Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ
********
(ኢ.ፕ.ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ብራሰልስ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል።

ኮሚሽነሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለህብረቱ ስትራቴጂያዊ አጋር ሃገር መሆንዋን የጠቀሱት፤ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ንፁሃን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥበት መንገድ ለማመቻቸት በመንግሥት የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

አቶ ደመቀ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአለምአቀፍ የሰብዓዊ ህግ ተፈፃሚ ለማድረግ ነባራዊ ሁኔታውን በማጥናት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የሚደረግበትን አግባብ አስረድተዋል።

ንፁሃን ዜጎች ለከፋ ቀውስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሲል የምክትል ጠቅላይ ሚኒ
አዛውንቱ ሚሊሻ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

- በምጸልይበትና በማስታርቅበት እድሜዬ ውጊያ ላይ
መገኘቴ ያሳዝነኛል፤

- የአስም በሽተኛ ሆኜ፤ የልብ ቀዶ ህክምናም አድርጌ ወደ
ውጊያው ተልኬያለሁ፤

- የጡረታ ደመወዜን ይዘው ሲያስፈራሩኝ ለዘመቻ ወጣሁ

አቶ መብራቱ ታደለ የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው፤ ስድስት ሴት ልጆችን ወልደው ስመዋል። የልጅ ልጆችን አፍርተውም አያት ሆነዋል።

አዛውንቱ የአስም ህመምተኛ ናቸው። የጤናቸው እክል አስም ብቻ እንዳልሆነና በቅርቡም የልብ ቀዶ ጥገና ማድረጋቸውን ይናገራሉ።

አረጋዊነታቸው የጤና እክላቸውና አቅመ ደካማነታቸው ከህወሓት ጁንታዎች ዓይን አላዳናቸውም። ይህ ዘራፊ ቡድን በዝርፊያና በአፈና ለኖረበት ስልጣኑ ማራዘሚያ ይሆኑ ዘንድ ሚሊሻ በሚል ስም አስታጥቆ መከላከያ ሰራዊትን ይወጉ ዘንድ ላካቸው።

‹‹ይህ ዘመኔ ውጊያ የማደርግበት ሳይሆን የምጸልይበትና የማስታርቅበት ነበር፤ በዚህ እድሜዬ በማይጠበቅ ቦታ መገኜቴ ይጸጽተኛል ይላሉ” አቶ መብራቱ።

የሚሊሻ አባል የሆኑት ፈልገው ሳይሆን ታጥቀው ካልተዋጉ የሚከፈላቸው የጡረታ ደሞዝ እንደሚቆምባቸው በጁንታው ማስፈራሪያ ስለተሰጣቸው እንደሆነ ይናገራሉ።

“ደመወዜን አታገኝም በመባሌ ነው ወደ ሚሊሻው የተቀላቀልኩት። ልክ እንደእኔው ሁሉ መሳሪያ የያዙ በሙሉ እንዲዋጉ ተገድደዋል›› ይላሉ አቶ በሪሁን፡፡

ለጥበቃ ስራ የተሰጣቸውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ለጁንታው ታጣቂዎች ሰጥተው እርሳቸው ሚንቶፍ ይዘው እንዲዋጉ መደረጋቸውን አዛውንቱ ይናገራሉ፡፡ የመዋጋት ፍላጎትም አቅምም የለኝም ያሉት እኚህ አዛውንት፤ ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ከመሰሎቻቸው ጋር ጠፍተው እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊት ሰጥተዋል፡፡

ቀሪ እድሜያቸውን ለልጆቻቸው፣ ለልጅ ልጆቻቸው እና ለአገራቸው በጸሎት ማሳለፍ የሚመኙት አዛውንቱ አቶ በሪሁንም ለትግራይ ታጣቂዎችና ሚሊሻ አባላት መልዕክት አላቸው፤ “እንደ አባት የምነገርችሁ የመንግስትን ጥሪ አዳምጡ በሰላማዊ መንገድ እጃችሁን ስጡ ዓላማ የሌለው ሞት አትሙቱ”።
በእያሱ መሰለ
የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ለሕወሓት ወንጀለኛ ቡድን የተሰጠው በሰላም እጅ የመስጫ የ72 ሰአት ጊዜ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።
በዚህም ሕግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሩን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።
በተሰጠው የ72 ሰአታት ጊዜም በሺዎች የሚቆጠሩ የወንጀለኛው ቡድን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት መስጠታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
ኮሚሽኑ የቡድኑ እኩይ ዕቅድ መረጃ እንደደረሰውም አስታውቋል፡፡
መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑትን ሰዎች ማረድ ፣ አንገታቸውን በገመድ ማነቅ ፣ ንብረታቸውን መዝረፍ እና ማቃጠል፣ የመከላከያ ሠራዊታችንን የደንብ ልብስ በመልበስ ሰዎች ላይ በድንገት ተኩስ በመክፈት ሰሞኑን በማይካድራ የፈፀመውን ብሄርን መሰረት ያደረገ አስነዋሪ፣ አሳፋሪና አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለመድገም እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ይህንን እኩይ ተግባር ከፈፀመ በኋላም ድርጊቱ የተፈፀመው በመንግስት ነው ብሎ በሚዲያ ለማሰራጨት የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ መረጃ ደርሶኛል ነው ያለው ኮሚሽኑ።
በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ይህንን የጥፋት ሴራ ተከትሎ ጁንታው ቡድን ሊያሰራጭ የተዘጋጀውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳና ይህንን እኩይ ተግባር አስቀድሞ እንዲረዳና ተቀባይነት ያጣ ዘንድ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ማሳሰብ እንወዳለን ሲል ጥሪ አቅርቧል።
“በጁንታው ላይ የሚወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለመላው ኢትዮጵያ ሰላም መሰረት ነው”
– አቶ ደረጀ በቀለ የፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር
*******************
(ኢ ፕ ድ)
መቀሌ የመሸገው ጁንታ መወገድ ለመላው ኢትዮጵያ በተለይም ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ልማት መረጋጋጥ መሰረት እንደሚሆን የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሊቀ መንበር አቶ ደረጀ በቀለ ገለጹ።
ሊቀመንበሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት ወንጀለኛው ቡድን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ሲሰራ የነበረው ለኢትዮጵያም ሆነ ለትግራይ ህዝብ በማሰብ ሳይሆን የስልጣን ጥሙን ለማርካትና ሀብት ለማጋበስ ነበር። በዚህም ባለፉት 30 ዓመታት የትግራይን ህዝብ መደበቂያ አድርገው በርካታ ወንጀሎችን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ግን ከጁንታው ቡድን ያገኘው ጥቅም አልነበረም።
ከሁሉም በላይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ቆመንለታል የሚሉት ህዝብ የሚገለገልባቸውን መሰረተ ልማቶች ማውደም መጀመራቸው ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚያሳይ ነው።
በቅርቡ በማይካድራና በተለያዩ ሌሎች አካባቢዎች ለፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀልና ላወደሙት ንብረትም በተገቢው መንገድ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።
በተጨማሪ ራሳቸው የፈጠሩትን ችግር ወደሌሎች በማላከክ የትግራይ ህዝብን ወንድሞቹ ከሆኑት ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ለማጋጨትም እየሠሩ ይገኛሉ። የእነዚህ አካላት ፍፃሜ ማግኘት መላውን ኢትዮጵያ በተለይም የትግራይን ህዝብ ሰላም የሚያረጋግጥና ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር የሚያስችለው ነው። በመሆኑም የትግራይ ህዝብም ሆነ ቀሪው ኢትዮጵያዊ መንግሥት እየሠራ ያለውን ሰላም የማስጠበቅና ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በሙሉ አቅሙ ሊደግፈው ይገባል።
https://www.press.et/Ama/?p=42478
በአዲስ አበባ ከተማ ያለ ደረሰኝ ሲሸጡ የተገኙ ከ22 በላይ ድርጅቶች በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል ከ22 በላይ ድርጅቶች ያለደረሰኝ ሲሸጡ በመገኘታቸው በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንደገለጹት፤ በከተማዋ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተሰርቷል።
በዚህም ከ22 በላይ ድርጅቶች ያለደረሰኝ ሲሸጡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፖሊስ ልብስ በመልበስና የገቢዎች ቢሮ ሀሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ጠቁመዋል።
በከተማዋ የግብር ህግን አክብረው በማይሰሩ ነጋዴዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ግብር ከፉዩ የወጣውን የግብር ህግ አክብሮ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
ህብረተሰቡም የወጣውን የግብር ህግ አክብረው የማይሰሩ አጭበርባሪዎች ሲያጋጥሙት በ7075 ነጻ የስልክ መስመር እንዲጠቁም አቶ ሙሉጌታ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክረታሪያት አስተውቋል።
“መከላከያ ሕዝባዊ ማንነትን የተሸከመ፣ መቆምም መኖርም የሚችለው ከሕዝብ ጋር የሆነ ሠራዊት ነው”
-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከዳር ወጥተው ያወገዙት መከላከያ ህዝባዊ ማንነትን የተሸከመ፣ መቆምም መኖርም የሚችለው በህዝብ በመሆኑ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ አስታወቁ። የአራዳ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ አካላት የሰበሰበውን ከ70 ሚሊዬን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ አካላት የሰበሰበውን ከ70 ሚሊዬን ብር በላይ ድጋፍ ትናንት ባስረከበበት ወቅት ወይዘሮ አዳነች እንዳመለከቱት፣ መከላከያ ህዝባዊ ብቻ ሳይሆን ሞራሉም ስንቁም ህዝብ የሆነ ነው። መቆሙም መኖሩም ህዝብ እንደሆነ የሚያስብም ነው። ስለዚህም እንደ አዲስ አበባ ከተማ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ከማድነቅና ከማመስገን ጎን ለጎን ጁንታው ከጥፋቱ የሚታረምበትን መቀየስ ላይ መሥራት ይገባል።
ይህ አስነዋሪና የከሃዲነት ተግባር በመረዳዳትና ወደ ነበርንበት ወንድማማችነት በመመለስ ካልተገታ በምንም አይከሽፍም ያሉት ወይዘሮዋ፣ ይህንን መልካም እሴት ማብዛት ላይ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።
አፀያፊው ተግባር ሲፈፀም ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከዳር ያወገዙት ያለምክንያት እንዳልነበር የጠቀሱት ምክትል ከንቲበዋ፤ መከላከያ ህዝባዊ ማንነትን የተሸከመ፤ መቆምም መኖርም የሚችለው በህዝብ የሆነ ነው።
የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ ብሎ ህዝቡን ተጋላጭ እያደረገ ራሱን ብቻ እየጠበቀ የሚንቀሳቀሰውን ጁንታ በከተማ ያላችሁ የትግራይ ተወላጆች ጭምር እያወገዛችሁና በሃሳብ ሳትሰረቁ ሕግ የማስከበሩን ተግባር እንድትደግፉ ሲሉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊ መሆናችን የሚያቃቅረን ሳይሆን ውበትና ድምቀታችን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ማሳየት የምንችልበት ነው ወይዘሮ አዳነች፤ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ጠል የሆነው ጁንታ ቡድን ይህ እንዳይሆን ለፍቷል፤ ሠርቷል።
ነገር ግን ማህበረሰባችን ከልቡ የታተመ በመሆኑ በዚህ ተግባሩ ሳይረበሽ አሁንም በድጋፉ ከተቸገሩና ከሕግ ማስከበሩ ጎን መቆሙን ማሳየት እንዳለበትም ተናግረዋል። የአራዳ ክፍለ ከተማ ያደረገውን ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ትልቅ ስንቅና ከአገርም ሆነ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዳለ የሚያሳይ መሆኑንም ገልፀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=42469
የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ለመከላከያ ድጋፍ አደረጉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀብት ማሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የልማት ተቋማት፣ ነጋዴዎች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ለመከላከያ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ከተለገሰው ገንዘብ ውስጥ ከ7 መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በከተማው ከሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች የተሰበሰበ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ሺሰማ፣ 4 መቶ 30 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ ከልማት ተቋማት፣ ነጋዴዎች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተገኘ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የገቢ ማሰባሰቡን ሥራ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሣቸው ፍቃድ መጀመራቸውን ያስታወቁት አቶ ሺሰማ፣ የመንግሥት አመራሮች ለድጋፉ የመጡ አካላትን ከማስተባበር ያለፈ ሥራ እንዳልነበራቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ለአመራሩ ሥራውን እንዳቀለለት አመልክተዋል፡፡
የህዝቡ ድጋፍ ዘርፈ ብዙ ነው የሚሉት አቶ ሺሰማ፤ ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ወደ 8 ሺ ዩኒት የደም ልገሳ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በፈቃደኝነት ግንባር ድረስ በመሄድ ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
እየተደረገ ያለውን የሕግ ማስከበር ሥራ በታሰበለት ልክ እንዲሄድ የህዝቡ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ሰብሳቢው፣ ህዝቡ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ከፀጥታ አካላቱ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች 66 ሚሊዮን 361 ሺህ 380 በላይ ገንዘብ እና 4 ሺ 6 መቶ 57 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሠራዊቱ መለገሳቸውን ገልፀዋል ፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=42470
“21ኛ ክፍለ ጦር የተሰጠውን ተልዕኮ በስኬት እየተወጣ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ ነው”
– ኮሎኔል መኳንንት ሲሳይ የ21ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
21ኛ ክፍለ ጦር የተሰጠውን ሕግ የማስከበር ተልዕኮ በስኬት እየተወጣ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮለኔል መኳንንት ሲሳይ አስታወቁ፡፡
ኮሎኔሉ ትናንት በአካባቢው ለሚገኘው የጋዜጠኖች ቡድን እንዳስታወቁት፣ 21ኛ ክፍለ ጦር የአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች የተመኩባቸውን ሦስት ወሳኝ ምሽጎች ደረማምሶ፤ ከባድ መሣሪያዎችን አውድሞ እግር በእግር እየተከተለ በጁንታው ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብኣዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል፡፡
የጁንታው ታጣቂዎች የ21ኛው ክፍለ ጦርን የጀግንነት ገድል የሚያውቁ በመሆኑ እፊቱ ቆመው አይዋጉም ያሉት ኮሎኔሉ፣ ጁንታው በአሁኑ ወቅት ከእጁ እየወጡ ለመከላከያ ሠራዊቱ እጃቸውን የሚሰጡ ታጣቂዎች ቁጥር ዕለት ተዕለት እየጨመረ በመምጣቱ የታጣቂዎቹን የተሸናፊነት ሥነ ልቦና ለማበረታታት ሲል 21ኛው ክፍለጦር ላይ ጉዳት አድርሻለሁ እያለ በማስወራት ላይ ነው ብለዋል፡፡ ጁንታው በበርተክላይ፣ ቶኦ እና በአዲቀይህ መውጫ የሚመካባቸው ምሽጎቹ በ21ኛው ክፍለጦር ከተደረማመሱ በኋላ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት የተበታተኑ ታጣቂዎቹን ለማሰባሰብ እየሞከረ መሆኑን ጠቁመው፣ ያሸነፈና ያጠቃ ሃይል ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አይሸሽም ብለዋል። ወደ ኋላ እየሮጠ አጥቅቻለሁ ማለቱ የተለመደ የውሸት ባህሪው ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
ጁንታው የያዘው ፕሮፓጋንዳ የትህነግ ታጣቂዎች 21ኛው ክፍለ ጦር ከተደመሰሰ እጃቸውን ከመስጠት ይልቅ የመዋጋት ሥነ ልቦና ገንብተው ወደ ውጊያ በሙሉ ልብ ይመለሳሉ ከሚል ቀቢፀ-ተስፋ መሆኑን ገልፀዋል።
21ኛው ክፍለ ጦር በድል ላይ ድል እየተቀዳጀ፤ ወኔውና ሞራሉ እየጨመረ ወደፊት በመገስገስ ላይ ነው ያሉት ኮሎኔል መኳንንት፣ ክፍለጦሩ ወደፊትም የሚሰጡትን ግዳጆች በድል ለመወጣት በሙሉ አቋምና ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ከጁንታው መለያ ባህሪዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ውሸት ነው ያሉት ምክትል አዛዡ፣ የዚህ ኦፕሬሽን አላማም ይህንን ውሸታም፣ ስግብግብና ዘራፊ ቡድን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ነው ብለዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=42459
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ ።
ቢሮው ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ፈተና እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
በአዲስ አበባ የገጽ ለገጽ ትምህርት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በየደረጃው እንደሚጀመር ተገለጸ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የገጽ ለገጽ ትምህርት ከፊታችን ሰኞ (ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በየደረጃው እንደሚጀመር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆእንዳስታወቁት፤ በግል ትምህርት ቤቶቸ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል።
በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር አቶ አዲሱ ተናግረዋል።
ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመማሪያ ክፍል ግንባታ እስኪጠናቀቅ በቤት እንደሚቆዩ የገለጹት አቶ አዲሱ፤ ወላጆች ለልጆቻቸው ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።
በመንግስትም በግልም ትምህርት ቤት ያሉ የቅድመ ትምህርት (ኬጂ) የገጽ ለገጽ ትምህርቱ ለተወሰነ ጊዜ እንደማይጀመርም አስታውቀዋል።
በእነጀዋር መሀመድ የክስ መዝገብ ተከሳሾች ባቀረቡት ቅሬታ ላይ አቃቤ ህግ የፅሁፍ መቃወሚያውን አቀረበ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የዐቃቤ ህግን መቃወሚያ ለመስማት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዐቃቤ ህግ መቃወሚያውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
በዚህ ችሎት ላይ ተከሳሾች አቶ ጀዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ወደ ችሎቱ ያልቀረቡ ሲሆን ለዚህም፤ በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዲሁም ባለን ፖለቲካዊ ተሳትፎ የተነሳ እንዲሁም በማረሚያ ቤቱ እና በፍርድ ቤት መሀከል ያለው እርቀት ሰፊ በመሆኑ ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ፈጥሮብናል፤ በዚህ ምክንያትም መቅረብ አልቻልንም በመሆኑም በቀጣይ ለሚኖረው የፍርድ ሂደት በአቅራቢያችን ጊዜያዊ ችሎት ይቋቋምልን የሚል አቤቱታቸውን በጠበቆቻቸው በኩል በፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ዐቃቤ ህግ 11ኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ 14ኛ ተከሳሽ አቶ ብ/መስቀል አበበ እና 15ኛ ተከሳሽ አቶ ፀጋዬ ረጋሰ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለማድረግ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሊቀርቡ ስላልቻሉ በሌሉበት ክሳቸው እንዲታይ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ጠይቆ፤ ተከሳሾች በተቋሙ ላይ ላቀረቡት ቅሬታ በፅሁፍ ምላሽ መስጠቱን ገልጾ ነገር ግን ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ እንዲቀርቡ የተፃፈ ትዕዛዝ ባለመኖሩ ሊቀርቡ አለመቻላቸውን አስረድቷል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የፌዴራል 1ኛ የፀረ ሽብርና ህገ-መንግስት ጉዳዮች ችሎት፡-
1. በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልተገኙ ተከሳሾችን በሚመለከት ክሳቸው በሌሉበት እንዲታይ ወስኗል፤
2. በሌላም በኩል እነ አቶ ጀዋር መሀመድ ያቀረቡትን ጊዚያዊ ችሎት ይቋቋምልን ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር አቅርቦ ምላሽ እንዲሰጥበት እንደሚደረግ፤
3. ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በግለሰብ ደረጃ ቀርበው ምላሽ ይስጡበት ለሚለው የተከሳሾች ቅሬታ ላይ ለትዕዛዝ ለመስጠት በሚድያ ቀረበ የተባለው አስተያየት በእንግሊዘኛ እና አማርኛ ኮፒ ተደርጎ በሲዲ ከቀረበ በኋላ ትዕዛዝ የሚሰጥበት መሆኑን በመግለፅ ቀጣዩን ቀጠሮ ለታህሳስ 08 ቀን 2013 ዓ.ም በማድረግ የእለቱ ችሎት ተፈፅሟል፡፡
ጁንታው ተስፋ በመቁረጥ ድልድዮችንና መንገዶችን ቢያፈርስም የሰራዊቱን እንቅስቃሴ መግታት እንዳልቻለ ተገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ራያ ግንባር፡- ጁንታው ህግን ለማስከበር በራያ ግንባር የተሰማራውን መከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ ለመግታት ድልድዮችንና መንገዶችን ቢያፈርስም ሰራዊቱ መሰናክሎቹን እያለፈ ወደፊት መገስገሱን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ገልጸዋል፡፡
የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክ ክፍል ሃላፊ ኮሎኔል የሱፍ አደም እንደገለጹት፤ ጀግናው መከላከያ ሰራዊት በራያ ግንባር ህግን የማስከበር ርምጃ መውሰድ ከጀመረ ወዲህ ጁንታው የሚመካባቸውን ምሽጎችና ከባድ መሳሪያዎች በመደምሰስ ወደፊት እየገሰገሰ ነው።
የተሰጡትን ተደጋጋሚ የሰም አማራጮች አልቀበልም በማለት ጦርነትን የመረጠው ይህ ስግብግብና ከሀዲ የህወሓት ቡድን የመረጠው መንገድ እንደማያዋጣው ሲያውቅና አቅሙ ሲዳከም መሰረተ ልማቶችን እያወደመ መሸሽ ጀምሯል ብለዋል፡፡
የጁንታው ታጣቂዎች ‹‹ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል›› በሚል በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ ኮንክሪት የአስፋልት መንገዶችን፣ ድልድዮችን እና ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በዶዘር በመቆፈር እና ቆርጦ በመጣልና መንገድ በመዝጋት የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ለመግታት ሞክሯል ያሉት ሃለፊው፤ ቡድኑ ድልድዮችን አፍርሷል፤ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊ ገመዶችን በጣጥሷል፤ ትምህርት ቤቶችን፣ የመንግስት መገልገያ ተቋማትንና ቤተ እምነቶችን ማረፊያና ምሽግ አድርጓቸዋል ነው ያሉት፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ በአንድ በኩል እየተዋጋ በሌላ በኩል የጥፋት ቡድኑ የሚያፈርሳቸውን መንገዶችና ድልድዮችን እየሰራ ተሸከርካሪዎችን በማሳለፍ የጁንታውን እጅ ለመያዝ የሚያደርገውን ጉዞ እንደቀጠለ ገልጸዋል፡፡
ሰራዊቱ ወደ ግዳጅ ሲገባ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሎጂስቲኮችን በሙሉ ማሟላቱን የገለጹት ኮለኔሉ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከጁንታው ነጻ በወጡ ከተሞች ያለው ህዝብ ሳይቀር የሚያደርግለት ድጋፍም ሌላ አቅም ፈጥሮለታል ነው ያሉት፡፡
ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ መሰናክሎችን እያለፈ ለመሄድ የሚያስችል የተሟላ የሎጂስቲክ አቅም ስላለው ምንም አይነት እንቅፋት ቢገጥመው ወደፊት ከመሄድ የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም ብለዋል፡፡
ጁንታው አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ ሆኖም እንኳ የጥፋት እጆቹን መሰብሰብ አልቻለም ያሉት ኮለኔሉ፤ በወንጀል ላይ ሌላ ወንጀል እየሰራ መሆኑን በመግለጽ፤ በቅርቡም ከሀዲና ወንጀለኛዎቹን የህወሓት አባላት ለህግ እንደሚያቀርቡ ያላቸውን እምነት ገልጸውልናል።
በኢያሱ መሰለ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በራያ አላማጣ ከተማ ከአንድ የመንግስት ቢሮ ውስጥ በርካታ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።

በስፍራው አግኝተን ያነጋገርናቸው ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ እንደገለፁት ይህን መታወቂያ የሚጠቀሙት ግለሰቦች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀልና የሽብር ጥፋት ለማድረስ ነው ብለዋል።

ይህ የትህነግ ድርጊት በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀል በመፈፀም የአማራን ህዝብ ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ለማጋጨት ያሴሩት ሴራ ነው ሲሉ ምክትል ኮማንደሩ ጨምረው ገልፀዋል።

ሁሉም የሀገራችን ህዝብ እና የፀጥታ አካላት መታወቂያ በሚያዩበት ጊዜ በደንብ ማስተዋል ይገባል።አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ- የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን
የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ሁለተኛ ዙር የአዲስ አበባ የህክምና ባለሙያዎች ልዑካን ወደ ስፍራው አቀኑ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተውጣጡ ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎችን እና ሁለት ድጋፍ ሰጪ አምቡላንሶች ለመከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ወደ ስፍራው አቅንተዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለህክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት አድርገዋል ።

የሀገር ጥሪን በመቀበል ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት የጤና ባለሙያዎቹ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

በመጀመሪያው ዙር 48 የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በአንድ ሳምንት ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

ከህዳር 11 ጀምሮ ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግምታዊ ዋጋቸው ከ42 ሚሊዮን 749 ሺህ በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባምድ ዕቃዎች መያዙ ተገለጸ።

የተያዙት እቃዎች የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጥይት፣ አደንዛዥ ዕጽ፣ ቡና፣ ግመሎች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መሆናቸውና በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በአዲስ አበባ ኤርፖርት፣ በሐዋሳ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሞያሌ፣ በባህርዳር፣ ጅማ፣ በአዳማ፣ በኮቦልቻ እና በአሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች የተያዙ መሆኑ ተገልጿል።

ዕቃዎቹ ሊያዙ የቻሉት በጉምሩክ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ኅብረተሰብ ጥቆማ፣ በክልል ፖሊስ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአድማ በታኝ እና በመከላከያ አባላት የጋራ ጥረት መሆኑም ለማወቅ ተችሏል።

ከኮንትሮባንድ ዕቃዎች ማስተላለፍ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አካላት እና አሸከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል
- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር አሳይቷል። ጁንታው ካስታsጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቀሌ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ አድርጓል። ይህም የሠራዊቱን ድልና የጁንታውን ሽንፈት አፋጥኖታል።

ስግብግቡ ጁንታ በየትኛውም መመዘኛ ለትግራይ ሕዝብ አይመጥነውም። የትግራይ ሕዝብ ከእውነት ጋር በመቆምና የጁንታውን እኩይ ዓላማ በመፃረር ከቀበሌ ቀበሌ፣ ከዞን ዞን መቀሌ እስኪገባ ድረስ ተመሳሳይ ድጋፍ ለሠራዊቱ ሰጥቷል። ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ጁንታው በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ተ/ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን እያወደመ ሄዷል። በዚህም የገዛ ወገኑ ጠላት መሆኑን አሳይቷል። ጁንታው እኔ ከሞትኩ ብሎ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ።

በዚህ ዘመቻችን ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል።
ክብር ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን!!!
በህወሓት ጁንታ በክህደት ከጀርባው የተወጋው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን መላውን ትግራይ በከፍተኛ ጀግንነት ከጁንታው ጨቋኝ አገዛዝ ነጻ አውጥቷል::
የመከላከያ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ሰራዊቱ መቀሌን መቆጣጠሩን ከገለጹ በኃላ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ከተሞች ደስታቸውን ገልጸዋል፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን አመስግነዋል፤ አውድሰዋል።:
ክብር ለመከላከያ ሰራዊታችን!!!
ክብር ዘላቂ ሰላምና የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ ለታገላችሁ!!!!
ክብር ለኢትዮጵያ!!!!!!
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ በወቅታዊ
አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ይሰጣሉ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ በወቅታዊ
አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚገኘው መሰብሰቢያ አደራሽ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ማካሄድ ይጀምራል፡፡
አጀንዳዎቹም
1. የም/ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ
መርምሮ ማጽደቅ፣
2. የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በወቅታዊ
አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች
የሚሰጡትን መልስ ማዳመጥ እንደሆነ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በሁመራ ከተማ ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
ዋና ሳጅን ታከለ እሸቴ ይባላል ፤የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሁመራ ከተማ ሰላም እያስከበረ ይገኛል።
ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ሰላም እያስከበረ በሚገኝበት ሁመራ ከተማ ላይ በአንድ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ(ባጃጅ) ላይ ሁለት ግለሰቦች ሁለት ሻንጣ ይዘው በመጓዝ ላይ ሳሉ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ፍተሻ በሚያደርግበት ጊዜ ሁለቱም ሻንጣ ሙሉ ብር ሆኖ ተገኝቷል።
በወቅቱ ግለሰቦቹ "አንዱን ሻንጣ ሙሉ ብር እንስጥህና ልቀቀን"ቢሉትም ቃል የገባለትን ህዝብ እና ሙያውን በማስበለጥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።
በአሁኑ ሰዓት በሁለቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል።