Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለ2ኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ
********
(ኢ.ፕ.ድ)

በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለ2ኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ።

በከተማዋ ህግን የማስከበር ግዳጅ እየተወጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ህገወጥ ድርጊቶችን ለማስወገድ እና የህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ እየሠሩ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮማንደር ሙላት ማሞ ገልፀዋል።

ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ በአንድ ሰው ስም የተመዘገቡ 11 የቤት ካርታዎች እና በዚሁ ግለሠብ ስም ከፍተኛ ገንዘብ የተዘዋወረበት ቼክ ተገኝቷል።

ተጨማሪ ገጀራዎች፣ መጥረቢያዎች እና የወንድ ማንኮላሻም መገኘቱን አብመድ ዘግቧል።
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች አረጋገጡ።
ወሮ ኬርያ የሕወሐት ከፍተኛ አመራርና በመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት የበበራቸው ቢሆንም የከሀዲው የህወሓት ቡድን ይሻለኛል ብለው ወደ መቀሌ መሄዳቸው ይታወሣል።
“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” - ዶክተር ዳንኤል በቀለ ኢሰመኮ ኮሚሽነር
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶክተር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል።
ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል፡፡
በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል። በመሆኑም ኢኮኖሚያቸው እዲያንሰራራ እና ስነ ልቦናዊ ቀውስን መቋቋም እንዲችሉ ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ተጎጂዎቹ አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ የሚፈልጉ መሆናቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአካባቢው የሚገኙ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል
የማይካድራ ጥቃት ቀላል የወንጀል ድርጊት አይደለም ፣ አስቀድሞ የታቀደ እና በጥንቃቄ የተቀናጀ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው ያሉት ዶክተር ዳንኤል፤ የአካባቢው የፀጥታ መዋቅር ለጥቃቱ ተጠያቂ ከሆነው ሳምሪ ከሚባለው ቡድን ጋር ተባብሮ ንጹሃንን ከጉዳት ከመጠበቅ ይልቅ ጥቃቱን መደገፉንና በጥቃቱ መሳተፉን አስረድተዋል፡፡
ወንጀሉ በአካባቢው በነበረው ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ድጋፍና ተሳትፎ የተፈጸመ ነው ያሉት ዶክተር ዳንኤል፤ ለወንጀለኞች ድጋፍ ያደረጉ እና የተሳተፉ የአካባቢው የፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በሕግ ፊት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል ፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ተፈጽሞ የማይታወቅ አይነት ጭካኔ የተሞላበት የወንጀል ድርጊት እንዴት እንደተፈጸመና እንደተቀነባበረ ተጨማሪ ምርመራዎችን ማካሄድ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
የቅድሚያ ሪፖርቱ በቁጥር እና በጉዳት መጠን ላይ ትኩረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ዳንኤል፤ ጭፍጨፋው ያስከተለው የስነልቦና-ማህበራዊ ተፅእኖው እንዲሁም ወንድም ወንድም ላይ እንዴት እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ሊፈጽም እንደቻለ የዘርፉን ባለሙያዎች ትንታኔ እና አካታች ጥናት እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡
በምርጫ 2013 ላይ የተኮረ ውይይት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተወያዩ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተገኘበት ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።
ውይይቱ ዐበይት ባለ ድርሻ አካላት ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም የምርጫ ስርዓትን በሚያስቃኝ ገለጻ ተጀምሯል።
በጉጉት የሚጠበቀው እና ዐበይት ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መሠረታዊ ለውጥ ማካሄዳቸውን ተከትሎ የሚከናወነው ታሪካዊ ምርጫ፣ ከ2010 አንስቶ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና የምታደርገው ጉዞ ዓይነተኛ ማሳያ ይሆናል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ የፈነዳው ቦምብ ምንም ጉዳት አለማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ዛሬ (ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ/ም) ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ከአካባቢው ሰዎች በደረሰው ጥቆማ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች ወደ ቦታው በማቅናት ለማምከን ባደረገው ሙከራ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሊፈነዳ ችሏል።
በዚህም አንድ ግለሰብ የቦንቡ ፍንጣሪ በቅርብ ርቀት ከሚሰራበት ጋራዥ ቅጥር ግቢ በስራ ላይ ሳለ በፍንጣሪው ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ ተጎጂው የህክምና ርዳታ በማግኘት ወደ ቤቱ መመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት እንደደረሰው እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
በተመሳሳይ በዚሁ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፖሊስ በደረሰ መረጃ መሰረት ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ቦንቡን የማምከን ስራ ሰርተዋል፡፡
በነብስ ውጪ ግቢ ጣር ላይ የሚገኘው የጁንታው ተላላኪዎች በአዲስ አበባ በንፁሃን ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ የሚደርጉትን መንፈራገጥ ለማምከን የሚቻለው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ በማጠናከርና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል።
መንግስት በከሀዲው የህወሓት ቡድን ላይ ለወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቀረቡ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በምርጫ 2013 ዙሪያ በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች መንግስት በህወሓት ጁንታ ላይ ለወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቀረቡ።
መንግስት ህግና ስርአት የማስፈን ሃላፊነት ያለበት እንደመሆኑ ላለፉት 27 አመታት በተለይ ደግሞ ከለውጡ ወዲህ የሀገርን አንድነት ለመናድ የተንቀሳቀሰን ሀይል በአጭር ግዜ በቁጥጥር ሰር ማዋል መቻሉ ለመንግስትም ለኢትዮጵያ ህዝብም ትልቅ ድል ነው ብለዋል የፓርቲ አመራሮቹ።
በተለይ የመከላለያ ሰራዊት አባላትና አመራሮች ባልጠበቁት ሁኔታ ትልቅ ጥቃት ደርሶባቸው ያንን በመቀልበስ ሰላም ለማስፈንና ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያደረጉት ተጋድሎ በታሪክ የሚወሳ ይሆናል ሲሉም ነው አክብሮታቸውን የገለጹት።
መንግስት የወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ ሀገር ለማፍረስ የተንቀሳቀሰውን ከሀዲ የህወሓት ጁንታ ብቻ ሳይሆን የዚህ አይነት ሀሳብ ያላቸውንም አንገት የሚያስደፋ በመሆኑ መንግስትን ሊያስመሰግን የሚገባ ተግባር መሆኑን አመራሮቹ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም መንግስት እርምጃ ለመውሰድ ዘግይቷል የሚል እይታ እንደነበራቸው በማንሳትም ከትናንት በስቲያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረገላቸው ገለጻ የነበረባቸውን ብዥታ እንዳነሳላቸውም አመራሮቹ ተናግረዋል።
በቀጣይም በየቦታው በተንጠባጠበ አካሄድ የሀገርን አንድነት ለማፍረስና የህዝብን ሰላም ለማወክ በሚንቀሳቀሱት ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መንግስት ሊወስድ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በራስወርቅ ሙሉጌታ
ፌዴራል ፖሊስ ነጻ በወጡ የትግራይ አካባቢዎች የሕብረተሰቡን ሰላም እያስጠበቀ እንደሆነ ተገለጸ
- የአክሱም ጺዮን ማሪያም ንግስ በዓልም በሰላም ተከናውኗል
*************************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጁንታው ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ላይ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የጽዮን ማሪያም ንግስም በሰላም መከናወኑ ተገልጿል፡፡
ከሀዲው የህወሓት ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ያስታወሰው ኮሚሽሽኑ፤ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት እያስከበር ይገኛል። ህብረተሰቡም መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መጀመሩ ተገልጿል።
ለተመሳሳይ የጸጥታ ማስከበር ስራ ወደ አክሱም ከተማ የገባው የፀረ-ሽብር ልዩ ኮማንዶ ሀይል ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ/ም በአክሱም ከተማ የተከበረውን ዓመታዊ የፅዮን ማርያም ንግስ በዓል ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ያለምንም የፀጥታ ችግር ማክበር እንዲችል አድርጓል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪ የጁንታው አባላትን ከገቡበት ገብቶ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀረ-ሽብር ልዩ ኮማንዶ ሀይል ወደ አካባቢው በማሰማራት የክትትል ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
በዚህ ወቅት በተሰራው ጠንካራ የጸጥታ ማስከበር ስራ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ለእኩይ ተግባሩ ሊጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ያለው ኮሚሽኑ፤
ይህ መስዋዕትነት ተከፍሎበት እየተሰራ ያለው የህግ ማስከበር ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በመሀመድ ሁሴን
ከሃዲው የህውሃት ቡድን ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ሰላም ማጣት እጁ እንደለበት በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ገለጹ
👉በደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ሂደት ላይ የህወሃት አፍራሽ ሴራን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መግለጻቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከሃዲው የህውሃት ቡድን ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ሰላም ማጣት እጁ እንደለበት በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ገለጹ፡፡
አምባሳደር ጄምስ ፒታ ሞርጋን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የደቡብ ሱዳን ሰላም ስምምነት ድርድር በከሃዲው የህውሃት ከፍተኛ አመራር አማካኝነት በመደረጉ ለሱዳን ህዝብ አንዳችም ውጤት አላስገኘም፡፡
የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ሂደትን በከሃዲው የህውሃት ቡድን አባል በሆኑት አቶ ስዩም መስፍን አሸማጋይነት ድርድሩ ቢደረግም፤ በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ባለው የህወሃት የተዛባ አስተሳሰብና አድሏዊ አቋም ከውጤት መድረስ አለመቻሉንም አምባሳደሩ አብራርተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ሂደት ላይ የከሃዲውን የህወሃት አፍራሽ ሴራን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መግለጻቸውን አስታውሰው፣ እ ኤ አ በ2015 በሱዳን ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካካል በአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት ቢፈረምም፣ በአደራዳሪው የጁንታው መሪ ስዩም መስፍን በወሰደው ግልፅ አድልዎ እውን እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ለግጭቱ የታሰበውን መፍትሄ አላመጣም ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዳስደሰታቸው በመግለጽ ለደቡብ ሱዳን መንግሥት ከለላ መሆኑን ያብራሩት አምባሳደሩ ሁለቱ ሀገራት ለረጅም ጊዜ የቆየውን መልካም ግንኑነት ይበልጥ ለማጠናከር የህወሓትን መጥፎ ፍላጎት ማጋለጥና ከሕዝብ እንዲነጠል ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
“ደቡብ ሱዳን በአንድ አመራር ታምናለች፣ እሱም የአብይ አህመድ መንግስትና አመራር ነው” ያሉት አምባሳደር ሞርጋን ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር አንጋፋ ነፃ ሀገር እንደመሆኗ ውስጣዊ ችግሮቿን በሰላማዊ መንገድ የመያዝና የመፍታት ልምድና እውቀት ያላት ሀገር ናት ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ አያይዘውም የሁለቱ አገራት ግንኙነት በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በህዝብ ለህዝብ ድንበር ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቅሰው አህጉራዊ ና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ተግዳሮት እንደምታልፍ እና የልማት ፕሮጀክቶ በተረጋጋና በተቀላጠፈ ሁኔታ እንደምትቀጥል ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በመሃመድ ሁሴን
ጁንታው ለጥፋት ዓላማው ሊያውለው የነበረ የመሳሪያ ክምችት በመከላከያ አማካኝነት ለመንግሥት ገቢ ተደረገ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ሽሬ ፦ ጁንታው ለጥፋት ዓላማው አስቦና አቅዶ በሽሬ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ ስፍራ በርካታ የመሳሪያ ተተኳሾች እና ፈንጂ መሳሪያዎች አከማችቶ ነበር። የተተኳሽ የመሳሪያ ዴፖው በመከላከያ ሠራዊት እዝ ስር ቢሆንም የጁንታው ታጣቂዎች ግን የሚወጣ እና የሚገባውን ንብረት ሁሉ ከመንግሥት በመሰወር ሲያከማቹ ቆይቷል።
ጁንታው መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ለጥፋት ዓላማው ሊያውላቸው ዝግጅት ሲያደርግ ከርሟል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሸሬን እና አካባቢውን በፊት በተቆጣጠረበት ወቅት የመሳሪያ ክምችቱ ያለበትን ቦታ በአጭር ጊዜ በመቆጣጠር የጁንታውን አጥፊ ዓላማ ማምከን መቻሉን የህግ ማስከበር ዘመቻው የተተኳሽ ክፍል ኃላፊ ኮሎኔል መካሽ ጀምበሬ ገልጸዋል።
ከዘመናዊ ታንክ እና ላውንቸር አንስቶ እስከ አነስተኛ ጥይቶች ድረስ በአካባቢው ሰፊ ክምችት እንደነበረ የተናገሩት ኮሎኔል ጀምበሬ፤ ከመከላከያ እውቅና ውጪ ጁንታው ቡድን መሳሪያዎቹን ጥቅም ላይ ሲያውል የነበረ ቢሆንም ሠራዊቱ በፍጥነት ዕርምጃ በመውሰድ በቁጥጥሩ ስር አውሎታል።
መከላከያ ሠራዊት ሠራዊቱ በአጭር ደቂቃ ውስጥ በማከማቻው በነበሩ የጁንታው ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ በመውሰድ ለጥፋት ዓላማ ሊውል የነበረ የሃገር ሀብት ማዳን መቻሉን አስረድተዋል።
የጁንታው ቡድን አባላት የመሳሪያ ክምችቱን ለማውደም እና ህዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ ፈንጂ ለመጥመድ ሲሞክሩ ሠራዊቱ እንደደረሰባቸው ገልጸው፤ ፈንጂውን እንኳን በአግባቡ ሳይጠምዱት ሠራዊቱ ደርሶ ዕርምጃ እንደወሰደ አስታውቀዋል። በዚህም አኩሪ ተግባር በህዝብና መንግሥት ወጪ ተገዝተው ለሀገራዊ ግዳጅ ሊውሉ የተዘጋጁ በርካታ ተተኳሾች ለጥፋት ዓላማ ሳይውሉ ለመንግሥት ገቢ ተደርገዋል።
በተያያዘ የጁንታው ታጣቂዎች ከመከላከያ ደብቀው ሲጠቀሙበት የነበረ እና በሽሬ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ዳቦ ቤት እና የተለያዩ የሠራዊት ትጥቆችን መያዙን ኮሎኔል መካሽ ጀምበሬ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል ስምሪት ላይ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት ከባድ ተሽከርካሪዎች ቅያሬ ጎማ የለም በሚል እንዲቆሙ ሲደረግ እንደነበር ያስታወሱት ኮሎኔል መካሻ፤ በመጋዘኖቹ ውስጥ ግን አዳዲስ የተሽከርካሪ ጎማዎች ተከማችተው መገኘታቸውን ለጋዜጠኞች አሳይተዋል።
በመጋዘኖቹም የኢትዮጵያ ሠራዊት መለዮዎች እና ዩኒፎርሞች እንዲሁም የጁንታው ታጣቂዎች አልባሳት ተገኝተዋል። በተጨማሪ የስንዴ ዱቄት ክምችት እና የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችም ተገኝተዋል።
ይህም ጁንታው ለረጅም ጊዜ በጦርነት እቆያለሁ በሚል አቅዶ ሲሠራባቸው የነበሩ ዝግጅቶች እንደነበሩ ማሳያ ነው። ይሁንና መከላከያ ሠራዊት በወሰደው የህግ ማስከበር ዕርምጃ የጁንታው እቅድ ሁሉ ፈራርሶ ህልም ሆኖ ቀርቷል። ንብረቱም በመከላከያ አማካኝነት ለመንግሥት ገቢ ተደርጓል።
ጌትነት ተስፋማርያም
አዲስ ዘመን ህዳር 24/2013
በትግራይ ክልል በወረዳና ቀበሌ ደረጃ የጊዜያዊ አስተዳደር እየተመሰረተ ነው
- በሽሬ ከተማ በህዝብ የተመረጠ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቋመ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጁንታው ቡድን ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች በወረዳ እና ቀበሌ ደረጃ የጊዜያዊ አስተዳደር እየተመሰረተ ነው። በሽሬ ከተማ በህዝብ የተመረጡ አባላትን የያዘ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚቴ ተቋቋመ።
በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት፤ የትግራይ ከተሞች ከጁንታው ቡድን ነፃ ወጥተዋል። በየከተሞቹም ከሚገኘው ህዝብ ጋር በመወያየት ህብረተሰቡን ዋና ተዋናይ ባደረገ ሁናቴ በወረዳ እና ቀበሌ ደረጃ አካባቢዎቹን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድሩ አባላት እየተመረጡ ነው።
በትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላይ ተዟዙረው በመጎብኘት እና በማወያየት ህዝብ በአጭር ጊዜ የተለመደ ሥራውን የሚጀምርበትን ሁኔታ እያመቻቸ ይገኛል። በተለይም የቀበሌ እና ወረዳ አስተዳደሮች በመመረጣቸው አስፈላጊውን የመንግሥት አገልግሎት ለህዝብ ለመስጠት ወሳኝነታቸው የጎላ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
በዞን ደረጃ የተቋቋመ ምክር ቤት በትግራይ ባይኖርም እንኳን በቀበሌ እና ወረዳ ደረጃ የነበሩ ምክር ቤቶች በፍጥነት ሥራቸውን እንዲጀምሩ እና አመራሮቻቸውን እንዲመረጡ እንደሚደረግ አመልክተው ፣ በሽሬ ከተማ በህዝብ የተመረጡ አባላትን የያዘ የጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል።
“ የመከላከያ ሠራዊት በሽሬ ከተማ የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ እና ደህንነት ሰላማዊ እንዲሆን ሲሠራ ቆይቷል” ያሉት ዶክተር ሙሉ፣ ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲጠናከር ህዝብ ራሱ የወከላቸው የጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች አስፈጻሚ አካላት እንዲመረጡ መደረጉን አመልክተዋል። አባላቱ በአገባቡ በተደራጀ የጸጥታ ማስከበር ኮሚቴ ውስጥ ሆነው የከተማዋን መረጋጋት አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ከፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
አምስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዳግም እንዲራዘምአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠየቁ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በኮቪድ 19 ምክንያት የተራዘመው አምስት ሀገራዊ ምርጫ ዳግም እንዲራዘም አንዳንድ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጠየቁ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ መርጫውን ዳግም ማራዘም የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት አንደሚካሄድ አስታወቀ።
«ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ» በሚል ርዕስ ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ውይይት በተካሄደበት ወቅት የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሰጡት አስተያየት፣ እስከአሁን በሀገሪቱ አምስት ምርጫዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ቢከናወኑም አንዳቸውም በህዝብ ዘንድ ተአማኒነትን አላገኙም። አሁን የምናካሂደው ምርጫ ተአማኒነት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ አሁን በሀገሪቱ ያለው አጠቃለይ ሁኔታ ምቹ አይደለም ብለዋል።
ምርጫው ይካሄድ ከተባለ መነሻ የሚሆነው ህገ መንግሥቱና የምርጫ ህጉ ነው ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፣ በእነዚህ ውስጥ ደግሞ በተለያዩ አካላት እየቀረቡ ያሉ ስጋቶች አሉ። ከእነዚህም መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ አስፈጻሚዎች ጉዳይን በተመለከተ መተማመን ላይ አልተደረሰም ብለዋል። በምርጫ ህጉ መሰረት አንድ ዕጩ እንዲሰበስብ የሚጠየቀው የድጋፍ ፊርማ ብዛትም ሌላው ጉዳይ ነው፤ አምስት መቶ አርባ ሰባቱንም ወንበር ለማሳተፍ የሚፈልግ ፓርቲ እንዲሰበደስብ የሚጠበቅበት ፊርማ በአስር ሚሊዮኖች ይሆናል፡፡ ይህ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን የማይደረስበትም እንዳልሆነ አመልክተዋል።
"ከዚህ በተጨማሪም የምርጫ ክልሎች አከፋፈል ጉዳይም ብዙ ጊዜ ሲያጋጭ የኖረና አሁንም ስጋት ያለበት ነው፤ በፊት አንድ ወረዳ የነበረ አሁን ሦስት የሆነ አለ፤ እንዲሁም በሁለት ክልሎች መካከል ያሉና የህዝብ ቆጠራ ጉዳይ የሚመለከታቸው ቦታዎችም ጉዳይ ያልተመለሰ ጥያቄ ነው። የምርጫ እንቅስቃሴ ወጪን በተመለከተም ያልጠራ ነገር አለ። በህገመንግሥቱ ላይም ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ፤ ያሸነፈም የተሸነፈም ተማምኖ እንዲቀጥልና ለሌላ ምርጫም መሰረት እንዲሆን እነዚህ ጉዳዮች በጥንቃቄ ሊታይ ስለሚገባው ስጋቶች እስኪቀረፉ ድረስ ምርጫው ሊዘገይ ይገባል" ብለዋል።
የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ተክሌ ቦረና በተመሳሳይ መልኩ፣ "አጠቃለይ በሀገሪቱ ያለው ሰላም አስተማማኝ አይደለም፣ ይሄ ደግሞ ነፃ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ ለማካሄድ አያስችልም። ሰዎች በየቦታው እየታሰሩና እየተንገላቱ ባሉበት ሁኔታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ህዝብ ቀርበው ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ምቹ ሁኔታ አይኖርም። በአጠቃለይም ምርጫ ቦርድ መራጩ ተመራጭና ሚድያው በተገቢው መንገድ በመንቀሳቀስ የሚጠበቅባቸውን መወጣት የሚችሉበት ሁኔታ የለም። በተጨማሪ በደቡብ ክልል በክልል አከላለል ረገድም የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ። በመሆኑም እነዚህ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ምርጫው ሊራዘም ይገባል "ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ (ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም) መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ይጀምራል።

ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
‹‹ ጁንታው በቁጥጥር ስር ካልዋለ ለትግራይ ክልልም ሆነ ለአገሪቱ ሰላም ስጋት መሆኑ አይቀርም ›› - አቶ ሚኪ ተስፋዬ የፈንቅል አስተባባሪ
******************************
( ኢ ፕ ድ)
መንግሥት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል የጁንታውን አባላት ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ማቅረብ እንደሚኖርበት የፈንቅል አስተባባሪ አመለከቱ። ይህን ማድረግ ካልተቻለ ቡድኑ ለትግራይ ክልልም ሆነ ለአገሪቱ ሰላም ስጋት መሆኑ እንደማይቀር አሳሰበ።
የፈንቅል አስተባባሪ አቶ ሚኪ ተስፋዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በማለት በተለያየ መንገድ አገሪቱን ለማፍረስ ሲሠራ የቆየው ጁንታው፤ በተለይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ በፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር የፌዴራል መንግሥት ተገዶ ህግ ወደማስከበር ገብቷል።
የህውሓት ጁንታው አገሪቱን እኔ ካልመራኋት አፈርሳታለሁ የሚል ዓላማ አንግቦ አገር የማተራመስ ሥራ ሲሠራ መንግሥት ሆደሰፊነቱን በልኩ አድረጎ ዕርምጃ ሊወስድ ይገባል በሚል ግፊት ሲያደርጉ እንደነበር አቶ ሚኪ ጠቁመው፤ ጁንታው የመንግሥትን ሆደ ሰፊነት እንደተሸናፊነት በመቁጠር ከ20 ዓመት በላይ ክልሉን ከጠላት ሲጠብቅ በነበረው በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር አሳፋሪ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥት ተገዶ በገባበት ህግን የማስከበር ዘመቻ የመከላከያ ሠራዊቱ የክልሉን ዋና ከተማ መቐለን ጨምሮ አብዛኛውን የክልሉን አካባቢዎች መቆጣጠሩን አመልክተው ፣ ይሁን እንጂ የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ለህግ አስካልቀረቡ ድረስ የሰላም ስጋት ሆኖ መቀጠሉ አይቀርም ብለዋል።
የጁንታው አባላት እጃቸውን አስካልሰጡ ወይም አስካልተወገዱ ድረስ በትግራይ ክልል ብሎም በአገሪቱ ሰላም ይመጣል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው ያሉት አስተባባሪው፤ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ሥራ ገብቶ የህብረተሰቡን የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄ ሊመልስ የሚችለው እንዲሁም በክልሉ ብሎም በአገሪቱ ሰላም የሚሰፍነው መንግሥት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ አጠናክሮ በማስቀጠል ጁንታውን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ሲያቀርብ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።
የማፊያው ቡድን በቁጥጥር ስር ውሎ በህግ ፊት አስኪቀርቡ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ ለአገር መከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፤ ጁንታው ሙሉ ለሙሉ በቁጥር ስር ባለመዋሉ በአንድ አካባቢዎች ሰርጎቦችን በማሰማራት ግጭት እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል።
በትግራይ ክልል የተለያዩ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የማንነት ወዘተ የመሳሰሉ ጥያቄዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ የፈለገ ጥያቄ ቢኖረው እንኳን የጁንታው ግብዓተ መሬት ከተፈጸመ በኋላ በቀላሉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ጥያቄዎቹ ስለሚፈቱ አሁን ላይ ጥያቄዎቹን ወደ ጎን ብሎ በአንድነት የጁንታውን ግብዓተ መሬት ማፋጠን እንደሚገባው አሳስበዋል።
ጁንታው በህብረሰቡ የሚነሱ የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎቹን ቀልብሶ ለጥፋት ሊያውል ፣ እንዲሁም ዕድሜው በተራዘመ ቁጥር አቅም እየፈጠረ የአገሪቱን የሰሜኑን ክፍል የግጭት ቀጠና ሊያደርግ ስለሚችል መንግሥት እየወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር ዕርምጃ ይደር ሳይል አጠናክሮ በመቀጠል ጁንታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፍርድ ማቅረብ እንዳለበት አሳስበዋል።
ሶሎሞን በየነ
‹በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ሁሌም ያሸንፋል›› - ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ
************************
( ኢ ፕ ድ)
በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በጦረነት እውቀትና በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ያለው ኢትዮጵያዊነት የገባው ወታደር ሁልጊዜም የድል ባለቤት መሆኑን ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ አስታወቁ።
ብርጋዴር ጀኔራሉ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት፣ የህውሓት ጁንታ ቀደም ሲል ከ15 ዓመታት በላይ ሲዋጉ ጠንካራ የሚገዳደራቸው ወታደር ነበር፤ አሁንም ለሀገሩ የሚዋጋ ጠንካራ አቅም ያለው የመከላከያ ሠራዊታችን የቀደመ ታሪካቸውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል።
ድሮም ምንም አቅም ምንም እውቀት ኖራቸው አያውቅም ነበር ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ከሳዬ፣ ባዶ ውሸትና ትምክህት ብቻ በሞላው ልባቸው ወደጦርነት በመግባታቸው የሽንፈትን ፅዋ ለመጨለጥ ተገደዋል ብለዋል። ድሮም ወደ ስልጣን መምጣት የቻሉት የተዋጊነት አቅም ኖሯቸው ሳይሆን በደርግ መንግሥት ስህተትና ድክመት ህዝቡ መሰላቸት እና የሀያላን ሀገር ጣልቃ ገብነት በመጨመሩ እንደነበር ጠቁመዋል።
በህውሓት ጁንታ አሁን በጠላትነት የተፈረጀው የኢትዮጵያ ህዝብ እያበላ፥ እያጠጣ፥ መንገድ እየመራ ደጀን መሆን ደግፎ ወደስልጣን አወጣው እንጂ በፊትም ወታደራዊ ብቃት እንዳልነበራቸው አስታውቀዋል። ለዚህ ውለታው ህዝቡን በዘር በመከፋፈል ከማጫረስ በስተቀር ምንም ሳይጠቅሙት መኖራቸውን ገልጸዋል።
የህዝብ ዕንባ የመከላከያ ሠራዊቱ ጥንካሬ ከዚህ ቡድን ነፃ ስላወጣን ምስጋና ሊቸረው ይገባል ብለዋል።
በባዶ ጉራ ሙሉ የመከላከያ ሠራዊቱን በቁጥጥራቸው ስር አውለው፤ በጦር መሳሪያና በሹመት ብዛት የሚያሸንፉ መስሏቸው ሲፎክሩ ቆዩ እንጅ ወታደራዊ ብቃት ያለነበራቸው ቡድኖች መሆናቸውን መከላከያ ሠራዊታችን በገልፅ አሳይቷል ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ፣ ለሁሉም ደባና ተንኮል የሚያስከፈለውን ዋጋ በአግባቡ ለመመልከት እንደቻሉ ጠቁመዋል።
የተዋጊያቸውን አቅም ያላገናዘቡት እነዚህ ተንኳሽ ቡድኖች ዘመኑ የቴክኖሎጂ መሆኑን ሳያስተውሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈው ጦር ሠራዊታችን ባሳየው የኃይልና የእውቀት ብልጫ ትምክህተኛውን ለማሸነፍ መቻሉ የሚያኮራ ይበል የሚባል ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን የሚያከብር ህዝብ መሆኑን እዚህ በተገኘሁበት ወቅት ተመልክቻለሁ የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ፣ እንግዳ የሚቀበል ሰው አክባሪ የሆነ ጠንከራ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገርን እኛ ካላስተዳደርን ይፍረስ ብሎ መዝለል ተገቢ እንዳልሆነም ጠቁመዋል።
ከአንድ መቶ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያለባት ሀገር ሁሉም ህዝብ ወንበር መያዝ ቢፈልግ የማይችል መሆኑን አስረድቶ ሁሉም በያለበት ሀገርን የማሳደግ ኃላፊነትን ከመወጣት ባለፈ የግድ ልምራ ማለት ፍትሐዊ ያልሆነ ጥያቄ እንደሆነ ገልጸዋል።
የትግራይ ህዝብ ከዚህ በፊትም ታፍኖ የኖረ አሁንም ታፍኖ ነው ያለው ህዝቡ ፤ ህዝቡ በስሙ ተነገደበት እንጂ ምንም ያልተሠራለት ዛሬም ይህ ህዝብ የተራበ የተጠማ እንደሆነ አመልክተዋል። ልጆቹ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ናቸው። የህውሓት ጁንታ ለፕሮፖጋንዳ የሚያሳዩትን ያህል ሳይሆን በጥልቀት ሲታይ በችግር እንዲኖር ያደረጉት ይህን የተጎዳ ህዝብ በመካስ ይህን ጨዋ ህዝብ ወደ እውነተኛ ማንነቱ መመለስ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ይጠበቃል ብለዋል።
አስመረት ብስራት
የወታደሮቹ ሚስቶች የስቃይ ትውስታ
*********************
( ኢ ፕ ድ)
እምባባ ታረቀኝና ባለቤቷ የተዋወቁት እንደሃዋርያት በሚባል ቦታ ነው የተዋወቁት። እርሷ የወታደሮች ምግብ አብሳይ ሆና፤ ባለቤቷ ደግሞ በሰሜን እዝ መከላካያ ሠራዊት ውስጥ ዳር ድንበርን የመጠበቅ ተልእኮውን በመፈጸም ላይ በነበረበት ወቅት።
እምባባ የትግራይ ተወላጅ ስትሆን ባለቤቷ ደግሞ የኦሮሞ ተወላጅ ነው። ከቋንቋ ልዩነቱ በላይ ኢትዮጵያዊነት አስተሳስሯቸው ትወደዋለች፤ ይወዳታል። ትዳር መስርተው መኖር ከጀመሩም ጥቂት ዓመታትን አሳልፈዋል።
አሁን የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር መሆኗን ነግራናለች። በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መከፈቱን ተከትሎ እምባባ ያሳለፈችው ፈተና ብዙ ነው። ‹‹ ሠራዊቱ ላይ በድንገት ጥቃት ሲፈጸም እኔና ባለቤቴ አብረን አልነበርንም፣ አርሱ ምሽግ ውስጥ ነበር፤ አኔ ደግሞ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ ነኝ፤ ምሽግ አካባቢ የነበሩ ወታደሮች በራሳቸው ወገን በድንገት የተከፈተባቸውን ጥቃት እየተከላከሉ ወደ ኤርትራ መሻገራቸውን ሰማሁ። እኔም የባለቤቴን ዱካ ተከትዬ መጓዝ ጀመርኩኝ ፤ ብዙ ካፈላለኩ በኋላ በህይወት መኖሩን ሳረጋግጥ ተረጋጋሁ። በኋላም ባለቤቴ በሌላ ግንባር ከሠራዊቱ ጋር ተደራጅቶ ህግ ወደ ማስከበር ሥራ መግባቱን ስሰማ ወዳለበት ግንባር ሄድኩኝ።
ከሠራዊቱ ኋላ ኋላ እየከተልኩና በሚያስለቅቋቸው ከተሞች እያረፍኩ ሠራዊቱን እየተከተልኩ መጓዜን ቀጠልኩ። በእግርና በተሽከርካሪ አድካሚ ጉዞ እየተጓዝኩ ባለቤቴ ከፊት እኔ ከኋላ ሆነን መቀሌ መግባት ቻልን ትላለች።
መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ህዝብ በማህበራዊ ህይወት የተሳሰሩ ናቸው የምትለው እምባባ፣ ከዚያም አልፎ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ልክ እንደእርሷው ሁሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የሠራዊቱን አባላት አግብተው መውለዳቸው፣ ይህም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በደም እንድንተሳሰር ያደረገ መልካም አጋጣሚ ነው ትላለች።
በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በጣም እንዳሳዘናት እና ድርጊቱ የትግራይን ህዝብ የማይወክል፣ በጥቃቱ የትግራይ ተወላጆችም ተጎጂ መሆናቸውን የእርሷ ህይወት በቂ ምስክር እንደሚሆንም ገልጻለች። ባለቤቷን ለመግደል የመጣ አካል የእርሷም ገዳይ እንጂ ወዳጅ አለመሆኑን እማባባ ትናገራለች።
አበባ በየነ የአክሱም አካባቢ ተወላጅ ነች። አበባ የአማራ ተወላጅ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት አባል አግብታ እንደምትኖር ትናገራለች። ከባለቤቷ ጋር የስድስት ዓመት ቆይታ አላት፤ አንድ ልጅም አፍርተዋል።
ባለቤቷ አዲግራት አካባቢ ሲኖር እርሷ ደግሞ እንደሃዋሪያት አካባቢ ልጇን እያሳደገች ትኖራለች። በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የባለቤቷ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቷት ነበር። የባለቤቷ ነገር ሰላምና እረፍት ሲነሳት ልጇን ይዛ በኤርትራ አቆራርጣ ጾረና ከወታደሮች ምሽግ አቅራቢያ ትደርሳለች። የባሏ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ያላወቀችው ይቺ የወታደር ሚስት ባሏን በህይወት ስታገኘው የነበራት ደስታ በቋንቋ ለመግለጽ እንደሚከብዳት ስትናገር ያ ስሜት አሁንም ከውስጧ እንዳልጠፋ ያሳብቅባታል።
ባሏን በህይወት ካገኘችው በኋላ እርሱ ህግ ወደ ማስከበር ሥራው ገባ፤ እርሷም የእርሱን ዱካ እየተከተለች ተያይዘው መቀሌ መግባታቸውን ትገልጻለች። ባሌን ሊገድል የመጣ የእኔ ወዳጅም ተቆርቋሪም ሊሆን እይችልም ትላለች።
የትግራይ ነፃ አውጪ ነን እያሉ ወንጀል የሚሠሩ አካላት ትግራይን አይወክሉም። የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር እሴቱን ጠብቆ በፍቅር የሚኖር ማህበረሰብ ነው የምትለው አበባ፣ ባልን ከሚስቱና ከልጆቹ እየለዩና እየገደሉ በትግራይ ህዝብ ስም መነገድ ተገቢ አይደለም፤ተቀባይነት የለውም ትላለች።
ወታደር የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ነው፤ እኔም እንደባለቤቴ ኢትዮጵያዊነትን የማስቀድም የወታደር ሚስት ነኝ። ምንም ባልጠረጠሩበት ሁኔታ ድንገተኛ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ማየቴ እጅግ አስከፍቶኛል፤ በጣም አዝኛለሁ። መንግሥት ህግን ለማስከበር ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑ ደግሞ አስደስቶኛል። አጥፊዎችና ነፍሰ ገዳዮች ለህግ መቅረብ ይኖርባቸዋልም ትላለች።
በእያሱ መሰለ
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጀግናው የአገር የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ሰልፍ አካሄዱ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጀግናው የአገር የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ዝግጅት አካሂደዋል።
አይበገሬው የመከላከያ ሰራዊታችን በከሃዲውና ጽንፈኛው የህዎሓት ቡድን የተቃጣበትን ጥቃት መክቶ በፍጥነት አገራችን ወደ ድል ብስራት በማሸጋገሩ ያላቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ለዚህ የአገር መከታ መከላከያ ሃይል ድጋፍ ለማድረግና በጽንፈኛው ህወሓት ርጥባን ተከፋዮች የሚነዛውን የሃሳት ፕሮፖጋንዳ ለማክሸፍ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።
ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስተባባሪነት የተካሄደ ነው።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሰላም አምባሳደሮች ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ
****************************
( ኢ ፕ ድ)
በየዓመቱ ህዳር 29 ይከበር የነበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሰላምና አንድነትን በሚሰብኩ የሰላም አምባሳደሮች ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ። በጭፈራ ብቻ ሲከበር የቆየው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሰላምና አንድነትን ሊያመጣ በሚችል መንገድ መከበር እንደሚኖርበት ተጠቆመ ።
ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር በዓሉን አስመልክተው ከትናንትበስቲያ በሰጡት መግለጫ ፣ የኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት የሁነቶች አደራጅ አቶ ቢኒያም ፈቃዱ እንደገለጹት፤ በዚህ ዓመት በሚከበረው 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ‹‹ቆንጂት አንድነት›› የተሰኘ የቁንጅና ውድድር ይካሄዳል።
ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ሦስት ሦስት ቆነጃጅት ተወዳድረው አሸናፊዎች በየክልላቸው የሰላም አምባሳደር ይሆናሉ ብለዋል። የሚመረጡት የሰላም አምባሳደሮች ሰላምና አንድነትን በመስበክ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎችን ይሠራሉ።
የማጠቃለያ ዝግጅቱም የፊታችን ዕሁድ ህዳር 27 ቀን በሸገር ፓርክ እንደሚካሄድ ጠቁመው፣ የሚመረጡት ቆነጃጅት የመጡባቸውን አካባቢዎችና የወከሏቸውን ብሄሮች ባህልና ትውፊት እንደሚያስተዋውቁ አስታውቀዋል።
በአምባሳደርነታቸውም እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ በየአካባቢያቸው ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በሰላም ዙሪያ ይሠራሉ። ይህም በአገሪቱ ሲሸረሸር የቆየውን ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲስተካከል ይረዳል ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=36686
‹‹ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ ድባቡ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚመጣበት ነው›› - ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም
አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ ድባቡ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚመጣበት ፍልስፍናን የያዘ እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ።
ዘርፎም ሆነ በኮንትሮባንድ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን ጁንታ በ25 ቀናት ውስጥ የዛሬ 47 ዓመት ወደነበረበት ዋሻ ተመልሶ እንዲገባ መደረጉን አስታወቁ።
ዶክተር ቢቂላ በተለይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ መከላከያ ሠራዊት የዓይኑ ብሌን በሆነች በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር ነው።
በግራም ይሁን በቀኝ ዘርፎም ሆነ በኮንትሮባድ አግበስብሶ እስከአፍንጫው የታጠቀውን የጁንታውን ቡድን በ25 ቀን ውስጥ የዛሬ 47 ዓመት ከነበረበት ዋሻ ውስጥ መልሶ ከቶታል።
ይህም የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ጥንካሬና ጀግንነት ነው፤ይህ ጀግንነት ደግሞ ህዝቡም ውስጥ ያለ እና የኖረ እንደሆነ የጠቆሙት ኃላፊው፣ የህዝቡ ጀግንነት መከላከያ ሠራዊታችን ውስጥ በተግባር የተረጋገጠ መሆኑንም አመልክተዋል። እንደ ዶክተር ቢቂላ ገለጻ፤ ይህ መሰሪና አጥፊ ቡድን የዛሬ 47 ዓመት አካባቢ ዋሻ ውስጥ ነበር፤ በአሁኑ ሰዓትም 47 ዓመታት ወደኋላ ተንፏቆ ቀድሞ በነበረበት ዋሻ ውስጥ ይገኛል። ይሁንና ከዚያ አፈር ውስጥ ተለቅሞ ይወጣል። ወደነበረበት ጉድጓድ እንዲገባ ያደረገው የኢትዮጵያውያን አንድነት ምልክት የሆነው መከላከያ ሠራዊት ሲሆን፣ የህዝቡም ጥምረት ውጤት ነው። ጁንታው በተንኮልና ክፋት የተወረሰ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ተንኮልና ክፋት ደግሞ የፈለገውን ያህል አንገቱን ቀና ቢያደርግ አንድ ቀን ተንኮሉና ክፋቱ ራሱን መልሶ መብላቱ አይቅርም ብለዋል። ስለዚህ መነሻ የምናደርው እውነት ሁልጊዜ ታሸንፋለች፤ ተንኮልና ክፋት ሁልጊዜ ይሸነፋል የሚለውን ነው ብለዋል። ሁሌም የአሸናፊነት ምስጢር እውነት እንደሆነችም አስታውቀዋል። ከዚህ ከእውነት ጋር የታገለ ማንኛውም ኃይል እንደሚወድቅ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁልጊዜ የሚቆመው ከእውነትና ከሐቅ ጋር መሆኑን ጠቅሰው፤ ትልቁ አቅምና ጉልበት የነበረው ይኸው እንደሆነ አመልክተዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል ተንኮለኛው ቡድን መቀሌ ሲኮለኮል፤ ኢትዮጵያውያኑ ደግሞ አንድ ወደሚያደርጋቸው ነገር ሲሳቡ ቆይተዋል። በመጨረሻ ግን ቡድኑ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፤ የአገራዊ አንድነት ምልክት በሆነው ላይ እና ኢትዮጵያውያን እንደ ዓይናቸው ብሌን በሚያይዋት ኢትዮጵያ ላይ እጁን በማንሳቱ እውነት መነካቱን አስታውቀዋል። መከላከያ ሠራዊቱም ጥቃትን መቋቋም ስላልሆነለት የኢትዮጵያዊነትን ልክ ማሳየት ችሏል ብለዋል። እንዲህ ዓይነት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊትም ትልልቅ አገራዊ ፈተናዎች ቢከሰቱ እንኳ ያልቃታል እንጂ አገሩን እንደማያስደፍር ማረጋገጡን አስረድተዋል። ከኋላው ያለው 115 ሚሊዮኑም ህዝብ የኢትዮጵያን መጠቃት ከመቃወም በተጨማሪ በሁለንተናው ድጋፍ እንዳበረከተ አመልክተዋል። ስለዚህ የፖለቲካው ድባብ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነትን እናመጣለን የሚል ፍልስፍና ነው የያዘነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ፖለቲካው በግራም በቀኝም ማጠንጠኛው ይህ ነው ብለዋል። ስለዚህ ይህ የጁንታው ቡድን ሲነቀል የፖለቲካ ድባቡ ከዘር ነጋዴነት እየተላቀቀ ይመጣል ሲሉም አብራርተዋል። ኃላፊው እንደተናገሩት፤ ብዝሃነትን ማቀፍና የዘር ነጋዴ መሆን ይለያያል። ቡድኑ ባለፉት 27 ዓመታት ብዝሃነትን የሚያቅፍ ሳይሆን የዘር ነጋዴ ነበር። ጁንታው የብሄር ነጋዴ ነው። በየቦታውም ሄዶ ግጭትን ሲያነሳ ሰንብቷል። ከዚህ በኋላ የብሄር ንግድ አክሳሪ ነው የሚሆነው፤ ነጋዴዎችም ከስረው ከገበያ ይወጣሉ። ብዝሃነትን ያቀፈ፣ ኢትዮጵያን የሚመስል፣ ሁሉንም ቋንቋም ሆነ ማንነት ወደመሃል ያመጣ፣ የሚያቅፍና የሚያሳትፍ፣ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ግን የማይደራደር ኢትዮጵያዊ አንድነት ይገነባል ብለዋል። ስለዚህ ቀስ በቀስ ከአክሳሪው፣ ከመሰሪውና ከተንኮለኛው የብሄር ንግድ እየተወጣ ወደ ብዝሃነትን ወደአቀፈች ጠንካራ ኢትዮጵያ ይመጣል ብለዋል። ፖለቲካ እየተቃኘ ያለው ወደዚህ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
በአስቴር ኢሊያስ
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት በጥገና እና በካሣ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር የትራንስፖርት አገልግሎት እና መሠረተ ልማት ደህንነት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በባቡር መስመር ላይ እያጋጠሙ ካሉ ተግዳሮቶች መካከል በመሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆት፣ ውድመት እና የባቡር አደጋዎች ተከትሎ የሚያጋጥሙ የባቡር እገታዎች እንደሚጠቀሱ የትራንስፖርት ሚንስትር ዴኤታ አወል ወግሪስ ተናግረዋል።
ባለፉት 3 ዓመታት 163 ጊዜያት ያህል ባቡሮች የታገቱ ሲሆን፣ በእገታዎቹ ከ652 በላይ ሰዓታት ባቡሮቹ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉን ተገልጿል።
በ875 እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን፣ 961 ጊዜ ስርቆት እና የንብረት ውድመት ማጋጠሙን፣ የ27 ሰዎች ሞት እና የ11 ሰዎች የአካል ጉዳት መመዝገቡን አቶ አወል ተናግረዋል።
በባቡር እገታ ምክንያት ለጥገና እና ለካሣ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና የደህንነት ባለሞያ ኢ/ር ጥበቡ ተረፈ ገልጸዋል።
በስርቆት እና በውድመት ብቻ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን ኢ/ር ጥበቡ ጠቁመዋል ሲል ዚቢሲ ዘግቧል።
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት የባቡር መሠረተ ልማቱንና አገልግሎቱን ደህንነት ለማስጠበቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ሚኒስትር ዴኤታ አወል ወግሪስ ጠይቀዋል።
‹‹ሰዎችን በጅምላ መግደል ሃይማኖታዊ ተጠያቂነቱ ከፍ ያለ ነው›› ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
************************
( ኢ ፕ ድ)
ሰዎችን በብሄራቸው ወይም በሃይማኖታቸው ምክንያት በጅምላ መግደል የኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ካለመሆኑም በላይ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸህ ሱልጣን አማን አስታወቁ።
ሸህ ሱልጣን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሰላም በእስልምና ከፍተኛ ቦታ አለው። የሃይማኖት ሰዎች ሲገናኙ ‹‹አሰላም አለይኩም›› ወይም ሰላም ለአንተ ይሁን የሚል ሰላምታ ተለዋውጠው ነው ወደቀሪ ጉዳያቸው የሚገቡት። ይህ ከሰላም በፊት የሚቀድም ጉዳይ እንደሌለ የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር ሰላም ከሌለ ሀገር የለም፤ ልማት የለም፤ በአግባቡ አምልኮንም ማከናወን አይቻልም የሚልም መልዕክት አለው።
“ነፍስን ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። አንድን ነፍስ ማጥፋት ዓለምን እንደማጥፋት ነው። እንኳን የሰው ነፍስን ቀርቶ ያለ አግባብ የነፍሳትን ነፍስ ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። ይሁን እንጂ አሁን በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ሰዎችን በጅምላ የመግደል ተግባሮች እንደሃይማኖት አባት በጣም የሚወገዝ ነው” ብለዋል።
‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ተባብረን፤ ተቃቅፈን ፤ ተዋደን ብሄርና ሃይማኖት ሳይለየን በሰላም ስንኖር የቆየን ህዝቦች ነን። አሁን ግን በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎችን እያየን ነው ያሉት ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን፣ ይህ ከኢትዮጵያውያን አማኝነትና ባህልና እሴት አንጻር በጣም የሚያሳፍርና እኛን የማይገልጽ እንደሆነ አመልክተዋል።
ፖለቲከኞች ሃይማኖትንና ብሄርን ሽፋን አድርገው በሳለም ለዘመናት የኖረውን ህዝብ ሲያባሉትና ሲያጫርሱት እየተመለከትን ነው›› ያሉት ፕሬዝደንቱ ፣ በየቦታው የሚታዩ ግጭቶችና ግድያዎች መንስኤያቸው ከሃይማኖትና ብሄር ይልቅ ፖለቲካ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሸህ ሱልጣን እንደሚሉት ፖለቲከኞች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም ሲሉ አንድን ብሄር ከሌላው ጋር ወይም ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር እያጋጩ የሚፈጽሙት ድርጊት እንጂ ኢትዮጵያውያን እንደዚህ አይነት ታሪክም ሆነ ስነልቦና የላቸውም።
https://www.press.et/Ama/?p=36736