Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የ2013 በጀት ዓመት የችግኝ ተከላ ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ ምክክር እየተደረገ ነው
***************************
(ኢ ፕ ድ)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ውጤትና በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎችን አስመልክቶ በአዳማ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት ብቻ 9 ቢሊዮን ያህል ችግኞችን መትከል የተቻለ ሲሆን፤ እ.አ.አ እስከ 2022 ድረስ ሀያ ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተጥሎ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
በዚሁ አጠቃላይ ማዕቀፍ መሠረት እስካሁን በተተከሉ ችግኞች እንክብካቤና ጥበቃ ሥራዎች ላይ የ2013 በጀት ዓመት የችግኝ ተከላ ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ በተለይ የኮቪድ 19 ወሩርሽኝ ኢ-ተገማች ተጽእኖን በመቋቋም ችግኝ ተከላውን ተፈጻሚ ማድረግ ተችሏል። ይህም ራስን ከወረርሽኙ እየተከላከሉ ማምረት እንደሚቻል አመላክቷል።
በቀጣይም የማይበገር የተቀናጀ የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋት ይሰራል።
በምክክር መድረኩ፤ ስራውን በአቢይና በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ የሚመሩና የሚያስተባብሩ፣ ከፌዴራልና ከክልል መንግስታት የዘርፍ መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ስኳር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክን ያሽመደመደው የቀድሞው መንግሥት ደካማ አሠራር ታክሎበት ስለመሆኑ ተነገረ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ስኳር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክን ያሽመደመደው የቀድሞው መንግሥት ደካማ አሠራር ጭምር መሆኑን በሜቴክ እና በስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባልነትና አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩ ምሁር አስታወቁ፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ስኳር ለማምረት እያደረገችው ያለው ጥረት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር በላይ ወልደየስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በኢትዮጵያ ስኳር ለማምረት የሚያስችላት ሰፊ አቅም እንዲሁም ከ80 በመቶ በላይ አርሷደር የሚፈልገውን ማዳበሪያን ለማምረት የምትችልበት አቅም ያላት ቢሆንም፤ የስኳር ምርቱ ኋላ ቀር፣ ማዳበሪያ ለማምረት ያደረገችው ጥረትም በግንባታ ደረጃ መክኖ የቀረ ሆኗል፡፡ በመሆኑም የስኳር ምርቱም ሆነ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ለኪሣራ የተዳረገው ተገቢውን አሰራር መከተል ባለመቻሉ ነው፡፡
እንደ ፕሮፌሰር በላይ ገለፃ፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሸንኮራ ተክልን ለማልማት የሚያስችል የአየር ፀባይና ሰፋፊ ተፋሰሶች ያሉባት ሀገር ናት፡፡ ይሁንና ካላት ምቹ ሁኔታ በጣም ባነሰ ከ50 ዓመት ጀምሮ ስኳርን ከሸንኮራ ተክል እያመረተች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ እያመረተች ያለው በዋናነት ስኳር ሲሆን፤ በሁለት ፋብሪካዎች በጣም በጥቂቱ ለተሽከርካሪ ነዳጅ የሚሆነው ‹‹ኤታኖል›› ይመረታል፡፡ ሆኖም ይህ አሠራር ወደ ኋላ የቀረ ነው፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=38171
“ አንድ አንድ የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን ከጁንታው ጋር በማበር የመረጃ ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተዋል"
- አቶ ዛዲግ አብርሃ
በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከአቶ ዛዲግ አብረሃ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑንን እንገልጻለን።
«የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር» -የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች
*******************
(ኢ ፕ ድ)
«የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር ወደ ፊትም ይኖራል» ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ትናንት ተወያይቷል።
የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች «የህወሓት ቡድን» በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን፤ ቡድኑ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የትግራይን ሕዝብ የማይወክልና ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ከዚህ ቀደም የፓርቲና የመንግሥት ሥራ ተደበላልቆእንደነበረ ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከዚህ ተምሮ ማስተካከል እንዳለበት የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ «የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር ወደ ፊትም ይኖራል» ብለዋል። በከተማዋ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር ሕዝባዊ ፖሊሶች በአግባቡ ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡም ጠይቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38227
«ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ ነው» ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ መሆኑ፤ በእሳት መጫወቱ ካልተጠነቀቁ ማንንም ወደማይምር ሰደድ እሳት እንደሚለውጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በቀን፣ በማታ ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 87 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰላም ሚኒስትርና ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በተገኙበት ትናንት አስመርቋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ ነው። በእሳት መጫወቱ ካልተጠነቀቁ ማንንም ወደማይምር ሰደድ እሳት ይለወጣል። እኔ ላይ አይደርስም ማለት የዋህነት ነው፤ ይህንን ደግሞ ከሌሎች ሀገሮች መማር ይገባል።
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ንፁሃን ዜጎቻችን እና ለፍቶ አደር ሕዝባችን በማንነት፣ በዘር እና በሃይማኖት ምክንያት ውድ ሕይወታቸውን እጅግ ዘግናኝ በሆነ መንገድ እያጡ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፤ በሕይወት የመኖር መብትን የቀደመ ሌላ መብት ባለመኖሩ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ንፁሃን ሕይወታቸውን እንዲያጡ ማንም መፍቀድ እንደሌለበት ተናግረዋል።
ከተደገሰልን እልቂት ለማዳን ሕግን የማስከበር ተግባራት በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ ለሁላችንም ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ ሞትን እና ቀውስን የሚደግሱልን እንዳሉ አይተናል እያየንም ነው፤ በታሪካችን የሀገራችንን ኅልውናን የሚፈታተኑ አደጋዎች ጥለውብን ካለፉት ጥቁር ጠባሳዎች ተገቢውን ትምህርት ወስደን ማንኛውንም ስጋት አራግፈን በጋራ መነሳት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38229
የትግራይ ወጣት በኢትዮጵያዊነቱ እንዲደራደር ሁለት አመት መርዝ ተዝርቶበታል፣

ከሁሉም ወንድም ብሄር ብሄረሰብ እንዲጣላ ጁንታው ሰርቷል፤

የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር የማቀራረብ ስራ ሊሰራ ይገባል
- የመቀሌ ከተማ ወጣቶች
****************^
(ኢ.ፕ.ድ)

የመቐለ ከተማ ወጣቶች በከተማዋ ፀጥታ እና መረጋጋት ዙሪያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ዛሬ እያካሄዱ ነው።

በከተማው እየተነዛ ያለው የውሸት ወሬዎችን ሳይሰሙ ስለ ከተማው ፀጥታ ለመወያየት ወደ ውይይቱ የመጡ ወጣቶችን የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሃይለስላሴ አመስግነዋል።

ውይይቱን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር መሉ ነጋ፣ የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ የመቐለ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ሃይለስላሴ እየመሩ ናቸው።

በመቐለ ከተማ ያጋጠመው ዝርፊያ ከማረሚያቤት በተለቀቁ ታራሚዎች እና ሌሎች ሌቦች እንደሆነ ዶ/ር መሉ ለተወያዮቹ አብራርተዋል።

የክልሉም ሆነ የከተማዋ ግዚያዊ አስተዳደር ለፀጥታ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራበት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።

በመቐለ ከተማ የተበተነ የጦር መሳርያ እንዳለ እና በሰላማዊ መንገድ ወደ ፀጥታ አካላት ማስረከብ እንደሚገባ ዶ/ር ሙሉ አስታውቀዋል።

የከተማዋ ወጣቶች የውሸት ወሬዎችን መታገል እንዳለባቸው ጨምረው ገልፀዋል።

ጁንታው የከተማዋ መሰረተ ልማት እንዲወድም ያደረገ ሲሆን የፌደራል መንግስት ባፋጣኝ መሰረተ ልማቱ እየመለሰ መሆኑን ዶ/ር ሙሉ ነጋ ገልፀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ "ሌቦችም ከኛው፣ የሚሰረቀውም የኛው ስለሆነ ሁላችንም ፀጥታችን ማስከበር አለብን" ሲሉ ተናግረዋል።

በየሰፈሩ የውሸት ወሬዎች የሚፈበርኩ ሰዎች ሆነ በውጪ ሆነው ህዝብ እያደናገሩ ህዝቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ ሚዲያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶቹ ጠይቀዋል።

"የትግራይ ወጣት በኢትዮጵያዊነቱ እንዲደራደር ሁለት አመት መርዝ ተዝርቶለታል፣ ከሁሉም ወንድም ብሄር ብሄረሰብ እንዲጣላ ጁንታው ሰርቷል። የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር የማቀራረብ ስራ ሊሰራ ይገባል" ሲሉ መናገራቸውን ውይይቱን እየተከታተለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ አስታውቋል።

በአማንመስፍን ሚካኤል

- ፎቶ ፋይል
«የትግራይን ሕዝብ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እንጂ እንዲጎዳ በማሰብ የሚሰራ ሥራ የለም»
- አቶ ዛድግ አብርሃ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር
*********************
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ እንጂ ሆን ተብሎ እንዲጎዳ የተሰራም ሆነ የሚሰራ ሥራ አለመኖሩን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
ሚኒሰትሩ አቶ ዛድግ አብርሃ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፣ መንግሥት የሰሜን ዕዝ መጠቃቱን ተከትሎ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ እንዳለ ሆኖ ወደ ጦርነት የገባበት ዋናው ምክንያት መስዋዕትነትም ተከፍሎ ቢሆን የጁንታው ቡድን እንደመያዣ የያዘውን የትግራይን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት ነው። የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን እንደመሆኑ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ እንጂ እንዲጎዳ በማሰብ የሚሰራ ሥራ የለም ብለዋል አቶ ዛዲግ።
እንደ አቶ ዛድግ ገለጻ ጁንታው ቡድን መንገድ፣ ድልድይ፣ አየር ማረፊያ አውድሟል፤ ተንቀሳቃሽ የገንዘብ መስጫ (ኤቲኤም) ማሽኖች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል፤ በኢትዮ ቴሌኮም መስመሮች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሶባቸዋል፤ ከዚህ አንጻር በክልሉ የደረሰው የመሠረተ ልማት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ በአንድ ጀምበር መልሶ መገንባቱም ከባድ ነው።
እንደዚህ ዓይነት አቅም ቢኖረንማ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የመሠረተ ልማት ችግር ባልተፈጠረ ነበር ያሉት አቶ ዛድግ እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም ፤ የፈራረሱትን ወደነበሩበት ለመመለስ ጊዜ ይወስዳል ፤ አሁንም ግን ሥራዎች እየተሰሩ ነው፤ በክልሉ የባንክ አገልግሎት ለምን አይጀመርም ተብሎ ለሚቀርበው ጥያቄም መልሱ ይኸው ነው ብለዋል።
ጁንታው በስንት ዓመት በብዙ ልፋትና ጥረት የተገነባን መሠረተ ልማት በ30 ቀን ነው ያወደመው፤ በአሁኑ ወቅትም መንግሥት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው፤ መንገዶች እየተጠገኑ፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማቱም እንደገና ወደ ሥራ እንዲገባ ሰፋፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፤ የባንክ አገልግሎቱም እንደዚያው፤ ነገር ግን ሕዝቡም አክቲቪስቱም ሌላውም እንደሚፈልገው በአንድ ቀን መስራት አይቻልም፤ ይህም ቢሆን ግን መንግሥት የለጋሽ አካላትን አቅም በማንቀሳቀስ ሁሉ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
እንደ አቶ ዛድግ ገለጻ አንዳንድ አካላት እንደሚሉት ሆን ተብሎ የትግራይን ሕዝብ ለመበደል የተሰራ ሥራ የለም፤ ይህንን ለማድረግ የሚያስብ መንግሥትም አለመኖሩን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል በመሰረተ ልማቱ ላይ የደረሰው አደጋ ከፍተኛ በመሆኑና መንግሥት ብቻውን የሚፈታው ባለመሆኑ ሕዝቡም ሌላውም አቅሙን አሟጦ እንዲጠቀም ኮማንድ ፖስቱ እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አቶ ዛድግ ገልጸዋል።
«ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው”
- ዶክተር ሙሉነሽ አበበ
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
«ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው» ሲሉ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ተናገሩ። «አካል ጉዳተኞችን አካታች፣ ምቹ እና ዘላቂ የተሻለ ዓለምን በድኅረ ኮቪድ 19 እንገንባ» በሚል መሪ ሐሳብ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም ለ29ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው ዶክተር ሙሉነሽ በበዓሉ ሥነሥርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ አካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው ሙሉ አካል እንዳላቸው ሰዎች እኩል ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ መሥራት ይችላሉ። ለዚህም በርካታ ምስክሮች አሉ። ዋናው ጉዳይ ግን ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው። ልባቸው የተሠወሩት እኩያን ከሰው ስብእና ውጪ በመሆን ወገኖቻችንን በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨፈጨፉ ይገኛሉ። በመሆኑም ከዚህ መጥፎ ተግባር ለመውጣት ሁሉም ቆም ብሎ ማሰብ ይጠበቅበታል።
የፌዴራል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ለዓለማችን ታላላቅ አስተዋጽኦ አበርክተው ያለፉ አካል ጉዳተኞች ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሁሌም ሲዘከሩ ይኖራሉ። ለሀገራችንም እድገት እና ብልጽግና አስተዋጽኦ እያደረጉ የሚገኙ በርካታ አካል ጉዳተኞች አሉ።
በመሆኑም አካል ጉዳተኞች ጠንክራችሁ ከሠራችሁ «ለሀገራችን ጠቃሚ እንጂ ተጠቃሚ አንሆንም» የሚለውን አስተሳሰብ መያዝ ይገባል። በሀገራችን የአካል ጉዳተኞች አስገዳጅ ሕግ አልነበረም፤ በዚህ ዓመት ግን የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ ይውላል፤ ይህም መንግሥት ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠቱን ያመላክታል።
https://www.press.et/Ama/?p=38342
በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል
***************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ71 ሺህ 476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ቢሮ ገልጻል፡፡
ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች 80 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል፡፡
የፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬዉ እለት የተሰራጨ ሲሆን ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ውጤታችሁን በየትምህርት ቤቶቻችው መመልከት እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በመቀሌ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት በመቀለ ከተማ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።
ከንቲባው አቶ አታክልቲ ሀይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቁት፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ከዛሬ ከሰአት በሁዋላ ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በጁንታው አማካኝነት በመቀሌ ከተማ ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎችና ሌሎች ዘራፊዎች የተነሳ በከተማዋ ላይ የጸጥታ ችግር መኖሩን በማንሳት ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲያስተካክልላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የጠየቁ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት በነበረው የወጣቶች ውይይትም ወጣቱ የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ከአስተዳደሩ ጋር ሆኖ ለመጠበቅ ቃል መግባቱ ይታወሳል።
የከተማዋ ነዋሪና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረትም የባንክ አገልግሎቱ ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ በንግድ ባንክ ቅርንጫፎቹ ተገኝቶ ተመልክቷል።
የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል።
በአማንሚካኤል መስፍን (መቀሌ)
የክልሉ ምክር ቤት የ4 የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሱትም፡-
1. አቶ አድጎ አምሳያ
2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ
3. አቶ ግርማ መኒ
4. አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የቀረቡትን የ4ቱን የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ በደረሰው ሞት፣ ጉዳትና መፈናቀል እጅግ ማዘናቸውን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የማያመው እና የማያወግዝ ሊኖር አይገባም ብለዋል፡፡
በዞኑ የተፈጠረው ችግር የከፋ ያደረገው አመራር የተሳተፈበት መሆኑን የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት፣ ዞኑን ከመረጋጋት አልፎ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ በድርጊቱ በተሳተፉ አካላት ላይ የተጀመረው የህግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ያኮረፉ አካላት፣ ህዝቦች እንዳይረጋጉና በሠላም እንዳይኖሩ እያደረጉ በመሆኑ ከመንግስት ቁርጠኛ እርምጃ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡
እናቶች፣ ህጻናትን ጨምሮ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ለተፈናቀሉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ፣ አካባቢውን አረጋግቶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መሥራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታደለ ተረፈ፣ በመተከል ዞን በዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት እጅግ አሳዛኝና ሊደገም የማይገባው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ተጨማሪ ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት እንዳይከሰት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን የክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
‹‹ተቃዋሚዎችም ብቻ ሳይሆን እንደ እኔ ያሉ የፖርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦች የተካተቱበት ስለሆነ አሁን ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አቃፊ ነው››
- ዶክተር አሰፋ በቀለ የትግራይ ክልል መንገድና
ትራንስፖርት አስተባባሪ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ የፖለቲካ አባላትና አባል ያልሆኑ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተካተቱበት መሆኑን የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ ተናገሩ::
ከአማራ ክልልና የፀጥታ አካላት ጋር በመነጋገር ከመቐለ አዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት መጀመሩም ተገልጿል::
የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ ፖለቲካዊ እሳቤ ያዙ ሰዎችን ያቀፈ ነው::በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ ሆነው ህዝብን ለማገልገል ፍላጎት ያላቸውን አካላት ጭምር በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ውስጥ አካትተዋል::
‹‹ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ብዙ ጉድለት ነበረበት::አሁን ባለው አስዳደር ግን በፖለቲካ አመለካከት ሳይገደብ ህዝብ ማገልገል ተችሏል፤” ያሉት ዶክተር አሰፋ፤ አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊ በመሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ አባላት በጊዜያዊ አስተዳደር ታቅፈው እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል::“እኔን ጨምሮ የፓርቲ አባል ያልሆንን ግለሰቦች ህዝቡን በማገልገል ላይ እንገኛለን›› ብለዋል::
https://www.press.et/Ama/?p=38379
የሕወሓት ጁንታ ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ተገኙ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሕወሓት ጁንታ በተደጋጋሚ ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር እና አስመራ ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው መገኘታቸውን የልዩ ዘመቻ ኮማንድ አስታወቀ።
የመከላከያ ሠራዊት መቐለ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ የልዩ ዘመቻ ኮማንድ 2ኛ ብርጌድ አንድ ወጋገን ሻለቃ ባደረገው አሰሳ እና ፍተሻ በመጋዘን ውስጥ ያልተተኮሱ 13 ሮኬቶች የተገኙ ሲሆን፣ 7 ሮኬቶች ደግሞ ከማስቀመጫው ሳጥን ወጥተው ተተኩሰው እንደነበርም አስታውቋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ፤ በተጨማሪም የተተኳሽ ሮኬት ማስወንጨፊያ ከባድ ተሽከርካሪ ከመቐለ ከተማ ዳርቻ ባለ ስፍራ ተደብቆ ተገኝቷል።
20 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ለመከተብ የሚያስችል የኮሮና ክትባት በቅርቡ አገር ውስጥ ይገባል ተባለ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
ከኮቫክስ የተገኘውና 20 በመቶ ለሚሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የኮሮና ክትባት በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚመጣ የጤና ሚኒስትሯ አስታወቁ።
ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለደሃ አገሮች በዕርዳታ መልክ ለማቅረብ ካቀደው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ውስጥ፣ ኢትዮጵያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት መጠን በጥቂት ወራት እንደምታገኝ የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ማስታወቃቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገልጿል።
የመቀሌ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ 15 አባላት ያሉት የመማክርት ኮሚቴ አቋቋመ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በዛሬው እለት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ውይይት ላይም የንግዱ ማህበረሰብ 15 አባላት ያሉት መማክርት ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ከመቀሌ ከተማ ኮምንኬሽን ፅ/ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ይህ ኮሚቴም በነገው ዕለት ተሰብስቦ የራሱን አመራሮች እንደሚመርጥ ታውቋል።

የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬው ውይይት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፤ በዋናነትም በከተማዋ ያለው የፀጥታና የማረጋጋት ስራ በትኩረት እንዲሰራ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ የንግዱ ማህበረሰብ በተረጋጋ መንገድ ስራውን ለመስራት ፍራቻ እንዳላበት በውይይት ላይ የተሳተፉ የምግዱ ማህበረሰብ አባላት መግለፃቸው ተጠቁሟል።

ከገንዘብ ቅያሬው ጋር በተያያዘ በክልሉ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው የንግዱ ማህበረሰብ በእጁ ላይ ያለውን ገንዘብ መቀየር ባለመቻሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለዚህ ችግር መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል ተብሏል።

አሁን ላይ በከተማዋ የኢትዮጵያ ንግድ አገልግሎት በመሰጠት ላይ መሆኑ የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሱት ነጋዴዎቹ፤ በተመሳሳይ የግል ባንኮችም ስራ እንዲጀምሩ ጥያቄ አቅርበዋል።

የሌሎች ባንክ ደንበኛ የሆኑ በከተማዋ ያሉ ነጋዴዎች የባንክ ሂሳባቸውን ለማንቀሳቀስ መቸገራቸውን ገልፀው አሁን ላይ ገንዘብ ይላክላቸውን ስራ ይጀምሩ መባሉንም ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ ያለው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት የከተማዋ ትልቁ የንግድ ማዕከል የሆነው ቀዳማዊ ወያኔ የተባለው ገበያ ስራ እንደሚጀምር ከኮምንኬሽን ቢረ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በከተማዋ በአሁኑ ወቅት መደበኛ የትራፊክ ፖሊስ እና የታክሲ አገልግሎት ስራ የጀመረ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ አድርገው የነበሩ ታክሲዎችም ወደ መደበኛ ታሪፍ እንደተመለሱና በመደበኛ መስመር ላይ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

በሀይማኖት ከበደ
“የህወሓት ጁንታዎች ለዉጡን የተቃወሙት በራሳቸዉ ቁመትና ስፋት ልክ ከሰፋት የአገዛዝ ስርዓት ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ነዉ”
አቶ ሌንጮ ለታ
የቀድሞ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር
******************
(ኢ ፕ ድ)

“የህወሓት ጁንታዎች ለዉጡን የተቃወሙት በራሳቸዉ ቁመትና ስፋት ልክ ከሰፋት የአገዛዝ ስርዓት ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ነዉ” ሲሉ የቀድሞ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተናገሩ።

የህዝቡ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት በአምባገነቱ የሕወሃት ጁንታ እጅ ውስጥ በመውደቁ ሲመኝ የነበረዉ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ መክኖ መኖሩንም ነው አቶ ሌንጮ ያብራሩት።

አቶ ሌንጮ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት የታገሉለት የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ በአምባገነቱ የሕወሃት ጁንታ እጅ ወድቆ ኖሯል።

በዚህም ምክንያት ህዝቡ ሲመኝ የነበረዉ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት መክኖ መቆየቱን የጠቀሱት አቶ ሌንጮ፤ አለም የህወሓት ጁንታ ፍጹም አምባገነንነትን እንዳያዉቅበት ክልሎችን በሞግዚትነት በራሱ ሰዎች አማካኝነት ሲያስተዳድር መኖሩን ተናግረዋል።

እንደ አቶ ሌንጮ ገለጻ፤ ጁንታው ዴሞክራሲን እራሱ እንዳመጣ አስመስሎ ሲሰብክ ቢቆይም እዉነቱ ግን የዴሞክራሲ ጸር መሆኑ ከተግባሩ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለ መብቱ የሚጠይቅን ዜጋ ሲያፍን፣ ሲገድል፣ አካል ሲያጎድልና በእስር ቤት ሲያሰቃይ ኖሯል። ይህ እወነታ ለአገርም ሆነ ለአለም ግልጽ ሆኗል።

ጁንታው በአገሪቷ የተደረገውን ለዉጥ የተቃወመው አባላቱ በራሳቸዉ ቁመትና ስፋት ልክ ከተሰፋዉ የአገዛዝ ስርዓት ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ነዉ ብለዋል አቶ ሌንጮ።

ላለፉት 27 አመታት በጁንታው አገዛዝ ምክንያት ታፍኖ የኖረውና አሁን በየአከባቢዉ እየፈነዳ ያለዉ የዘመናት ብሶት በአግባቡ ካልተስተናገደ አገራችንን ወደ አደገኛ ቀዉስ ሊወስዷት ይችላልና ጥንቃቄ ያስፈልጋልም ነው ያሉት አቶ ሌንጮ።

በዋቅሹም ፍቃዱ
‹‹ቀድሞ በነበረው የበሰበሰ ርዕዮተ ዓለም መገለባበጥና መዋሸት የለመዱ አካላት እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዳይተገበር እንቅፋት እየሆኑ ነው›› አቶ አባተ ኪሾ የቀድሞው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
***************************
(ኢ ፕ ድ)
በኢህአዴግ ዘመን በነበረው የበሰበሰ ርዕዮተ ዓለም መገለባበጥና መዋሸት የለመዱ አካላት እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዳይተገበር እንቅፋት እየሆኑ ነው ሲሉ የቀድሞ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባተ ኪሾ ገለጹ። እውነተኛ ፌዴራሊዝም ባለመኖሩ ለ30 ዓመታት ክልል ከክልል ብቻ ሳይሆን ቀበሌ ከቀበሌም እርስበእርስ እንዲጠራጠሩ ማድረጉንም አመልክተዋል።
አቶ አባተ ኪሾ፣ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታየው ቀውስ እውነተኛ ፌዴራሊዝም ካለመተግበሩ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። አሁንም ትክክለኛ ፌዴራሊዝም እንዳይተገበር የሚያደርጉት ቀድሞ በነበረውና በበሰበሰው የኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ሲገለባበጡና ሲዋሹ በነበሩ አካላት ናቸው።
ችግሩ ያለው በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም የአገሪቱ ክፍሎች በመኖሩ ሊታዩና ሊፈተሹ የሚገባቸው ብዙ ናቸው ያሉት አቶ አባተ፣ በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለው የቀድሞውን የፖለቲካ ድፍድፍ በአግባቡ ሳይጠራ የጠጣ ኃይል እንዳለ ነው ብለዋል።
ያ ስካር እስካሁን ያለቀቀው እንዳለ ጠቁመው፣ ይህ ሃይል የሚሰራውን እንደማያውቅ አስታውቀዋል። የበሰበሰው ርዕዮተ ዓለም አሁንም ድረስ አገሪቱን በማመስ ላይ የሚገኘውም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።
የዚህ ርዕዮተ ዓለም ተከታዮችና የበሰበሰውን ሃሳብ ለማሳካት የሚንገታገቱ ቡድኖች በየቦታው መኖራቸውን የሚናገሩት አቶ አባተ፤ ስለዚህም መመልከት ያለብን አንድን አካባቢ ብቻ ሳይሆን በየአቅጣጫው ነው ብለዋል። የበሰበሰው ርዕዮተ ዓለም ቫይረሱ በብዙ ቦታ የተዳረሰ ከመሆኑ አኳያ ሁሉንም ቦታ በአግባቡ በመፈተሽ ቫይረሱን ማምከን የግድ እንደሚልም ተናግረዋል። ይህ ካልሆነ ግን የታለመው እውነተኛ ፌዴራሊዝም ተተግብሮ ማየት የማይቻል መሆኑን ገልጸዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38453
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ በድጋሚ ተጀመረ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው ከ1ዐዐ ሺህ ብር በታች የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ድጋሚ መጀመሩን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
ባንኩ እንዳስታወቀው፤ መንግስት በክልሉ በወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬው ተቋርጦ እንደነበር አስታውሶ አሁን ላይ በተወሰኑ የክልሉ ከተሞች የመብራትና የኢንተርኔት አገልግሎት በመጀመሩ በእነዚሁ አካባቢዎች ባንኮች ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ መሰረት ተቋርጦ የነበረውን የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ባንኮች ሥራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ አሮጌ ብር እንዲቀይሩ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ጀምሮ መወሰኑንም ነው ባንኩ ያስታወቀው።
ባንኮችም ይህንኑ ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ በመጠቆም በብር መቀየሩ ሂደት የነበሩ መመሪያዎችና አሠራሮች እንደተጠበቁ መሆናቸውንም ገልጿል።
ከባንክ በጥሬ ገንዘብ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ላይ በተሻሻለው መመሪያ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን ከ1ዐዐ ሺህ እስከ 1.5 ሚሊየን አሮጌ ብር ያላቸው የመቀየሪያው የጊዜ ገደብ የህግ ማስከበሩ ከመጀመሩ በፊት የተጠናቀቀ በመሆኑ ብር መቀየር የሚችሉት ከ1ዐዐ ሺህ ብር በታች ያላቸው መሆናቸውን ባንኩ አስታውቋል።
ባንኮችም ይህንኑ ሥራ የሚከታተል ግብረ ኃይል በማቋቋም መመሪያን በጠበቀ መልኩ እንዲሠሩ እና በእያንዳንዱ የባንክ ቅርንጫፍ የብር መቀየር ሥራ የተጀመረበትንና የተጠናቀቀበት ቀን እና የተለወጠ የብር መጠን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሳምንቱ ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳስቧል።
ከመስከረም 6 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ወራት በመላ ሀገሪቱ አሮጌ ብር በአዲስ ብር የመቀየር ሥራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል።
በትግራይ ክልል ባንኮች ስራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ አሮጌ ብርን እንዲቀይሩ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን ጀምሮ መወሰኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል በህግ ማስከበር ዘመቻው የፈጸመው ግዳጅ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል ከእዞችና ከሌሎች የሠራዊት አሀዶች ጋር በመጣመር በህግ ማስከበር ዘመቻው የፈጸመው ግዳጅ ውጤታማ እንደነበር የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ በቀለ ገለጹ፡፡
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉ በተለይም በራያና በምዕራብ ግንባሮች በጁንታው ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ሀያልነቱን አስመስክሯል ብለዋል፡፡
አዲቀይህ አካባቢ በነበረው ፈታኝ ግዳጅ የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉ የኮማንዶ ዩኒት በጁንታው ጀርባ በኩል ምሽግ ሰብሮ በመግባት የፈጸመው ጀብዱ ለወገን አኩሪ እንደነበር የገለጹት ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ፣ እስከ መቀሌ በነበረው ተልዕኮም ውጤታማ ግዳጅ መፈጸሙን አስረድተዋል ፡፡
በምዕራቡ ግንባርም ከሁመራ እስከ ዳንሻ የሚሸሸውን የጁንታ ተዋጊ የማገትና የመቆጣጠር ስራ ተሰርቷል ፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተንጠባጠበውን የህወሀት ታጣቂ በማደን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉ ከህግ ማስከበር ዘመቻው በተጓዳኝ ፣ በምዕራብ ወለጋና በመተከል ሽፍቶችን የመደምሰስ ተልዕኮውን በተሳካ መንገድ በመፈጸም ላይ ይገኛልም ብለዋል ፡፡
የተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው ፍትሀዊ ስለነበረ እግረኛው ፣ ሜካናይዝዱ ፣ ልዩ ሀይሉ ፣ አየር ሀይሉ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በጥምረትና በቁርጠኝነት እንዲሁም በብልህ የጦር አመራር የተፈጸመ ዘመቻ በመሆኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ያኮራ ተግባር ተፈጽሟል ያሉት ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ፣ ህዝባችን እስካሁን እያደረገ ያለው ድጋፍ ለውጤቱ መሰረታዊ ድርሻ እንደነበረው መግለጻቸውን ከመከላኬ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡