በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ተገለጸ
*****************
( ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል በተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት በየደረጃው እውቅና እንደሚሰጥ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የክልል ልዩ ሃይሎች በየቦታው የነበራቸው አስተዋጽ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ትናንት ከኦቢኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ እንዳስታወቁት፤ በዚህ የህግ ማስከበር ላይ የተሳተፉ የሰራዊቱ አባላት እንደየደረጃቸው የተለያዩ ሽልማቶችን የሚሸለሙ ይሆናል። ሜዳሊያ እና ማዕረግ የሚሸለሙ እንዲሁም ሌሎች የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ስርአቶችም የሚሰጡ ይሆናል።
“ጀግኖች ይሸለማሉ ታሪካቸውም ተፅፎ ለትውልድ ይቀመጣል” ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፤ እነዚህ ጀግኖች የሀገር ቅርስ ስለሆኑ እነሱን ማስተዋወቅ፣ መጠበቅና ማበረታታት ተገቢ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
እንደ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ማብራሪያ፤ በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ የአማራ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአፋር፣ የሶማሌ እና ሌሎችም ክልሎች በተለያዩ መንገዶች ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አብራርተዋል።
የቆሰሉ የሰራዊቱ አባላት በአብዛኛው በአማራ ክልል ሆስፒታሎች ሲታከሙ መቆየታቸውን የገለጹት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በክልሉ ያሉ ሆስፒታሎችና የህክምና መስጫ ተቋማት ለሰራዊቱ ክፍት እንዲሆኑ በማድረግ አምቡላንስና የህክምና ባለሙያ መድበው ቁስለኞችን በሰፊው ማከማቸውንና ሪፈር የተባሉት ብቻ ወደማዕከል መምጣታቸውን አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37843

“መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ይፈለጋል”ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የሰላም ሚኒስቴር
**********************
( ኢ ፕ ድ)
መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ስለሚፈለግ ለሁሉም የሆነች አገርን በመገንባት ሂደት ላይ ሁሉንም ለማሳተፍ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ፡፡
ትናንት በይፋ የተጀመረውን የብሔራዊ የማህረበሰብ ተኮር የምክክር መድረክን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን መሰረታዊ ተልዕኮ ለመወጣት ከባለድርሻዎች ጋር በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
እንደ አገር መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ስለሚፈለግም፤ ብዝሃነት ባለበት አገር ሁሉም ድምጾች እንዲደመጡ እድል መስጠት የሚያስችል ስራዎችን አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ከተሰጡት መሰረታዊ ተልዕኮዎች መካከል አንዱ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የህግ የበላይነት እና የዳበረ ዴሞክራሲ እንዲገነባ፣ እናም ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ ይሄን መሰረት በማድረግም በሁለት እርከን የተከፈለ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ሰፋፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=37844

“በኃይል ወንበር እይዛለሁ ብሎ የሚመጣ ይጎዳል እንጂ አይጠቀምም ” ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ
*******************
( ኢ ፕ ድ)
ጥሩ አላማ እና ህዝብ ይጠቅማል የሚል ሃሳብ ይዞ ከመቅረብ ያለፈ በሃይል ወንበር እይዛለሁ ብሎ የሚመጣ ማንኛውም ኃይል ከመጎዳት ያለፈ ምንም እንደማይጠቀም የህወሓት ጁንታ አፍኗቸው ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ።መከላከያ ሰራዊቱም በሰላማዊ መንገድና በዴሞክራሲያዊ አካሄድ የሚመጣውን ብቻ ተቀብሎ ለመሄድ የሚሰራ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ እንደተናገሩት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ለዓመታት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ላይ ተጠምዶ ከማሳለፉ ባሻገር በሃይል ወንበር ለመያዝ እንዲያመቸው በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ላይ የፈጸመው ጥቃት ውድቀቱን አፋጥኖለታል።
መከላከያ ሰራዊቱም ለዚህ የሚመች ሃይል አለመሆኑን አሳይቷል። በመሆኑም የተሻለ ዓላማ ለህዝብ በሚጠቅም ሃሳብ ይዞ ከመስራት ባለፈ በሃይል ወንበር ለመያዝ የሚደረግ ሙከራ የማይጠቅም፤ ይልቁኑም ያንን ኃይል የሚጎዳ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡
እንደ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ ገለጻ፤ የጁንታው ቡድን በህዝቡ ውስጥ ብቻ ሳይሆን መከላከያ ሰራዊትን የማጠልሸት እና የመከፋፈል ስራዎች ቀድሞ ሲያከናውን ነበር። ሰራዊቱ በአንድ መምሪያ እና ተቋም ስር ሆኖ ሳለ የሰሜን እዝ መጥፎ ነው ምዕራብ አሊያም ምስራቅ ዕዝ ጥሩ ነው የሚል መከፋፈል ሲታይ ቆይቷል። በማህበራዊ ድረገጾች እና በአካል ጭምር ሰራዊቱን የማጠልሸት ስራዎችን አከናውነዋል፤ በቻሉት መጠን የሰራዊቱን የውስጥ አንድነት ያናጋል ብለው የሚያስቡትን ለማድረግ ያልወረወሩት ጠጠር የለም።
https://www.press.et/Ama/?p=37845

www.press.et
“በኃይል ወንበር እይዛለሁ ብሎ የሚመጣ ይጎዳል እንጂ አይጠቀምም ” ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ጠቅሰው ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተብሏል።
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ መክረዋል።
ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላትና ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
"ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

"ይሄንን ጽኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮች እንዳይደገሙ አድርገን እንፈታዋለን"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮች እንዳይደገሙ አድርገን እንፈታዋለን" ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ።
ዛሬ በመከተል ተገኝተው በውቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከህዝቡ ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " ጠላቶች ኢትዮጵያን በብሔርና በሃይማኖት ለመከፋፈል ያላቸው ፍላጎት ዛሬም አልጠፋም፡፡ በጽናትና በአንድነት ስንታገለው ግን ይህ ፍላጎት መና ሆኖ ይቀራል" ሲሉ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመተከል ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የተመለከቱት ሕዝቡ ለአንድነት፣ ለሰላም፣ ለልማትና ለብልጽግና ያለው ፍላጎት ከማንኛውም ከፋፋይ አጀንዳ እንደሚበልጥ ነው የገለጹት ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕታቸውም፤ " ይሄንን ጽኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮችን እንዳይደገሙ አድርገን እንፈታቸዋለን" ሲሉ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት በቻይና ሄይናን ክፍለ ሀገር ዌን ቻንግ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ መጥቃለች
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት በቻይና ሄይናን ክፍለ ሀገር ዌን ቻንግ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ ማምጠቋን በቻይና የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቻይና - ቤጂንግ ከሚገኘው Smart Satellite Technology Corporation Limited ከተባለ ኩባንያ ጋር በትብብር ሳተላይት ለማልማትና ጥቅም ላይ ለማዋል ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በደረሰው ስምምነት መሠረት የግንባታ ሥራዋ ሲካሄድ የቆየውና ለሀገራችን ሁለተኛ የሆነችው “ET-SMART-RSS” የመሬት ምልከታ ሳተላይት በትላንትናው ዕለት በቻይና ሰዓት አቆጣጠር 12:37 ላይ በቻይና ሄይናን ክፍለ ሀገር ዌን ቻንግ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ መጥቃለች።
የሳተላይቷ ወደ ህዋ መምጠቅ በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን ወዳጅነት፤ በመንግሥታቱ መካከል ያለው የትብብር መንፈስ በግሉም ሴክተር እየታየ ለመምጣቱ ከኩባንያው ጋር ሳተላይቷን በማልማት የተሰራው የተቀናጀ ሥራ አመላካች ነው።
ሳተላይቷ በአካባቢ ጥበቃና ተፈጥሮ እንክብካቤ ረገድ ከምትሰጠው ጠቀሜታ በላይ በማልማቱ ሂደት የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ያገኙት ዕውቀትና ክህሎት ሀገሪቱ በቀጣይ ለምታመጥቃቸው ሳተላይቶች መሰረት የሚጥል ነው ተብሏል፡፡
ወደፊት በሀገር ውስጥ ሳተላይት ለማበልጸግ ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥርም ነው። የሳተላይቷ ወደ ህዋ መምጠቅ በቀጣይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ግንባታ አቅም የሚፈጥር መሆኑም ታውቋል።
የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት “ETRSS-1” እስካሁን በህዋ ላይ በነበራት ቆይታ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለግብርና፣ ለደን፣ ለውሀ ሃብትና ለመሳሰሉት የምርምርና የክትትል ስራዎች የሚያገለግል 800GB የምስል ዳታ እንጦጦ ለሚገኘው የምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ልካለች።
አሁን ወደ ህዋ የተመነጠቀችው ሁለተኛዋ ሳተላይት ተመሳሳይ ጠቀሜታ የሚኖራት ሲሆን ከመጀመሪያዋ ጋር ስትወዳደር የዕይታ ጥራቷ የተሻለ መሆኑ በዘርፉ ባለሙያዎች መግለጻቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡

ትእምት (ኢፈርት) በጥቂቶች ተይዞ ቢቆይም የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑን የትግራይ ብልፅግና ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ትእምት (ኢፈርት) ምንም እንኳ በጥቂቶች ተይዞ ቢቆይም የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑን የትግራይ ብልፅግና ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ።
ዶ/ር አብርሃም ዛሬ ለጋዜጠኞች በመቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ትእምት (ኢፈርት) በጥቂት የጁንታው አባላት ተይዞ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ተቋሙ የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት ወስኗል።
እንደ ዶ/ር አብርሃም ማብራሪያ፤ በተቋሙ ላይ የተጀመረው የፍርድ ቤት ጉዳይ ጎን ጎን ይቀጥላል።
የትእምት ሰራተኞች ስራቸውን እንዲጀምሩ አቅጣጫ መቀመጡን የገለጹት ዶ/ር አብረሃም፤ አመራሩ በባለአደራ እንዲመራ መንግስት አምኖበት ለፍርድ ቤት ለውሳኔ አቅርቧል ነው ያሉት።
የባለ አደራ ቦርድ አባላቱ 7 አባላት አሉት፤ 5ቱ በትምህርት እና በተመሳሳይ ዘርፍ ልምድ ያላቸው ናቸው ያሉት ዶ/ር አብርሃም፤ ሁለቱ ደግሞ ከገንዘብ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተመረጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የትእምት ጉዳይ በፍርድ ቤት የተያዘ ቢሆንም የተወረሰ ነገር የለም ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ የተቋሟቱ ሰራተኞች ደሞዝ እንዲከፈል እና ሰራተኞቹ ስራ እንዲጀምሩ መንግስት ወስኗል ብለዋል።
ከህግ ማስከበር ዘመቻው በተቃራኒ በመቆም በውግያ የተሳተፉ የተቋማቱ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ጉዳይም በህግ አግባብ ይታያል ነው ያሉት ዶ/ር አብረሃም።

የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የአምራች ኢንዱስትሪውን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት የሚያስችል የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በሰጡት መግለጫ፤ የአምራች ኢንዱስትሪውን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት የሚያስችል የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ከአለም ባንክ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በብድር የተገኘው ገንዘቡ ለሊዝ ፋይናንሰ፣ ለፕሮጀክት ፋይናንስና ለስራ ማስኬጃ ይውላል ብለዋል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪውን ከሚያጋጥሙት ችግሮች መካከል አንዱ የፋይናንስና የውጭ ምንዛሬ እጥረት መሆኑን የገለጹት አቶ መላኩ፣ ከዓለም ባንክ የተገኘው የ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ችግሩን ለማቃለል ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።
ከአለም ባንክ የተገኘው ብድር 1 ሺህ 990 ነባር ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም አዲስ ለሚቋቋሙ ኢንዱስትሪዎች የሚደርስ መሆኑንም አቶ መላኩ አመልክተዋል።
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በሁሉም አካባቢ እንዲደርስ ከማድረግ አንጻር ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።
በቀጣይም ሌሎች የዘርፉ ማነቆዎችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ለኢፈርት ድርጅቶች ሰባት አባላት ያሉት ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሹመት ተሰጠ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅራቢነት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመ/ቁ 263499 ለኢፈርት ድርጅቶች ሰባት አባላት ያሉት ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾሟል፡፡
ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ድርጅቶችን ወደ ሥራ ማስገባት፣ በእያንዳንዱ ድርጅት ዉስጥ ተቀጥረዉ ከሚሰሩ ብዛት ያላቸዉ ሠራኞች የሥራ ዋስትና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍና የድርጅቶቹን ንብረት ከብክነት መከላከል በአግባቡ ጠብቆ ለመያዝ ያመች ዘንድ የወንጀልና የሃብት ምርመራዉ ተጠናቆ በጉዳዩ ላይ ፍ/ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር የሚመራ ይሆናል፡፡
በዚህም መሠረት ባለአደራ አስተዳደሩ በፍ/ቤት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት የማስተዳደር ሥራን የሚያከናዉን ሲሆን በየጊዜዉ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሾመዉ ፍ/ቤት እንዲሁም ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
የጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደሩ አባላት ገለልተኝነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የሙያ ሥነ ምግባር እና ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት፣ በቦርድ አመራርነት እንዲሁም አባልነት በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆናቸዉን ተገልጻል፡፡
ለኢፈርት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለ አደራ አስተዳደር በማሾም ሂደት ውስጥ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዳስትሪ ሚኒስቴር እና የትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍና አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የወንጀል ምርመራ ጎን ለጎን የሀብት ጥናት እና ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን የድርጅቶችን ንብረት የማሸሽና ማባከን ተግባራትን ለመከላከል ሕግ በሚፈቅደዉ አግባብ ጊዜያዊ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ ስለነበረበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለፍ/ቤት የዕግድ አቤቱታ በማቅረብ የድርጅቶቹ የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ፣ ሌሎች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እንዳይሸጡና እንዳይለወጡ፤ በሌላ ማንኛዉም መንገድ ወደ ሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ማሳገዱ ይታወሳል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ በሲውዝርላንድ ጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ።
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ የኢዮጵያ መንግስት ደስተኛ አይደለም ያሉት አምባሳደር ዘነበ፤ ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስት አቅራቢነትና ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ መሆናቸውን አስታውሰዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ድጋፍ ጭምር አሁን ላሉበት ከፍተኛ የስራ ሃለፊነት መብቃታቸውን ያስታወሱት አምባሳደሩ፤ በዚህ ከፍተኛ ቦታ ላይ ሆነው በእንደዚህ አይነት ወገንተኝነት የታየበት ተግባር ላይ መሰማራታቸው ደስተኞች አይደለንም ብለዋል።
ይህንን የዶ/ር ቴድሮስ ተግባር መንግስት አግባብ ባለው መልኩ የሚሄድበትና ምላሽ የሚሰጥበት ይሆናል” ሲሉም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።

በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቀቀ
*************************
( ኢ ፕ ድ)
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡
በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 18 መማሪያ ክፍሎች፣ቤተመፀሀፍት፣ቤተሙከራዎች፣የአስተዳደር ህንፃ፣መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ፈንታ በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶችን ከመጠቀም ጀምሮ ተገቢ የሆነ የባለሙያ ክትትል ተደርጎለታል ተብሏል፡፡
የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ኃላፊው የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ቅጥርም እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመረዳት እድሉን መስጠቱ በከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ስም ምስጋና ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ግብአት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከተው የመንግስት ተቋም፣የአካባቢው ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ጥሪ ማቅረቡን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ላለፉት 30 አመታት በጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩት የደርግ ባለስልጣናት እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የኖሩትና የደርግ ባለስልጣናት የነበሩት ኮለኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄነራል አዲስ ተድላ እንዲለቀቁ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች አረጋገጡ።
ፍርድቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የሁለቱን ግለሰቦች ጉዳይ ተመልክቶ በአመክሮ እንዲፈቱ ወስኗል።
ቀደም ብሎ በእነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የክስ መዝገብ ስር ተፈርዶባቸው የነበረው ቅጣት ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮ እንደነበር በመግለጽ፤ የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የአመክሮ አስተያየትን ከይቅርታ ሰነዶች ጋር ለፍርቤት ማቅረቡን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የእድሜ ልክ ፍረደኛ በአመክሮ መታሰር ያለበት ለ20 አመት በመሆኑ ግለሰቦቹ በአመክሮ ቢፈቱ ተቃውሞ የለንም የሚል አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
ፍርድቤቱም ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን የህግ መንግስት ድንጋጌዎችና ሌሎች ህጎች መርምሮ ግለሰቦቹ ከኢንባሲው እንዲለቀቁ ወስኖ ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትዛዝ ሰጥቷል።
ትዛዙ በቀጥታ ለጣሊያን ኤምባሲ ሳይሆን በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለጣሊያን ኤምባሲ እንዲሁም ለቀድሞ ፍርደኞች ሻለቃ አዲስ ተድላ እና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ እንዲደርስ ይደረግ ዘንድ አዟል።
ሻለቃ አዲስ ተድላ እና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ የቀድሞ ፍርደኞች አሁን ግን በአመክሮ በፍርድ ቤት የተለቀቁ መሆኑን አውቀው መብታቸውን ለማስከበር ጥበቃም ሆነ ክትትል እንዲያደርጉ ለሚመለከተው አካል እንዲጻፍ ፍርድ ቤቱ አዟል።

የሕግ የበላይነት ባለመከበሩ፣ እንደ አገር ከተመዘገቡት ድሎች ያመለጡት ዕድሎች በእጅጉ የበዙ መሆናቸው ተገለፀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች፣ ህዝቦቿም በአንድም በሌላ በደም የተሳሰሩ ቢሆንም ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ፣ የአገር ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ህግ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ባለፉት ዓመታት እንደ አገር ከተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያመለጡ በረከቶች በእጅጉ እንደሚያመዝኑ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ገለጹ፡፡
ኮሚሽነሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፤ አገራችን በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ በቀላሉ ሰርተው የሚለወጡባት፣ አየሯ ተስማሚና ለኑሮ የምትመች ናት፡፡ ይሁን እንጂ በከፋፋይ አስተሳሰብ የተቃኘና ከአገር ይልቅ የቡድኖች ህግ ለዘመናት ገዝፎ በመቆየቱ ለሌላ መትረፍ የምትችል አገር በምግብ እንኳ ራሷን መቻል አቅቷት ለውጭ እርዳታ እጇን ስትዘረጋ ቆይታለች፡፡ ዛሬም ከውጭ እርዳታ ባለመላቀቋ እና የዚህ ምክንያቱም ተፈጥሯዊ ሳይሆን ሰው ሰራሽ እንደመሆኑ ሁሉም ዜጋ በቀጣይ በኢትዮጵያ እድል ላይ አስቦና ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል።
እንደ ኮሚሽነር አበረ ገለጻ፤ ህግና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ያለፉት ታሪኮች አገርና ህዝብ ባልተስተካከለ ሚዛን የሚመራ ህግ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ኢትዮጵያ አስከፊ ብጥብጥና ውድመት ለማስተናድ ተገዳለች። ይህ ደግሞ አገሪቱን አቅም አሳጥቶ፣ አመት ሙሉ ምርት ማምረት የሚያስችሉ ወንዞችና ለም አፈር እያላት የስንዴ ለማኝ ሆናለች።
ወደ ዘመነ መሳፍንትና ከዚያ በፊት ያሉ ዘመናት በታሪክ ሲቃኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከዳር ወደ መሀል አገር እንዲሁም ከመሀሉ ወደ ዳር በተደረገው እንቅስቃሴ በጋብቻ ያልተሳሰረና ያልተዋለደ እንደሌለ የሚናገሩት ኮሚሽነሩ፤ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ጎጠኝነት በመንሰራፋቱ ምክንያት በደም መተሳሰራችን ተረስቶ፣ የህግ የበላይነትም ጠፍቶ፣ ይልቁንስ ህግ በአገር እይታ ሳይሆን በቡድን እይታ የሚተረጎምበትና የሚተገበርበት ዘመናት እንደ ነበሩ ያስረዳሉ።
https://www.press.et/Ama/?p=37981

ላለፉት 30 አመታት በኤምባሲ ውስጥ በተከለለ ቦታ ተገድበው የኖሩትን የቀድሞ የደርግ አመራሮችን ከዚህ በላይ ነጻነታቸወን ገድቦ ማቆየት የፍትህ ዓላማን ከማሳካት አንጻር የሚጨምረው ነገር ባለመኖሩ በአመክሮ እንዲፈቱ መደረጉ ተገለጸ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ላለፉት 30 አመታት በኤምባሲ ውስጥ በተከለለ ቦታ ተገድበው የኖሩትን የቀድሞ የደርግ አመራሮችን ከዚህ በላይ ነጻነታቸወን ገድቦ ማቆየት የፍትህ ዓላማን ከማሳካት አንጻር የሚጨምረው ነገር ባለመኖሩ በአመክሮ እንዲፈቱ መደረጉ ተገለጸ።
በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ጸጋዬ እንዳስታወቁት፤ ግለሰቦቹ እስካሁን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ነጻነታቸው ተገድቦ መቆየቱ አስተማሪነት ያለው መሆኑ ከግምት ገብቶ በአመክሮ እንዲለቀቁ ጥያቄውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጋር በጋራ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ወስኖዋል።
እንደ አቶ ፍቃዱ ማብራሪያ፤ ከዚህ በላይ እነኚህን ሰዎች ነጻነታቸውን ገድቦ ማቆየት የፍትህ አላማን ከማሳካትም አንጻር የሚጨምረው ውጤት የማይኖር በመሆኑ፣ እንዲሁም ከፍርደኞቹ እድሜ እና የጤና ሁኔታ አንጻር የሰብዐዊነት እይታን ከግምት በማስገባት ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ነው የተወሰነው።
በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የቀድሞ ደርግ አመራሮችም ከ10 ዓመታት በፊት ከእስር ወጥተው ከማህበረሰቡ ጋር እየኖሩ ይገኛሉ ያለው ዓቃቤ ህግ፤ በተቃራኒው በጣልያን ኤምባሲ ውስጥ ተወስነው ለ30 ዓመታት የቆዩት እነኚህ ሰዎች ከመደበኛው የእርምት ስፍራ ባልተናነሰ በተወሰነ አነስተኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ወደ ህክምና ተቋማት እንኳን መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መኖራቸው መረጋገጡን አቶ ፍቃዱ ገልጸዋል።
በኤምባሲው ውስጥ በቆዩባቸው አመታት ከመንግስትም ሆነ ከቆዩበት የኤምባሲ ቅጥር ግቢ አሰተዳዳሪ ምንም አይነት እንክብካቤ እና ድጋፍ ሳያገኙ መቆየታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በእስር ቢቆዩ ኖሮ ከሚፈጠርባቸው የመብት ገደብ አንጻር ቢበዛ እንጂ የሚያንስ አንዳልሆነ ግንዛቤ ተወስዶበታልም ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ፡፡

በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸምን ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን- ብልጽግና ፓርቲ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ብልጽግና ፓርቲ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ጥቃት አጥብቆ ያወግዛል፡፡
ዜጎችን በማንነት ለይቶ በማጥቃት ምንም አይነት የፖለቲካ ትርፍ ሊገኝ አይችልም፡፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተደጋጋሚ በዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የትኛውንም የህዝብ ክፍል የማይወክልና ኃላፊነት የማይሰማቸው የግጭት ነጋዴዎች ሴራ መሆኑን መላው የሀገራችን ህዝቦች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
በጨካኝ አረመኔ የጥፋት ኃይሎች ጥቃት በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰው ላለው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን ለዘመናት ተከባብሮ ክፉና ደጉን አብሮ ያሳለፈን ህዝብ በማጋጨት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጣጣሩ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች የማይሳካላቸው መሆኑን አጥብቀን ልንገልጽላቸው እንወዳለን፡፡
በዜጎች ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸውንና ችግሩ እንዲፈታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች ላይ ጥብቅ ፖለቲካዊ፣ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ለፍቶ አዳሪ ንጹሃን ዜጎችን በማንነታቸው ብቻ ለይቶ በማጥቃት ሀገርንና ህዝብን ወደ ትርምስ ለማስገባት ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ የውስጥም ሆነ የውጭ ጨካኝ የጥፋት ኃይሎችን አጥብቆ የሚያወግዝና በእነዚህ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ ብልጽግና ፓርቲ አጥብቆ የሚታገል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ችግሩን ለመፍታት በተለያየ መልኩ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን ጥቃት ከማስቆም እና ችግሩን ከመፍታት አንጻር በተለያየ መልኩ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ መንግስት ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአከባቢው ያለውን ችግር ከመፍታት አኳያ በተለያየ መልኩ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ “በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል፤ በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ፤ ብለዋል።
ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የጠላቶቻችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው፤ ይህ የሚሳካ አይደለም፣” ብለዋል።
መንግሥትም ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን በመግለጽም፤ “የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ሁላችንም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንድንሠራ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊት በመተከል ዞን ተገኝተው ከክልሉ አመራሮች፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች ጋር በመወያየት የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫን በማስቀመጥ ለአካባቢው ሰላም ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ እንደሚገባ ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው።

በመተከል እየተፈጸመ ያለው ግድያ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እጅጉን መዳከሙን እንደሚያሳይ ኢሰመኮ ተናገረ
*******************************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተበራከተ የመጣው እና ከሰሞኑ ሌሊት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን የሚያሳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። ኮሚሽኑ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ መሆኑንም ተናግሯል።
ኮሚሽኑ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን ነው። በመሆኑም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው።
በመግለጫው እንደተመላከተው፤ ኢሰመኮ የጥቃቱን ሂደት በተመለከተ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከሚመለከታቸው አካላት እና ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ሲከታተልና ሲያጣራ ቆይቷል። በኩጂ ቀበሌ ከወረዳው መቀመጫ ከሆነችው ቡለን ከተማ 90 ኪ.ሜ. ርቃ የምትገኝ ሲሆን የሺናሻ፣ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ይኖሩባታል። ለቀበሌው የተመደበ የፖሊስ ወይም የፀጥታ ኃይል አለመኖሩን ኮሚሽኑ በክትትሉ መሰረት ተረድቷል።
https://www.press.et/Ama/?p=38060

ፖርት ሱዳንን ለኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ንግድ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለማድረግ ከፖርት ሱዳን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አጓጓዥ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደረገ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ፖርት ሱዳንን ለኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ንግድ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለማድረግ ከፖርት ሱዳን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አጓጓዥ ድርጅቶች ጋር ውይይት መደረጉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው የልዑካን ቡድን ፖርት ሱዳንን ለአገራችን የወጪገቢ ንግድ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ በማድረግ ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን በዚሁ ወደብ በመጠቀም ለሰሜንና ምዕራቡ የአገራችን ክፍል ተደራሽ ለማድረግ መሻሻል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከፖርት ሱዳን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም አጓጓዥ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው የልዑካን ቡድን ከሱዳን መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትር፣የማእድንና ኢነርጂ ሚኒስትር፣የሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ኃላፊ፣ከሱዳን ባቡር ኮርፖሬሽን እና መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ከንግድ ሚኒስቴር እና ጉምሩክ መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች በትራንስፖርት ዘርፍና በተለያዩ መስኮች በጋራና በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደርሷል፡፡
ፖርት ሱዳንን ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለማድረግ፣በኢትዮጵያ-ሱዳን የምድር ባቡር መስመር ዝርጋታ የመጀመሪያ አዋጭነት ጥናት ሂደት፣በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከርና በአጋርነት መስራት፣ በየብስ ትራንስፖርት ዘርፍ ያጋጠሙ ማነቆዎችን በጋራ በመፈተሽ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከስምምነት መድረሳቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የሱዳን ትራንስፖርትና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ሚ/ር ሃሺም ኢብንኦፍ ሱሌይማን በኢትዮጵያና ሱዳን መካካል በትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት የተደረሰባቸውን ነጥቦች በአፋጣኝ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያግዝ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

መቐለ ያሉ የመንግስት መስርያቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
👉 ከማረሚያቤት ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎች ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንዲፈጠር ተደርጓል፤
👉 ጁንታው “ጦርነት አላለቀም” በሚል ወሬ እያስነዛ ህዝቡ ወደ ስራ እንዳይገባ አድርጎታል፤
****************
(ኢ ፕ ድ)
መቐለ ያሉ የመንግስት መስርያቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ በሰማዕታት አደራሽ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።
የዚሁ ውይይት ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፤ መቐለ ያሉ የመንግስት መስርያቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል፤ በዚህም ህብረተሰቡ እየተጉላላ ይገኛል።
በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የደረሰው ክህደትና ጥቃት ያወገዙት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጭር ጊዜ ህግ የማስከበሩን ስራ በማጠናቀቁ እናመሰግናለን ሲሉም ተናግረዋል።
የህወሓት ጁንታ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ማረሚያቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሆን ብሎ በመቐለ በትኖ ሄዷል ያሉት ተወያዮቹ፤ በእነዚህ ከማረሚያቤት ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎች ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንዲፈጠር ተደርጓል ሲሉም ነው ያስታወቁት።
የሀሰት ወሬ በመቐለ ከተማ እየተነዛ ህዝቡ እየተሸበረ ስለሆነ አስተዳደሩ ይሄን ያጥራልን ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ ነጋዴው ከመሃል ሃገር ሸቀጥ እንዳያመጣ “ጦርነት አላለቀም” በሚል ወሬ እየተነዛ ወደ ስራ እንዳይገባም አድርገውታል ነው ያሉት።
በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጊዚያዊ አስተዳደሩንም ሆነ ህዝቡን ማገዝ አለበት ያሉት ተወያዮቹ፤ በደቡብ ትግራይ እና ምዕራብ ትግራይ አካባቢ ያሉ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የሰሜን ዕዝ አዛዡ ጄነራል በላይ ስዩም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መከላከያ የአገር ዳር ድንበርን የሚያስከብር ሃይል ነው። ነገር ግን ጁንታው የገደለው ይሄንን ሃይል ነው በማለት የተፈጸመውን ክህደትና ግፍ ለተወያዮቹ አብራርተዋል።
“እንደመከላከያ ጓዶቻችን በጁንታው ተገድለዋል፣ የሰራዊቱ ንብረት ተዘርፏል፤ እንደ አገርም በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅእኖ ተፈጥሯል” ያሉት ጄነራሉ፤ የዘጠና አመት አዛውንቶች መጥተው ይመሩናል ብላችሁ ተስፋ እንዳታደርጉ፤ በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ጁንታው ከዚህ በሁዋላ አይመለስም፤ ስለዚህ ተረጋግታችሁ ጊዚያዊ አስተዳደሩን ማገዝ አለባችሁ” ሲሉም ለመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የመቐለ ከንቲባ አቶ ኣታኽልቲ ሃይለስላሴ እና የሰሜን እዝ አዛዥ ጀነራል በላይ ስዩም መገኘታቸውን በመቀሌ ከተማ ያለው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ያደረሰን መረጃ ያሳያል።