያሉት ትንኮሳ ዋነኛ አላማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ነው፡፡ በተለይም ሱዳን የቅኝ ግዛት ውልን በማጣቀስ ያደረገችው ትንኮሳ ግድቡ የሚገነባበትን አካባቢ ሰላም በማወክ ውሃውን ከግብፅ ጋር ብቻ የመጠቀም ፍላጎታቸውን ለማስቀጠል ከመሻት ነው፡፡ ከትንኮሳ በስተጀርባም የግብፅ ወታደራዊ መንግሥት እጅ ያለበትና ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግለት ነው፡፡
‹‹የሱዳን ዋነኛ ፍላጎት ቸኩለን እንድንገጥማት ነው›› ያሉት ዶክተር ጥላሁን ይህንን ማድረጉ ደግሞ አገሪቱ ካለችበት ፖለቲካዊ ችግር ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የትንኮሳውን ዋነኛ አላማ በመረዳት ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ እንደሚገባው አመልክተዋል፡፡
መላው ኢትዮጵያውያንም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለአገራቸው ሰላም በህብረት መቆም እንደሚገባቸው የተናገሩት ዶክተር ጥላሁን ለዚህ ደግሞ በብሔርና በጎሳ ለመለያየት የሚደረገውን የጠላት ኃይሎች ጥረት እንዳይሰምር በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=39157