Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
«ጁንታው ሕጋዊ የንግድ ውድድርን ማዛባት ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪዎችን የማጥፋት አካሄድ ይከተል ነበር » - አቶ ውብሸት ሙላት የህግ ባለሙያ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ወንጀለኛው የህውሓት ጁንታ ሁሉንም የቢዝነስ ተቋማት በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ማንኛውም የንግድ ውድድር እንዳይኖር ከማድረግ በዘለለ ተፎካካሪ ሊሆኑ የሚችሉ የግልና የመንግስት የንግድ ተቋማትን እስከማጥፋት መሄዱን የሕግ ምሑሩ አቶ ውብሸት ሙላት አስታወቁ ።
አቶ ውብሸት በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ይህ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው መስክ አግላይ ብቻ ሳይሆን ሌላውንና ከሱ ውጭ የሆነውን የሚያስወግድ እና አፋኝ ነበር ። በኢኮኖሚውም መስክ በኢትዮጵያ ትልቁ ኢንቨስተር ይህ ቡድን ነበር ፤ከፌደራል መንግሥት በላይ የኢኮኖሚ አቅም የፈጠረ ነው ።
አንድ ቡድን በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው የበላይ ከሆነ እና በዚያ ላይ ያለው አስተሳሰብ አግላይ ከሆነ አገርን አደጋ ላይ ይጥላል የሚሉት አቶ ውብሸት፤ አገር ማፍረስን ጨምሮ የፈለገውን እንዲያደርግ እድል ይሰጠዋል፤ በወንጀለኛው ጁንታ የሆነው ይኸው ነው ብለዋል ።
https://www.press.et/Ama/?p=36925
"ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል ዝግጁ እናደርጋለን"
- አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል ዝግጁ እናደርጋለን ሲሉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስተወቁ።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ተብሎ አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር መደረጉን ያስታወሱት ወ/ሮ አዳነች፤ "አሁን ጃንሜዳን መልሶ ለጥምቀት በዓል እና ሌሎች ማሀበራዊ አገልግሎቶች ዝግጁ ላማድረግ ቦታውን ማጽዳት እና ማስተካከል ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ዛሬ ማለዳ በቦታው በመገኘት የጽዳት ስራ አስጀምረናል"ብለዋል።
በቦታው ያሉ ነጋዴዎችም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በሃይሌ ጋርመንት እና በሌሎች አካባቢዎች ወደተዘጋጁ የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉና ለዚህ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ከንቲባዋ አሳስበዋል።
"አዳዲሶቹ የአትክልት ገበያዎች የሚርቋቸው የከተማችን ነዋሪዎች ይቅርታ እየጠየኩ በገርጂ፣ ጀሞ፣ አቃቂ፣ ጉለሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ተጨማሪ የገበያ ስፍራ እያዘጋጀን መሆኑን እና ችግሩ ጊዜአዊ እንደሆነ ማሳወቅ እወዳለሁ" ሲሉም ተናግረዋል።
ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለበዓሉ አከባበር በኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ በመተባበር፣ በመቻቻል እና መተሳሰብ መንፈስ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
“አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለው፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ ያንን ተቋቁመን ባንዘግበው፤ ቦታው ላይም ባንቆም ኖሮ ወንጀሉ ተዳፍኖ ይቀር ነበር” - ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ አመት የምስረታ በአሉን አመቱን ሙሉ በተለያቱ መድረኮች እያከበረ ይገኛል። የበአሉ አካል በማድረግም በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የምስጋና እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በዚሁ መርሀ ግብር ላይም ወደ ግንባር ከተላኩ ጋዜጠኞች መካከል የማይካድራውን ጭፍጨፋ በስፍራው ተገኝቶ የዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን የተመለከተውን ለእለቱ ታዳሚያን አጋርቷል።

አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለው፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ ያንን ተቋቁመን ባንዘግበው ቦታውም ላይ ባንቆም ኖሮ ወንጀሉ ተዳፍኖ ይቀር ነበር” ሲል ነው ጋዜጠኛ ወንድአጥር ምልከታውን ያጋራው።

የተመለከትኳቸው ነገሮች የሚያሙ ናቸው፤ እነዚህ ህመሞች እኛን አመው ባይቆሙ ኖሮ ኢትዮጵያም ኢትዮጵያ ሆና አትቀጥልም ነበር፤ እውነት ለመናገር የማይካድራ ህዝብ ህመሙን ባይችለው ኖሮ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና አትቀጥልም ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ወንድአጥር በእለቱ በሰጠው የአይን ምስክርነት ላይም ያነሳቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፤

👉በማይካድራ ላይ የሞተው በዋናነት አማራ ይሁን እንጂ ኦሮሞም ሞቷል፤
ወላይታም ሞቷል፤ ሶማሌም ሞቷል፤

👉ትህነግ ለማንኛውም ነገር እንደማይመለስ የስለት ጫፍ ድረስ ከመጨከን
ወደኋላ እንደማይል ያሳየበት ቦታ ማይካድራ ነው፤

👉የትህነግ ጥላቻ ከ1968 ማኔፌስቶውም በፊት ነው፤ ማንፌስቶው እኮ
የአስተሳሰቡ ውጤት ነው፤

👉የትህነግ የማይካድራ ጭካኔና ጭፍጨፋ በፊት ከመጋረጃ ጀርባ እንደሚፈጸም
በሀሜት ደረጃ ይሰማ የነበረው አሁን መጋረጃው የተገለጠበት ሰይጣንም
ያፈረበት ስራው ነው፤

👉የጁንታው ውሸት አስገራሚ ነበር፤ እኔ ሁመራ ሆኜ ዘገባ እየሰራሁ፤ በሬዲዮ
የሰማሁት የእነሱ ዜና ሁመራን ተቆጣጥረናል የሚል ነው፤ ደነገጥኩ የት ነው
ያለሁት እኔ ነኝ ወይንስ ሁመራ ነው ወደሌላ ቦታ የሄደው እስክል ድረስ
ተገረምኩ፤

👉እነሱ ቢዋሹም አይናቸውና እጃቸው አይዋሽም ነበር፤ በሚዲያዎቻቸው
እየቀረቡ ሲዋሹ ሁሉም ነገር ያስታውቅባቸው ነበር፤

👉የትህነግ ሀይል ገኖ ነበር የመጣው፤ በተለይ እኔ በነበርኩበት አብድራፊ በኩል
አብድራፊን ተቆጣጥሮ ወደ ጎንደር፤ ሶሮቃን በዳንሻ በኩል ተቆጣጥሮ ወደ
ጎንደር፤ በራያ በኩል ወደ ወልዲያ የመሄድ እቅድ ነበረው፤ 23ኛው ክፍለ ጦር
ተበትኖ ስለነበረ ምንም አያስቀረውም ነበር።

👉ነገር ግን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ዝግጁ ስለነበረና የኮንትሮባንድ ስራን
ሲቆጣጠሩ በነበሩ ከተፈጸመባቸው ጥቃት ያመለጡ የፌዴራል ፖሊስ አባላትም
ባደረጉት ተጋድሎና ጀግንነት ትህነግ ሊቆም ችሏል፤

👉ከፊት ለፊት በመሳሪያ ከጎናቸው በጓደኞቻቸው አስከሬን ሽታ ተፈትነው ድል
ነስተዋል፤ ይሄንን ድል ያደረጉት በኢትዮጵያ ፍቅር ነው፤ በኢትዮጵጽያዊነት ነው፤

👉የአማራ ልዩ ሀይል ወደማይካድረ ከመሄዱ በፊት ሁለት የግዴታ አማራጮች
ነበሩት፤ አንደኛው ያለውን ስንቅና ጥይት ለተበተኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት
እያጋራ መዝለቅ፤ የተማረከውን ሀይል ደግሞ ለመከላከያ እየሰጠ መሄድ
ነበረበት፤ ይሄንን አደረገ፤

👉ሁለተኛው አማራ ልዩ ኃይል ሌላኛው ጫና እነማይካድራን ማስለቀቅ፣ የሉግዲ
መሿለኪያን ማስለቀቅ ወደ ሱዳን የሚሄደውን የትህነግ ኃይል የሚሾልከበትን
በር መዝጋትና የሁመራን ቦታ መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን የተከበቡ የመከላከያ
ሰራዊት አባላትን ከጓደኞቻቸው የአስክሬን ሽታ፣ ከተከበቡበትም ሕይወታቸውን
ማትረፍ ግዴታው ነበረ፤ ሀላዊና በረከት ላይ ይህንን አደረገ፤

👉ወደ ማይካድራ ስንደርስ ደም ፈሷል፤ ሁሉም አዝኗል፤ ሁሉም ይተኩሳል፤
ከመኪና ስንወርድ ሁሉም በእኛ ተቆጥቷል፤ ምክንያቱም እኛ ድሉን ስናበስር
ነው የቆየነው፤

👉እዛ ቦታ ላይ ደም ፈሷል፤ የራሳችንን ወገን ደም ረግጠናል፤ እዛ ቦታ ላይ በወደቀ
የአስክሬን ብዛት መካከል መቆም ምናልባትም ትንፋሽን መቁጠር እስከሚያክል
ድረስ የምንተነፍሰው አየር ያስጨንቀን ነበር፤

👉በእንደዚህ አይነት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ትንፋሽ ቅንጦት ነው፣ የልብ ምት
ቅንጦት፤ ሁሉም ጭንቅላታቸው ተከፍቷል፤ ሁሉም ሆዳቸው ተከፍቷል፤ ሁሉም
ደምተዋል፤ ሁሉም ወድቀዋል፤ አልጋ ያገኙት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ በእነዚህ
መሃል መቆም በጣም ከባድ ነበር፤

👉በጋራ ሆነን ይህንን ነገር ለዓለም ማሳወቅ ነበረብን፤ ይህንን ዘግተነው ካለፍን
አደገኛ ነበረ፤ መበርታት ነበረብን፣ ደም ረግጠን ነው የቆምነው፤ ሁላችንም
ደም ረግጠናል፡፡

👉ይህንን ለቅሶ እዛ አላለቀስኩትም፣ ሰላም ስለሆነ ነው፤ ማልቀስም ሰላም
በሆነበት ቦታ ነው የሚቻለው፣

👉ህዝብን አነጋገርን ወስደው እንደ ቀበሯቸው ነገሩን፤ ነገር ግን የተገደሉት እነዚህ
ብቻ አይደሉም አሉን፤

👉ከቢሮ መቀሌ ትገባላችሁ የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶናል፤ መቀሌ መግባት ለእኛ
መዝናናት ነበር፤ ስለሆነም በየቦታው የተደፉ ሰዎችን ማሳየት ነበረብን፤ አሞራና
ዝንብ እየተከተለን በየቦታው የወደቁ አስከሬኖችን አሳየን፤

👉 ዓለም የትህነግን መጥፎነት ያየው ያን ቀን ነበር፤ ምክንያቱም በፕሮፓጋንዳ
ተሸፍኖ ነበረ፤ እኛ ገለጥነው፤

👉 ከአከባቢው ሰው ጋር ተባብረን በመጀመሪያው ቀን የ74 ሰዎችን አስከሬ
አገኘን፤ 74ቱም ስዎች በጋራ ነው የተቀበሩት፤ የህጻናት ጫማ ነበረ፣ የሴቶች
ነጠላ ነበረ፤

👉 አቡነ አረጋዊ በሚባለው ቦታ ላይ የተቀበሩት ሰዎች ቁጥራቸው አይታወቅም፤
በጣም የሚገርመው አስክሬኖቹን መቅበር የማይቻልበት ጊዜ ነው የተደረሰው፤
የአካባቢው ሰው የአስከሬኑን ሽታ ለመቋቋም ሲል ሽቶ ተጠቅመዋል፤

👉 ከሁለት ቀናት በኋላ ተመሳሳይ ጥቆማ ደረሰን፤ አሞራ አከባቢውን ይዞራል፤
ዝንቦች ወረውታል፤ 18 የደረቀ አስክሬን አንድ ላይ ሳይቀበሩ አገኘን፤ እንዲሁ
ነው የተደፉት፤

👉 እስከ መቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው አሁን ያለን አማራጭ ኢትዮጵያ
የሁላችንም ድምቀት መሆን አለባት፤ የሁላችንም ጌጥ ነው መሆን ያለባት፤

👉 ኢትዮጵያን ተጭኖ የተለያዩ ብሔሮችን ዘር እየለየ የሚያጭድ የተንኮል ገበሬ
ካለና እሱ ካልፀዳ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያ መሆን አይችልም፤

👉 እያንዳንዱ ወታደር የተዋጋው በሸተተ ጓደኛው አስክሬ ጎን ሆኖ ነው፤ እዚህ
ቦታ ላይ መቆም አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔ

አይቻለሁ ከዚህ በፊት ልጄን ቀብሬያለው፤ አልከበደኝም፤ ማይካድራ ላይ ግን
መቆም አይቻልም፤ ይሀንን መመስከር አይቻልም፤

👉 ሰው ካልሆንን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፤ እነዛ ሰዎች ሰውነታቸው
ስለካዳቸው ነው ኢትዮጵያዊ መሆን ያልቻሉት፤

👉 ከዚህ በኋላ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የመጨረሻውን የተንኮል ስለት የያዘው አካል
በመከላከያ ሰራዊት፣ በልዩ ኃይል አባላት፣ በአፋር ልዩ ኃይል አባላት፣ በሁሉም
ኢትዮጵያዊ ደጀንነት ተሰናብቷል፤
ወታደሮችን በሲኖ ትራክ እስከመጨፍለቅ የዘለቀው የጁንታው የክፋት ጥግ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
ሃምሳ አለቃ ደረጀ አንበሳ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ የጥገና ባለሙያ ናቸው። በሙያቸው አገራቸውን ሌት ተቀን ከማገልገላቸውም በላይ እንደማንኛውም የመከላከያ አባል ለትግራይ ህዝብ በችግሩ ጊዜ ከጎኑ በመቆም አጋርነታቸውን ሲገልጹ ኖረዋል። የህዝብና የአገር ከለላና መከታ የሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ አባል እንደመሆናቸው አንድም ቀን በአገር ልጅ የባንዳነት ተግባር ይፈጸምብኛል ብለው አስበውም አያውቁም።
ይሁንና በእናት ጡት ነካሾች ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ከምሽቱ አራት ሰዓት ያልታሰበ ጥቃት ተፈጸመባቸውና ያለምንም ጥፋታቸው ተይዘው ለእስር መዳረጋቸውንና ቀላሚኖ እሰርቤት መታሰራቸውን ይገልጻሉ።
"ከቀላሚኖ እስር ቤት ወደ አግቤ በመቀጠልም ከትንሽ ቀን በኋላ ወደ ተንቤን መምህራን ኮሌጅ ወሰዱን። የመከላከያ ሠራዊትን የከባድ መሳሪያ ድምፅ ሲሰሙ የ90 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ አስጀመሩን። ልክ 40 ኪሎ ሜትር እንደተጓዝን ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ሲኖ ትራክ መኪና ከኋላችን መጣ። ተጓዡ ወደ 1,200 ሰው ነበር። ከአስፋልት እንድንወጣ ካለመፈቀዱም በላይ ከአስፋልቱ መሀል ከወጣን ልዩ ሀይል ተኩሶ ይመታን ነበር። ከግራና ከቀኝ ገደላማ የሆነ ጠባብ ቦታ ላይ ስንደርስ ሲኖ ትራክ መኪና ልከው ከኋላችን ነዱብንና የሚገድለውን እየገደለ፣ ያቆሰለውን እያቆሰለ ሄደብን።
እኔንም አንድ እግሬን አገኘኝና እግሬ ከተሰበረ በኋላ ተንከባልዬ ጉድጒድ ውስጥ ገባሁ። እዚያው ጉድጓዱ ውስጥ ከተጎዱ ጓደኞቼ ጋር ተኝቼ አደርኩ። ሲኖ ትራኩ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር የተጓዘው በሰዎች ላይ ነበር። በዚህም ግማሹ ሞተ፣ ግማሹ ቆሰለ የቀረውም ወደገደል ገባ። እንግዲህ የራሳችን ወገን ነው እንዲህ አይነት በደል የፈፀመብን። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው። ስንት ዓመት ሙሉ አብረናቸው ኖረን በመኪና ሲጨፈልቁን በጣም ነው የተሰማኝ፤ በጥይት ቢገድሉኝ ይሻል ነበር" ይላል::
በወቅቱ ሴቶችም ህፃናትም አብረውን ነበሩ ማን እንደሞተ ማን እንደተረፈ አንኳን አላውቅም ያለው ወታደሩ "በወቅቱ በሕይወት የተረፋትም ተበታተኑ፤ አንዳንዶቹም ቆስለው ወደጫካው ገቡ፤ የሞቱትም እዛው ቀሩ አምስት የምንሆን ሰዎች እዛው አድረን ከሞቱት ሰዎች መሀል በሕይወት ወጣን። የሞቱ ልጆችን እንኳን ለመለየት አልቻልኩም፤ አጠገቤ ነው እየጮሁ የሞቱት፤ ምንም ልረዳቸው አልቻልኩም። በወቅቱ እኔም በሁለት እግሬ መቆም አልችልም ነበርና በጉልበቴ ዳዴ እያልኩ ነው የወጣሁት" ሲል የውቅቱን አሳዛኝ ሁኔታ ይገልፃል::
"እኛኮ ከሌሊቱ 11 ሰዓት እየተነሳን አጨዳ የምናጭድ፤ ኮረና ገባ ሲባል ብር እያዋጣን የምንደግፍና ከደሞዛችን እየቆረጥን የልማት ስራዎችን የምንሰራ ነን። እኛ ለትግራይ ህዝብ ልማት ወደኋላ ብለን አናውቅም። ይሁንና ጁንታውና የእሱ ተላላኪዎች በሰው ላይ የማይፈፀም ድርጊት ነው የፈፀሙብን። ሰብስበው በቦንብ ቢያቃጥሉን ወይም በጥይት ቢገድሉን ይሻል ነበር። የውጪ ጠላት እንኳን በመኪና ሰውን ደፍጥጦ አይገድልም። ድርጊቱ ከተፈፀመብን በኋላ በመኪና መንገድ ላይ ስንሄድ እየተሸማቀቅን ነው። ጭንቅላታችን ራሱ ተጎድቷል::
ሌላው ተመሳሳይ ድርጊት የተፈፀመበት አምሣ አለቃ ወንድማገኝ ወልደገብርኤል ነው። እሱ እንደሚገልፀው በልዩ ሀይል እና በሚሊሻ ታጅበን በእግር እየተጓዝን ሳለ ከአስፓልቱ እንዳትወጡ አሉን እኛም ፈንጂ ያለ መስሎን የአስፋልቱን መሀል ይዘን መጓዝ ጀመርን። ጨለምለም ሲል ከኋላችን ሲኖትራክ መኪና መጣ፤ ከፊት ለፊት ተኩስ ተከፈተብን፤ እንዳንመታ ብለን ሁላችንም ተኛን፤ በዚህ ወቅት ሲኖ ትራኩ እየጨፈለቀን ሄደ ።
ግማሹ እየተንከባለለ ወደገደል ገባ፤ ተገጭተን የተረፍነው በማግስቱ ተነሳን፤ ብዙዎች ግን በሚያሳዝን ሁኔታሞቱ፤ አንዳንዶቹም ቆሰሉ፤ አሽከርካሪው ለመትረፍ የሚሞክሩ ሰዎችንም ዚግዛግ እየነዳ ነበር ሲጨፈልቃቸው የነበረው። በእግራችን መሄድ አቅቶን ጅብ ይብላን ብለን እዛው ከተኛን በኋላ ታፍነው በመከላከያ ሰራዊት እርዳታ የተለቀቁ እስረኞች እየረዱን የተወሰነ ርቀት ከተጓዝን በኋላ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ደርሰው ወደዚህ አመጡን። ሲሉ ደረሰባቸውን ግፍ አስረድተዋል።
ኢያሱ መሰለ
ታማኙ ሳጅን!
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ዋና ሳጅን ታከለ እሸቴ ይባላል። በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር መተማ ዮሀንስ የወንጀል መከላከል ኦፊሰር ነው። በስራው ባህሪ የተነሳ ብዙጊዜ ከወንጀለኞች ጋር ተናንቆ ለህግ ማቅረብ መለያ ባህሪው እንደሆነ ባልደረቦቹ ይናገራሉ። በዚህም የተነሳ በተደጋጋሚ በወንጀለኞች ጉዳት ደርሶበታል።
በአንድ ወቅትም በዚሁ የህግ ማስከበር ስራ ላይ እያለ ኮንትሮባንዲስቶችን ለማስቆም በሚያደርገው ጥረት ቦንብ ተወርውሮበት ቆስሎ እንደነበር ነግሮናል።
ዋና ሳጅን ታከለ በተለመደው ስራው ላይ እንዳለ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም በመተማ ከተማ ቀበሌ 3 መናኸሪያ አካባቢ ካለ አንድ ሆቴል ጥቆማ ይደርሰዋል፤ “የሆቴሎ እንግዶች የያዙትን ሻንጣ አላስፈትሽም አሉ” የሚል። ጊዜ አላጠፋም ወዲያውኑ ወደሆቴሉ አቀና። በስፍራው የነበሩ እንግዶች የዋና ሳጅኑን መምጣት ሲመለከቱ በባጃጅ ለማምለጥ ሞከሩ። ነገር ግን አልተሳካላቸውም ዋና ሳጅን ታከለ አስቆማቸው።
ግለሰቦቹ ወደህግ ቦታ እንዲሄዱ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልሆኑም፤ ሻንጣቸውን እንዲያስፈትሹ ቢታዘዙም በተመሳሳይ ለመተባባር ፈቃደኛ አልሆኑም። ይህን ጊዜ ዋና ሳጅን ታከለ ጥርጣሬው ከፍ አለ። ሰዎቹ ወንጀለኛ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት በመውሰድ ወደ ህግ ቦታ እንዲሄዱ ደጋግሞ ጠየቃቸው። ግለሰቦቹ ግን በቀደመው አቋማቸው በመጽናት እንቢታቸውን አጥብቀው ያዙ።
የዋና ሳጅኑን የከረረ አቋም የተመለከቱት ግለሰቦቹ የያዟቸው ሻንጣ ውስጡ ብር መሆኑን በመንገር እንዲለቃቸውና አንዱን ሻንጣ ብር እሱ እንዲወስደው ጠየቁት። ዋና ሳጅኑ ግለሰቦቹ ያንን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ያገኙት እንዳልሆነ አመነ። ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በህጋዊ መንገድ የያዘወን ገንዘብ ለማያውቀው ሰው ሊሰጥ አይችልም፤ ይሄንን ያህል ገንዘብም በአሁኑ ወቅት ከባንክ ውጭ ማንቀሳቀስ አይችልምና ነው።
ስለሆነም ያቀረቡለትን ገንዘብ እንደማይቀበል ይለቁንንም ወደ ህግ እንዲሄዱ በተደጋጋሚ ይጠይቃቸዋል። ግለሰቦቹ ግን አሁንም ሌላ አማራጭ አቀረቡለት። ገንዘቡን በሙሉ ውሰድ እኛን ልቀቀን የሚል። ዋና ሳጅን ታከለ በዚህም ሃሳብ አልተሰማማም። በጭራሽ እንደማይሆን በመንገር ወደህግ እንዲያቀኑ ይጠይቃቸዋል። ግለሰቦቹም በተመሳሳይ በእንቢታቸው ጸኑ። ለማምለጥም የተለያዩ ሙከራዎችን ማድረግ ጀመሩ።
በዚህ መካከል የሃሳብ ልውውጡ እየከረረ በመሄዱ ግለሰቦቹ ሃይለቃልና ዛቻ መሰንዘርም ጀመሩ። በአጋጣሚ በአካባቢው የሚያልፍ የመከላከያ ሰራዊት የዋና ሳጅንኑንና የግለሰቦቹን ጭቅጭቅ ተመልክቶ ቀርቦ ምን እንደሆነ ጠየቃቸው።
ዋና ሳጅን መልስ ሰጠ። ግለሰቦቹ በወንጀል ስለተጠረጠሩ ወደ ህግ እንዲሄዱ ቢጠየቁም ሊተባበሩ እንዳልቻሉ ለመከላከያ ሰራዊት አባሉ አስረዳው። ይህ የሰራዊት አባልም የዋና ሳጅን ሃሳብን በመደገፍ ግለሰቦቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄዱ ነገራቸው። አማራጭ ስላልነበራቸው የተባሉትን አደረጉ።
“ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰድናቸው፡፡ ሻንጣው ሲፈተሽ እንደተባለውም ውስጡ ገንዘብ ሆኖ ተገኘ። ሲቆጠርም አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር መሆኑ ተረጋገጠ። በአከባቢው ይሄን ያህል ብር ይዞ መሄድ የተለመደ አይደለም። ይሁንና በዛን ዕለት ሌሊቱን በአከባቢው የነበረ ባንክ መዘረፉን ስለሰማሁ ለማጣራት ሞከርኩ። በእርግጥም ባንከ መዘረፉ ታወቀ።” ይላል ዋና ሳጅን ታከለ።
“ብሩን እንስጥህ ልቀቀን ባሉኝ ሰዓት እኔ ምንም ስሜቱም አልነበረኝም። ምንም ልቤ አልተቀበለውም ወንጀለኞች ስለሆኑ በህግና በህግ ነው መቀጣት ያለባቸው” የሚለው ዋና ሳጅን፤ በ”ስራ ዘመኔ ብዙ ነገሮችን አይቻለሁ፤ ይህ በጣም ቀላል ነው። ከዚህም በላይ ከባድ ፈተናዎች አልፌያለሁ። ህግን ስታስከበር የሚገጥሙህ ነገሮች ብዙ ናቸው። ከዚህን ቀደም ጉምሩክ ላይ ህገወጥ እቃዎችን ለመያዝ እሰራ በነበረበት ወቅት በጣም ብዙ ነገሮችን ተጋፍጫለሁ። በቦንብ ጥቃት ደርሶብኝ ከሞት አፋፍ ነው የተመለስኩት። ይህንን ሁሉ ስላለፍኩ ተጠርጣሪዎቹ ላቀረቡልኝ የሻንጣ ሙሉ ገንዘብ አልጓጓሁም” ሲል እምነቱን ነግሮናል።
ዋና ሳጅን ታከለ፤ “ማንም ህግ አስከባሪ የዚህ አይነትም ይሁን ሌላ ወንጀል ላይ ተጠርጣሪዎች የሚያቀርቡትን አማላይ የጉቦ ስጦታ መቀበል የለባቸውም፤ ይልቁንም ህዝብና መንግስት የጣለብንን አደራ በሃላፊነት መወጣት ይኖርብናል። እንዲህ ስናደርግ ነው አገርም ህዝብመ የሚጠቀመው” ሲል መልዕክቱን ለሙያ መሰሎቹ መልዕክቱን አስተላልፏል።
በሀይማኖት ከበደ
“መከላከያ ውስጥ ያየኋት ኢትዮጵያ የሰርጓ ቀን የደረሰ ሙሽራን ትመስላለች፡፡ የሰራዊቱ አባላት ፊታቸው ላይ የሚታየው ስሜት ውጊያ አይደለም የሚመስለው፡፡ ሁሉም ለኢትዮጵያ ሲሉ በወኔና በደስታ ነው የሚዋጉት። በይበልጥ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ተወልደው ያደጉ ልጆች ይህ ስሜት እንዲጋባባቸው እፈልጋለሁ”
ጋዜጠኛ ኑረዲን አወል
የአዲስ ቲቪ ጋዜጠኛ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ አመት የምስረታ በአሉን አመቱን ሙሉ በተለያቱ መድረኮች እያከበረ ይገኛል። የበአሉ አካል በማድረግም በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የምስጋና እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በዚሁ መርሀ ግብር ላይም ወደ ግንባር ከተላኩ ጋዜጠኞች መካከል የአዲስ ቲቪው ጋዜጠኛ ኑረዲን አወል የተመለከተውን እንዲህ ተናግሯል።
👉 ከግንባር ከመጣሁ በኋላ ጓደኞቼ ተሰበሰቡ፤ እስኪ ስለአገራችን ስለኢትዮጵያ የገጠመህን ንገረን አሉኝ፡፡ ስለየትኛዋ ኢትዮጵያ፤ መከላከያ ውስጥ ስላለችው ነው? ወይንስ እዚህ ቁርስ ስላልበላን ትፈርሳለች ስለምትባለዋ ኢትዮጵያ ነው ’የምነግራችሁ? አልኳቸው፡፡
👉 መከላከያ ውስጥ ያየኋት ኢትዮጵያ የሰርጓ ቀን የደረሰ ሙሽራን ትመስላለች፡፡ የሰራዊቱ አባላት ፊታቸው ላይ የሚታየው ስሜት ውጊያ አይደለም የሚመስለው፡፡ ሁሉም ለኢትዮጵያ ሲሉ በወኔና በደስታ ነው የሚዋጉት። በይበልጥ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ተወልደው ያደጉ ልጆች ይህ ስሜት እንዲጋባባቸው እፈልጋለሁ፡፡
👉ኢትዮጵያ ስትባል ብዙ ነገር ነች፡፡ ግን ከምንናገረው በላይ በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የሚታየው ኢትዮጵያዊነት ለእኛ በሕይወታችን ላይ ትልቅ ጥቅም አለው ብዬ አምናለሁ፡፡
👉 በዚህ አጋጣሚ ለእኔ ትውልድ ለሆኑት ወጣቶች መምከር የምፈልገው ነገር አለ፡፡ ለእኛ መኖር ትልቅ መስዕዋትነት የሚከፍሉልን የመከላከያ ሰራዊቶች አሉና እነሱን እንዲያመሰግኑልኝ፤ ማመስገን ብቻም ሳይሆን እንደ ግዴታ ሆኖ የትኛውም ወጣት መዝመት አለበት ብዬ ነው የማምነው፡፡
👉 የምንዘምተው ለምንድን ነው አንደኛ ፍቅርን የምናገኘው እዚያ ነው፡፡ ስርዓትን የምናገኘው እዛ ነው፡፡ ለሰው መኖር መቻል እንዳለብን የሚገባን እዚያ ነው፡፡ ከሚበሉት ነገር ቆርሰው እና በሐይላንድ ቁራጭ ከሚጠጡት ሻይ ከፍለው ለእንደእኔ አይነቱ እንግዳ አስቀድመው ይሰጣሉ፡፡
👉 እኔ እንደዛ ነወይ የምኖረው? አይደለም፡፡ እነሱ ግን እንደዚህ መተዛዘን በተሞላበት መንገድ ነው የሚኖሩት፡፡ ያ ነገር ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ ትርፍ የምናተርፍበትና ትልቅ ጥቅም የምናገኝበት ነው፡፡
👉 እኔ በሕይወቴ አሁን ብቻ አይደለም ወደፊትም ይሄን አይነት ትምህርት አገኛለሁ ብዬ አላስብም፡፡ ኮሮና የገባ ጊዜ ምን እንል ነበር ‹‹ፈጣሪ ሆይ ይችን ኮሮና ያሳልፍልን እንጂ ወደ እምነት ተቋሜ ተመልሼ አንተን አገለግላለሁ›› ብለን ነበር፡፡ አለፈ ፤ እኛም አልሄድንም፤ በነበርንበት እንደቀጠልን እንገኛለን፡፡
👉 ይህ ደግሞ ሁለተኛ የመማሪያ እድል ነው የተሰጠን ብዬ አምናለሁ፡፡ ሁሌም መጥፎ ነገሮች የምንማራቸው ስለሆኑ የእኔ ትውልድና በእኔ የእድሜ እኩያ የሚገኙ ወጣቶች አሁን ትልቅ ትምህርት የምናገኝበት ጊዜ ነው፡፡ ምንድን ነው ከአጠገባችን ያለ ሰው ጠላታችን ሊሆን ይችላል፡፡
👉እርግጠኞች አንሆንም፡፡ እኔን የማያውቁኝ ሰዎች ስለ እኔ እዚያ ጋ ይሞታሉ፡፡አያውቁኝም እኮ፡፡ እኔ ኑረዲን መኖሬን አያውቁም እኮ፡፡ ነገር ግን እዚያ ጋ ኢትዮጵያዊ የሚባል የሚጎዳ ዜጋ አለና መጎዳት የለበትም ብሎ ለእኔ የሚያስብና ሕይወቱን መስዕዋት የሚያደርግ ብዙ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊቶች አሉና እኔ ከመቀመጫዬ ተነስቼ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡
👉 ከዚህ በመቀጠል እኛ የነበርንበት አካባቢ ትንሽ መልክዓም ምድሩ ከባድ ነበር፡፡ መልክዓም ምድሩን ሳይ ለምን መጣሁ አልኩኝ፡፡ከዚያ በኅላ ግን ወታደሩ ፊት ላይ የሚታዬው ስሜት፣ፍቅር ጥልቅ ነው፡፡ አሁን እኔ ያንን በቃል ልግለጸው ብል ማርከስ ነው የሚሆንብኝ፡፡በቃል ባወራው ማሳነስ ነው የሚሆንብኝ፡፡
👉 ማውራት ያለብን ስለግለሰብ ጀብድ አይደለም ብዬ አስባለሁ፡፡ ይሄን ታሪክ የሰራው ሙሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነው፡፡የዚያ ታሪክ ተጋሪ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ ያንን አስቸጋሪ መልክዓ ምድር በመኪና ነው የወጣሁት፡፡ ነገር ግን ሴት የመከላከያ ሰራዊት በእግራቸው የሚተኩሱትን መሳሪያ ተሸክመው ሲወጡት ሳይ ለእኔ ብለው መሆኑን አይቼ አዘንኩ፡፡
👉 እኔ ለዚህች ኢትዮጵያ ለምትባለው አገር ምንድን ነው ያደረኩላት? እኛ እንጠይቅ ነበር፡፡ ደመወዝ ተጨመረልን ወይ ብለን፡፡ ቤት መንግስት ይሰጠን ይሆን ወይ ብለን፡፡ እዚያ ጋ ግን ደመወዝ የማይጠይቅ፣ ቤት ይሰጠኝ ይሆን ብሎ የማያስብ፣ ከፊት ለፊቱ ሞትን እያዬ ለአገሩ ክብር የሚገሰግሰውን የመከላከያ ሰራዊት አይቻለሁና ደስ ብሎኛል፡፡ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
👉 ከመደሰትም በላይ በእኔ ዙሪያ ያሉ ብዙ ወጣቶች አሉ፡፡እነዚያ ወጣቶች ብዙ ሊማሩበት ይገባል፡፡ ይሄን የምለው ለፕሮፖጋንዳ ትርፍ አይደለም፡፡ በሕይወት የኖርንባት እያንዳንዷ ቀን ትልቅ ትርጉም እንዲኖራ ከፈለግን ኢትዮጵያን እንወቃት፡፡ ለማወቅ ከፈለግን ደግሞ አገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እንግባ እላለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡
“እናትና አባትህ ይክዱኛል ብለህ የማትጠብቅበት አይነት ሁኔታ ውስጥ በሰራዊቱ ላይ ክህደት ተፈጽሟል። ቤታችን ነው ሰላም ነው ባልንበት ቦታ በተደራጀ ሃይል አፈና ተካሂዶብናል”
👉 የጁንታው አመራሮች በቅርበት ይከታተሉን ስለነበር የአየር ሀይላችን እነርሱን ነጥሎ ጠባብ መንገድ ላይ በአየር ድብደባ ተሸከርካሪዎቻቸውን አቃጥሏል፤
👉 የጁንታው አመራሮች ወደኋላ ሲመለሱ ደግሞ ተሸከርካሪዎቻቸውን በመምታት መንገዱ እንዲዘጋባቸው አድርጓል፤
👉 የጁንታው አመራሮች መሄጃ በማጣታቸው የነበራቸውን ተሽከረካሪዎች እና ንብረት እየጣሉና እያንጠባጠቡ ሲበታተኑ መከላከያ ሰራዊታችን ደርሶ አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ ነጻ አውጥቷል፤
👉 ሰራዊቱ የታፈኑትን ነጻ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል፤
ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ
የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
ሽሬ:- መከላከያ ሰራዊት በጁንታው ታጣቂዎች አማካኝነት የታፈኑትን የሰራዊቱ አመራርና አባላትን ነጻ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል ሲሉ ከታጋቾቹ መካከል አንዱ የነበሩት የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ።
የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ እንደገለጹት፤ መከላከያ ሰራዊቱ ታጋቾችን እና የጁንታውን ታጣቂ ለመለየት የተጠቀመው እርምጃ የሚደነቅ ነው። የሰራዊቱ አመራርና አባላትን በማይጎዳ መልኩ ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ፈጽሟል።
"መከላከያ ሰራዊታችን እኛ የታፈንነውን አመራርና አባላት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ እርምጃ ወስዷል። በተለይ የጁንታው አመራሮች በቅርበት ይከታተሉን ስለነበር እነርሱን በሚነጥል ሁኔታ በአየር ከፊት ጠባብ መንገድ ላይ ተሸከርካሪዎቻቸውን አቃጥሏል።
መከላከያ ሰራዊቱ የጁንታው አመራሮች ወደኋላ ሊመለሱ ሲሄዱ ከኋላ ተሸከርካሪዎቻቸውም በመምታት መንገዱ እንዲዘጋባቸው አድርጓል። በዚህ ወቅት የጁንታው አመራሮች መሄጃ በማጣታቸው የነበራቸውን ተሽከረካሪዎች እና ንብረት እየጣሉና እያንጠባጠቡ ሲበታተኑ መከላከያ ሰራዊታችን ደርሶ አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ ታጋቾችን ነጻ አውጥቷል" በማለት የሰራዊቱን እርምጃ አወድሰዋል።
ሰራዊቱ የታፈኑትን ነጻ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ደስተኛ የሆነበት እና ጥሩ ስራ የተከናወነበት ነው በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። <<መከላከያ ሰራዊታችንን በግሌም ሆነ አብረውኝ በነበሩ አመራሮች ስም ላመሰግን እወዳለሁ። በመከላከያ ሰራዊታችን ኮርተንበታል>> ብለዋል።
በአፈናው ወቅት ስለነበረው ሁናቴ ሲያስረዱም “ስሜቱን መግለጽ ያጥረኛል። እናትና አባትህ ይክዱኛል ብለህ በማትጠብቅበት ሰዓት በሰራዊቱ ላይ ክህደት ተፈጽሟል። ቤታችን ነው ሰላም ነው ባልንበት ቦታ በተደራጀ ሃይል አፈና ተካሂዶብናል” ነው ያሉት።
የአፈናው ጊዜ በሙሉ በርካታ ውጣ ውረዶች ያሉት ነው፤ ረጅም የእግር ጉዞዎች በቀንም በሌሊትም ያለዕረፍት ነበረው። ዞሮ ዞሮ ህይወታችንን ካተረፉን የመከላከያ ሰራዊት ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ታሪኩን በጽሁፍ በሰፊው የምናቀርበው ይሆናል በማለት ሁኔታውን በአጭሩ አስረድተዋል።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው የታፈኑት የሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ሽሬ ከተማ ሲደርሱ በሰራዊቱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በርካታ የሰራዊቱ አባላት ታፍነው የሰነበቱ አመራሮቹን እና ጓደኞቻቸውን ሲያገኙም ወደሰማይ በተተኮሰ የጥይት ድምጽ እና በጭፈራ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ህዳር 30 ቀን ከሰዓት በኋላ የጁንታው ቡድን አጋቾች አዴት በተባለ አካባቢ በእግር ሲያጓጉዟቸው የነበሩትን ከ1ሺህ በላይ የሰራዊቱን መኮንኖች በመልቀቅ በየአቅጣጫው መበታተኑ ታውቋል። ታፍነው የሰነበቱ የሰራዊቱ አመራሮች መንግስት ላደረገው የህይወት አድን ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
ለምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች 31 ሺ 500 ኩንታል የስንዴና የታሸጉ ምግቦች ድጋፍ ቀረበ
******^*****^*
(ኢ.ፕ.ድ)
ሽሬ:- ከምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 31ሺ 500 ኩንታል ስንዴ እና የታሸጉ ምግቦች ድጋፍ መቅረቡን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደጋ ምላሽና ክትትል ቡድን መሪ እና በትግራይ ክልል ለሚቀርበው ድጋፍ አስተባባሪ አቶ ታዬ ጌታቸው እንደገለጹት፤ በምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ስንዴ እና ለህጻናት፣ እናቶችና አረጋውያን የሚሆኑ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ዘይት፣ አልሚ ምግብ እና የማብሰያ ቁሳቁሶች ቀርቧል።
እንደ አቶ ታዬ ገለጻ፤ መንግስት ያቀረበውን ድጋፍ ለተፈናቃይ ዜጎች ለማከፋፈል በትግራይ ክልል ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በጋራ እየተሰራ ይገኛል። በተለያዩ ማዕከላት ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተለይተዋል። ማምረት እና መስራት የማይችሉ ዜጎች ጭምር ቤት ለቤት የምግብ ድጋፉ ይቀርብላቸዋል። አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተለዩ 13ሺ ዜጎች ቅድሚያ ድጋፉ እየቀረበላቸው ይገኛል።
የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጎስ በርሄ በበኩላቸው እንደገለጹት ፤ ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሽሬ ከተማዋ የሚገኙ ዜጎች በዩኒቨርሲቲ እና በትምህርት ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።
እንደ አቶ ሃጎስ ገለጻ፤ መንግስት ችግሩን ተገንዝቦ ለተፈናቃዮች እርዳታውን በተጠየቀ ጊዜ ቶሎ በማድረሱ ምስጋና ይገባዋል። ድጋፉን በፍትሃዊነት ለማከፋፈል እንዲቻል በጊዜያዊ አስተዳደሩከቀበሌ አንስቶ እስከ ከተማ አስተዳደር ጀምሮ የሰዎች ምደባ ተደርጓል።
በከተማ ደረጃ ህብረተሰቡን ለማረጋጋት እና ድጋፎችን ለማከፋፈል አምስት የካቢኔ አካላት እና 25 የወረዳ ምክር ቤት አባላት ተመርጠዋል። በየቀበሌው አምስት አመራር እና 15 ጊዜያዊ የምክር ቤት አባላት አሉ። በተጨማሪ የድጋፍ ክፍፍሉን የሚያስተባብሩ አካላት ከኅብረተሰቡ ተመርጠው በተቻለ መጠን ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
አሁን ላይ ሃብታሙም ድሃውም ህብረተሰብ የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት እኩል የሆኑበት አጋጣሚ አለ የሚሉት አቶ ሃጎስ፤ ይሁንና ችግሩን ቀስ በቀስ ለመፍታት ጥረት በማድረግ በቅድሚያ ግን ህጻናት፣ ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን እና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎች አስቸኳይ ድጋፉ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል። ድጋፉ ሲዳረስም የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ ደመወዛቸው በባንክ ያሉ ነዋሪዎች እና ለሌሎች ዜጎች ድጋፍ ማቅረብ እንደሚቻል ገልጸዋል።
ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት የተላኩ ተወካዮች በትግራይ ክልል የሚኖሩ ዜጎች ያሉባቸውን የሰብአዊ ድጋፍ እና አስቸኳይ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች እንዲሁም ተያያዥ ችግሮች በቀጣይነት የሚፈቱበት ሁኔታ ላይ በትግራይ ከተቋቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል።
ህብረተሰቡ በውሃ በኩል ያለበትን ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ከውሃ መስኖ ሚኒስቴር የመጡ ተወካዮች እንደሚያስተባብሩ ታውቋል። የህጻናት፣ እናቶችን እና አረጋውያን ጉዳዮችን ደግሞ የሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴር ተወካዮች ያስተባብራሉ።
ቀድሞ በሴፍቲ ኔት ታግዘው ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ ስር የሰደደ የምድብ አቅርቦት ችግር ያለባቸውን ዜጎችን ጉዳይ ደግሞ የግብርና ሚኒስቴር እንደሚስተባብር ታውቋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትግራይ ክልል የድርጅቱ ሰራተኞች ለፈጸሙት ድርጊት ይቅርታ ጠየቀ
*******************
( ኢ ፕ ድ)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በትግራይ ክልል የድርጅቱ ሰራተኞች ለፈጸሙት ድርጊት ይቅርታ መጠየቁን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሕዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለውጭ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው።
በመግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ከተነሳው ጥያቄዎች አንዱ መንግስት በትግራይ ክልል በተመድ ሰራተኞች ላይ ተኩሷል መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ የሚል ነበር።
አምባሳደር ሬድዋን በትግራይ ክልል የፍተሻ ጣቢያዎችን የጣሱ የተመድ ሰራተኞች ላይ መተኮሱንና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ከተደረገ በኋላ መለቀቃቸውን ገልጸዋል።
የድርጅቱ ሰራተኞች ወዳልተፈቀደላቸው ቦታ ሲያመሩ እንደነበረና ሁለት የፍተሻ ጣቢያዎችን ካለፉ በኋላ ሶስተኛ የፍተሻ ጣቢያ ጥሰው ሊያልፉ ሲሞክሩ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ተመድን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስትን መመሪያ ማክበር እንደሚገባቸውና መንግስት ከስጋት ነጻ ናቸው ብሎ ቦታዎችን ከለየ በኋላ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ አምባሳደር ሬድዋን በመግለጫቸው አንስተው ነበር።
የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር በተመድ ሰራተኞች ድርጊትና በፍተሻ ጣቢያው በተፈጠረው ክስተት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።
ተመድ በትግራይ ክልል የድርጅቱ ሰራተኞች ለፈጸሙት ድርጊት መንግስትን ይቅርታ መጠየቁንም ሰላም ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል።
የተመድ የኢትዮጵያ የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ የጠየቁትን ይቅርታ የኢትዮጵያ መንግስት መቀበሉን ገልጿል።
ተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ትብብር የሚሸረሽሩና ከፍተኛ የአደጋ ስጋት የሚደቅኑ ተመሳሳይ ጥሰቶች ዳግም እንዳይፈጸሙ የሚያስችሉ ስርዓቶችን እንደሚዘረጋ መግለጹንም አመልክቷል።
መንግስት ሕዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከተመድ ጋር በደረሰው ስምምነት አማካኝነት በትግራይ ክልል ለሚደረገው ድጋፍ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ነው የሚኒስቴሩ መግለጫ የሚያመለክተው።
በስምምነቱ መሰረት ድርጅቱ ከመንግስት ጋር በመሆን አስፈላጊውን የሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችልም ጠቁሟል።
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት በትግራይ ክልል አስቸኳይ የድጋፍ አቅርቦት እንዲደርስ ያላቸውን ፍላጎት መንግስት እንደሚረዳና ተቋማቱ ድጋፉን ማድረግ የሚችሉት ከፌዴራል ተቋማት አስፈላጊውን ፈቃድ ሲያገኙ እንደሆነ ሊረዱት እንደሚገባ ገልጿል።
ሁሉም የሰብአዊ ድጋፍ ሰራተኞች መንግስት ያወጣውን መመሪያ መከተል እንደሚገባቸውና መንግስት ሰራተኞቹና የድጋፍ አቅርቦቶች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ያለበትን ግዴታ እንደሚወጣም ነው የሰላም ሚኒስቴር ያስታወቀው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከተመድ ኤጀንሲዎች ጋር ላለው ትብብርና ኤጀንሲዎቹ ለኢትዮጵያ የልማት ፕሮግራሞችና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች ለሚያደርጉት ወሳኝ ድጋፍ ትልቅ አክብሮት እንዳለውም ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሚችለው አቅም በትግራይ ክልልና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ላሉ የሰብአዊ ጉዳይ ፈተናዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በአስፈላጊው ጊዜ ለተቸገሩ ዜጎች ለሚያደርጉት ወሳኝ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ምስጋውን እንደሚገልጽ የሰላም ሚኒስቴር በመግለጫው ያተተው።
መንግስት በትግራይ ክልል ያለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተጠናቆ ተልዕኮው ወደ "ወንጀሎችን የማደንና መልሶ ግንባታ" ምዕራፍ መሸጋገሩን መግለጹ የሚታወስ ነው።
ከታጋቾች አንደበት
👉 ዋናው ነገር የሃገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም፤ ጓደኞቻችን ግን ነጻ አውጥተውናል፤
👉 የጁንታው ታጣቂዎች የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መልዕክት በግዳጅ እንዲያስተላልፉ አዘዟቸው፤
👉 “እኔ ትጥቄን ፈትቻለሁ እናንተም ፍቱ፤ እኔን ግን ከዚህ በኋላ አታገኙኝም” በሚል ለሰራዊቱ ውስጠ ወይራ መልዕክት አስተላለፉ፤
👉 በኦሮምኛ ደግሞ ለሰራዊቱ ትጥቅ እንዳይፈታ የሚያዝዝ መልዕክት አስተላለፋ፤
ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን የመከላከያ ሰራዊት 20ኛ ክፍለጦር አዛዥ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በጁንታው ቡድን ታግተው ከቆዩ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን ናቸው። ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ በወቅቱ የጁንታው ታጣቂዎች የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መልዕክት በግዳጅ እንዲያስተላልፉ አዘዟቸው። እርሳቸውም “እኔ ትጥቄን ፈትቻለሁ እናንተም ፍቱ፤ እኔን ግን ከዚህ በኋላ አታገኙኝም” በሚል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚገልጽ ውስጠ ወይራ መልዕክት አስተላለፉ። አክለውም በኦሮምኛ ለሰራዊቱ ትጥቅ እንዳይፈታ የሚያግዝ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ያስታውሳሉ።
መከላከያ ሰራዊቱም ጥቃቱ ከተፈጸመ ማግስት ጀምሮ በመከላከልና የህግ ማስከበር እርምጃ በመፈጸም ህይወት የማዳን እና አጥፊዎቹን የመቅጣር እርምጃውን ገፋበት። በርካታ የሰራዊቱ አባላት እና አመራሮችም ከብዙ እንግልት በኋላ ከጁንታው እጅ ነጻ ወጡ። ከታጋቾች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ነጻ ከወጡ በኋላ ሲቃ በተሞላበት ንግግራቸው ሁናቴውን አስረድተዋል።
<<ከሁሉ በፊት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊትም እንኳን እንኳን ለዚህ ድል አበቃን ፤ እኛንም ከአንድ ወር ልፋትና እንግልት በኋላ እንኳን በሰላም አገናኘን። ዋናው ነገር የሃገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም በሚል ተስፋ ቆርጠን ነበር። ጓደኞቻችን ግን መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ኦፕሬሽናቸውን በመፈጸም ነጻ አውጥተውናል።
በርካታ ቀናትን ያለምግብ እና ውሃ በተለያየ መልከአምድር ላይ ተንገላተናል። በርካታ የሰራዊት አባላትም ይህን እንግልት ተቋቁመን አሁን የደረስንበት ደረጃ በመድረሳችን በታጋቾች እና በእራሴ ስም ለመከላከያ ሰራዊት ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።
በአጠቃላይ በሰራዊታችንም ሆነ በህዝባችን ሲከናወን የነበረውን ነገር በተለያየ መንገድ የሰማነው ስለሆነ እኛም ደስ ብሎናል። ለመከላከያ ሰራዊትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለድል ያበቃችሁን አንድነታችሁን በማጠናከር የቀሩትን ስራዎችም እንድታጠናቅቁ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፤
ለአንድ ወር ከስድስት ቀን በጁንታው ታጣቂዎች ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ ታግተው በረሃብና በእንግልተ የቆዩት የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በሰራዊቱ አማካኘነት ነጻ ከወጡ በኋላ ህይወታቸውን ለማትረፍ ለተደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ

**********

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት በሙሉ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በአካባቢው ለሕዝቡ የተጀመረው ሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀጥልና መንግስት በሕግ ማስከበሩ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በተለይም ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚሰሩ ስራዎች ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመቀሌ ቆይታቸው
👉ከሀገር መከለከያ ሰራዊት አመራሮች ጋርም በድሉ ዙሪያ ውይይት
አድርገዋል፤ በዚሁ ወቅት የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች
*********************
(ኢ ፕ ድ)
👉 ጠላት በርከት ያሉ የእኛን መኮንኖች ይዞ ስለቆየ እነሱን ይዞ ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ ስለሆነም ማታ ማታ በምናደርገው ኦፕሬሸን በርከት ያለ ሰው በሚኖርበት ሰአት ይህ ሀይል የእኛ ሃይል ሊሆን ይችላል በሚል ያቆየናቸው ሚሳየሎችና ቦንቦች ዛሬ ያኮሩኛል። ያንን ተጠቅመን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመካከላችን ያሉትን መኮንኖች አናያቸውም ነበር፤
👉 ይህ ኢትዮጵያን የመታደግ ኢትዮጵያን የማኩራት ብቃት፤ ተልዕኮን በአጭር ጊዜ የመፈጸም ብቃት የተቋማችን የሁልጊዜ አርማ መሆን አለበት፤
👉 በተደጋጋሚ እንዳልኩት የመከላከያ ሰራዊት የብልጽግና ሰራዊት አይደለም፤ የአብይ ሰራዊት አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መከታና ኩራት የሆነ ወታደር ነው፤
👉 እኛ የምንፈልገው ፕሮፌሽናል ጠንካራ አርሚ እንድትሆኑ እንጂ ለአንድ ፓርቲ የሚገዛ እንድትሆኑ አንፈልግም፤
👉 ኢትዮጵያ ከብልጽግናም ከፓርቲም በላይ ናት፤ ትልቋን አገር የመታደግ ሃላፊነት ተጥሎባችኋል፤
👉 ፖለቲካው የተበላሸ ነው፤ የማያውቀውን የደም ስር እና ሀረግ እየፈለገ የሚቧደን ነው፤ እናንተ ግን ጀግኖች ብቻ ሳትሆኑ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፤
👉 ጦርነቱን ስንጀምር በጣም ብዙ ሰዎች በአጠረ ጊዜም ብቻ ሳይሆን ማሸነፍም ይከብዳል የሚል ግምግማና ግምት ይናገሩ ነበር፤ ይሄ አልሆነም፤
👉 እኛን የሚዋጉን ሰዎች ዘመናዊ ጦርነት አያውቁም፤ የጦርነት ሳይንስ አያውቁም፤ የሚያውቁት የሽምቅ ውጊያ ነው፤ እሱ የሽፍቶች ውጊያ ነው፤ እሱ በሰው ሃይልና በተተኳሽ ቁጥር ማሸነፍ የምናረጋግጠብት ውጊያ ነው፤
👉 የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ስንት ሺህ ወጣት እንዳስከፈለን ስንት ጊዜ እንደወሰደ እናውቀዋልን፤ ይሄ የአሁኑ ኦፕሬሽን ደግሞ በምን ያህል ባነሰ የሰው ሃይልና መስዋዕትነት ለድል እንደበቃን ታውቃላችሁ፤
👉 ከሁመራ መቀሌ በእግር መጓዝ ማለት ብዙዎች አዲስ አባበ ሆነው ዝም ብሎ ጀግና እንደሚሉት አይደለም፤ በዚህ መልክዐ ምድር በዚህ ሙቀት ስንቅና ትጥቅ ተሸክሞ ይሄንን ያህል ጉዞ መጓዝ የማንም አገር ወታደር አይደግመውም፤
👉 ይሄንን ጀግንነት ወንጀለኞችን በመያዝ መድገም ያስፈልጋል፤ ወታደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መቶ በመቶ አሳክቷል፤ የሚቀረው ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ነው እሱንም በፍጥነት ማከናወን ያስፈልጋል፤
👉 ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የትግራይ ህዝብ ሃላፊነት አለበት፤ የተደበቁትን ሰዎች፣ ከመኪና ወርደው እግረኛ የሆኑትን ሰዎች በመያዝ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለትግራይ አስተዳደር ማስረከብ አለበት፤ ያ ካልሆነ ወታደሩ አገር የመጠገን ጊዜውን ወንጀለኛ በማደን ስለሚያሳልፍ የሚጎዳው ራሱ ህዝቡ ነው፤
👉 ከኢትዮጵያ መንግስት ልማት ድጋፍ መጠየቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ወንጀለኞችን አሳልፈው መስጠት ደግሞ ግዴታ ነው፤ ይህ ስምምነት ካለ ነው ስራችንን በአጭር ጊዜ በማከናወን ወደልማት የምንገባው፤
በርካታ ወንጀለኞችን እንደተያዙ፤ የተቀሩትም የት እንዳሉ መረጃው አለኝ፤
👉 የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝቦች ኩራት መሆኑን፤ በዚህ ቀጣና የሚነሳ ማንኛውንም አደጋ በሚፈለገው ልክ ለመመከት የሚያስችል ብቃት ያለው ጦር መሆኑን በድጋሜ አረጋግጧል፤
👉 የጁንታው ሃይል በቁጥር ከ80 ሺህ በላይ ይገመታል፤ አዳዲስ መሳሪያዎችን ታጥቋል፤ ከፍተኛ የተተኳሽ ዲፖዎች ነበሩት፤ ኮማንዶ ሜካናይዝድ ሮኬት መተኮስ የሚችሉም ሰዎችነበሩት፤ እኛ ግን መቀሌ እስከገባንበት ቀን ድረስ ሮኬት አልተኮስንም በእኛና በጁንታው መካከል ያለው ልዩነት ይሄ ነው፤ እኛ ያልተኮስነው ህዝባችን እዚህ እንዳለ ስለምናውቅ ነው፤
👉 እኛ ሮኬት የተጠቀምነው ጁንታው መቀሌን ለቆ በረሀ ለበረሃ ለማምለጥ ሲሞክር ነው፤ ይሄ የእውነት ይሄ የፍትሃዊነት ልዩነታችን አሸናፊ አድርጎናል፤