Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የክልሉ ምክር ቤት የ4 የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሱትም፡-
1. አቶ አድጎ አምሳያ
2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ
3. አቶ ግርማ መኒ
4. አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የቀረቡትን የ4ቱን የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ በደረሰው ሞት፣ ጉዳትና መፈናቀል እጅግ ማዘናቸውን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የማያመው እና የማያወግዝ ሊኖር አይገባም ብለዋል፡፡
በዞኑ የተፈጠረው ችግር የከፋ ያደረገው አመራር የተሳተፈበት መሆኑን የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት፣ ዞኑን ከመረጋጋት አልፎ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ በድርጊቱ በተሳተፉ አካላት ላይ የተጀመረው የህግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ያኮረፉ አካላት፣ ህዝቦች እንዳይረጋጉና በሠላም እንዳይኖሩ እያደረጉ በመሆኑ ከመንግስት ቁርጠኛ እርምጃ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡
እናቶች፣ ህጻናትን ጨምሮ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ለተፈናቀሉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ፣ አካባቢውን አረጋግቶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መሥራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታደለ ተረፈ፣ በመተከል ዞን በዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት እጅግ አሳዛኝና ሊደገም የማይገባው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ተጨማሪ ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት እንዳይከሰት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን የክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
‹‹ተቃዋሚዎችም ብቻ ሳይሆን እንደ እኔ ያሉ የፖርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦች የተካተቱበት ስለሆነ አሁን ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አቃፊ ነው››
- ዶክተር አሰፋ በቀለ የትግራይ ክልል መንገድና
ትራንስፖርት አስተባባሪ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ የፖለቲካ አባላትና አባል ያልሆኑ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተካተቱበት መሆኑን የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ ተናገሩ::
ከአማራ ክልልና የፀጥታ አካላት ጋር በመነጋገር ከመቐለ አዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት መጀመሩም ተገልጿል::
የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ ፖለቲካዊ እሳቤ ያዙ ሰዎችን ያቀፈ ነው::በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ ሆነው ህዝብን ለማገልገል ፍላጎት ያላቸውን አካላት ጭምር በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ውስጥ አካትተዋል::
‹‹ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ብዙ ጉድለት ነበረበት::አሁን ባለው አስዳደር ግን በፖለቲካ አመለካከት ሳይገደብ ህዝብ ማገልገል ተችሏል፤” ያሉት ዶክተር አሰፋ፤ አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊ በመሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ አባላት በጊዜያዊ አስተዳደር ታቅፈው እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል::“እኔን ጨምሮ የፓርቲ አባል ያልሆንን ግለሰቦች ህዝቡን በማገልገል ላይ እንገኛለን›› ብለዋል::
https://www.press.et/Ama/?p=38379
የሕወሓት ጁንታ ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ተገኙ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሕወሓት ጁንታ በተደጋጋሚ ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር እና አስመራ ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው መገኘታቸውን የልዩ ዘመቻ ኮማንድ አስታወቀ።
የመከላከያ ሠራዊት መቐለ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ የልዩ ዘመቻ ኮማንድ 2ኛ ብርጌድ አንድ ወጋገን ሻለቃ ባደረገው አሰሳ እና ፍተሻ በመጋዘን ውስጥ ያልተተኮሱ 13 ሮኬቶች የተገኙ ሲሆን፣ 7 ሮኬቶች ደግሞ ከማስቀመጫው ሳጥን ወጥተው ተተኩሰው እንደነበርም አስታውቋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ፤ በተጨማሪም የተተኳሽ ሮኬት ማስወንጨፊያ ከባድ ተሽከርካሪ ከመቐለ ከተማ ዳርቻ ባለ ስፍራ ተደብቆ ተገኝቷል።
20 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ለመከተብ የሚያስችል የኮሮና ክትባት በቅርቡ አገር ውስጥ ይገባል ተባለ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
ከኮቫክስ የተገኘውና 20 በመቶ ለሚሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የኮሮና ክትባት በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚመጣ የጤና ሚኒስትሯ አስታወቁ።
ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለደሃ አገሮች በዕርዳታ መልክ ለማቅረብ ካቀደው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ውስጥ፣ ኢትዮጵያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት መጠን በጥቂት ወራት እንደምታገኝ የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ማስታወቃቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገልጿል።
የመቀሌ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ 15 አባላት ያሉት የመማክርት ኮሚቴ አቋቋመ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በዛሬው እለት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ውይይት ላይም የንግዱ ማህበረሰብ 15 አባላት ያሉት መማክርት ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ከመቀሌ ከተማ ኮምንኬሽን ፅ/ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ይህ ኮሚቴም በነገው ዕለት ተሰብስቦ የራሱን አመራሮች እንደሚመርጥ ታውቋል።

የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬው ውይይት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፤ በዋናነትም በከተማዋ ያለው የፀጥታና የማረጋጋት ስራ በትኩረት እንዲሰራ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ የንግዱ ማህበረሰብ በተረጋጋ መንገድ ስራውን ለመስራት ፍራቻ እንዳላበት በውይይት ላይ የተሳተፉ የምግዱ ማህበረሰብ አባላት መግለፃቸው ተጠቁሟል።

ከገንዘብ ቅያሬው ጋር በተያያዘ በክልሉ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው የንግዱ ማህበረሰብ በእጁ ላይ ያለውን ገንዘብ መቀየር ባለመቻሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለዚህ ችግር መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል ተብሏል።

አሁን ላይ በከተማዋ የኢትዮጵያ ንግድ አገልግሎት በመሰጠት ላይ መሆኑ የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሱት ነጋዴዎቹ፤ በተመሳሳይ የግል ባንኮችም ስራ እንዲጀምሩ ጥያቄ አቅርበዋል።

የሌሎች ባንክ ደንበኛ የሆኑ በከተማዋ ያሉ ነጋዴዎች የባንክ ሂሳባቸውን ለማንቀሳቀስ መቸገራቸውን ገልፀው አሁን ላይ ገንዘብ ይላክላቸውን ስራ ይጀምሩ መባሉንም ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ ያለው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት የከተማዋ ትልቁ የንግድ ማዕከል የሆነው ቀዳማዊ ወያኔ የተባለው ገበያ ስራ እንደሚጀምር ከኮምንኬሽን ቢረ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በከተማዋ በአሁኑ ወቅት መደበኛ የትራፊክ ፖሊስ እና የታክሲ አገልግሎት ስራ የጀመረ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ አድርገው የነበሩ ታክሲዎችም ወደ መደበኛ ታሪፍ እንደተመለሱና በመደበኛ መስመር ላይ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

በሀይማኖት ከበደ
“የህወሓት ጁንታዎች ለዉጡን የተቃወሙት በራሳቸዉ ቁመትና ስፋት ልክ ከሰፋት የአገዛዝ ስርዓት ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ነዉ”
አቶ ሌንጮ ለታ
የቀድሞ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር
******************
(ኢ ፕ ድ)

“የህወሓት ጁንታዎች ለዉጡን የተቃወሙት በራሳቸዉ ቁመትና ስፋት ልክ ከሰፋት የአገዛዝ ስርዓት ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ነዉ” ሲሉ የቀድሞ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተናገሩ።

የህዝቡ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት በአምባገነቱ የሕወሃት ጁንታ እጅ ውስጥ በመውደቁ ሲመኝ የነበረዉ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ መክኖ መኖሩንም ነው አቶ ሌንጮ ያብራሩት።

አቶ ሌንጮ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት የታገሉለት የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ በአምባገነቱ የሕወሃት ጁንታ እጅ ወድቆ ኖሯል።

በዚህም ምክንያት ህዝቡ ሲመኝ የነበረዉ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት መክኖ መቆየቱን የጠቀሱት አቶ ሌንጮ፤ አለም የህወሓት ጁንታ ፍጹም አምባገነንነትን እንዳያዉቅበት ክልሎችን በሞግዚትነት በራሱ ሰዎች አማካኝነት ሲያስተዳድር መኖሩን ተናግረዋል።

እንደ አቶ ሌንጮ ገለጻ፤ ጁንታው ዴሞክራሲን እራሱ እንዳመጣ አስመስሎ ሲሰብክ ቢቆይም እዉነቱ ግን የዴሞክራሲ ጸር መሆኑ ከተግባሩ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለ መብቱ የሚጠይቅን ዜጋ ሲያፍን፣ ሲገድል፣ አካል ሲያጎድልና በእስር ቤት ሲያሰቃይ ኖሯል። ይህ እወነታ ለአገርም ሆነ ለአለም ግልጽ ሆኗል።

ጁንታው በአገሪቷ የተደረገውን ለዉጥ የተቃወመው አባላቱ በራሳቸዉ ቁመትና ስፋት ልክ ከተሰፋዉ የአገዛዝ ስርዓት ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ነዉ ብለዋል አቶ ሌንጮ።

ላለፉት 27 አመታት በጁንታው አገዛዝ ምክንያት ታፍኖ የኖረውና አሁን በየአከባቢዉ እየፈነዳ ያለዉ የዘመናት ብሶት በአግባቡ ካልተስተናገደ አገራችንን ወደ አደገኛ ቀዉስ ሊወስዷት ይችላልና ጥንቃቄ ያስፈልጋልም ነው ያሉት አቶ ሌንጮ።

በዋቅሹም ፍቃዱ
‹‹ቀድሞ በነበረው የበሰበሰ ርዕዮተ ዓለም መገለባበጥና መዋሸት የለመዱ አካላት እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዳይተገበር እንቅፋት እየሆኑ ነው›› አቶ አባተ ኪሾ የቀድሞው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
***************************
(ኢ ፕ ድ)
በኢህአዴግ ዘመን በነበረው የበሰበሰ ርዕዮተ ዓለም መገለባበጥና መዋሸት የለመዱ አካላት እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዳይተገበር እንቅፋት እየሆኑ ነው ሲሉ የቀድሞ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባተ ኪሾ ገለጹ። እውነተኛ ፌዴራሊዝም ባለመኖሩ ለ30 ዓመታት ክልል ከክልል ብቻ ሳይሆን ቀበሌ ከቀበሌም እርስበእርስ እንዲጠራጠሩ ማድረጉንም አመልክተዋል።
አቶ አባተ ኪሾ፣ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታየው ቀውስ እውነተኛ ፌዴራሊዝም ካለመተግበሩ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። አሁንም ትክክለኛ ፌዴራሊዝም እንዳይተገበር የሚያደርጉት ቀድሞ በነበረውና በበሰበሰው የኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ሲገለባበጡና ሲዋሹ በነበሩ አካላት ናቸው።
ችግሩ ያለው በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም የአገሪቱ ክፍሎች በመኖሩ ሊታዩና ሊፈተሹ የሚገባቸው ብዙ ናቸው ያሉት አቶ አባተ፣ በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለው የቀድሞውን የፖለቲካ ድፍድፍ በአግባቡ ሳይጠራ የጠጣ ኃይል እንዳለ ነው ብለዋል።
ያ ስካር እስካሁን ያለቀቀው እንዳለ ጠቁመው፣ ይህ ሃይል የሚሰራውን እንደማያውቅ አስታውቀዋል። የበሰበሰው ርዕዮተ ዓለም አሁንም ድረስ አገሪቱን በማመስ ላይ የሚገኘውም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።
የዚህ ርዕዮተ ዓለም ተከታዮችና የበሰበሰውን ሃሳብ ለማሳካት የሚንገታገቱ ቡድኖች በየቦታው መኖራቸውን የሚናገሩት አቶ አባተ፤ ስለዚህም መመልከት ያለብን አንድን አካባቢ ብቻ ሳይሆን በየአቅጣጫው ነው ብለዋል። የበሰበሰው ርዕዮተ ዓለም ቫይረሱ በብዙ ቦታ የተዳረሰ ከመሆኑ አኳያ ሁሉንም ቦታ በአግባቡ በመፈተሽ ቫይረሱን ማምከን የግድ እንደሚልም ተናግረዋል። ይህ ካልሆነ ግን የታለመው እውነተኛ ፌዴራሊዝም ተተግብሮ ማየት የማይቻል መሆኑን ገልጸዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38453
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ በድጋሚ ተጀመረ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው ከ1ዐዐ ሺህ ብር በታች የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ድጋሚ መጀመሩን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
ባንኩ እንዳስታወቀው፤ መንግስት በክልሉ በወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬው ተቋርጦ እንደነበር አስታውሶ አሁን ላይ በተወሰኑ የክልሉ ከተሞች የመብራትና የኢንተርኔት አገልግሎት በመጀመሩ በእነዚሁ አካባቢዎች ባንኮች ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ መሰረት ተቋርጦ የነበረውን የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ባንኮች ሥራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ አሮጌ ብር እንዲቀይሩ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ጀምሮ መወሰኑንም ነው ባንኩ ያስታወቀው።
ባንኮችም ይህንኑ ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ በመጠቆም በብር መቀየሩ ሂደት የነበሩ መመሪያዎችና አሠራሮች እንደተጠበቁ መሆናቸውንም ገልጿል።
ከባንክ በጥሬ ገንዘብ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ላይ በተሻሻለው መመሪያ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን ከ1ዐዐ ሺህ እስከ 1.5 ሚሊየን አሮጌ ብር ያላቸው የመቀየሪያው የጊዜ ገደብ የህግ ማስከበሩ ከመጀመሩ በፊት የተጠናቀቀ በመሆኑ ብር መቀየር የሚችሉት ከ1ዐዐ ሺህ ብር በታች ያላቸው መሆናቸውን ባንኩ አስታውቋል።
ባንኮችም ይህንኑ ሥራ የሚከታተል ግብረ ኃይል በማቋቋም መመሪያን በጠበቀ መልኩ እንዲሠሩ እና በእያንዳንዱ የባንክ ቅርንጫፍ የብር መቀየር ሥራ የተጀመረበትንና የተጠናቀቀበት ቀን እና የተለወጠ የብር መጠን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሳምንቱ ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳስቧል።
ከመስከረም 6 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ወራት በመላ ሀገሪቱ አሮጌ ብር በአዲስ ብር የመቀየር ሥራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል።
በትግራይ ክልል ባንኮች ስራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ አሮጌ ብርን እንዲቀይሩ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን ጀምሮ መወሰኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል በህግ ማስከበር ዘመቻው የፈጸመው ግዳጅ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል ከእዞችና ከሌሎች የሠራዊት አሀዶች ጋር በመጣመር በህግ ማስከበር ዘመቻው የፈጸመው ግዳጅ ውጤታማ እንደነበር የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ በቀለ ገለጹ፡፡
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉ በተለይም በራያና በምዕራብ ግንባሮች በጁንታው ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ሀያልነቱን አስመስክሯል ብለዋል፡፡
አዲቀይህ አካባቢ በነበረው ፈታኝ ግዳጅ የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉ የኮማንዶ ዩኒት በጁንታው ጀርባ በኩል ምሽግ ሰብሮ በመግባት የፈጸመው ጀብዱ ለወገን አኩሪ እንደነበር የገለጹት ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ፣ እስከ መቀሌ በነበረው ተልዕኮም ውጤታማ ግዳጅ መፈጸሙን አስረድተዋል ፡፡
በምዕራቡ ግንባርም ከሁመራ እስከ ዳንሻ የሚሸሸውን የጁንታ ተዋጊ የማገትና የመቆጣጠር ስራ ተሰርቷል ፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተንጠባጠበውን የህወሀት ታጣቂ በማደን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉ ከህግ ማስከበር ዘመቻው በተጓዳኝ ፣ በምዕራብ ወለጋና በመተከል ሽፍቶችን የመደምሰስ ተልዕኮውን በተሳካ መንገድ በመፈጸም ላይ ይገኛልም ብለዋል ፡፡
የተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው ፍትሀዊ ስለነበረ እግረኛው ፣ ሜካናይዝዱ ፣ ልዩ ሀይሉ ፣ አየር ሀይሉ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በጥምረትና በቁርጠኝነት እንዲሁም በብልህ የጦር አመራር የተፈጸመ ዘመቻ በመሆኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ያኮራ ተግባር ተፈጽሟል ያሉት ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ፣ ህዝባችን እስካሁን እያደረገ ያለው ድጋፍ ለውጤቱ መሰረታዊ ድርሻ እንደነበረው መግለጻቸውን ከመከላኬ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
“አሁን በየቦታው የምናየው ግጭቶችና አለመግባባቶች ጁንታው ለአገራችን ያስቀመጣቸው አደገኛ የቤት ስራዎች ናቸው” አቶ ሌንጮ ለታ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
አሁን በየቦታው የምናየው ግጭቶችና አለመግባባቶች የህወሀት ጁንታ ባለፉት 27 ዓመታት ለአገራችን ያስቀመጣቸው አደገኛ የቤት ስራዎች መሆናቸውን የቀድሞ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ አስታወቁ። ህዝቡ እውነታውን በአግባቡ በመገንዘብ ለአገሩ ከልብ በመስራት ሰላም እንዲያወርድ ጥሪ አቀረቡ።
አቶ ሌንጮ ለታ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉትቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፣ መላው ህዝባችን ለዘመናት የታገለለት የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ በአምባገነኑ የሕወሓት ጁንታ እጅ በመውደቁ ሲመኝ የነበረው ራስን በራስ የማስተዳደር ተስፋው መክኖ ቆይቷል።
በአገራችን የዴሞክራሲ ስርዓት ታይቶ በመጥፋቱ በህገ መንግስቱ የተደረደሩት የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚሉና ሌሎችም የዴሞክራሲ መርሆዎች በጁንታው በሀይል መታፈናቸውን ጠቁመው፣ ዛሬ ላይ ህዝቡ በተወሰነ መልኩ መብቱንና ግዴታውን መለማመድ መጀመሩን አስታውቀዋል።
አሁን በየቦታው የምናየው ግጭቶችና አለመግባባቶች ጁንታው ባለፉት 27 ዓመታት ለአገራችን ያስቀመጣቸው አደገኛ የቤት ስራዎች መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ሌንጮ፣ ህዝቡ እውነታውን በአግባቡ በመገንዘብ ለአገሩ ከልብ በመስራት ሰላም እንዲያወርድ ጠይቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38543
የክልሎች ሕገመንግሥት የዜጎችን በአገራቸው የመኖር መብት የነፈገ መሆኑ ተገለጸ
👉በሀገሪቱ እየተፈጠሩ ላሉ ግጭቶች መሰረት መሆኑም ተጠቆመ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የክልሎች ሕገመንግሥት የዜጎች በአገራቸው የመኖር መብት የነፈገ በመሆኑ በየቦታው ግጭቶች እንዲበራከቱ ማድረጉን የሕግና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ገለጹ።
በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ታሪክ መምህሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ ሕገመንግስት መልካም ነገሮች እንዳሉት ሁሉ ክፋት ያዘሉ ሕጎችም የተካተቱበት ነው። በተለይም ከክልሎች አወቃቀር ጀምሮ ያለው የብሔር፣ የቋንቋ አስተሳሰብ ብዙ ነገሮችን አዛብቷል።
ከእነዚህ መካከል ክልሎች ሕገመንግስት ሲያረቁ አግላይ እንጂ አቃፊና አሳታፊ እንዲሆን አድርገው እንዳልሆነ ያመለከቱት ዶክተር አልማው ፣ ልዩነቱ ገዝፎ አንድ ብሔር በአንድ ክልል ላይ ፈላጭ ቆራጭ እንዲሆን ማድረጉን አስታውቀዋል ።
አገሪቱ ስትሰራ በሕዝቦች መስተጋብር፣ በሕዝቦች ትግል፣ በሕዝቦች ተሳትፎ እንጂ በአንድ ብሔር ማንነትና ብልጽግና እንዳልሆነ የሚያነሱት ዶክተር አልማው፤ የክልሎች ሕገመንግሥት አቀራረጽ ግን ከዚህ የተለየ እንደሆነ አመልክተዋል ።
“የክልሎች ሕገመንግሥት ሲቀረጽ ልዩነቶችን አግዝፎ ሕብረ ብሔራዊነትን አክስቶ ያቀርባል። በሕግ የተሰጠን የባለቤትነት መብት የእኛ ብቻ ነው በሚል በውጣልኝ አስተሳሰብ ተገንብቷል። ይህ ደግሞ ዜጎች በፈለጋቸው ቦታ የመኖር መብታቸውን ከመንፈጉም በላይ ያፈሩትን ሀብት ጭምር ለዚያ ክልል እንዲያስረክቡና ባዷቸውን እንዲሰደዱ ያደርጋል። ግጭቶችም ቢሆኑ የአገር ይገባኛል ባይነት ጥያቄዎች የፈጠሯቸው ናቸው” ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38522
ግብጾች በአምባሳደር ዲና ገለጻ 'አንድ አንድ ሃይሎች' በሚል የተገለጽነው እኛ ነን ካሉ ኢትዮጵያ ግብፅን ወክላ መከራከር አይቻላትም ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮቻችን ገለጹ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በሳምንታዊው የሚኒስቴሩ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ "አንዳንድ ሃይሎች ሱዳንን ከወዳጅ ሀገር ኢትዮጵያ በድንበር ውዝግብ ሰበብ ግጭት ውስጥ እንድትገባ በመገፋፋት፣ ቀጣናውን በማተራመስ የውስጥ ችግሮቻቸውን አቅጣጫ ለማሳት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው" በሚል ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር አሕመድ ሀፊዝ “ግብፅ የግድቡን ግንባታ የምትቃወመው በሀገሪቱ ያለባትን ቀውስ ለማቀዝቀዝ ነው ማለታቸው ተገቢ አስተያየት አይደለም” ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል፤ በዚሁ መግለጫቸው አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጠቅሰው ወቀሳ ሰንዝረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጉዳዩን ለማጣራት ጥረት አድርጓል።

በዚህም መሰረት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮቻን ያገኘው መረጃ አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው የማንንም አገር ስም ያልጠቀሱ ሲሆን፤ የእርሳቸውን ማብራሪያ ተከትሎ ኬንያ ፣ ጂቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን ወይም ሶማሊያ እኛን ይሆን ብለው እንዳልተጨነቁ እና ማብራሪያም እንዳልጠየቁ አረጋግጠናል።

በተቃራኒው ከግብፅ በኩል የአምባሳደሩ ማብራሪያ በርግጠኝነት እኛን ማለት ነው የሚሉ ድምፆች በይፋ እየተደመጡ ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮቻችን፤ ግብፆች ስም ባንጠቅስም የምንሰራውን እናውቃለንና በትክክል እኛ ነን ካሉ ኢትዮጵያ ግብፅን ወክላ መከራከር አይቻላትም ሲሉ ጉዳዩን አጣጥለውታል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ የንባብ ሳምንት ጉባዔ እየተካሄደ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሀዲስ አለማየሁ ተቋምና ከአማራ ክልል ባህል ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር " መጻህፍት የእውቀት ገበታ፤ መዛግብት የዘመን ትውስታ" በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት የፓናል ውይይትና አውደ ርዕይ በደብረ ማርቆስ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ሁነቱ ለትውልድ የንባብ ባህል በማካፈልና አንባቢ ትውልድ በመፍጠር እንዲሁም ለአገሩ የሚጠቅም ዜጋ ለማፍራት እንደሚረዳ ተመላክቷል።
በተለይም የመረጃ ቋት የሆኑት ቤተ መጻፍትና ቤተ መዛግብት የዘመኑን ቴክኖሎጂ እንዲዋጁ አቅጣጫ ለማስቀመጥም መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ኤጀንሲው ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ከክልሎችና ከከተማ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎችና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የንባብ ሳምንት ማዘጋጀት ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ 888 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገለጸ
👉56 ሽልማቶችን ለባለ ዕድለኛ ደንበኞቹ አስረከበ
***********************
( ኢ ፕ ድ)
የ‹‹ይቆጥቡ ይሸለሙ›› ፕሮግራም ከተጀመረበት ከ2004 ዓ.ም ወዲህ በየዓመቱ በአማካኝ ከ2 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት የባንኩን ጠቅላላ ሀብት 888 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የ‹‹ይቆጥቡ ይሸለሙ›› የ10ኛ ዙር የሽልማት መርሐ ግብር ላይ ለባለ ዕድለኛ ደንበኞቹ ሽልማታቸውን ባስረከቡበት ዕለት እንደገለጹት፤ ባንኩ ይህን ሽልማት ከመጀመሩ በፊት የነበረው ጠቅላላ ሀብት 74 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ ሽልማቱን በጀመረ በአስር ዓመት ውስጥ 888 ቢሊዮን ብር መድረስ ችሏል ብለዋል።
እንዲሁም ከአስር ዓመት በፊት 2 ነጥብ 2 የነበረውን የቁጠባ ሂሳብ ብዛት ከ26 ሚሊዮን በላይ በማሳደግ 56 ቢሊዮን ብር የነበረውን ጠቅላላ የባንኩን ተቀማጭ ገንዘብ ወደ 670 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
ባንካችን የውጭና የሀገር ውስጥ ገንዘብ ለማሰባሰብ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል አንዱ የ‹‹ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ›› እና ‹‹ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ›› ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህ ስልት ህብረተሰቡ የቁጠባ ባህሉን እንዲያሳድግ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38593
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የህውሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተሸብበው በሀሰት ዘገባ ላይ ተጠምደው እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በትግራይ ክልል የተወሰደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ትክክለኛ ገጽታ ወደጎን በመተው የህውሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተጠምደው የሀሰት ዘገባ ሲያሰራጩ እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በኩል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ላይ እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ ሚዲያው የህውሓት ጁንታ በሚነዛው የሐሰት መረጃ ተሸብቦ የሀሰት ዘገባ ሲያሰራጭ እንደነበር በግልጽ የታየበት ሁኔታን መመልከት ተችሏል።
ይህ የሚዲያዎች ሁኔታ ትምህርት የተወሰደበት ነው ያሉት አቶ ደመቀ፤ በፕሮፓጋንዳ የተደገፈውን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አስተሳሰብ ለመለወጥ ራሱን የቻለ ስራ እንደበነረም አብራርተዋል።
"ሁኔታው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን በጁንታው የሐሰት መረጃ ተሸንፈው የፌዴራል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ እንደሆነ መዘገባቸውን ያየንበትና ትምህርት የውስድንበት ነው" ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
የዓለም አቀፍ ሚዲያው መሬት ላይ ለው እውነት ከመፈለግ ይልቅ የጁንታውን የሐሰት ወሬ በማራገብ የህግ ማስከበር እርምጃው ቡድኑን ለማጥቃት እንጂ ህግን ለማስከበር አይደለም በማለት የሀስት መረጃ ሲያሰራጩ እንደነበርም ነው አቶ ደመቀ የገለጹት፡፡https://www.press.et/english/?p=27767#
ጁንታው የሞቱበትን ከፍተኛ አመራሮቹን ከሰብአዊ ርህራሄ ውጭ በሆነ መልኩ እንዳይታወቁ አንገታቸውን ቆርጦ ለየብቻ ስለሚቀብራቸው ለመለየት አዳጋች መሆኑን ተገለጸ

- በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቸውን እና መደምሰሳቸው ተገለፀ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቸውን እና መደምሰሳቸውን የመከላከያ ሐይል ሥምሪት መምሪያ ሐላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አስታወቁ።

በውጭ የሚገኙ የጁንታው ሚዲያዎች የሐሰት ኘሮፓጋንዳ ቢያናፍሱም፣ የመከላከያ ሐይልና ፌዴራል ፓሊስ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ፣ በርካቶች መማረካቸው ተገልጿል። እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትም ተደምስሰዋል ብለዋል።

የተቀሩትም በየእምነት ተቋማትና ገዳማት፣ ዋሻና ሸለቆዎች እራሳቸውን ደብቀው እንደሚገኙ መረጃ እንዳላቸው የገለፁት ጄኔራሉ፣ ጁንታው የሞቱበትን ከፍተኛ አመራሮቹን ከሰብአዊ ርህራሄ ውጭ በሆነ መልኩ እንዳይታወቁ አንገታቸውን ቆርጦ ለየብቻ ስለሚቀብራቸው ለመለየት አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል።

የጁንታ ሐይል ተደምስሷል፣ በየሸለቆው የደበቃቸው የህዝብና የመንግስት ንብረት ተይዟል ያሉት ሐላፊው በአንዳንድ አካላት ከውጭ የሚነዛው ኘሮፖጋንዳ ፍፁም ሐሳት መሆኑን አስረድተዋል ሲል የመከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።
ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች አለኝ የሚሉትን ሐሳብ በሰላማዊ፣ የህዝብና የሐገርን ሰላም በማያውክ መንገድ ሐሳቡን መሸጥ ይችላሉ"
- አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
(ኢ ፕ ድ)
ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች አለኝ የሚሉትን ሐሳብ በሰላማዊ፣ የህዝብና የሐገርን ሰላም በማያውክ መንገድ ሐሳቡን መሸጥ እንደሚችሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ገለፁ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ከሶማሌ ክልል ቴሌቭዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ከለውጡ ወዲ በፍትህ ተቋማት፣በዲሞክራሲ ግንባታና በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ጥሩ ስራዎች ቢሰሩም መሻሻል ያለባቸው ስራዎች እንዳሉም ጠቅሰው እንደ ክልል በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሩ ጤናማና ህዝብንና መንግስትን በተሻለ መንገድ ያቀራረበ መሆኑን ገልፀዋል ።
የክልሉ የለውጥ አመራር በሐሳብ ብዝሐነትና ልዕልና የሚያምን የዜጎችን የመናገር ነፃነት የሚያከብር ነው ያሉት አቶ ህዝብም የተሰማውን በሰለጠነ መንገድ መንግስትን የመጠየቅ የዲሞክራሲ ባህልን ማዳበር እንደሚገባና የክልሉ መንግስትም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ተግቶ ይሰራል ብለዋል።
ካለፉት አመታት የተሻለ የፖለቲካ ምህዳር መኖሩን ጠቅሰው ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች አለኝ የሚሉትን ሐሳብ በሰላማዊ መንገድ ፣የህዝብና የሐገርን ሰላም በማያውክ መንገድ ሐሳቡን መሸጥ ይችላሉ ብለዋል ።
በአዳማ ከተማ የግብርና ምርቶችን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ እና ባዛር ተከፈተ
****************************
(ኢ ፕ ድ)

በኦሮሚያ ክልል የግብርና ምርቶችን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ እና ባዛር የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በአዳማ ከተማ በአባገዳ አዳራሽ ተከፈተ፡፡

በአውደ ርዕይና ባዛር ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች፣ አርሶ እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም የግብርናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በአውደ ርዕይ እና ባዛሩ ላይም የተለያዩ የግብርና ምርቶችና ውጤቶች ቀርበዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በአውደ ርዕይ እና ባዛር ላይ እንድገለጹት የፕሮግራሙ ዓላማ በግብርና ምርት ውጤቶችና ቴክኖሎጂዎች ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፣ ለዘርፉ ዕድገት ድጋፍ ላበረከቱ ምሁራን እና ባለሀብቶች ዕውቅና መስጠታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
“የኢትዮ – ሱዳን ድንበር ግጭት የሱዳን መንግሥትና ህዝብ ፍላጎት አይደለም”አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
***********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮ – ሱዳን ድንበር ግጭት ሱዳን መንግሥትና ሰፊው የሱዳን ህዝብ ፍላጎት እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ። ግጭቱ ለማንም እንደማይበጅ የኢትዮጵያ አቋም መሆኑንም አመለከተዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በግጭቱ ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር 100 ዓመት ያስቆጠረ ቢሆንም በሌሎችም የአፍሪካ አገራት እንደሚታየው ከቅኝ ገዥዎች የተወረሱ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በቅኝ ገዥዎች ባትገዛም ሱዳን በቅኝ ግዥዎች ስር ስለነበረች፣ ድንበሩ ምንም እንኳ ምልክቶች ቢኖሩትም በዘመናዊ ዘዴ በትክክል ባለመካለሉ አንዳንዴ በሁለቱም አገሮች የድንበር አካባቢዎች መገፋፋቶች ይፈጠራሉ ብለዋል፡፡
አሁን ያለው ድንበር ባህላዊ መሆኑን ጠቁመው፣ ሰሞኑን የሱዳን ኃይሎች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የኢትዮጵያን መሬት መያዛቸው ስህተት መሆኑ እንዳለ ሆኖ አንዳንድ የሱዳን ሚዲዎችና ባለስልጣናት መሬታቸውን እንዳስመለሱ አድረገው በመግለጫ የሚያሰራጩት መረጃ ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ መሆኑ አስታውቀዋል።
አንዳንድ የሱዳን ባለስልጣናት ከኋላ ሆነዉ ጉዳዩን ለሚያቀጣጥሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች መጠቀሚያ ሆነው ቢያገለግሉም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ግጭቱ የሱዳን ህዝብና መንግሥት ፍላጎት ነው የሚል መደምደሚያ ላይ እንዳልደረሰ ገልጸዋል።
ይልቁንስ መጠቀሚያ እየሆኑ ያሉ የሱዳን ባለስልጣናት ድርጊታቸው ሱዳንንም ሆነ ኢትዮጵያን በፍጹም ስለማይጠቅም ያሉትን ችግሮች በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግሥት እያሳሰበ መሆኑን ገልጸዋል። ድንበሩም በድንበር ኮሚሽን መርሆዎች ብቻ እንዲፈታም የኢትዮጵያ አቋም እንደሆነም አስታውቀዋል።
ግጭቱ የሱዳን መንግሥትና የሱዳን ህዝብ ፍላጎት እንዳልሆነ የሚገልጹ “እኛ ከኢትዮጵያ ጋር ፈጽሞ ወደ ግጭት አንገባም” የሚሉ ድምፆች እየጨሩ መምጣታቸውን የጠቆሙት አምባሳደር ዲና፣ ከበስተጀረባው ግን የተለያዩ ኃይሎች እንዳሉ ጠቁመዋል።
እነዚህ ኃይሎች ለዘመናት ያልጠቀሟትን ሱዳን ወዳጅ በማስመሰል የጥፋት አጀንዳቸውን ለማሳካት እየታተሩ እንደሚገኙ ጠቁመው ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም ወዳዱ የሱዳን ህዝብ እና ባለስልጣናት ፣ እንዲሁም ለሰላም ወዳዱ የአረቡ ማህበረሰብ ፣ ግጭቱ ለማንም እንደማይበጅ በተጨባጭ እያሳወቀች መሆኑን አመልክተዋል።
አንዳንድ የሱዳን ወታደሮችና ሚሊሻዎች ሰሞኑን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ህይወት ማጥፋታቸውና ንብረት ማውደማቸውን አመልክተው፣ መንግሥትም ጸጥታን ከማስከበር ጎን ለጎን ችግሩ በድርድር እንዲፈታ እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።