Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከ124 አመት በፊት የአጼ ምንሊክ የክተት አዋጅ
*እግዚእብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ እገር እስፍቶ እኖረኝ ፣ እኔም በእግዚእብሔር ቸርነት ጉዛሁ።እንግዲህ ብሞትሞ ሞት የሁሉም ነውና። ስለ እኔ ሞት እላዝንም ደግሞ እግዚእብሔር አሳፍሮኝ እያውቅም ከእንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ እልጠራጠርም ፣ አሁንም አገር የሚያጠፋ ሀይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚእብሔር የወሰነልንን የባህር በር እልፎ መጥቷልና አሁን ግን ሀገሬን አሳልፌ እልስጥውም ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሽዋ ስው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድርስ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ"
የአድዋ ተጓዧች እዚች ታሪካዊ ከተማ ደርሰው ደማቅ አቀባበል ተድርጎላቸዋል።
ፎቶ ዳኜ አበራ
በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ በመለያ ማእከል ገብቶ የነበረው ግለሰብ ከበሽታው ነጻ መሆኑ ተገለጸ
*************************
(ኢ.ፕ.ድ)

ዛሬ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶበት በመለያ ማዕከል ተለይቶ ክትትል ሲደረግለት የቆየው ግለሰብ ከበሽታው ነጻ መሆኑ ተገለጸ።

ከግለሰቡ ናሙናው ተወስዶ በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አ ታውቋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ለካራማራ ድል በዓል ያስተላለፉት መልእክት
************************

ከዚያድ ባሬ መራሹ የሶማሊያ ወራሪ ኃይል ጋር በነበረን ተጋድሎ ወሳኝ ድል ላስመዘገብንበት የካራማራ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የ1967ቱ የሶማሊያ ወረራ ሀገራችን ከአብዮት ፍንዳታው ጭጋግ ባልወጣችበትና የእርስ በርስ ግጭት ላይ በነበረችበት ጊዜ የተከሠተ ነው።

ኢትዮጵያን የወረሩ አብዛኞቹ ኃይሎች እንደሚሠሩት ስሕተት ዚያድ ባሬም ተሳሳተ።

ሀገር የደከመች መስሎት ኢትዮጵያን የማሸነፊያ ጊዜ የደረሰለት መሰለው። በዚህ የተሳሳተ ስሌት ተመርቶ ወረራውን ፈጸመ። በመጀመሪያ አካባቢ እንዳሰበውም የጎላ መከላከል ሳይገጥመው ሰፊ የሀገራችንን መሬት ማካለል ችሎ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን እንደፍግ ተኝተው እንደ እቶን በተነሡ ጊዜ ምን እንደሚያደርጉ በዚህ ወረራ ጊዜ ታየ።

በአጭር ጊዜ “የእናት ሀገር ጥሪ” የተሰባሰቡ፣ በቂ የሥልጠናም ሆነ የዝግጅት ሁኔታ ያልነበራቸው፣ ነገር ግን ከየትም የማይበደሩት የሀገር ፍቅርና የማሸነፍ ወኔ ያላቸው ውድ ኢትዮጵያውያን ወረራውን በስኬት መቀልበስ ቻሉ።

መንግሥታትን በሀገር ውስጥ ክዋኔያቸው በአንድም በሌላም ልንመዝናቸው እንችላለን። ነገር ግን የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ለማስጠበቅ የሚከፈሉ መሥዋዕትነቶች በየትኛውም ዘመን ቢፈጸሙ የሀገራችን ታሪካዊ ኩራት ናቸው።

የደርግ መንግሥትም በአጭር ጊዜ ጥሪ አቅርቦ፣ አሠልጥኖና አደረራጅቶ የሀገርን ክብር ለማስመለስ ያደረገው ተጋድሎና ያስመዘገው ድል የሁላችንም የኢትዮጵያውያን የአልበገር ባይነትና ለሀገር የመሥዋዕትነት የመክፈል ታሪካችን አካል ነው።

ሁሌም በውስጣችን ክፍተት ሲኖር የውጭ ጠላት እንጋብዛለን፤ ስንጠናከር ግን የታፈርንና የተከበርን እንሆናለን።
የአለም ባንክ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብርን ለመደገፍ 25 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ በኢትዮጵያ የአለምባንክ ዳይሬክተር ሚስ ካሮላይን ተርክ ጋር ተነጋግረዋል።

ዳይሬክተሯ የአለም ባንክ የተማሪዎች ምገባን ለመደገፍ 25 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑንም ገልፀዋል።

የተቋሙ ድጋፍ የከተማ ልማት አቅም መደገፊያ/Urban Productivity Safety Net Program/ አካል ነው።

የአለም ባንክ የከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ያሉ የልማት ስራዎችን በቀጣይነት እንደሚደግፍ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል

እስከ የካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ 15541 ዜጎች በአዋጁ መሰረት ወደ ተቀባይ አገራት ተሰማርተዋል

የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከተጀመረ ጀምሮ መንግሥት የሥራ ስምምነት ወደ አደረገባቸው አገራት የሥራ ዕድል አግኝተው ወደ ሣውዲ ዐረቢያ፣ ኳታር፣ ጆርዳን፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ 15541 ዜጎቻችን ለሥራ ተሰማርተዋል፡፡ እነዚህ ዜጎቻችን በህጋዊ መንገድ መጓዛቸው ክብራቸው መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ዓይነት የጉዞ ወጪ ሳያወጡ በነፃ በውጭ ሀገር ለሥራ የተሰማሩ ናቸው፡፡

ህብረተሰባችንም በህጋዊ መንገድ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ተጀምሮ ዜጎች ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑን ተረድቶና ተገንዝቦ ልጆቹን ከህገ-ወጥ ደላላና ከህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ከህገ-ወጥ የበረሃ ጉዞ እንዲታቀቡ ለማሳሰብ እየወደድን ከላይ የተገለፀው ዳታ በየክልሉ እንደሚከተለው ተመላክቷል ፡፡
የብልፅግና ፓርቲ አመራር አካላት ከጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድና የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ እ/ር ታከለ ኦማ የአዲስ አበባ ገዳናዎችን የማፅዳትና ባለፈው ክረምት የተተከሉ ችግኞችን ተንከባከቡ።
ቤቲ ጂ (ብሩክታዊት ጌታሁን) የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በጎ ፈቃደኛ አምባሳደር ሆና ተመረጠች
ለቦይንግ 737 አውሮፕላን ሰለባዎች የሙት አመት መታሰቢያ ተደረገ
************************
(ኢ.ፕ.ድ)

መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ET302 ማክስ 8 አውሮፕላን የተከሰከበት ቦታ ላይ ዛሬ የሙት አመት መታሰቢያ ስነስርአት እየተከናወነ ይገኛል።

ስነስርአቱ የተዘጋጀው በአካባቢው ነዋሪዎች ሲሆን በሚልኪ የማስታወቂያ ስራዎች አስተባባሪነት የሚከናወን መሆኑን የሚልኪ አድቨርታይዚንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ቀልቤሳ መገርሳ ተናግረዋል።

በስነስርአቱ ለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ጸሎት ያደረጉ ሲሆን የአካባቢው ፈረሰኞች ዛሬ ለአመት የዘለቀው ሀዘን የሚያበቃበት ቀን መሆኑን ለማሣወቅ ጥቁርና ነጭ ሰንደቅ አላማዎየችን በመያዘ ተገኝተዋል። አባ ገዳዎችም ምስጋና አቅረበዋል።

በአውሮፕላኑ ተሣፍረው የነበሩ የ33 አገር ዜጎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉና ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታውጆ እንደ ነበር ይታወሳል።

ዘገባ እና ፎቶ በራስወርቅ ሙሉጌታ
የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨባቸው ሃገሮች
/ የካቲት 30, 2012 / ከቀኑ 10:00 ሠዓት /

★ ጣሊያን (Italy)
※ 7,424 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 1,541 ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።
※ 366 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። ከእነዚህ መካከል 133 ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ ሞተዋል።

★ ኢራን (Iran)
※ 7,161 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 595 ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።
※ 237 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። ከእነዚህ መካከል 43 ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ የሞቱ ናቸው።

★ ደቡብ ኮሪያ (South Korea)
※ 7,478 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 165 ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።
※ 53 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። ከእነዚህ መካከል 2 ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ የሞቱ ናቸው።

የሌሎች ሃገሮች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት

★ ስፔን (Spain)
※ በስፔን 235 አዲስ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በአጠቃላይ 909 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

★ ጀርመን (Germany)
※ በጀርመን 200 አዲስ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በአጠቃላይ 1,112 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

★ አልባኒያ (Albania)
※ አልባኒያ 2 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ስዎች እንዳገኘች ሪፖርት አድርጋለች።

★ ግብጽ (Egypt)
※ ግብጽ በቫይረሱ የመጀመሪያ ሰው (1 ሰው) እንደሞተባት ሪፖርት አድርጋለች።

መልካም ጤንነት!!

EthioTena - ኢትዮጤና
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ (face mask) አጠቃቀምና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው ልብ ይበሉ::
***********************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (face mask) አጠቃቀሙና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው በቅጡ ባለመረዳት ሰዎች ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ሲዳረጉ ይስተዋላል፡፡

ለመሆኑ ማስክ መጠቀም ያለባቸው እነማን ናቸው?

ጤና ሚኒስቴር መልስ አለው ....

1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የሚያስፈልገን በበሽታው የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው አጠገብ ወይም እየተንከባከብን ከሆነ ብቻ፣

2. ሳልና ትኩሳት ካለብን ለሌላው ጥንቃቄ በማድረግ ሲያስለን ወይም ሲያስነጠሰን ነው። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ሰው የሚበዛበት ቦታ ከመሄድ ራስን መቆጠብ ፣ እጅ በደንብ መታጠብ ፣ መጨባበጥ ማቆም እና ማስኩን በስርዓት ማስወገድ እና ለባለሙያ ማሳወቅ ያስፈልጋል::

3. የማስክ አጠቃቀምም ውጤታማ የሚሆነው እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ ሲቻል እና አወገገዱም ጥንቃቄ የተሞላበት ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ህብረተሰባችን መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

የበለጠ መረጃ ሲያስፈልግ ነጻ በሆነው 8335 የስልክ መስመር ላይ መደወል ይቻላል፡፡