Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በከሀዲው ህወሓት ቅጥረኛ ኦነግ ሸኔ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አንጸበራቂ ድሎችን በማስመዘገብ ላይ ይገኛል ሲሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አስታወቁ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ህዝብን የሚወጉ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪውና ቅጥረኛው የኦነግ ሸኔ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አንጸበራቂ ድሎችን በማስመዘገብ ላይ ይገኛል ሲሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
ለዝግጅት ክፍላችን የተላከው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ መልዕክት እንደሚገልጸው፤ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪና ቅጥረኛው የኦነግ ሸኔ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አንጸበራቂ ድሎችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር ተልዕኮውን በድል አጠናቆ ወደ ቀድሞው መደበኛው ስራው እስኪመለስ ድረስ ህዝባችን እስከ ህይወት መስዕዋትነት ከጀግናው መከላከያችን ጎን ለመቆም የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኦነግ ሸኔን በመጠራረግ ህዝቦች፣በወንድማማችነት፡በዕኩልነት፡በፍቅርና በሰላም ሚኖሩባትን ኢትዮጵያና ኦሮሚያ እናስቀጥላለን በለዋል።
ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ባጋጠመን የቴክኒክ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ባጋጠመን የቴክኒክ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
በቴክኒክ ችግር የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የቴክኒክ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
የማይካድራ ሲቪል ሰዎች ጭፍጨፋ የግፍና ጭካኔ ወንጀል ነው:: ጭፍጨፋው በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን መካሄዱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አረጋግጧል
****************
(ኢፕድ)
ኮሚሽኑ ለኢፕድ በላከው መግለጫ በማይካድራ የተጎዱትን ማቋቋም እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል ብሏል::
በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል (crimes against humanity) እና የጦር ወንጀል (war crime) ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ስለሆነ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡
በቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡ ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን በአገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል፡፡
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹በማይካድራ ከተማ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል፤ ስለ ወደፊት በሰላም አብሮ መኖርም ተስፋ ይሰጣል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹የተጐዱ ሰዎችን እና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና ከመጠገን በተጨማሪ፤ በዚህ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ገለፁ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ዛሬ ሮም ጣሊያን ገብቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ አቅርበዋል።
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ደመቀ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ሁለቱ ሃገራት ረጅም ዘመን የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ወደ ተሻለ የትብብር ከፍታ ለማድረስ ጠንክረው እንደሚሰሩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
የኢትዮጵያና የቻይና የንግድ ግንኙነት 26 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ
****************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት 50 ዓመታት የኢትዮጵያ እና የቻይና የንግድ ግንኙነት 26 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ቻይና የኢትዮጵያ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በልማት የነበራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያሰቆጠረ መሆኑ ሚኒስቴሩ ጠቅሶ፣ እ.ኤ. አ. ከ2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ መጠን በ26 በመቶ አድጓል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራ ከምትልካቸው ምርቶች የኢትዮጵያ ቡና እና አበባ በቻይና ገበያ ውስጥ በሰፊው ተወዳጅ ናቸው፡፡ የሰሊጥ ምርትም በቻይና አንድ አሥረኛ ድርሻ አለው፡፡
በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው ከሚገኙ ቻይና ኩባንያዎች ከአንድ ሺህ 500 በላይ ፕሮጀክቶች አንድ ነጥብ 153 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ አጠቃላይ ኢንቨስትመንት 60 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሰራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡
ቻይናና ኢትዮጵያ በአምባሳደሮች ደረጃ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ 50ኛ ዓመትን እያከበሩ ባለበት በዚህ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ጠንካራ የንግድ፣ የኢንቨስትምንት፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትስስር ፈጥረዋል ፡፡
በወንድማገኝ አሸብር
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ተገለጸ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን እንዳጠናቀቀ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን መግለፃቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑም ተገልጿል።
ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናው አቅርቧል።
"በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ፣ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን" ጥሪ ቀርቧል።
በሰበታ ከተማ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

በሰበታ ከተማ 04 ቀበሌ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ ጉዳት ሳያደርስ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ፡፡

ፈንጂው መሀመድ ረጃ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የተገኘ መሆኑን የሰበታ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

መስጂድ አቅራቢያ ላይ መጠመዱ በተቋሙና በምዕመናን ላይ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የተፈፀመ መሆኑን የቀበሌው አስተዳደርና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ተሬሳ ገልፀዋል፡፡

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ፤ ይሁንና በህብረተሰቡ ጥቆማ ጉዳት ሳያደርስ መክሸፉን ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጥቆማ ሲደርሰው በፍጥነት ወደ አካባቢው በማምራት የማክሸፍ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡ አካባቢውን ከጥፋት ኃይሎች በንቃት እንዲጠብቅና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲታዘብ ጥቆማ እንዲያደርሰው የከተማው ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ
********
(ኢ.ፕ.ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ብራሰልስ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል።

ኮሚሽነሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለህብረቱ ስትራቴጂያዊ አጋር ሃገር መሆንዋን የጠቀሱት፤ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ንፁሃን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥበት መንገድ ለማመቻቸት በመንግሥት የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

አቶ ደመቀ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአለምአቀፍ የሰብዓዊ ህግ ተፈፃሚ ለማድረግ ነባራዊ ሁኔታውን በማጥናት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የሚደረግበትን አግባብ አስረድተዋል።

ንፁሃን ዜጎች ለከፋ ቀውስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሲል የምክትል ጠቅላይ ሚኒ
አዛውንቱ ሚሊሻ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

- በምጸልይበትና በማስታርቅበት እድሜዬ ውጊያ ላይ
መገኘቴ ያሳዝነኛል፤

- የአስም በሽተኛ ሆኜ፤ የልብ ቀዶ ህክምናም አድርጌ ወደ
ውጊያው ተልኬያለሁ፤

- የጡረታ ደመወዜን ይዘው ሲያስፈራሩኝ ለዘመቻ ወጣሁ

አቶ መብራቱ ታደለ የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው፤ ስድስት ሴት ልጆችን ወልደው ስመዋል። የልጅ ልጆችን አፍርተውም አያት ሆነዋል።

አዛውንቱ የአስም ህመምተኛ ናቸው። የጤናቸው እክል አስም ብቻ እንዳልሆነና በቅርቡም የልብ ቀዶ ጥገና ማድረጋቸውን ይናገራሉ።

አረጋዊነታቸው የጤና እክላቸውና አቅመ ደካማነታቸው ከህወሓት ጁንታዎች ዓይን አላዳናቸውም። ይህ ዘራፊ ቡድን በዝርፊያና በአፈና ለኖረበት ስልጣኑ ማራዘሚያ ይሆኑ ዘንድ ሚሊሻ በሚል ስም አስታጥቆ መከላከያ ሰራዊትን ይወጉ ዘንድ ላካቸው።

‹‹ይህ ዘመኔ ውጊያ የማደርግበት ሳይሆን የምጸልይበትና የማስታርቅበት ነበር፤ በዚህ እድሜዬ በማይጠበቅ ቦታ መገኜቴ ይጸጽተኛል ይላሉ” አቶ መብራቱ።

የሚሊሻ አባል የሆኑት ፈልገው ሳይሆን ታጥቀው ካልተዋጉ የሚከፈላቸው የጡረታ ደሞዝ እንደሚቆምባቸው በጁንታው ማስፈራሪያ ስለተሰጣቸው እንደሆነ ይናገራሉ።

“ደመወዜን አታገኝም በመባሌ ነው ወደ ሚሊሻው የተቀላቀልኩት። ልክ እንደእኔው ሁሉ መሳሪያ የያዙ በሙሉ እንዲዋጉ ተገድደዋል›› ይላሉ አቶ በሪሁን፡፡

ለጥበቃ ስራ የተሰጣቸውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ለጁንታው ታጣቂዎች ሰጥተው እርሳቸው ሚንቶፍ ይዘው እንዲዋጉ መደረጋቸውን አዛውንቱ ይናገራሉ፡፡ የመዋጋት ፍላጎትም አቅምም የለኝም ያሉት እኚህ አዛውንት፤ ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ከመሰሎቻቸው ጋር ጠፍተው እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊት ሰጥተዋል፡፡

ቀሪ እድሜያቸውን ለልጆቻቸው፣ ለልጅ ልጆቻቸው እና ለአገራቸው በጸሎት ማሳለፍ የሚመኙት አዛውንቱ አቶ በሪሁንም ለትግራይ ታጣቂዎችና ሚሊሻ አባላት መልዕክት አላቸው፤ “እንደ አባት የምነገርችሁ የመንግስትን ጥሪ አዳምጡ በሰላማዊ መንገድ እጃችሁን ስጡ ዓላማ የሌለው ሞት አትሙቱ”።
በእያሱ መሰለ
የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ለሕወሓት ወንጀለኛ ቡድን የተሰጠው በሰላም እጅ የመስጫ የ72 ሰአት ጊዜ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።
በዚህም ሕግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሩን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።
በተሰጠው የ72 ሰአታት ጊዜም በሺዎች የሚቆጠሩ የወንጀለኛው ቡድን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት መስጠታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
ኮሚሽኑ የቡድኑ እኩይ ዕቅድ መረጃ እንደደረሰውም አስታውቋል፡፡
መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑትን ሰዎች ማረድ ፣ አንገታቸውን በገመድ ማነቅ ፣ ንብረታቸውን መዝረፍ እና ማቃጠል፣ የመከላከያ ሠራዊታችንን የደንብ ልብስ በመልበስ ሰዎች ላይ በድንገት ተኩስ በመክፈት ሰሞኑን በማይካድራ የፈፀመውን ብሄርን መሰረት ያደረገ አስነዋሪ፣ አሳፋሪና አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለመድገም እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ይህንን እኩይ ተግባር ከፈፀመ በኋላም ድርጊቱ የተፈፀመው በመንግስት ነው ብሎ በሚዲያ ለማሰራጨት የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ መረጃ ደርሶኛል ነው ያለው ኮሚሽኑ።
በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ይህንን የጥፋት ሴራ ተከትሎ ጁንታው ቡድን ሊያሰራጭ የተዘጋጀውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳና ይህንን እኩይ ተግባር አስቀድሞ እንዲረዳና ተቀባይነት ያጣ ዘንድ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ማሳሰብ እንወዳለን ሲል ጥሪ አቅርቧል።
“በጁንታው ላይ የሚወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለመላው ኢትዮጵያ ሰላም መሰረት ነው”
– አቶ ደረጀ በቀለ የፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር
*******************
(ኢ ፕ ድ)
መቀሌ የመሸገው ጁንታ መወገድ ለመላው ኢትዮጵያ በተለይም ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ልማት መረጋጋጥ መሰረት እንደሚሆን የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሊቀ መንበር አቶ ደረጀ በቀለ ገለጹ።
ሊቀመንበሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት ወንጀለኛው ቡድን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ሲሰራ የነበረው ለኢትዮጵያም ሆነ ለትግራይ ህዝብ በማሰብ ሳይሆን የስልጣን ጥሙን ለማርካትና ሀብት ለማጋበስ ነበር። በዚህም ባለፉት 30 ዓመታት የትግራይን ህዝብ መደበቂያ አድርገው በርካታ ወንጀሎችን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ግን ከጁንታው ቡድን ያገኘው ጥቅም አልነበረም።
ከሁሉም በላይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ቆመንለታል የሚሉት ህዝብ የሚገለገልባቸውን መሰረተ ልማቶች ማውደም መጀመራቸው ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚያሳይ ነው።
በቅርቡ በማይካድራና በተለያዩ ሌሎች አካባቢዎች ለፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀልና ላወደሙት ንብረትም በተገቢው መንገድ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።
በተጨማሪ ራሳቸው የፈጠሩትን ችግር ወደሌሎች በማላከክ የትግራይ ህዝብን ወንድሞቹ ከሆኑት ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ለማጋጨትም እየሠሩ ይገኛሉ። የእነዚህ አካላት ፍፃሜ ማግኘት መላውን ኢትዮጵያ በተለይም የትግራይን ህዝብ ሰላም የሚያረጋግጥና ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር የሚያስችለው ነው። በመሆኑም የትግራይ ህዝብም ሆነ ቀሪው ኢትዮጵያዊ መንግሥት እየሠራ ያለውን ሰላም የማስጠበቅና ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በሙሉ አቅሙ ሊደግፈው ይገባል።
https://www.press.et/Ama/?p=42478
በአዲስ አበባ ከተማ ያለ ደረሰኝ ሲሸጡ የተገኙ ከ22 በላይ ድርጅቶች በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል ከ22 በላይ ድርጅቶች ያለደረሰኝ ሲሸጡ በመገኘታቸው በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንደገለጹት፤ በከተማዋ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተሰርቷል።
በዚህም ከ22 በላይ ድርጅቶች ያለደረሰኝ ሲሸጡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፖሊስ ልብስ በመልበስና የገቢዎች ቢሮ ሀሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ጠቁመዋል።
በከተማዋ የግብር ህግን አክብረው በማይሰሩ ነጋዴዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ግብር ከፉዩ የወጣውን የግብር ህግ አክብሮ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
ህብረተሰቡም የወጣውን የግብር ህግ አክብረው የማይሰሩ አጭበርባሪዎች ሲያጋጥሙት በ7075 ነጻ የስልክ መስመር እንዲጠቁም አቶ ሙሉጌታ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክረታሪያት አስተውቋል።
“መከላከያ ሕዝባዊ ማንነትን የተሸከመ፣ መቆምም መኖርም የሚችለው ከሕዝብ ጋር የሆነ ሠራዊት ነው”
-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከዳር ወጥተው ያወገዙት መከላከያ ህዝባዊ ማንነትን የተሸከመ፣ መቆምም መኖርም የሚችለው በህዝብ በመሆኑ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ አስታወቁ። የአራዳ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ አካላት የሰበሰበውን ከ70 ሚሊዬን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ አካላት የሰበሰበውን ከ70 ሚሊዬን ብር በላይ ድጋፍ ትናንት ባስረከበበት ወቅት ወይዘሮ አዳነች እንዳመለከቱት፣ መከላከያ ህዝባዊ ብቻ ሳይሆን ሞራሉም ስንቁም ህዝብ የሆነ ነው። መቆሙም መኖሩም ህዝብ እንደሆነ የሚያስብም ነው። ስለዚህም እንደ አዲስ አበባ ከተማ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ከማድነቅና ከማመስገን ጎን ለጎን ጁንታው ከጥፋቱ የሚታረምበትን መቀየስ ላይ መሥራት ይገባል።
ይህ አስነዋሪና የከሃዲነት ተግባር በመረዳዳትና ወደ ነበርንበት ወንድማማችነት በመመለስ ካልተገታ በምንም አይከሽፍም ያሉት ወይዘሮዋ፣ ይህንን መልካም እሴት ማብዛት ላይ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።
አፀያፊው ተግባር ሲፈፀም ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከዳር ያወገዙት ያለምክንያት እንዳልነበር የጠቀሱት ምክትል ከንቲበዋ፤ መከላከያ ህዝባዊ ማንነትን የተሸከመ፤ መቆምም መኖርም የሚችለው በህዝብ የሆነ ነው።
የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ ብሎ ህዝቡን ተጋላጭ እያደረገ ራሱን ብቻ እየጠበቀ የሚንቀሳቀሰውን ጁንታ በከተማ ያላችሁ የትግራይ ተወላጆች ጭምር እያወገዛችሁና በሃሳብ ሳትሰረቁ ሕግ የማስከበሩን ተግባር እንድትደግፉ ሲሉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊ መሆናችን የሚያቃቅረን ሳይሆን ውበትና ድምቀታችን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ማሳየት የምንችልበት ነው ወይዘሮ አዳነች፤ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ጠል የሆነው ጁንታ ቡድን ይህ እንዳይሆን ለፍቷል፤ ሠርቷል።
ነገር ግን ማህበረሰባችን ከልቡ የታተመ በመሆኑ በዚህ ተግባሩ ሳይረበሽ አሁንም በድጋፉ ከተቸገሩና ከሕግ ማስከበሩ ጎን መቆሙን ማሳየት እንዳለበትም ተናግረዋል። የአራዳ ክፍለ ከተማ ያደረገውን ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ትልቅ ስንቅና ከአገርም ሆነ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዳለ የሚያሳይ መሆኑንም ገልፀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=42469
የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ለመከላከያ ድጋፍ አደረጉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀብት ማሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የልማት ተቋማት፣ ነጋዴዎች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ለመከላከያ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ከተለገሰው ገንዘብ ውስጥ ከ7 መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በከተማው ከሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች የተሰበሰበ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ሺሰማ፣ 4 መቶ 30 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ ከልማት ተቋማት፣ ነጋዴዎች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተገኘ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የገቢ ማሰባሰቡን ሥራ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሣቸው ፍቃድ መጀመራቸውን ያስታወቁት አቶ ሺሰማ፣ የመንግሥት አመራሮች ለድጋፉ የመጡ አካላትን ከማስተባበር ያለፈ ሥራ እንዳልነበራቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ለአመራሩ ሥራውን እንዳቀለለት አመልክተዋል፡፡
የህዝቡ ድጋፍ ዘርፈ ብዙ ነው የሚሉት አቶ ሺሰማ፤ ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ወደ 8 ሺ ዩኒት የደም ልገሳ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በፈቃደኝነት ግንባር ድረስ በመሄድ ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
እየተደረገ ያለውን የሕግ ማስከበር ሥራ በታሰበለት ልክ እንዲሄድ የህዝቡ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ሰብሳቢው፣ ህዝቡ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ከፀጥታ አካላቱ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች 66 ሚሊዮን 361 ሺህ 380 በላይ ገንዘብ እና 4 ሺ 6 መቶ 57 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሠራዊቱ መለገሳቸውን ገልፀዋል ፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=42470
“21ኛ ክፍለ ጦር የተሰጠውን ተልዕኮ በስኬት እየተወጣ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ ነው”
– ኮሎኔል መኳንንት ሲሳይ የ21ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
21ኛ ክፍለ ጦር የተሰጠውን ሕግ የማስከበር ተልዕኮ በስኬት እየተወጣ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮለኔል መኳንንት ሲሳይ አስታወቁ፡፡
ኮሎኔሉ ትናንት በአካባቢው ለሚገኘው የጋዜጠኖች ቡድን እንዳስታወቁት፣ 21ኛ ክፍለ ጦር የአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች የተመኩባቸውን ሦስት ወሳኝ ምሽጎች ደረማምሶ፤ ከባድ መሣሪያዎችን አውድሞ እግር በእግር እየተከተለ በጁንታው ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብኣዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል፡፡
የጁንታው ታጣቂዎች የ21ኛው ክፍለ ጦርን የጀግንነት ገድል የሚያውቁ በመሆኑ እፊቱ ቆመው አይዋጉም ያሉት ኮሎኔሉ፣ ጁንታው በአሁኑ ወቅት ከእጁ እየወጡ ለመከላከያ ሠራዊቱ እጃቸውን የሚሰጡ ታጣቂዎች ቁጥር ዕለት ተዕለት እየጨመረ በመምጣቱ የታጣቂዎቹን የተሸናፊነት ሥነ ልቦና ለማበረታታት ሲል 21ኛው ክፍለጦር ላይ ጉዳት አድርሻለሁ እያለ በማስወራት ላይ ነው ብለዋል፡፡ ጁንታው በበርተክላይ፣ ቶኦ እና በአዲቀይህ መውጫ የሚመካባቸው ምሽጎቹ በ21ኛው ክፍለጦር ከተደረማመሱ በኋላ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት የተበታተኑ ታጣቂዎቹን ለማሰባሰብ እየሞከረ መሆኑን ጠቁመው፣ ያሸነፈና ያጠቃ ሃይል ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አይሸሽም ብለዋል። ወደ ኋላ እየሮጠ አጥቅቻለሁ ማለቱ የተለመደ የውሸት ባህሪው ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
ጁንታው የያዘው ፕሮፓጋንዳ የትህነግ ታጣቂዎች 21ኛው ክፍለ ጦር ከተደመሰሰ እጃቸውን ከመስጠት ይልቅ የመዋጋት ሥነ ልቦና ገንብተው ወደ ውጊያ በሙሉ ልብ ይመለሳሉ ከሚል ቀቢፀ-ተስፋ መሆኑን ገልፀዋል።
21ኛው ክፍለ ጦር በድል ላይ ድል እየተቀዳጀ፤ ወኔውና ሞራሉ እየጨመረ ወደፊት በመገስገስ ላይ ነው ያሉት ኮሎኔል መኳንንት፣ ክፍለጦሩ ወደፊትም የሚሰጡትን ግዳጆች በድል ለመወጣት በሙሉ አቋምና ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ከጁንታው መለያ ባህሪዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ውሸት ነው ያሉት ምክትል አዛዡ፣ የዚህ ኦፕሬሽን አላማም ይህንን ውሸታም፣ ስግብግብና ዘራፊ ቡድን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ነው ብለዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=42459
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ ።
ቢሮው ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ፈተና እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
በአዲስ አበባ የገጽ ለገጽ ትምህርት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በየደረጃው እንደሚጀመር ተገለጸ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የገጽ ለገጽ ትምህርት ከፊታችን ሰኞ (ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በየደረጃው እንደሚጀመር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆእንዳስታወቁት፤ በግል ትምህርት ቤቶቸ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል።
በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር አቶ አዲሱ ተናግረዋል።
ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመማሪያ ክፍል ግንባታ እስኪጠናቀቅ በቤት እንደሚቆዩ የገለጹት አቶ አዲሱ፤ ወላጆች ለልጆቻቸው ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።
በመንግስትም በግልም ትምህርት ቤት ያሉ የቅድመ ትምህርት (ኬጂ) የገጽ ለገጽ ትምህርቱ ለተወሰነ ጊዜ እንደማይጀመርም አስታውቀዋል።
በእነጀዋር መሀመድ የክስ መዝገብ ተከሳሾች ባቀረቡት ቅሬታ ላይ አቃቤ ህግ የፅሁፍ መቃወሚያውን አቀረበ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የዐቃቤ ህግን መቃወሚያ ለመስማት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዐቃቤ ህግ መቃወሚያውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
በዚህ ችሎት ላይ ተከሳሾች አቶ ጀዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ወደ ችሎቱ ያልቀረቡ ሲሆን ለዚህም፤ በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዲሁም ባለን ፖለቲካዊ ተሳትፎ የተነሳ እንዲሁም በማረሚያ ቤቱ እና በፍርድ ቤት መሀከል ያለው እርቀት ሰፊ በመሆኑ ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ፈጥሮብናል፤ በዚህ ምክንያትም መቅረብ አልቻልንም በመሆኑም በቀጣይ ለሚኖረው የፍርድ ሂደት በአቅራቢያችን ጊዜያዊ ችሎት ይቋቋምልን የሚል አቤቱታቸውን በጠበቆቻቸው በኩል በፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ዐቃቤ ህግ 11ኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ 14ኛ ተከሳሽ አቶ ብ/መስቀል አበበ እና 15ኛ ተከሳሽ አቶ ፀጋዬ ረጋሰ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለማድረግ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሊቀርቡ ስላልቻሉ በሌሉበት ክሳቸው እንዲታይ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ጠይቆ፤ ተከሳሾች በተቋሙ ላይ ላቀረቡት ቅሬታ በፅሁፍ ምላሽ መስጠቱን ገልጾ ነገር ግን ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ እንዲቀርቡ የተፃፈ ትዕዛዝ ባለመኖሩ ሊቀርቡ አለመቻላቸውን አስረድቷል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የፌዴራል 1ኛ የፀረ ሽብርና ህገ-መንግስት ጉዳዮች ችሎት፡-
1. በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልተገኙ ተከሳሾችን በሚመለከት ክሳቸው በሌሉበት እንዲታይ ወስኗል፤
2. በሌላም በኩል እነ አቶ ጀዋር መሀመድ ያቀረቡትን ጊዚያዊ ችሎት ይቋቋምልን ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር አቅርቦ ምላሽ እንዲሰጥበት እንደሚደረግ፤
3. ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በግለሰብ ደረጃ ቀርበው ምላሽ ይስጡበት ለሚለው የተከሳሾች ቅሬታ ላይ ለትዕዛዝ ለመስጠት በሚድያ ቀረበ የተባለው አስተያየት በእንግሊዘኛ እና አማርኛ ኮፒ ተደርጎ በሲዲ ከቀረበ በኋላ ትዕዛዝ የሚሰጥበት መሆኑን በመግለፅ ቀጣዩን ቀጠሮ ለታህሳስ 08 ቀን 2013 ዓ.ም በማድረግ የእለቱ ችሎት ተፈፅሟል፡፡
ጁንታው ተስፋ በመቁረጥ ድልድዮችንና መንገዶችን ቢያፈርስም የሰራዊቱን እንቅስቃሴ መግታት እንዳልቻለ ተገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ራያ ግንባር፡- ጁንታው ህግን ለማስከበር በራያ ግንባር የተሰማራውን መከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ ለመግታት ድልድዮችንና መንገዶችን ቢያፈርስም ሰራዊቱ መሰናክሎቹን እያለፈ ወደፊት መገስገሱን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ገልጸዋል፡፡
የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክ ክፍል ሃላፊ ኮሎኔል የሱፍ አደም እንደገለጹት፤ ጀግናው መከላከያ ሰራዊት በራያ ግንባር ህግን የማስከበር ርምጃ መውሰድ ከጀመረ ወዲህ ጁንታው የሚመካባቸውን ምሽጎችና ከባድ መሳሪያዎች በመደምሰስ ወደፊት እየገሰገሰ ነው።
የተሰጡትን ተደጋጋሚ የሰም አማራጮች አልቀበልም በማለት ጦርነትን የመረጠው ይህ ስግብግብና ከሀዲ የህወሓት ቡድን የመረጠው መንገድ እንደማያዋጣው ሲያውቅና አቅሙ ሲዳከም መሰረተ ልማቶችን እያወደመ መሸሽ ጀምሯል ብለዋል፡፡
የጁንታው ታጣቂዎች ‹‹ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል›› በሚል በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ ኮንክሪት የአስፋልት መንገዶችን፣ ድልድዮችን እና ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በዶዘር በመቆፈር እና ቆርጦ በመጣልና መንገድ በመዝጋት የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ለመግታት ሞክሯል ያሉት ሃለፊው፤ ቡድኑ ድልድዮችን አፍርሷል፤ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊ ገመዶችን በጣጥሷል፤ ትምህርት ቤቶችን፣ የመንግስት መገልገያ ተቋማትንና ቤተ እምነቶችን ማረፊያና ምሽግ አድርጓቸዋል ነው ያሉት፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ በአንድ በኩል እየተዋጋ በሌላ በኩል የጥፋት ቡድኑ የሚያፈርሳቸውን መንገዶችና ድልድዮችን እየሰራ ተሸከርካሪዎችን በማሳለፍ የጁንታውን እጅ ለመያዝ የሚያደርገውን ጉዞ እንደቀጠለ ገልጸዋል፡፡
ሰራዊቱ ወደ ግዳጅ ሲገባ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሎጂስቲኮችን በሙሉ ማሟላቱን የገለጹት ኮለኔሉ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከጁንታው ነጻ በወጡ ከተሞች ያለው ህዝብ ሳይቀር የሚያደርግለት ድጋፍም ሌላ አቅም ፈጥሮለታል ነው ያሉት፡፡
ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ መሰናክሎችን እያለፈ ለመሄድ የሚያስችል የተሟላ የሎጂስቲክ አቅም ስላለው ምንም አይነት እንቅፋት ቢገጥመው ወደፊት ከመሄድ የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም ብለዋል፡፡
ጁንታው አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ ሆኖም እንኳ የጥፋት እጆቹን መሰብሰብ አልቻለም ያሉት ኮለኔሉ፤ በወንጀል ላይ ሌላ ወንጀል እየሰራ መሆኑን በመግለጽ፤ በቅርቡም ከሀዲና ወንጀለኛዎቹን የህወሓት አባላት ለህግ እንደሚያቀርቡ ያላቸውን እምነት ገልጸውልናል።
በኢያሱ መሰለ