Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጀግናው የአገር የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ሰልፍ አካሄዱ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጀግናው የአገር የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ዝግጅት አካሂደዋል።
አይበገሬው የመከላከያ ሰራዊታችን በከሃዲውና ጽንፈኛው የህዎሓት ቡድን የተቃጣበትን ጥቃት መክቶ በፍጥነት አገራችን ወደ ድል ብስራት በማሸጋገሩ ያላቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ለዚህ የአገር መከታ መከላከያ ሃይል ድጋፍ ለማድረግና በጽንፈኛው ህወሓት ርጥባን ተከፋዮች የሚነዛውን የሃሳት ፕሮፖጋንዳ ለማክሸፍ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።
ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስተባባሪነት የተካሄደ ነው።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሰላም አምባሳደሮች ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ
****************************
( ኢ ፕ ድ)
በየዓመቱ ህዳር 29 ይከበር የነበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሰላምና አንድነትን በሚሰብኩ የሰላም አምባሳደሮች ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ። በጭፈራ ብቻ ሲከበር የቆየው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሰላምና አንድነትን ሊያመጣ በሚችል መንገድ መከበር እንደሚኖርበት ተጠቆመ ።
ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር በዓሉን አስመልክተው ከትናንትበስቲያ በሰጡት መግለጫ ፣ የኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት የሁነቶች አደራጅ አቶ ቢኒያም ፈቃዱ እንደገለጹት፤ በዚህ ዓመት በሚከበረው 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ‹‹ቆንጂት አንድነት›› የተሰኘ የቁንጅና ውድድር ይካሄዳል።
ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ሦስት ሦስት ቆነጃጅት ተወዳድረው አሸናፊዎች በየክልላቸው የሰላም አምባሳደር ይሆናሉ ብለዋል። የሚመረጡት የሰላም አምባሳደሮች ሰላምና አንድነትን በመስበክ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎችን ይሠራሉ።
የማጠቃለያ ዝግጅቱም የፊታችን ዕሁድ ህዳር 27 ቀን በሸገር ፓርክ እንደሚካሄድ ጠቁመው፣ የሚመረጡት ቆነጃጅት የመጡባቸውን አካባቢዎችና የወከሏቸውን ብሄሮች ባህልና ትውፊት እንደሚያስተዋውቁ አስታውቀዋል።
በአምባሳደርነታቸውም እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ በየአካባቢያቸው ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በሰላም ዙሪያ ይሠራሉ። ይህም በአገሪቱ ሲሸረሸር የቆየውን ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲስተካከል ይረዳል ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=36686
‹‹ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ ድባቡ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚመጣበት ነው›› - ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም
አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ ድባቡ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚመጣበት ፍልስፍናን የያዘ እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ።
ዘርፎም ሆነ በኮንትሮባንድ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን ጁንታ በ25 ቀናት ውስጥ የዛሬ 47 ዓመት ወደነበረበት ዋሻ ተመልሶ እንዲገባ መደረጉን አስታወቁ።
ዶክተር ቢቂላ በተለይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ መከላከያ ሠራዊት የዓይኑ ብሌን በሆነች በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር ነው።
በግራም ይሁን በቀኝ ዘርፎም ሆነ በኮንትሮባድ አግበስብሶ እስከአፍንጫው የታጠቀውን የጁንታውን ቡድን በ25 ቀን ውስጥ የዛሬ 47 ዓመት ከነበረበት ዋሻ ውስጥ መልሶ ከቶታል።
ይህም የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ጥንካሬና ጀግንነት ነው፤ይህ ጀግንነት ደግሞ ህዝቡም ውስጥ ያለ እና የኖረ እንደሆነ የጠቆሙት ኃላፊው፣ የህዝቡ ጀግንነት መከላከያ ሠራዊታችን ውስጥ በተግባር የተረጋገጠ መሆኑንም አመልክተዋል። እንደ ዶክተር ቢቂላ ገለጻ፤ ይህ መሰሪና አጥፊ ቡድን የዛሬ 47 ዓመት አካባቢ ዋሻ ውስጥ ነበር፤ በአሁኑ ሰዓትም 47 ዓመታት ወደኋላ ተንፏቆ ቀድሞ በነበረበት ዋሻ ውስጥ ይገኛል። ይሁንና ከዚያ አፈር ውስጥ ተለቅሞ ይወጣል። ወደነበረበት ጉድጓድ እንዲገባ ያደረገው የኢትዮጵያውያን አንድነት ምልክት የሆነው መከላከያ ሠራዊት ሲሆን፣ የህዝቡም ጥምረት ውጤት ነው። ጁንታው በተንኮልና ክፋት የተወረሰ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ተንኮልና ክፋት ደግሞ የፈለገውን ያህል አንገቱን ቀና ቢያደርግ አንድ ቀን ተንኮሉና ክፋቱ ራሱን መልሶ መብላቱ አይቅርም ብለዋል። ስለዚህ መነሻ የምናደርው እውነት ሁልጊዜ ታሸንፋለች፤ ተንኮልና ክፋት ሁልጊዜ ይሸነፋል የሚለውን ነው ብለዋል። ሁሌም የአሸናፊነት ምስጢር እውነት እንደሆነችም አስታውቀዋል። ከዚህ ከእውነት ጋር የታገለ ማንኛውም ኃይል እንደሚወድቅ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁልጊዜ የሚቆመው ከእውነትና ከሐቅ ጋር መሆኑን ጠቅሰው፤ ትልቁ አቅምና ጉልበት የነበረው ይኸው እንደሆነ አመልክተዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል ተንኮለኛው ቡድን መቀሌ ሲኮለኮል፤ ኢትዮጵያውያኑ ደግሞ አንድ ወደሚያደርጋቸው ነገር ሲሳቡ ቆይተዋል። በመጨረሻ ግን ቡድኑ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፤ የአገራዊ አንድነት ምልክት በሆነው ላይ እና ኢትዮጵያውያን እንደ ዓይናቸው ብሌን በሚያይዋት ኢትዮጵያ ላይ እጁን በማንሳቱ እውነት መነካቱን አስታውቀዋል። መከላከያ ሠራዊቱም ጥቃትን መቋቋም ስላልሆነለት የኢትዮጵያዊነትን ልክ ማሳየት ችሏል ብለዋል። እንዲህ ዓይነት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊትም ትልልቅ አገራዊ ፈተናዎች ቢከሰቱ እንኳ ያልቃታል እንጂ አገሩን እንደማያስደፍር ማረጋገጡን አስረድተዋል። ከኋላው ያለው 115 ሚሊዮኑም ህዝብ የኢትዮጵያን መጠቃት ከመቃወም በተጨማሪ በሁለንተናው ድጋፍ እንዳበረከተ አመልክተዋል። ስለዚህ የፖለቲካው ድባብ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነትን እናመጣለን የሚል ፍልስፍና ነው የያዘነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ፖለቲካው በግራም በቀኝም ማጠንጠኛው ይህ ነው ብለዋል። ስለዚህ ይህ የጁንታው ቡድን ሲነቀል የፖለቲካ ድባቡ ከዘር ነጋዴነት እየተላቀቀ ይመጣል ሲሉም አብራርተዋል። ኃላፊው እንደተናገሩት፤ ብዝሃነትን ማቀፍና የዘር ነጋዴ መሆን ይለያያል። ቡድኑ ባለፉት 27 ዓመታት ብዝሃነትን የሚያቅፍ ሳይሆን የዘር ነጋዴ ነበር። ጁንታው የብሄር ነጋዴ ነው። በየቦታውም ሄዶ ግጭትን ሲያነሳ ሰንብቷል። ከዚህ በኋላ የብሄር ንግድ አክሳሪ ነው የሚሆነው፤ ነጋዴዎችም ከስረው ከገበያ ይወጣሉ። ብዝሃነትን ያቀፈ፣ ኢትዮጵያን የሚመስል፣ ሁሉንም ቋንቋም ሆነ ማንነት ወደመሃል ያመጣ፣ የሚያቅፍና የሚያሳትፍ፣ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ግን የማይደራደር ኢትዮጵያዊ አንድነት ይገነባል ብለዋል። ስለዚህ ቀስ በቀስ ከአክሳሪው፣ ከመሰሪውና ከተንኮለኛው የብሄር ንግድ እየተወጣ ወደ ብዝሃነትን ወደአቀፈች ጠንካራ ኢትዮጵያ ይመጣል ብለዋል። ፖለቲካ እየተቃኘ ያለው ወደዚህ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
በአስቴር ኢሊያስ
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት በጥገና እና በካሣ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር የትራንስፖርት አገልግሎት እና መሠረተ ልማት ደህንነት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በባቡር መስመር ላይ እያጋጠሙ ካሉ ተግዳሮቶች መካከል በመሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆት፣ ውድመት እና የባቡር አደጋዎች ተከትሎ የሚያጋጥሙ የባቡር እገታዎች እንደሚጠቀሱ የትራንስፖርት ሚንስትር ዴኤታ አወል ወግሪስ ተናግረዋል።
ባለፉት 3 ዓመታት 163 ጊዜያት ያህል ባቡሮች የታገቱ ሲሆን፣ በእገታዎቹ ከ652 በላይ ሰዓታት ባቡሮቹ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉን ተገልጿል።
በ875 እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን፣ 961 ጊዜ ስርቆት እና የንብረት ውድመት ማጋጠሙን፣ የ27 ሰዎች ሞት እና የ11 ሰዎች የአካል ጉዳት መመዝገቡን አቶ አወል ተናግረዋል።
በባቡር እገታ ምክንያት ለጥገና እና ለካሣ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና የደህንነት ባለሞያ ኢ/ር ጥበቡ ተረፈ ገልጸዋል።
በስርቆት እና በውድመት ብቻ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን ኢ/ር ጥበቡ ጠቁመዋል ሲል ዚቢሲ ዘግቧል።
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት የባቡር መሠረተ ልማቱንና አገልግሎቱን ደህንነት ለማስጠበቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ሚኒስትር ዴኤታ አወል ወግሪስ ጠይቀዋል።
‹‹ሰዎችን በጅምላ መግደል ሃይማኖታዊ ተጠያቂነቱ ከፍ ያለ ነው›› ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
************************
( ኢ ፕ ድ)
ሰዎችን በብሄራቸው ወይም በሃይማኖታቸው ምክንያት በጅምላ መግደል የኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ካለመሆኑም በላይ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸህ ሱልጣን አማን አስታወቁ።
ሸህ ሱልጣን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሰላም በእስልምና ከፍተኛ ቦታ አለው። የሃይማኖት ሰዎች ሲገናኙ ‹‹አሰላም አለይኩም›› ወይም ሰላም ለአንተ ይሁን የሚል ሰላምታ ተለዋውጠው ነው ወደቀሪ ጉዳያቸው የሚገቡት። ይህ ከሰላም በፊት የሚቀድም ጉዳይ እንደሌለ የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር ሰላም ከሌለ ሀገር የለም፤ ልማት የለም፤ በአግባቡ አምልኮንም ማከናወን አይቻልም የሚልም መልዕክት አለው።
“ነፍስን ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። አንድን ነፍስ ማጥፋት ዓለምን እንደማጥፋት ነው። እንኳን የሰው ነፍስን ቀርቶ ያለ አግባብ የነፍሳትን ነፍስ ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። ይሁን እንጂ አሁን በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ሰዎችን በጅምላ የመግደል ተግባሮች እንደሃይማኖት አባት በጣም የሚወገዝ ነው” ብለዋል።
‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ተባብረን፤ ተቃቅፈን ፤ ተዋደን ብሄርና ሃይማኖት ሳይለየን በሰላም ስንኖር የቆየን ህዝቦች ነን። አሁን ግን በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎችን እያየን ነው ያሉት ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን፣ ይህ ከኢትዮጵያውያን አማኝነትና ባህልና እሴት አንጻር በጣም የሚያሳፍርና እኛን የማይገልጽ እንደሆነ አመልክተዋል።
ፖለቲከኞች ሃይማኖትንና ብሄርን ሽፋን አድርገው በሳለም ለዘመናት የኖረውን ህዝብ ሲያባሉትና ሲያጫርሱት እየተመለከትን ነው›› ያሉት ፕሬዝደንቱ ፣ በየቦታው የሚታዩ ግጭቶችና ግድያዎች መንስኤያቸው ከሃይማኖትና ብሄር ይልቅ ፖለቲካ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሸህ ሱልጣን እንደሚሉት ፖለቲከኞች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም ሲሉ አንድን ብሄር ከሌላው ጋር ወይም ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር እያጋጩ የሚፈጽሙት ድርጊት እንጂ ኢትዮጵያውያን እንደዚህ አይነት ታሪክም ሆነ ስነልቦና የላቸውም።
https://www.press.et/Ama/?p=36736
የጁንታው የጭካኔ ጥግ በሰሜን እዝ ላይ - በወታደሮቹ አንደበት
👉 "አንድ የሰራዊቱ አባል እጁን ከሰጠ በኋላ በታንክ ደፈጠጡት"
👉 "አራስ ልጄን ይዤ የታጣቂዎችን አስከሬን ተሸከሙ አሉን"
👉 "....ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው"
👉 "የሴቶችን ጡት እንደቆረጡም ሰምተናል"
👉 "የተሰው የሰራዊቱ አባላትን አስከሬን በመንገድ ላይ እየጎተቱ ግፍ ፈጽመዋል"
👉 "....አይናቸው ውስጥ በርበሬ እየጨመሩ ያሰቃይዋቸው ነበር"

*********
(ኢፕድ)

አስር አለቃ ቤቴልሄም በዛ ትባላለች፡፡ የ11ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል ነች፡፡ የከሀዲው ህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ጥግ ተመልክታለች:: ደርሶባታልም፤ የጁንታው ጭካኔ እንኳንስ በወገን ላይ ቀርቶ በሰው ልጅ ላይ ሊታሰብ የማይችል መሆኑን ትናገራለች።

‹‹ሁኔታው ከመፈጸሙ በፊት በሰራዊቱ ውስጥ የጁንታው ተላላኪዎች የሆኑ የሻለቃው አባላት እየተደበቁ በየቀኑ ይሰበሰቡ ነበር፡፡ የዋርዲያ ተራቸውን ጠብቀው ስለማይሰሩም የተቀረው ወታደር ያለእረፍት የእነርሱንም ጭምር ሲሸፍን ቆይቷል። የተቀረው ሰራዊት ቀን ቀን አንበጣ እንዲያባርር ይደረጋል። ደምም ሰጥተናል፡፡ በብዙ ሌሎች ነገሮችም ማህበረሰቡን እንደግፋለን” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም፡፡

ጥቃቱ በተፈጸመበት እለትም ቀኑን በሙሉ አንበጣ ሲያባርሩ ውለው ጎናቸውን ለማሳረፍ ጋደም ባሉበት ቅፅበት ነዉ አብረዋቸው በኖሩ በሰራዊቱ ውስጥ በነበሩ ከሀዲ የጁንታው ተላላኪዎች ከጀርባ የተወጉት:: አስር አለቃ ቤቴልሄም ትናገራለች፤ “በዕለቱ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ተኩል ከውጭ ወደ ውስጥ የጥይት ሩምታ ተከፈተብን፡፡ ከውስጥ ደግሞ እነዛ አስቀድመው ሲሰበሰቡና ሲያሴሩ የቆዩት የጁንታው እኩይ አላማ ፍፃሚ የሰራዊቱ አባላት የገዛ ጓደኞቻቸው የሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ በተኙበት በጥይት መምታት ጀመሩ፡፡ ከተኛንበት እየተጣደፍን ወደ ውጭ ወጣን፤ ትጥቃችን ወዳለበት መጋዘን ሄድን። የመሳሪያ ግምጃ ቤቱ ግን ተቆልፏል፡፡ የመጋዘኑን ቁልፍ የያዘውን ወታደር አስቀድመው ገድለውታል” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም፡፡

በእለቱ ዋርድያ ላይ የነበሩ የሰራዊቱ አባላት በኮለኔል ሀጎስ መገደላቸውን የምትናገረው አስር አለቃ ቤቴልሄም፤ “ባዶ እጃችንን ስለሆንን እራሳችንን ለመከላከል አልቻልንም፡፡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ የሚከላከሉት፡፡ ብዙዎችን ገደሉ፡፡ እጅ የሰጡትንም ጭምር ገደሏቸው” ትላለች።

የጁንታው ታጣቂዎች ግፍና ጭካኔ የትየለሌ መሆኑን የምተናገረው አስር አለቃዋ፤ “አንድ የአራተኛ ክፍለ ጦር አባል የነበረ ወታደር እጁን ከሰጠ በኋላ በታንክ ደፈጠጡት፡፡ መትረፍ የሚችሉ ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው፡፡ ሬሳቸውን ሳይቀብሩ የራሳቸውን ሰዎች ሬሳ ብቻ አንሰተው ሄዱ” ስትል ነው የጓዶቿ በከሀዲ የሰራዊቱ አባላትና በጁንታው ታጣቂዎች የተፈጸመባቸውን ግፍ የምትናገረው።

ከዚህ ሁሉ ግፍና ጭካኔ በኋላ የተረፉትን እንድነ አስር አለቃ ቤቴልሄም ያሉ የሰራዊቱ አባላትን የጁንታው ታጣቂና ከሀዲ የሰራዊቱ አባላት በሲኖትራክ ጭነው አጉላ ወደተባለ ትምህርት ቤት ወስደው እንዳጎሯቸው ትናገራለች፤ “በህይወት የተረፉና ከሻምበል በላይ የነበሩ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮንኖችን ለብቻቸው አስቀመጧቸው፡፡ ትኩረታቸው በነሱ ላይ ነበር፡፡ እስከ አሁንም የት እንዳደረሷቸው አላውቅም፡፡

ሴቶችን ለብቻችን በአንድ ክፍል ውስጥ አጎሩን፡፡ ሞባይላችንን፣ ልብሳችንንና ያለንን ዶክመንት፣ ገንዘባችንን ሁሉ ዘረፉን፡፡ ያለምግብና ውሃ ለሶስት ቀን ወንበር ላይ እየተኛን አሳለፍን፡፡ አንዳንድ የወታደር ሚስት የሆኑ ነዋሪዎች ምግብ ሊሰጡን ሲሞክሩ ይከለክሏቸው ነበር፡፡ በረሀብ የተነሳ በጣም ተዳከምን፡፡ በመጨረሻ ጥሬ እየቆነጠሩ ይሰጡን ጀመር”

አፍኝ ቆሎ እየሰጡ አጉረው ለሁለት ሳምንት ያቆይዋቸውን የሰራዊት አባላት እጃቸውን ጠርንፈው አስረው ወደ መቀሌ እንዳመጧቸው ትነገራለች፤ “መቀሌ የእንሰሳት ጤና ኮሌጅ ውስጥ አስቀመጡን፡፡ ስድብ፣ እርግጫና ማንጓጠጥ ይደርስብን ነበር፡፡ ሌላ አካባቢ የሴቶችን ጡት እንደቆረጡም ሰምተናል፡፡ በእኛም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊቱ የሰጡ የጁንታው ታጣቂዎች ተናግረዋል፡፡ ህዳር 21 እቅዳቸውን ለመፈጸም ሲዘጋጁ ህዳር 20 የመከላከያ ኮማንዶዎች ደርሰው ነጻ አውጥተውናል” ስትል በሰራዊቱና በፈጣሪ ታምር መትረፋቸውን ተናግራለች።

ጁንታው ለእኩይ አላማው ያልተባብረውን ሁሉ ከማጥፋት የማይመለስ ጨካኝና ከሀዲ ነዉ ያለችው አለቃ ቤቴልሄም በትግራይ የኩያ ተወላጁን ወታደር ተጋድሎም ታስታውሳለች “የአራተኛ መካናይዝድ አባል የሆነ የኩያ አካባቢ ተወላጅ ከእኛ ወገን ቆሞ ያደረገውን ተጋድሎ ማንሳት ያስፈልጋል፡፡ ልጁ ታንከኛ ነው፤ ታንክ ውስጥ እንዳለ እጅህን ስጥ ይሉታል፡፡ እኔ የቆምኩት ለኢትዮጵያ ስለሆነ እጄን አልሰጥም ብሎ በታንክ መዋጋት ጀመረ፡፡ ታንክ ከታንክ ጋር ገጠሙና ተረባርበው ገደሉት”፡፡

ሌላዋ የአይን ምስክር ኮንስታብል አለምነሽ ገመዳ የሰባት ወር እመጫት ናት። የፌደራል ፖሊስ አባል ስትሆን የጁንታው ታጣቂዎችነ የሰራዊቱ ከሀዲ አባላት ለእሷና መሰል እመጫቶች እንኳን እንዳልራሩላቸው ትናገራለች።

ኮንስታብል አለምነሽ ምድብ የጥበቃ ስራዋ አክሱም አየር መንገድ ውስጥ ነው፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ አየር መንገዱ ውስጥ በጥበቃ ስራ ላይ ባሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመውን ክህደት ስታነሳ እንባዋን መቆጣጠር አትችልም።
“እኔ የሰባት ወር እመጫት ስለነበርኩ መሳሪያዬን ለሌሎች ሰጥቼ ማረፊያ ቤት ውስጥ አራስ ልጄን ይዤ ተቀምጬ ነበር፡፡ ጋንታ አመራሩ የጁንታው ተላላኪ ነው፡፡ ላካስ ከታጣቂዎች ጋር ተመካክሮ ጨርሷል፡፡ በጫካው በኩል አድርገው ወደ ጊቢው ገቡና እጅ ስጡ አሉ፡፡ እርሱ ቶሎ ብሎ መሳሪያውን ሰጣቸው፡፡ ሌሎቹ አንሰጥም ብለው አፈገፈጉ፡፡ ከዚያም ተኩስ ተጀመረ፡፡ አንድ ሃይል አመራር ከማማው ላይ ሆኖ ለመከላከል ሞከረ፡፡ መጨረሻም እጁን እንዲሰጥ አደረጉት፡፡ እጁን ከሰጠ በኋላ ግን በረንዳው ላይ እጁን በሰንሰለት አስረው በዱላ ጨፈጨፉት›› ትላለች ኮንስታብል አለምነሽ።

ኮንስታብል አለምነሽ በከሀዲዎች የተፈጸመው ግፍ ዛሬም ድረስ ከአይኗ አልጠፋ ብሎ አይኖቿ በእንባ እንደተሞሉ ሳግ እየተናነቃት ነበር ሁኔታውን የነገረችን።
“ከዚያ ወደ እኔ መጡ ቤቴን ዘግቼ እንደተቀመጥኩ የጥይት እሩምታ አወረዱብኝ፤ ውጪ አሉኝ ህጻን ልጅ ስለያዝኩ አልወጣም አልኳቸው፡፡ ጨካኞ ናቸው ለአራስ ልጄ እንኳን አልራሩም:: አስገድደው ገቡና ቤቱን ፈተሹ ፤ አንድም ነገር ሳልይዝ ባዶ እጄን አስወጡኝና ልጄን እንዳቀፍኩኝ በሶምሶማ ሩጪ አሉኝ፤ ከእኔ ጋር ሌላም አንድ ልጅ የያዘች ሴት ነበረች፡፡ እርሷ ግን ጭንቅላቷ አካባቢ ተመታ ደሟን እያፈሰሰች ሩጪ ተባለች። ሁለታችንም ህጻን ልጅ ይዘናል፤ እሩጡ እያሉ አስሮጡን፡፡ ስላሴ ወደሚባል ቤተክርስቲን ጫካ ውስጥ ወሰዱንና የሞቱ የነሱን ታጣቂዎች ተሸከሙ አሉን፡፡ ልብሳችንን ጫማችንም አስወልቀው በባዶ እግራችን አስኬዱን፤ እንደዚ አድርገው ወደ ሽሬ አመጡን፤ እጅ የሰጡ አመራሮቻችንንም ገደሏቸው፡፡ በተለይ ኦሮሞና አማራን እየለዩ አስቀሯቸው፡፡ የደቡብ ተወላጆች ላይም አይናቸው ላይ በርበሬ እየጨመሩ ያሰቃይዋቸው ነበር፡፡ በረሀብም የሞቱ አሉ፡፡ የሞቱትን አስፋልት ላይ ሲጎትቷቸው ነበር፤ አንዳንዶቹን አፍነው የት እንደወሰዷቸው አናውቅም፡፡ ከባ
ለቤቴ ጋር እስከ ሽሬ ድረስ አብረን ከመጣን በኋላ እርሱን እዛው አስቀሩት፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም” ከዚህ በላይ ኮንስታብል አለምነሽ መናገር አልቻለችም፤ እንባዋንም መግታት ተሳናት፡፡

ጁንታው በህግ ማስከበር ዘመቻው በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ከሁሉም የትግራይ አካባቢዎች ተወግዷል:: ከጁንታው አባላት መካከል እጃቸውን መስጠት የጀመሩ ያሉ ሲሆን ቀሪ የጁንታው አባላት በጠባብ አካባቢ መከላከያ ሰራዊቱ በቅርብ እየተከታትላቸው እንደሚገኝ መንግሥት መግለፁ ይታወሳል::

በኢያሱ መሰለ
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂ ፒ ኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚ ገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መም ሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል።

እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።

በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላ ፊው፤ በሠላማዊ መንገድ እጅ ለማይሰጡና የኃይል አማራጭ ለመጠቀም የሚሞክሩት ላይ ደግሞ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ።

እነዚህ ጸረ ሠላም አካላት አባ ቶርቤ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተው ፣ ኦሮሚያ ክልልን የግጭትና ጦር አውድማ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ሥራቸው አድርገው መቆየታቸውንም አመልክተዋል።

ማንኛውንም የፖለቲካ አመለካከት ያለው አካል በዴሞክራሲያዊ መንገድ የፖለቲካ አስተሳሰቡን ለህዝብ መሸጥ ይጠበቅበታል ያሉት ኮማንደር እንዳለ፤ ከዚህ ውጪ ሰላም በማደፍረስና ሠላማዊ ዜጎችን በመግደል ስኬታማ መሆን እንደማይቻል አስረድተዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስም ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነና የዜጎችን ሠላም ለመጠበቅ የተቋቋመ ነው ያሉት ምክትል ኮማንደር ፣ በየትኘውም ሁኔታ የዜጎችን ሰላም ችግር ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን አይታገስም ብለዋል። መንግሥትም ለዜጎች ሠላምና ደህንነት መቃወስ ምክንያት የሆኑ እንደ የህወሓት ጁንታና ፣ አባ ቶርቤ፣ ሸኔ እና ሌሎችንም ወደ ህግ ለማቅረብ ከመቼውም በላይ ጠንካራ ሥራ እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=36804
በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመ ጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ። በቆላ ተምቤን የጁንታውን አመራር ለመያዝ የሚ ደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የጁንታው አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል።

የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ቆላተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የጁንታው ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው ጁንታው በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል። በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=36796
የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ
**************
(ኢ ፕ ድ)
”አንድ በሬ ሸጬ ስድስት ዓመት በመቀሌ የታሰረውን የልጅ ልጄን በደከመ አቅሜ ሄጄ አስፈትቻለሁ። ከተፈታ በኋላም አፋኙ የህወሓት ጁንታ በሚደረግበት ጫናና ክትትል ተማሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዷል። የልጅ ልጄ ያለበትን ቦታና ምን እንዳጋጠመው ስለማላውቅ የበረሃ ራት ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነበር። አምና ግን ሳውዲ መግባቱን ስለሰማሁ ደስታዬ ወደር የለውም” የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው።

ቃፍታ ሁመራ ከተማ ከሀዲው የህወሓት ጁንታ ነጻ ከወጣች ሶስት
ሳምንት ሁኗታል። ከተማዋ ነጻነቷን በመቀናጀቷ እፎይታ ከተሰማቸው
ነዋሪዎች መካከል አንዷ ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። አፋኙ ቡድኑ
በማንነታቸው ምክንያት በእኚህ አዛውንት ላይ ከፍተኛ ማንገላታት፣
ሰቆቃና ግፍ ፈጽሞባቸዋል።

ማንነቴን አልሸጥም እኔ የወልቃይት አማራ ነኝ አባቴ፣ አጎቶቼ ይግባኝ ሲኖራቸው መቀሌ ሳይሆን ደባርቅና ዳባት ሄደው ሲያስፈጽሙ ነበር ብዬ በአደባባይ በመናገሬ እያረስኩና እያሳረስኩ ልጆቼን ያሳደኩበትን መሬቴን ተነጥቄያለሁ ይላሉ ።
https://www.press.et/Ama/?p=36795
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ
************************
(ኢ ፕ ድ)

መቀሌ፡- በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር ሶስተኛው ምእራፍ ከተጠናቀቀ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የትራይ ብሄራዊ ክልል ጊዜያዊ አስተዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ህግን የማስከበር ርምጃውን በጥንቃቄ በማከናወን ወደ ቀጣዩ ምእራፍ መሸጋገር ተችሏል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ስራ ተጀምሯል።

እስካሁንም በሽሬ እና በአክሱም የተለያዩ ቀበሌዎችንና ወረዳ አስተዳደሮችን መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል።

ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የተመረጡ ስራ አስፈጻሚዎች ስራ ጀምረዋል ያሉት ዶ/ር ሙሉ፤ በመቀሌ ከተማ ህዝቡ ወደ መደበኛው ስራው እንዲመለስ፣ የመንግስት ተቋማት ስራቸውን እንዲያከናውኑና የንግድ ተቋማትም ስራቸውን እንዲጀምሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶች ተደራጅተው ከመከላከያ ጎን እንዲቆሙ የልዩ ሃይልና የሚሊሻ አባላት እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጡም እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ሙሉ፤ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የመንግስትን እገዛ ሲጠባበቁ እንደነበርና በከተሞች አልፎ አልፎ የሚታየውን ዘረፋ ለማስቆም ከጸጥታ ሃይሉ ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በጸጥታ ስጋት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ሸሽተው የሄዱ ሰዎችን ወደ ነበሩበት የመመለሱና የማረጋጋት ስራው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

መከላከያ ሰራዊት መቀሌንና ሌሎች ከተሞችን የተቆጣጠረ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ወደሚኖርበት አካባቢ በመምጣት ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የህግ ማስከበሩ ስራ ለትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ጥቅም ይዞ የሚመጣ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ሙሉ፤ ህዝቡ ከነበረበት ጫና ወጥቶ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል ብለዋል፡፡

የክልሉን የካቢኔ አባላት የማዋቀር ስራ እንደሚሰራና እንደ ባንክ ፣ቴሎኮም፣ መብራት የመሳሉት አገልግሎት ሰጪ ቋማትን ከፌደራል መንግስት ጋር በመተባበር የማስጀመሩ ስራ ትኩረት ተሰጥጦታል ብለዋል፡፡

የስራ እንቅስቃሴ ከመቋረጡ ጋር ተያይዞ የምግብ እጥረት ሊፈጠር ስለሚችል አርዳታዎችን የማስተባበር ስራዎች እንደሚከናወኑ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል፡፡
በኢያሱ መሰለ
ከአላማጣ ወደ መቀሌ የሚሄደው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር እየተጠገነ ነው
***********
(ኢ.ፕ.ድ)

ከአላማጣ ወደ መቀሌ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር እየተጠገነ ነው።

በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ተዟዙሮ እንደተመለከተው፤ በከሀዲው የህወሓት ታጣቂዎች ጉዳት ደርሶበት የነበረው ይሄው የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ጥገና በፍጥነት እየተከናወነ ነው።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው ማለታቸውና ይህ ተግባር ሦስት መልኮች እንዳሉት ማስታወቃቸው ይታወቃል።

"ሰብአዊና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የተጎዳውን መሠረተ ልማት መልሶ መገንባት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር። እነዚህ ሥራዎች በስፍራው በተገኙ ቡድኖች አማካኝነት ተጀምረዋል" ማለታቸውም ይታወሣል።
ባለ ከዘራው ኮሎኔል
*********
(ኢ ፕ ድ)
ፊታቸው ላይ የአልበገርም ባይነት ስሜት ጎልቶ ይነበባል፤ እያነከሱም ቢሆን ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። መገናኛ ራዲዮናቸውን እና የምርኩዝ ከዘራቸውን ይዘው የጁንታው ቡድን አመራር ያለበት ቆላ ተንቤን አቅራቢያ በምትገኝ ሰዋራማ ስፍራ ላይ ጦሩን እየመሩ ይገኛል።
ኮሎኔል ሻምበል በየነ ይባላሉ። በቆሙበት የውጊያ ትዕዛዝ እየሰጡ ኮስታራ ፊታቸውን ወደእኛ ዘወር አደረጉ። ቆስለው አልታከምም በማለት በወኔ እየመሩ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራር መሆናቸውን ሰማንና ታሪካቸውን እንዲያካፍሉን ጠየቅናቸው።
ድንገተኛ ፈገግታ እያሳዩ ቀድሞም የጁንታው አባላት ውጊያ ሰራዊቱ ላይ ሊከፍቱ እንደሆነ ጥርጣሬ ነበረኝ በማለት በተረጋጋ ስሜት ትውስታቸውን ማጋራት ጀመሩ። እኔ የ31ኛ ክፍለጦር ምክትል የኦፕሬሽን አዛዥ ነበርኩ ዋና አዛዡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቀደም ብሎ የተወሰኑ አባላትን ሽሬ ድረስ ወስዶ ሲሰበስብ የሆነ ነገር ሊፈጥር እንደሚችል አስበው እንደነበር።
ማታውኑ ችግር ሊኖር እንደሚችል በማመን በግሌ ዝግጅት አደረግኩ። ስዘጋጅ በባንክ አካውንቴ የነበረውን ጥቂት ገንዘብ በቤተሰብ አዞርኩ። ከዚያም ጥቃት ለማድረስ ከበባ ሲፈጽሙብኝ ተከብቤያለሁ በሚል ለበላይ አካላት ሪፖርት አደረኩ ።
በመከላከያ ላይ ጥቃት ሲፈጸምም የክፍለጦሩ አዛዡ ከድቶ የጁንታውን ቡድን ተቀላቀለ። በዚህ ጊዜ የክፍለጦር ኮሚቴ ወይም ከበታች አዛዦች አባላት ጋር በመሆን ግብግብ ፈጸምን። እኔም ከፊቴ ያለውን በጥይት መትቼ ጣልኩ። እኔ ጋር የተጀመረች የመከላከል ተኩስ እስከታችኛው የሻለቃ አመራር ድረስ እየተደማመጠ የመከላከል እርምጃውን ወሰደ።
በኋላም የካምፑን ከበባ አጠናቅቄ ስወጣ ደግሞ የልዩ ኃይል ከውጭ ጠበቀኝ የሚሉት ኮሎኔል፤ እነሱንም ጥሼ በመውጣት ከስምንተኛ ሜካናይዝድ ጦር ጋር ተቀላቀልኩ ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሱታል።
በወቅቱ እግራቸው ላይ በጥይት መመታታቸው እምብዛም ቁብ አልሰጡትም። በዚያ ሁኔታ ላይ እያሉ ወደኤርትራ በማፈግፈግ በዚያ ከሚገኘው እና በጁንታው ታጣቂ ጥቃት ደርሶበት ከሚገኘው ጦራቸው ጋር ተገናኙ። ጦሩን አደራጅተው በመመለስ ሽራሮ ፣ሽሬ፣ አዲ አደራይ፣ አዲነብሪ እና በርካታ ቦታዎች በማስለቀቅ የህግ ማስከበር እርምጃቸውን በብቃት መወጣትም ቻሉ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከታፋቸው የሚፈስ ደም እንደ ነበር በቅርበት የሚያውቋቸው ወታደሮች ይናገራሉ። ቁስሉን በየሶስት ቀኑ በጦር ሜዳ አካባቢ እየታከምኩ አንዷ ጥይት ወጣች የሚሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ምርኩዝ ይዘው ግዳጃቸውን መወጣታቸውን ነግረውናል። ዋና አዛዡ ግን የጁንታውን ቡድን በመቀላቀል ለጁንታው አመራር ሽፋን ለመስጠት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
አሁን ላይ ቆላ ተንቤን ላይ ወንጀለኛ ለማስመለጥ እና ወንጀለኛ ለመያዝ ዋናው እና ምክትል አዛዡ ፊት ለፊት ተፋጠዋል። ምክትል አዛዥ ዋናውን ከነጀሌዎቹ እያባረረ እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል። ከሚመሩት ጦር ጋር በርካታ ሀገር የከዱ ጄኔራሎችን እያባረሩ ቆላ ተምቤን ላይ ያደረሱት ኮሎኔል ሻምበል፤ እዚህ በመድረሴ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ በኩራት ይናገራሉ።
ቆላ ተምቤን ላይ የመሸገውን የከሃዲው ቡድን አመራር አባላት ለህግ ሲቀርቡ በተሻለ ህክምና በጥይት የተመታውን እግራቸውን ሊታከሙት እንደሚችሉ እንደተወርዋሪ ኮኮብ መሳይ ብልጭታ ባለው ፈገግታቸው ታጅበው በለሆሳስ ነገረውናል። ቦታው ላይ ቆስለውም ቢሆን ጦሩን እየመሩ መገኘታቸው ለሰራዊቱም ብርታት መሆኑን አልሸሸጉንም።
በእጃቸው ከዘራቸውን ጨብጠው የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ በጉዳት እያሉም ቢሆን በህግ ማስከበር እርምጃ የጁንታውን አመራሮችን ለመያዝ ፀሐይ ውርጭ ሳይሉ በመታገል ላይ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን በየጊዜው አታጣም የሚባለው ብሂል እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ነው።
ጌትነት ተስፋማርያም
አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013 ዓ.ም