Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የአምራች ኢንዱስትሪውን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት የሚያስችል የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በሰጡት መግለጫ፤ የአምራች ኢንዱስትሪውን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት የሚያስችል የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በብድር የተገኘው ገንዘቡ ለሊዝ ፋይናንሰ፣ ለፕሮጀክት ፋይናንስና ለስራ ማስኬጃ ይውላል ብለዋል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪውን ከሚያጋጥሙት ችግሮች መካከል አንዱ የፋይናንስና የውጭ ምንዛሬ እጥረት መሆኑን የገለጹት አቶ መላኩ፣ ከዓለም ባንክ የተገኘው የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ችግሩን ለማቃለል ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።
ከአለም ባንክ የተገኘው ብድር 1 ሺህ 990 ነባር ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም አዲስ ለሚቋቋሙ ኢንዱስትሪዎች የሚደርስ መሆኑንም አቶ መላኩ አመልክተዋል።
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በሁሉም አካባቢ እንዲደርስ ከማድረግ አንጻር ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።
በቀጣይም ሌሎች የዘርፉ ማነቆዎችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
ለኢፈርት ድርጅቶች ሰባት አባላት ያሉት ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሹመት ተሰጠ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅራቢነት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመ/ቁ 263499 ለኢፈርት ድርጅቶች ሰባት አባላት ያሉት ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾሟል፡፡
ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ድርጅቶችን ወደ ሥራ ማስገባት፣ በእያንዳንዱ ድርጅት ዉስጥ ተቀጥረዉ ከሚሰሩ ብዛት ያላቸዉ ሠራኞች የሥራ ዋስትና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍና የድርጅቶቹን ንብረት ከብክነት መከላከል በአግባቡ ጠብቆ ለመያዝ ያመች ዘንድ የወንጀልና የሃብት ምርመራዉ ተጠናቆ በጉዳዩ ላይ ፍ/ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር የሚመራ ይሆናል፡፡
በዚህም መሠረት ባለአደራ አስተዳደሩ በፍ/ቤት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት የማስተዳደር ሥራን የሚያከናዉን ሲሆን በየጊዜዉ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሾመዉ ፍ/ቤት እንዲሁም ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
የጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደሩ አባላት ገለልተኝነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የሙያ ሥነ ምግባር እና ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት፣ በቦርድ አመራርነት እንዲሁም አባልነት በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆናቸዉን ተገልጻል፡፡
ለኢፈርት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለ አደራ አስተዳደር በማሾም ሂደት ውስጥ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዳስትሪ ሚኒስቴር እና የትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍና አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የወንጀል ምርመራ ጎን ለጎን የሀብት ጥናት እና ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን የድርጅቶችን ንብረት የማሸሽና ማባከን ተግባራትን ለመከላከል ሕግ በሚፈቅደዉ አግባብ ጊዜያዊ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ ስለነበረበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለፍ/ቤት የዕግድ አቤቱታ በማቅረብ የድርጅቶቹ የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ፣ ሌሎች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እንዳይሸጡና እንዳይለወጡ፤ በሌላ ማንኛዉም መንገድ ወደ ሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ማሳገዱ ይታወሳል፡፡
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ በሲውዝርላንድ ጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ።
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ የኢዮጵያ መንግስት ደስተኛ አይደለም ያሉት አምባሳደር ዘነበ፤ ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስት አቅራቢነትና ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ መሆናቸውን አስታውሰዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ድጋፍ ጭምር አሁን ላሉበት ከፍተኛ የስራ ሃለፊነት መብቃታቸውን ያስታወሱት አምባሳደሩ፤ በዚህ ከፍተኛ ቦታ ላይ ሆነው በእንደዚህ አይነት ወገንተኝነት የታየበት ተግባር ላይ መሰማራታቸው ደስተኞች አይደለንም ብለዋል።
ይህንን የዶ/ር ቴድሮስ ተግባር መንግስት አግባብ ባለው መልኩ የሚሄድበትና ምላሽ የሚሰጥበት ይሆናል” ሲሉም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።
በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቀቀ
*************************
( ኢ ፕ ድ)
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡
በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 18 መማሪያ ክፍሎች፣ቤተመፀሀፍት፣ቤተሙከራዎች፣የአስተዳደር ህንፃ፣መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ፈንታ በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶችን ከመጠቀም ጀምሮ ተገቢ የሆነ የባለሙያ ክትትል ተደርጎለታል ተብሏል፡፡
የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ኃላፊው የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ቅጥርም እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመረዳት እድሉን መስጠቱ በከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ስም ምስጋና ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ግብአት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከተው የመንግስት ተቋም፣የአካባቢው ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ጥሪ ማቅረቡን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ላለፉት 30 አመታት በጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩት የደርግ ባለስልጣናት እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የኖሩትና የደርግ ባለስልጣናት የነበሩት ኮለኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄነራል አዲስ ተድላ እንዲለቀቁ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች አረጋገጡ።
ፍርድቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የሁለቱን ግለሰቦች ጉዳይ ተመልክቶ በአመክሮ እንዲፈቱ ወስኗል።
ቀደም ብሎ በእነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የክስ መዝገብ ስር ተፈርዶባቸው የነበረው ቅጣት ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮ እንደነበር በመግለጽ፤ የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የአመክሮ አስተያየትን ከይቅርታ ሰነዶች ጋር ለፍርቤት ማቅረቡን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የእድሜ ልክ ፍረደኛ በአመክሮ መታሰር ያለበት ለ20 አመት በመሆኑ ግለሰቦቹ በአመክሮ ቢፈቱ ተቃውሞ የለንም የሚል አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
ፍርድቤቱም ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን የህግ መንግስት ድንጋጌዎችና ሌሎች ህጎች መርምሮ ግለሰቦቹ ከኢንባሲው እንዲለቀቁ ወስኖ ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትዛዝ ሰጥቷል።
ትዛዙ በቀጥታ ለጣሊያን ኤምባሲ ሳይሆን በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለጣሊያን ኤምባሲ እንዲሁም ለቀድሞ ፍርደኞች ሻለቃ አዲስ ተድላ እና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ እንዲደርስ ይደረግ ዘንድ አዟል።
ሻለቃ አዲስ ተድላ እና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ የቀድሞ ፍርደኞች አሁን ግን በአመክሮ በፍርድ ቤት የተለቀቁ መሆኑን አውቀው መብታቸውን ለማስከበር ጥበቃም ሆነ ክትትል እንዲያደርጉ ለሚመለከተው አካል እንዲጻፍ ፍርድ ቤቱ አዟል።
የሕግ የበላይነት ባለመከበሩ፣ እንደ አገር ከተመዘገቡት ድሎች ያመለጡት ዕድሎች በእጅጉ የበዙ መሆናቸው ተገለፀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች፣ ህዝቦቿም በአንድም በሌላ በደም የተሳሰሩ ቢሆንም ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ፣ የአገር ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ህግ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ባለፉት ዓመታት እንደ አገር ከተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያመለጡ በረከቶች በእጅጉ እንደሚያመዝኑ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ገለጹ፡፡
ኮሚሽነሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፤ አገራችን በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ በቀላሉ ሰርተው የሚለወጡባት፣ አየሯ ተስማሚና ለኑሮ የምትመች ናት፡፡ ይሁን እንጂ በከፋፋይ አስተሳሰብ የተቃኘና ከአገር ይልቅ የቡድኖች ህግ ለዘመናት ገዝፎ በመቆየቱ ለሌላ መትረፍ የምትችል አገር በምግብ እንኳ ራሷን መቻል አቅቷት ለውጭ እርዳታ እጇን ስትዘረጋ ቆይታለች፡፡ ዛሬም ከውጭ እርዳታ ባለመላቀቋ እና የዚህ ምክንያቱም ተፈጥሯዊ ሳይሆን ሰው ሰራሽ እንደመሆኑ ሁሉም ዜጋ በቀጣይ በኢትዮጵያ እድል ላይ አስቦና ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል።
እንደ ኮሚሽነር አበረ ገለጻ፤ ህግና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ያለፉት ታሪኮች አገርና ህዝብ ባልተስተካከለ ሚዛን የሚመራ ህግ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ኢትዮጵያ አስከፊ ብጥብጥና ውድመት ለማስተናድ ተገዳለች። ይህ ደግሞ አገሪቱን አቅም አሳጥቶ፣ አመት ሙሉ ምርት ማምረት የሚያስችሉ ወንዞችና ለም አፈር እያላት የስንዴ ለማኝ ሆናለች።
ወደ ዘመነ መሳፍንትና ከዚያ በፊት ያሉ ዘመናት በታሪክ ሲቃኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከዳር ወደ መሀል አገር እንዲሁም ከመሀሉ ወደ ዳር በተደረገው እንቅስቃሴ በጋብቻ ያልተሳሰረና ያልተዋለደ እንደሌለ የሚናገሩት ኮሚሽነሩ፤ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ጎጠኝነት በመንሰራፋቱ ምክንያት በደም መተሳሰራችን ተረስቶ፣ የህግ የበላይነትም ጠፍቶ፣ ይልቁንስ ህግ በአገር እይታ ሳይሆን በቡድን እይታ የሚተረጎምበትና የሚተገበርበት ዘመናት እንደ ነበሩ ያስረዳሉ።
https://www.press.et/Ama/?p=37981
ላለፉት 30 አመታት በኤምባሲ ውስጥ በተከለለ ቦታ ተገድበው የኖሩትን የቀድሞ የደርግ አመራሮችን ከዚህ በላይ ነጻነታቸወን ገድቦ ማቆየት የፍትህ ዓላማን ከማሳካት አንጻር የሚጨምረው ነገር ባለመኖሩ በአመክሮ እንዲፈቱ መደረጉ ተገለጸ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ላለፉት 30 አመታት በኤምባሲ ውስጥ በተከለለ ቦታ ተገድበው የኖሩትን የቀድሞ የደርግ አመራሮችን ከዚህ በላይ ነጻነታቸወን ገድቦ ማቆየት የፍትህ ዓላማን ከማሳካት አንጻር የሚጨምረው ነገር ባለመኖሩ በአመክሮ እንዲፈቱ መደረጉ ተገለጸ።
በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ጸጋዬ እንዳስታወቁት፤ ግለሰቦቹ እስካሁን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ነጻነታቸው ተገድቦ መቆየቱ አስተማሪነት ያለው መሆኑ ከግምት ገብቶ በአመክሮ እንዲለቀቁ ጥያቄውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጋር በጋራ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ወስኖዋል።
እንደ አቶ ፍቃዱ ማብራሪያ፤ ከዚህ በላይ እነኚህን ሰዎች ነጻነታቸውን ገድቦ ማቆየት የፍትህ አላማን ከማሳካትም አንጻር የሚጨምረው ውጤት የማይኖር በመሆኑ፣ እንዲሁም ከፍርደኞቹ እድሜ እና የጤና ሁኔታ አንጻር የሰብዐዊነት እይታን ከግምት በማስገባት ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ነው የተወሰነው።
በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የቀድሞ ደርግ አመራሮችም ከ10 ዓመታት በፊት ከእስር ወጥተው ከማህበረሰቡ ጋር እየኖሩ ይገኛሉ ያለው ዓቃቤ ህግ፤ በተቃራኒው በጣልያን ኤምባሲ ውስጥ ተወስነው ለ30 ዓመታት የቆዩት እነኚህ ሰዎች ከመደበኛው የእርምት ስፍራ ባልተናነሰ በተወሰነ አነስተኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ወደ ህክምና ተቋማት እንኳን መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መኖራቸው መረጋገጡን አቶ ፍቃዱ ገልጸዋል።
በኤምባሲው ውስጥ በቆዩባቸው አመታት ከመንግስትም ሆነ ከቆዩበት የኤምባሲ ቅጥር ግቢ አሰተዳዳሪ ምንም አይነት እንክብካቤ እና ድጋፍ ሳያገኙ መቆየታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በእስር ቢቆዩ ኖሮ ከሚፈጠርባቸው የመብት ገደብ አንጻር ቢበዛ እንጂ የሚያንስ አንዳልሆነ ግንዛቤ ተወስዶበታልም ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ፡፡
በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸምን ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን- ብልጽግና ፓርቲ
*********************
(ኢ ፕ ድ)


ብልጽግና ፓርቲ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ጥቃት አጥብቆ ያወግዛል፡፡

ዜጎችን በማንነት ለይቶ በማጥቃት ምንም አይነት የፖለቲካ ትርፍ ሊገኝ አይችልም፡፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተደጋጋሚ በዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የትኛውንም የህዝብ ክፍል የማይወክልና ኃላፊነት የማይሰማቸው የግጭት ነጋዴዎች ሴራ መሆኑን መላው የሀገራችን ህዝቦች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

በጨካኝ አረመኔ የጥፋት ኃይሎች ጥቃት በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰው ላለው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን ለዘመናት ተከባብሮ ክፉና ደጉን አብሮ ያሳለፈን ህዝብ በማጋጨት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጣጣሩ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች የማይሳካላቸው መሆኑን አጥብቀን ልንገልጽላቸው እንወዳለን፡፡

በዜጎች ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸውንና ችግሩ እንዲፈታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች ላይ ጥብቅ ፖለቲካዊ፣ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ለፍቶ አዳሪ ንጹሃን ዜጎችን በማንነታቸው ብቻ ለይቶ በማጥቃት ሀገርንና ህዝብን ወደ ትርምስ ለማስገባት ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ የውስጥም ሆነ የውጭ ጨካኝ የጥፋት ኃይሎችን አጥብቆ የሚያወግዝና በእነዚህ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ ብልጽግና ፓርቲ አጥብቆ የሚታገል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ችግሩን ለመፍታት በተለያየ መልኩ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን ጥቃት ከማስቆም እና ችግሩን ከመፍታት አንጻር በተለያየ መልኩ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ መንግስት ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአከባቢው ያለውን ችግር ከመፍታት አኳያ በተለያየ መልኩ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ “በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል፤ በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ፤ ብለዋል።
ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የጠላቶቻችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው፤ ይህ የሚሳካ አይደለም፣” ብለዋል።
መንግሥትም ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን በመግለጽም፤ “የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ሁላችንም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንድንሠራ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊት በመተከል ዞን ተገኝተው ከክልሉ አመራሮች፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች ጋር በመወያየት የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫን በማስቀመጥ ለአካባቢው ሰላም ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ እንደሚገባ ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው።
በመተከል እየተፈጸመ ያለው ግድያ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እጅጉን መዳከሙን እንደሚያሳይ ኢሰመኮ ተናገረ
*******************************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተበራከተ የመጣው እና ከሰሞኑ ሌሊት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን የሚያሳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። ኮሚሽኑ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ መሆኑንም ተናግሯል።
ኮሚሽኑ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን ነው። በመሆኑም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው።
በመግለጫው እንደተመላከተው፤ ኢሰመኮ የጥቃቱን ሂደት በተመለከተ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከሚመለከታቸው አካላት እና ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ሲከታተልና ሲያጣራ ቆይቷል። በኩጂ ቀበሌ ከወረዳው መቀመጫ ከሆነችው ቡለን ከተማ 90 ኪ.ሜ. ርቃ የምትገኝ ሲሆን የሺናሻ፣ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ይኖሩባታል። ለቀበሌው የተመደበ የፖሊስ ወይም የፀጥታ ኃይል አለመኖሩን ኮሚሽኑ በክትትሉ መሰረት ተረድቷል።
https://www.press.et/Ama/?p=38060
ፖርት ሱዳንን ለኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ንግድ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለማድረግ ከፖርት ሱዳን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አጓጓዥ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደረገ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ፖርት ሱዳንን ለኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ንግድ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለማድረግ ከፖርት ሱዳን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አጓጓዥ ድርጅቶች ጋር ውይይት መደረጉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው የልዑካን ቡድን ፖርት ሱዳንን ለአገራችን የወጪገቢ ንግድ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ በማድረግ ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን በዚሁ ወደብ በመጠቀም ለሰሜንና ምዕራቡ የአገራችን ክፍል ተደራሽ ለማድረግ መሻሻል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከፖርት ሱዳን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም አጓጓዥ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው የልዑካን ቡድን ከሱዳን መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትር፣የማእድንና ኢነርጂ ሚኒስትር፣የሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ኃላፊ፣ከሱዳን ባቡር ኮርፖሬሽን እና መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ከንግድ ሚኒስቴር እና ጉምሩክ መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች በትራንስፖርት ዘርፍና በተለያዩ መስኮች በጋራና በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደርሷል፡፡
ፖርት ሱዳንን ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለማድረግ፣በኢትዮጵያ-ሱዳን የምድር ባቡር መስመር ዝርጋታ የመጀመሪያ አዋጭነት ጥናት ሂደት፣በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከርና በአጋርነት መስራት፣ በየብስ ትራንስፖርት ዘርፍ ያጋጠሙ ማነቆዎችን በጋራ በመፈተሽ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከስምምነት መድረሳቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የሱዳን ትራንስፖርትና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ሚ/ር ሃሺም ኢብንኦፍ ሱሌይማን በኢትዮጵያና ሱዳን መካካል በትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት የተደረሰባቸውን ነጥቦች በአፋጣኝ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያግዝ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
መቐለ ያሉ የመንግስት መስርያቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
👉 ከማረሚያቤት ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎች ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንዲፈጠር ተደርጓል፤
👉 ጁንታው “ጦርነት አላለቀም” በሚል ወሬ እያስነዛ ህዝቡ ወደ ስራ እንዳይገባ አድርጎታል፤
****************
(ኢ ፕ ድ)
መቐለ ያሉ የመንግስት መስርያቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ በሰማዕታት አደራሽ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።
የዚሁ ውይይት ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፤ መቐለ ያሉ የመንግስት መስርያቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል፤ በዚህም ህብረተሰቡ እየተጉላላ ይገኛል።
በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የደረሰው ክህደትና ጥቃት ያወገዙት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጭር ጊዜ ህግ የማስከበሩን ስራ በማጠናቀቁ እናመሰግናለን ሲሉም ተናግረዋል።
የህወሓት ጁንታ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ማረሚያቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሆን ብሎ በመቐለ በትኖ ሄዷል ያሉት ተወያዮቹ፤ በእነዚህ ከማረሚያቤት ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎች ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንዲፈጠር ተደርጓል ሲሉም ነው ያስታወቁት።
የሀሰት ወሬ በመቐለ ከተማ እየተነዛ ህዝቡ እየተሸበረ ስለሆነ አስተዳደሩ ይሄን ያጥራልን ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ ነጋዴው ከመሃል ሃገር ሸቀጥ እንዳያመጣ “ጦርነት አላለቀም” በሚል ወሬ እየተነዛ ወደ ስራ እንዳይገባም አድርገውታል ነው ያሉት።
በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጊዚያዊ አስተዳደሩንም ሆነ ህዝቡን ማገዝ አለበት ያሉት ተወያዮቹ፤ በደቡብ ትግራይ እና ምዕራብ ትግራይ አካባቢ ያሉ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የሰሜን ዕዝ አዛዡ ጄነራል በላይ ስዩም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መከላከያ የአገር ዳር ድንበርን የሚያስከብር ሃይል ነው። ነገር ግን ጁንታው የገደለው ይሄንን ሃይል ነው በማለት የተፈጸመውን ክህደትና ግፍ ለተወያዮቹ አብራርተዋል።
“እንደመከላከያ ጓዶቻችን በጁንታው ተገድለዋል፣ የሰራዊቱ ንብረት ተዘርፏል፤ እንደ አገርም በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅእኖ ተፈጥሯል” ያሉት ጄነራሉ፤ የዘጠና አመት አዛውንቶች መጥተው ይመሩናል ብላችሁ ተስፋ እንዳታደርጉ፤ በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ጁንታው ከዚህ በሁዋላ አይመለስም፤ ስለዚህ ተረጋግታችሁ ጊዚያዊ አስተዳደሩን ማገዝ አለባችሁ” ሲሉም ለመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የመቐለ ከንቲባ አቶ ኣታኽልቲ ሃይለስላሴ እና የሰሜን እዝ አዛዥ ጀነራል በላይ ስዩም መገኘታቸውን በመቀሌ ከተማ ያለው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ያደረሰን መረጃ ያሳያል።
ምርጫ ቦርድ የመጪውን 6ተኛ አገራዊ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን 6ተኛ አገራዊ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ።
በዚህም መሰረት ግንቦት 28 ቀን ምርጫው እንደሚካሄድ የጊዜ ሰሌዳው ያሳያል።
የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም፤
ግንቦት 28 እና 29 ቀን 2013 ዓ.ም ለአገር አቀፍ ምርጫ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤት የሚገለጽባቸው ቀናት ናቸው ተብሏል፤
የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ከየካቲት 08 ቀን እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል፤
የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይከናወናል፤
ግንቦት 29 እስከ ሴነ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አጠቃላይ የምርጫ ውጤት በቦርዱ የሚገለጽበት ጊዜ ይሆናል፤
የትግራይ ህዝብ የህወሓት ጁንታ ተመልሶ ይመጣል ከሚል ሃሳብ መውጣት እንዳለበት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አብረሀም በላይ አስታወቁ
👉 ጃንሆይ ከወረዱ በኋላ ህዝቡ ይመለሳሉ ብሎ ሲጠብቅ ነበር፤ ደርግም ከወደቀ በኋላ ይመለሳል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ነበር፤ አሁንም እንደዛ እየጠበቀ ያለ ሰው አለ፤
********************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ ህዝብ የህወሓት ጁንታ ተመልሶ ይመጣል ከሚል ሃሳብ መውጣት እንዳለበት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አብረሀም በላይ አስታወቁ።
የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በዛሬው እለት እያደረጉት ያለው ውይይት እንደቀጠለ ነው።
በዚሁ መድረክ ላይ ለተነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ምላሽ እየሰጡ ካሉት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ ዶ/ር አብረሀም በላይ እንዳሉት፤ በከተማዋም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ላይ የህወሓት ጁንታን በተመለከተ “ተመልሰው ይመጣሉ” የሚል የሀሰት ወሬ እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ የተሳሳተ መሆኑን ህዝቡ ማወቅ አለበት።
ህዝባችን በውሸት ሊደናገር አይገባም ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ ድሮ ጃንሆይ ከወረዱ በኋላ ህዝቡ ይመለሳሉ ብሎ ሲጠብቅ ነበር፤ ደርግም ከወደቀ በኋላ ይመለሳል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ነበር። አሁንም እንደዛ እየጠበቀ ያለ ሰው አለ። ይህ መሆን የለበትም” ሲሉ ተወያዮቹ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።
የመንግስት ሰራተኛ ማለት የህዝብ አገልጋይ ነው፤ ሁሉም ወደ ስራው ገብቶ ከልብ ማገልገል አለበት ያሉት ደግሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደ/ር ሙሉ ነጋ ናቸው።
“በፊት ህዝብ ያሰቃዩ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር የሌላቸው ማልያ ቀይረው ወደ አመራር እንዳይመጡ ህዝቡ ሊያግዘን ይገባል” ሲሉም ነው ዶ/ር ሙሉ ለተወያዮቹ የገለጹት።
ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችም በህግ አግባብ ምላሽ እንደሚያገኙ ዶ/ር ሙሉ አብራርተዋል።
ዶ/ር ሙሉ አያይዘውም፤ “የትግራይን ህዝብ ከምትናገረው ስትሰማው ብዙ ትምህርት ትወስዳለህ። እኛ እየሰራን ነው፤ የቀረውን ህዝቡ ሊያግዘን ይገባል። ህዝባችን ያለንን ልንሰማ፣ ራሱ የፈለገውንም ሊመርጥ ይገባል” ሲሉ ለተወያዮቹ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች መሰራታቸው የቱሪስት ፍሰቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምረው ተገለፀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች መሰራታቸው የቱሪስት ፍሰቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምረው ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ቴድሮስ ሀብታሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መንግስት በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራው ያለው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ወደ ፊት በከፍተኛ ሁኔታ የቱሪስት ፍስቱን ላይ ለውጥ ያመጣሉ።
የቱሪዝም ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ጠቀሜታዎች ከሚያሳድጉ የልማት ዘርፎች አንዱና ዋንኛው ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ፤ መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት እየተሻሻለ መምጣቱ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ አለውም ብለዋል፡፡
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቨይረስ ለቱሪዝም ዘርፉ ፈታኝ ሆኖበታል ያሉት አቶ ሀብታሙ፤ አሁን ላይ ዘርፉ እንዲያገግም በሀገር ውስጥ ቱሪዝሙ ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ቱሪዝሙ በፍጥነት ማገገም ስለሚችል በዚህ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ላይ ያለው ግንዛቤ አናሳ ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ፤ ይህንን እወነታ ለመቀየር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡
እንድ አቶ ሀብታሙ ገለጻ፤ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት። ይህን በማሳደግ ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው ሀገሮች ተርታ ለመቀላቀል የምታደርገውን እንቅስቃሴ መደገፍ ይገባል፡፡
በተለይም አሁኑ ወቅት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የግንኙነት መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች የዘርፉን መልካም አጋጣሚዎች በመጠቀም የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን በመኖሪያ አካባቢዎች፣ በትምህርት ቤቶች እና በሥራ አካባቢዎች በስፋት በማስተዋወቅና የማህበረሰቡን የጉብኝት ባህል ማሳደግ የዘርፉን ጠቀሜታዎች ማሳደግ ከምን ጊዜው በላይ አስፈላጊ ነው ብለዋል አቶ ሀብታሙ፡፡
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚያዊ እድገት በማመጣጠን የማህበረሰብ ክፍሎችን የገቢ ምንጭ እና የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፆ አለውም ብለዋል፡፡
“ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና የሚተገብሩት አንድ ሊሆን ይገባል” ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር
***************************
(ኢ ፕ ድ)
ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ለማድረግ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና በተጨባጭ የሚተገብሩት አንድ አይነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ፡፡
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ባለው ሁኔታ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና በተጨባጭ የሚተገብሩት ለየቅል ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ አንዳንድ ፓርቲዎች ሲመቻቸው የሃይል አማራጭን በሌላ ጊዜ ደግሞ ሰላማዊ መስለው እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ሕጉን እና የሥነ ምግባር ደንቡን አክብሮ መንቀሳቀስ ይገባቸዋል፡፡ በዚህም ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ጊዜ እና በደህረ ምርጫ በሀገሪቱ ማንኛውም አይነት ግጭት እንዳይከሰት ከማድረግ አንፃር ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የራሳቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል፡፡
ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን በመሸጥ ህዝቡን አሳምነውእንዲመረጡ ለማድረግ በምርጫ ሕጉ እና በምርጫ ሥነ ምግባሩ መሰረት ሊንቀሳቀሱ ይገባል የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ በዚህም ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ማድርግ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38146
የ2013 በጀት ዓመት የችግኝ ተከላ ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ ምክክር እየተደረገ ነው
***************************
(ኢ ፕ ድ)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ውጤትና በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎችን አስመልክቶ በአዳማ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት ብቻ 9 ቢሊዮን ያህል ችግኞችን መትከል የተቻለ ሲሆን፤ እ.አ.አ እስከ 2022 ድረስ ሀያ ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተጥሎ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
በዚሁ አጠቃላይ ማዕቀፍ መሠረት እስካሁን በተተከሉ ችግኞች እንክብካቤና ጥበቃ ሥራዎች ላይ የ2013 በጀት ዓመት የችግኝ ተከላ ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ በተለይ የኮቪድ 19 ወሩርሽኝ ኢ-ተገማች ተጽእኖን በመቋቋም ችግኝ ተከላውን ተፈጻሚ ማድረግ ተችሏል። ይህም ራስን ከወረርሽኙ እየተከላከሉ ማምረት እንደሚቻል አመላክቷል።
በቀጣይም የማይበገር የተቀናጀ የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋት ይሰራል።
በምክክር መድረኩ፤ ስራውን በአቢይና በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ የሚመሩና የሚያስተባብሩ፣ ከፌዴራልና ከክልል መንግስታት የዘርፍ መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ስኳር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክን ያሽመደመደው የቀድሞው መንግሥት ደካማ አሠራር ታክሎበት ስለመሆኑ ተነገረ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ስኳር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክን ያሽመደመደው የቀድሞው መንግሥት ደካማ አሠራር ጭምር መሆኑን በሜቴክ እና በስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባልነትና አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩ ምሁር አስታወቁ፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ስኳር ለማምረት እያደረገችው ያለው ጥረት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር በላይ ወልደየስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በኢትዮጵያ ስኳር ለማምረት የሚያስችላት ሰፊ አቅም እንዲሁም ከ80 በመቶ በላይ አርሷደር የሚፈልገውን ማዳበሪያን ለማምረት የምትችልበት አቅም ያላት ቢሆንም፤ የስኳር ምርቱ ኋላ ቀር፣ ማዳበሪያ ለማምረት ያደረገችው ጥረትም በግንባታ ደረጃ መክኖ የቀረ ሆኗል፡፡ በመሆኑም የስኳር ምርቱም ሆነ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ለኪሣራ የተዳረገው ተገቢውን አሰራር መከተል ባለመቻሉ ነው፡፡
እንደ ፕሮፌሰር በላይ ገለፃ፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሸንኮራ ተክልን ለማልማት የሚያስችል የአየር ፀባይና ሰፋፊ ተፋሰሶች ያሉባት ሀገር ናት፡፡ ይሁንና ካላት ምቹ ሁኔታ በጣም ባነሰ ከ50 ዓመት ጀምሮ ስኳርን ከሸንኮራ ተክል እያመረተች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ እያመረተች ያለው በዋናነት ስኳር ሲሆን፤ በሁለት ፋብሪካዎች በጣም በጥቂቱ ለተሽከርካሪ ነዳጅ የሚሆነው ‹‹ኤታኖል›› ይመረታል፡፡ ሆኖም ይህ አሠራር ወደ ኋላ የቀረ ነው፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=38171