“ጁንታው ሕይወቱን ለማትረፍ እና ለሌላ ሴራና ተንኮል ጊዜ ለመግዛት እንደራደር ማለቱ የሚጠበቅ ነው”
- አቶ ታዬ ደንደኣ
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የህወሓት ጁንታ ሕይወቱን ለማትረፍ እና ለሌላ ሴራና ተንኮል ብሎም ለሌላ ጥፋት ጊዜ ለመግዛት እንደራደር የሚል አጀንዳ ይዞ መምጣቱ የሚጠበቅ እንደሆነ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ።
አቶ ታዬ በተለይ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መከላከያ ሠራዊት ምናልባትም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ሕዝቦች አሁን የሚፈልጉት የሕወሓት ጁንታ ስብስብ እንዲወገድ ነው ብለዋል።
ቡድኑ ላለፉት 27 ዓመታት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአልሸባብ ጋር ተዳምሮ ለቀጠናው የሰላምና መረጋጋት እጦት ምክንያት እንደነበር አመልክተው ፣ይህ ቡድን እንዲቀጥል እድል መስጠት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አለመረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ቀውስና መዳከም እንዲቀጥል መፍቀድ እንደሆነም አመልክተዋል ።
ጁንታው ቡድን ያሰበው ሁሉ ከንቱ ሆኖ ሲቀርበት ስለድርድር እየጮኸ ነው ያሉት አቶ ታዬ ደንደኣ፣ የቡድኑን የእንደራደር ጩኸት በሁለት መልኩ ማየት የተሻለ ነው ብለዋል። አንደኛውና ዋናው የዚህችን አገር ሕገ መንግስት ከጣሰ፤ የዚህችን አገር ሉዓላዊነት ከደፈረ ጁንታ ቡድን ጋር በምንም አይነት መልኩ ድርድር የሚቀመጥ አካል ሊኖር አይችልም።
ድርድር ሲታሰብ መጀመሪያ ከሕግ በታች በተለይም ከሕገ መንግስት በታች ባለው ነገር ላይ መሆን አለበት። መከላከያን ያጠቃ፤ የዚህችን አገር የሉዓላዊነት ምልክት የሆነውን፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ነጻነትና ክብር የሚንጸባረቅበት ተቋምን ለማፍረስ ይሄን አይነት ተንኮል የሸረበ ሴረኛ ጋር በፍጹም ድርድር አያስፈልግም ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=42094

‹‹ጁንታው የህወሓት ቡድን የፈጸመው ተግባር የውጭ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ነው›› - አርቲስት ደበበ እሸቱ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ጁንታው የህወሓት ቡድን በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የክህደት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የሀገሪቱን ህዝቦች ለማንበርከክ የሞከሩ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ተግባር መሆኑን አርቲስት ደበበ እሸቱ አስታወቀ።
አርቲስት ደበበ እሸቱ ጁንታው የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ትቃት አስመልክቶ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቀው ፤ ከሃዲው ቡድን ለ21 ዓመታት ክልሉንና ህዝቡን ሲጠብቅ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት የከሃዲነት ተግባር ከመሆኑም ባሻገር ትውልድም ይቅር የማይለው ነው።
‹‹ተስፋ የቆረጠ ሰው ብዙ ነገር ያደርጋል። ተስፋ ባይቆርጥ ኖሮ፣ አብሮት ሲሰራና አብሮት ሲበላ የቆየ ወንድሙን አይገድልም ነበር። መከላከያ ሠራዊቱ ከኋላዬም ከፊቴም ያለው የራሴው ወገን ነው ብሎ ወገኑን ተማምኖ በተኛበት በሌሊት ክህደት መፈጸሙ ቡድኑ የመጨረሻ ዘመኑ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው ።
“አርቲስት ደበበ እንደሚለው፤ የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የፈፀመው ክህደትና ጭካኔ የውጭ አገር ጠላትና ወራሪ እንኳን ያላደረገው ነው። ጣሊያን አላደረገውም፣ ደርቡሾች አላደረጉትም፣ እንግሊዞች ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን ለመያዝ በመጡበት ጊዜ እንዲህ አይነት አፀያፊ ድርጊት አልፈጸሙም። የራሳችን ወገን የተባለው ግን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት ፈጸመ። የሠራዊቱ አባላት ሲወጣ ‹‹ለማን ጥላችሁን ነው የምትሄዱ፣ እባካችሁ ቆዩልን›› ያለ አካል ይሄን ክህደት መፈጸሙ የግድያ ቀን እያመቻቸ ነበር ማለት ነው።
ሠራዊቱ ይህ ክህደት እንደሚፈጸምበት ቢያውቅ ጥሪውን ሳይቀበል ይወጣ ነበር። የወገን ጥሪ ሆኖበት ግን ቆይልኝ ሲባል እዚያው ቆየ። ወገን በወገኑ ላይ እንዲህ ሲጨክን ቅስም ይሰብራል።ኢትዮጵያዊ መሆኑንም እንድንጠራጠር አድርጎናል ብሏል።
‹‹እንዲህ አይነት የአውሬነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ነበሩ ለካ ሲመሩን የቆዩት›› ያለው አርቲስት ደበበ፤ እነዚህ ሰዎች የፈጸሙት አጸያፊ ተግባርም መላውን ኢትዮጵያዊ ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑንም ጠቁሟል።
እንደ አርቲስት ደበበ አስተያየት፤ ጁንታው የህወሓት ቡድን ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ዓመታት ለጥፋት የሚሆኑትን ገንዘብና ሌሎች ነገሮችን ቢያከማችም ሊያዛልቀው ግን አይችልም። አቅም ይሳነዋል። አሁን ላይ ማድረግ የሚችለው የመሰረተ ልማት ውጤቶችን ማውደም ብቻ ነው። ከአዲስ አበባ ጋር ግንኙነቱ ስለተቋረጠ የገንዘብ ምንጩም ይደርቃል። እስከ አሁን ግን ከዚህ በፊት በሰበሰበው ገንዘብ አፈ ቀላጢዎችን ቀጥሮ በውጭ መገናኛ ብዙኃን ብዙ እያስወራ ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=42138

ኦነግ ሸኔ እየተሽመደመደ መምጣቱ ተገለጸ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በጁንታው የህወሓት ቡድን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ የሚደረግለትና ህዝብን በማሸበር ላይ በሚገኘው የኦነግ ሸኔ ቡድን እየተሽመደመደ መምጣቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በቡድኑ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገለጸ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ እንደገለፁት፤ጁንታው የህወሓት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ የኦሮሚያ ክልልን ፀጥታ ለማደፍረስ በተናበበ መንገድ እየሰሩ ቆይተዋል፡፡
በዚህ እኩይ ተግባራቸው ክልሉን እየበጠበጡት ዜጎችን ሲያፈናቅሉ መቆየታቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፣ የክልሉ መንግሥት ህግን ለማስከበር በጀመረው እርምጃ የኦነግ ሸኔ ቡድን እየተሽመደመደ መምጣቱን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ቡድኑ ህዝቡን ከማስፈራራትና አልፎ አልፎ በአንዳንድ አካባቢዎች ድንገተኛ ጥቃት ከማድረስ በዘለለ እንደፈለገው መፈንጨት ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል ።
የኦነግ ሸኔ አሸባሪዎች እኩይ ሴራቸውን ለመከወን ህዝብ ውስጥ የተደበቁ መሆናቸውን አመልክተው፣ ህዝቡን በእምነትና በብሄር ለማጋጨት የወጠኑት ሥራ ሰፊ ቢሆንም በህዝቡና በጸጥታ ኃይሉ የተቀናጀ ሥራ መክሸፉን አስታውቀዋል።
ቡድኑን በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ሙሉ ለሙሉ ለማፅዳት በሰፊው እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ፣ለዚህም በአሁኑ ወቅትም ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት ስለ ቡድኑ እኩይ ተግባር ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽነር ጄኔራሉ ፣የኦነግ ሸኔ አባላትም ባገኙት አጋጣሚ ዘረፋ እያካሄዱ ሃብት ለማካበት እየሞከሩ ነው፡፡ ይሁንና የክልሉን የሚሊሻ ኃይል በማጠናከር እና ከህብረተሰቡ ጋር በተናበበ መንገድ በመስራት ዘራፊውን ቡድን የማጋለጥ ሥራዎች እየተሰሩ ነው፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=42139

ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠል እየተወሰደ ያለው ህግን የማስከበር እርምጃ እንደሚደግፍ ኢዜማ አስታወቀ
*********************
(ኢ ፐ ድ)
ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠልም እየተወሰደ ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ የሚደገፍ መሆኑንኢዜማ አስታወቀ ። ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚተላለፉ እኩይ መልእክቶችን በመመልከት የትግራይ ተወላጅ ወንድሞቻችን ከመሸማቀቅ ይልቅ አብሮ በመቆም ቀኑን ማሳለፍ እንደሚገባ ገለጸ ።
ኃላፊው አቶ ዘላለም ወርቅአገኘሁ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፣ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጋር በተያያዘ ቀዳሚ ተጠቂ የሆነውን የትግራይን ህዝበ ለመጠበቅ ኑሮውን እዛ ያደረገ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀም ከክህደት ሌላ ስም ሊሰጠው አይችልም ።
ከህዝቡ ጋር በሰላም የኖረ የህዝብ ልጅ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊትን ማጥቃት ተገቢ አለመሆኑን ያመለከቱት አቶ ዘላለም፣ ኢዜማ መንግሥት እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ የሚደግፍ መሆኑን አስታውቀዋል።
መንግሥት ያሳየው ትእግስት ጦርነት የሚያስከ ትለውን ጉዳት በማሰብ ቢሆንም የአንድነት፣ የሉአላዊነት እና የህልውና ምልክት የሆነው መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሲደርስ ዝም ማለት አለበት ብሎ ኢዜማ አያምንም ብለዋል። ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠልም እየተወሰደ ያለውን እርምጃ የሚደግፍ መሆኑን አመልክተዋል።
“የትግራይ ህዝብ ስልጡን ህዝብ ነው፤ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በሰላም መኖር የሚያውቅበት፤ የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ የአስተዳደር ስርአት የሚያውቅ ህዝብ ነው” ያሉት አቶ ዘላለም “ ጦርነቱ የሚያመጣውን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበረሰባዊ ጫና ለመቅረፍ መልሶ የማቋቋም ሥራ መሰራት ይኖርበታል ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ቡድኑ በፈጸመው ጥፋት በሱላይ ሊመጣ የሚችል አደጋ ባለመኖሩ ሊሰጋ እንደማይገባ አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=42148

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ልዑካን አማካኝነት ከህወሓት ቡድን ጋር ድርድር ሊያደረጉ ነዉ የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ነዉ::
************
(ኢፕድ)
የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ላይ እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ ልዑካኖችን በመቀበል ታነጋገራለች:: ይህ የልዑካን ቡድኑን መቀበል እና የማነጋገር ሂደት በየተናጠል ከልዑካን ቡድኑ አባላት ጋር ብቻ የሚካሄድ ነዉ::
መልእክተኞቹ የፌዴራል መንግስትን ክህወሓት ጁንታ ጋር ለማስታረቅ ወደ ኢትዮጵያ ይግዋዛሉ በሚል የተሰራጨው ዜና ሀሰተኛ ነዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ ማስከበር ርምጃው ላይ ድርድር የማይታሰብ መሆኑን ግልፅ ማደረጋቸውም ይታወሳል::

ላለፉት 27 አመታት የተተገበረው ፌዴራሊዝም የውሸት እና የአንድ ቡድን የበላይነት የነገሰበት እንደነበረ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ኸርማን ኮኸን ተናገሩ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ላለፉት 27 አመታት የተተገበረው ፌዴራሊዝም የውሸት እንደነበረና የአንድ ቡድን የበላይነት የነገሰበት እንደሆነ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ኸርማን ኮኸን ተናገሩ።
የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ኸርማን ኮኸን ኢትዮጵያ ለገባችበት ችግር ዘራፊው ህወሓት እና የእሱ ወዳጆች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ላይ ራሳቸው የበላይ በማድረጋቸው እና በአገሪቱም “ሀሰተኛ” የፌዴራል ስርዓት በመመስረታቸው ነው ብለዋል።
በ 1991 በጎሳዎች ላይ የተመሠረተ የክልሎች ስርዓት በኢትዮጵያ የተቋቋመ ቢሆንም ስርዓቱ የውሸት በመሆኑ ከትግራይ ውጪ ያሉ ክልሎች አንዳቸውም ቢሆኑ በአገሪቱ ላይ የመወሰን መብት አልነበራቸውም ያሉት ኸርማን ኮኸን፤ ሂደቱ የአንድ ፓርቲ የበላይነትን ያነገሰበት ከበርካታ ዓመታት በፊት በአፍሪካ ተሞክሮ የወደቀ አካሄድን የተከተለ ነው ብለዋል።
ጥቂት የህወሓት አባላት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ብቻቸውን በበላይነት በመቆጣጠራቸው ምክንያት ጥቅማ ጥቅሞችን ለእነርሱና እነርሱን ለሚመስሏቸው ብቻ ሲያደርጉ መኖራቸውን የጠቀሱት ኸርማን ኮኸን ፤ በዚህም ምክንያት ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጫና ተፈጥሮባቸዋል፤ የመሰረተ ልማትም ፍትሃዊነት በጎደለው መልኩ ለራሳቸው አድርገውታል፤ ይህ አይነት አካሄድ በሌሎች ላይ ቁጭትና ጫና ፈጥሮባቸዋል ብለዋል አምባሳደሩ።
ይሄንን አይነት በደለን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነትን ተቃውመው ሰልፍ በሚወጡ ባልታጠቁ ሰልፈኞች ላይ የህወሃት ኃይል የሚወስዳቸው እርምጃዎችም ያልተመጣጠነ እንደነበር ኸርማን ኮኸን አብራርተዋል።
ይህን ሁሉ የሰብጻዊ መብት ጥሰት ይፈጽም ለነበረ አካል አሜሪካ ለምንድን ነበር የምትደግፈው ተብለው የተጠየቁት አምባሳደሩ፤ “ ስትራቴጂካዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት ስንል ይህን ታግሰናል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬ ከተማ ከገባ በኋላ ከችግርና ውጥረት ታድጎናል- የሽሬ ከተማ ነዋሪዎች
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ከችግር፣ ውጥረትና ፍርሃት አንድንወጣ አድርጎናል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የህወሃት ቡድን ቀደም ሲል በክልሉ "ወራሪ፣ ዘራፊና የትግራይን ህዝብ የሚያጠፋ ሃይል እየመጣ ነው" በሚል ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ነበር ይላሉ ነዋሪዎቹ።
በዚህም በርካቶች ፍርሃት አድሮባቸው የነበረ ቢሆንም የአገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን እውነታውን ተረድተነዋል ብለዋል።
ሰራዊቱ ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ብዙዎቻችን ከችግር፣ ውጥረትና ፍርሃት ወጥተን ወደ ሰላማዊ ህይወት ገብተናል ነው ያሉት።
ህወሃት ሲያሰራጨው በነበረው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ፍራቻ አድሮብን የነበረ ቢሆንም፤ ሰራዊቱ ከተማዋን ሲቆጣጠር ህዝባዊነቱንና አብሮነቱን አሳይቶናል ብለዋል።
የህወሃት ታጣቂ ቡድን ከሽሬ በመውጣቱ ከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷንና የተለያዩ አገልግሎቶችም መጀመራቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት በሽሬ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችንና የከተማዋን ነዋሪዎችን ሰብስቦ በማናገሩም ተደስተናል ብለዋል።
ሰራዊቱ ክልሉን ከዘራፊዎችና ግለኞች ነፃ በማውጣት የህዝብን ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ የመጣ መሆኑንም ተረድተናል ነው ያሉት።
በህወሃት ካድሬዎች ፕሮፓጋንዳ ከአካባቢው ርቀው የነበሩ የከተማዋ ነዋሪዎችም ሰላም መሆኑን በመረዳት ወደ ቤታቸው እየተመለሱ መሆኑን ገልጸዋል።
የህዝቡ ንብረት በዘራፊዎች አንዳይወሰድ የአገር መከላከያ ሰራዊት የተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች ላይ ጥብቅ ጥበቃና ክትትል በማድረጉም ተደስተናል ብለዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ከችግር፣ ውጥረትና ፍርሃት ተላቀናል በቀጣይ ከሰራዊቱ ጎን በመሆን ሰላማችንን እናስጠብቃለን ሲሉም ነው የተናገሩት።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የከተማዋ ነዋሪዎች አሁን ላይ ለሰራዊቱ መረጃ በመስጠትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ፍቅሩን አሳይቶናል፣ አረጋግቶናል፣ ህወሃት ከፈጠረብን ውጥረትና ፍርሃት አንድንወጣም አድርጎናል በማለት ገልጸዋል።

የህወሃት ጁንታ አክሱም ኤርፖርትን በ26 የተለያዩ አካባቢዎች በግሬደር አርሶታል
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የህወሃት የጥፋት ቡድን አክሱም ኤርፖርትን በ26 የተለያዩ አካባቢዎች በግሬደር እንዳረሰው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ተናገሩ።
ቡድኑ በአገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ባይወሰድበት ኖሮ በአካባቢው ላይ የከፋ ጉዳት ያስከትል እንደነበርም ታውቋል።
የህወሃት ጁንታ አሁን ላይ ተስፋ እየቆረጠ በመምጣቱ በተለይ የህዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጥፋት እየፈፀመ ይገኛል።
የጥፋት ቡድኑ የአክሱም ኤርፖርትን ከ23 አስከ 26 የተለያዩ አካባቢዎች በግሬደር በማረስ የህዝቡ ጠላት መሆኑን ማሳየቱን ከሰራዊቱ አመራሮች መካከል ሻምበል አብይ ሩፋኤል ገልጸውልናል።
ጁንታው በሰራዊቱ አፋጣኝ አርምጃ ባይወሰድበት ኖሮ ኤርፖርቱን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም ቅርሶችን ሙሉ ለሙሉ የማውደም እቅድ ነበረውም ብለዋል።
የህወሃት ፅንፈኛ ሃይል በፊትም ለጥፋት የቆመ ሃይል ነው ያሉት ሻምበል አብይ፤ አሁን ደግሞ በይፋ የህዝብ ጠላትነቱን አሳይቷል ብለዋል።
በአክሱም ኤርፖርት የፈፀመውም የአውሮፕላን መንደርደሪያውን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመቆፈር ጉዳት አድርሷል።
በኤርፖርቱ ህንፃ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችንና ቅርሶችንም መዝረፉን ገልጸው፤ በሰራዊቱ ፈጣን እርምጃ ባይወሰድበት ኖሮ አካባቢው ላይ ተጨማሪ ጥፋት ያደርስ ነበር ብለዋል።
የህወሃት ጁንታ እየፈፀመው ያለው ተግባር የህዝብ ግልፅ ጠላት መሆኑን በአደባባይ ያረጋገጠ መሆኑን ሌላው የሰራዊቱ አመራር ሌተናል ኮሎኔል ወልዴ ሃይሌ ገልጸውልናል።
የጥፋት ቡድኑ በአገር መከላከያ ሰራዊት ፈጣን እርምጃ ባይወሰድበት ኖሮ በአካባቢው ላይ ሌላም የከፋ ጉዳት ያስከትል ነበር ያሉት ደግሞ ሻምበል ባሻ ሙላት ናቸው ።
የህወሃት ጁንታ የተለያዩ የእምነት ተቋማትን እንደ መደበቂያ በመጠቀም ጉዳት እንዲደርስባቸው ጥረት እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሌተናል ኮሎኔል ተመስገን ነጋ እንዳሉትም የህወሃት ታጣቂ ሃይል በተለይም ቤተክረስቲያናትን፣ መስጅዶችና ቅርሶች የሚገኙባቸውን አካባቢዎች በምሽግነት እየተጠቀማቸው ይገኛል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት ግን እስካሁን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የኦፕሬሽን ስራውን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የትግራይ ህዝብ የህወሃት ፅንፈኛ ቡድን እኩይ አላማ እና የጥፋት ተልእኮ ተረድቷል ያሉት አመራሮቹ፤ ለአገር መከላከያ ድጋፍና እገዛ እያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።
ህወሃት ለህዝብ የማያስብ፣ ሴረኛ፣ አጥፊና ለራሱ ህልውና ብቻ የሚያስብ የጥፋት ስብስብ መሆኑን የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ በአግባቡ ተገንዝቦታልም ብለዋል።

“የህወሓት ጁንታ አዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ ያላቸው ጄኔራሎችን ፈጥሯል”
– አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ረዳ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
መሰሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሆነ ፖለቲካ በቤተሰብ ኔትዎርክ በመያዝ አገሪቷን ሲዘርፍ መኖሩን የትግራይ ክልል የሽግግር ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት እና የድርጅት ንቅናቄ ዘርፍ አባል አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ረዳ አስታወቁ። ቡድን ሲፈጠር ጀምሮ ከአንድ ቤተሰብ (ከስብሃት ነጋ ቤተሰብና አከባቢ) የወጣ መሆኑንም አመለከቱ።
አቶ ሊላይ ኃይለማርያም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳመለከቱት፣ መሰሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን ሲፈጠር ጀምሮ ከአንድ ቤተሰብ (ከስብሃት ነጋ ቤተሰብና አካባቢ) የወጣ ነው ። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካ በዚህ የቤተሰብ ኔትዎርክ በመያዝ አገሪቷን ሲዘርፍ ኖሯል። በዚህም በቤተሰብና በአካባቢ ተደራጅቶ ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ሀብት ሲዘርፍ የቆየው የህወሓት ጁንታ ቡድን አዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንጻ ያላቸው ጄኔራሎችንም ፈጥሯል።
“ከስብሃት ነጋ ቤተሰብና አካባቢ የወጣው ይህ መሰሪ ቡድን ስልጣኑንም ኢኮኖሚውንም ለመቆጣጠር እንዲመቸው ሲል ከቤተ መንግስት እስከ ቤተ ክህነት ያለውን መዋቅር ሁሉ ተቆጣጥሯል። ለዚህ ደግሞ ስብሃት ነጋ መጀመሪያ አዲስ አበባ እንደገባ እና ስልጣን እንደያዘ አቡነ ጳውሎስን ከአሜሪካ አስመጥቶ ቤተ ክህነቱን አስያዘ። አቡነ ጳውሎስ ማለት ደግሞ የእነሱ ቤተሰብ ናቸው። አራት ኪሎ ቤተ መንግስቱን በመለስ አስያዙ፤ የመቀሌውን ቤተ መንግስት ደግሞ በቅዱሳን ነጋ ባል በአለቃ ፀጋዬ ነው የያዙት። እንዲህ አድርገው ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት ከተቆጣጠሩ በኋላ፤ ሁሉንም ነገር በኔትዎርክና በቤተብ ወደሚሰራ ሥርዓት አስገቡት” ብለዋል ።
ለምሳሌ፣ ቤተ ክህነት አንድ ህንጻ ቤተክርስቲያን ለማሳደስ ጨረታ ያወጣል። እናም አቡነ ጳውሎስ ያለምንም ጨረታ በአምስት ሚሊዮን ብር ጨረታውን ለኮሎኔል በላይ ይሰጡታል። ይሄ ሰውዬ ደግሞ ላይሰንስ የለውም፤ ኢንጂነርም አይደለም፤ ጡረታ የወጣ የደርግ ኮሎኔል እንደሆነ አመልክተዋል።
ሲኖዱሱም በአንድ ሚሊዮን የሚሰራ ስራ እንዴት በአምስት ሚሊዮን ይሰጣል በሚል ይሄንን አካሄድ ይቃወማል። የእሳቸውም ፀሃፊ የነበረውም በተመሳሳይ በመቃወሙ ጨረታው ይቆማል። ጨረታ ይውጣ ሲባል፣ 700 ሺህ፣ 800 ሺህ፣ አንድ ሚሊዮን የሚል ይወጣል። እሳቸው ደግሞ ይቆይ ብለው ያቆዩትና ከአንድ አራት ወር በኋላ በአምስት ሚሊዮን ብር ለእሱ ሰጥቼዋለሁ ብለው ያዛሉ። የዛኔም የሳቸው ፀሐፊ የነበረው በዚህ መልኩ አልሰራም ብሎ ስራውን ትቶ ወጥቷል። ከዛም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የስብሃት ነጋ ኔትዎርክ ሰዎች ናቸው ተሰብስበው እንዲገቡ የተደረገው እና የቤተ ክህነቱ የቢዝነስ መስመር በሙሉ ለእነሱ እንዲሰጥ ተደርጎ ሚሊየነር ሆነዋል ብለዋል።
እንደ አቶ ሊላይ ማብራሪያ፤ ከዚህ በተጓዳኝ የስዩም መስፍን፣ የስብሃት ነጋ እና የሌሎቹም ዘመዶቻቸው በኤርፖርት ይግቡ በጅቡቲ የጉምሩክ ታክስ ከፍለው አያውቁም። በአዲስ አበባ ተሸንሽኖ የተወሰደው መሬት ውስጥ አንዳቸውም በሊዝ ገዝተው አያውቁም፤ በሊዝ የገዙም ካሉ በሳንቲም ቤት ነው የሚገዙት። ይሄን ደግሞ ፋይሉን ከማዘጋጃ ቤት ወይም ከተማ ልማት ሊገኝ የሚችል ነው። እናም እነዚህ ሰዎች በሁሉም መስክ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረውት ቆይተዋል። ሌላው ቀርቶ ኮትሮባንድ ንግድ ከአብዲ ኢሌ ጋር ሆነው ሲሰሩ እንደነበር አመልክተዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=42253

የተሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው
መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑም ተገልጿል።
ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናው አቅርቧል።
"በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ፣ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን" ጥሪ ቀርቧል።

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች 40 የበሬ ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ74.8 ሚሊዮን ብር በላይ የቁሳቁስና ጥሬ ገንዘብ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ።
የጉሌሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጁንታው ህወሓት የጥፋትቡድን ላይ እየወሰደ ያላውን የህግ ማስከበር እርምጃ ለመደገፍ ለሰራዊቱ የሚሆን 40 የበሬ ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎቹ ያደረጉትን ድጋፍ የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ከመከላከያ ሰራዊቱ ተወክለው የተገኙት ብርጋዴል ጄነራል ደሳለኝ ደቼ አስረክበዋል፡፡
በርክክቡ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እንደገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተፈፀመን ጥቃት ለመመከት እየተዋጋ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡
ለሰራዊቱ በሁሉም ደረጃ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች እያደረጉት ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት አቶ መለሰ በስካሁኑ ድጋፉን በማስተባበር እና ድጋፍ በማድረግ ተሳትፎ ላደረጉ አካላት በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመከላከያ ሚኒስቴር የቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄነራል ደሳለኝ ደቼ በበኩላቸው፣ ህግ የማስከበር ስራዎች የህዝቡን ድጋፍ የሚሹ ናቸው፤ 100 የማይሞላውን የጥፋት ቡድን 100 ሚሊየን በላይ በሚልቅ የህዝብ ድጋፍ ድል እናደርጋለን” ብለዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ አባወይ ዮሃንስ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ነዋሪዎች፣የመንግስት ሰራተኞች ፣ባለሀብቶች፣የጤና ባለሙያዎች ፣መምህራን፣ነጋዴዎችና በተለያየ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ነዋሪዎች በፈቃደኝነት የለገሱት መሆኑን ገልጸዋል።

ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት የፈጸመውና ተኩስ የጀመረው ላለፉት 27 አመታት የሰራቸውን ወንጀሎችና ጥፋቶች ለመሸፋፈንና ከተጠያቂነት ለማምለጥ አስቦ እንደሆነ የቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊትና ላይ ጥቃት የፈጸመውና ተኩስ የጀመረው ላለፉት 27 አመታት የሰራቸውን ወንጀሎችና ጥፋቶች ለመሸፈፈን ብሎም ከተጠያቂነት ለማምለጥ አስቦ እንደሆነ የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።
አቶ ኃይለማርያም ለፎሬን ፖሊሲ መጽሄት በጻፉት ሰፋ ያለ ጽሁፍ፤ እርሳቸው በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የከሀዲው ህወሓት አመራሮችን ባህሪና ጥፋት ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ገልጸዋል።
ይሄው የህወሓት ከሀዲ ቡድን በማዕከላዊ መንግስት ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ከፈጸማቸው ጥፋቶች ለማምለጥ ሲል ወደ ተኩስ ገብቷል ነው ያሉት አቶ ኃይለማርያም።
ላለፉት 27 አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ብሎም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሰሩት ብሄር ተኮር መከፋፈሎች አገሪቷን ወደ ቀውስ ውስጥ እንደሚያስገባትና በዚህ መሀል እነሱ የራሳቸውን ሰዎችና አቅም ተጠቅመው የሚፈልጉትን ማድረግ እንደሚችሉ አድርገው ያስቡ ነበር ያሉት አቶ ኃይለማርያም፤ ነገሩ ግን በተቃራኒው ሄዶባቸው የፌዴራል መንግስቱን እና ኢትዮጵያዊያንን ከመቼውም በላይ አንድ አድርጎ እንዳጠናከራቸው አብራርተዋል።
መንግስትነ ህዝቡም ወንጀለኞችን ለፍትህ ለማቅረብ የተቀናጀ ስራ እንዲሰሩ አስችሏቸዋል ሲሉም ነው አቶ ኃይለማርያም የገለጹት።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን ከዚህ በፊት ሲፈጽመው ከነበረውና አሁንም እየፈፀመው ካለው ወንጀል ራሱን ለማስመለጥ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ እንደሆነ የገለጹት አቶ ኃይለማርያም፤ ድርድር የሚለውም ለጊዜ መግዣና ችግሩን ዓለም አቀፍ ይዘት ለማሰጠት በዚህ መሀልም ወንጀሉን ደባብቆ ለማስቀረት ከተሳካለትም ስልጣን ለመጋራት ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ድርድር የሚባለው ጉዳይ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የማይሆን መንገድ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ኃይለማርያም፤ መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ በአስቸኳይ ንፁሃን የክልሉን ነዋሪዎች በማይጎዳ መልኩ ፈጽሞ ከሀዲ ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ብቸኛው መፍትሄ ነው ሲሉ ከከሃዲው ጁንታ ባህሪ ተነስተው አብራርተዋል።

በከሀዲው ህወሓት ቅጥረኛ ኦነግ ሸኔ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አንጸበራቂ ድሎችን በማስመዘገብ ላይ ይገኛል ሲሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አስታወቁ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ህዝብን የሚወጉ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪውና ቅጥረኛው የኦነግ ሸኔ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አንጸበራቂ ድሎችን በማስመዘገብ ላይ ይገኛል ሲሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
ለዝግጅት ክፍላችን የተላከው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ መልዕክት እንደሚገልጸው፤ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪና ቅጥረኛው የኦነግ ሸኔ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊስ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አንጸበራቂ ድሎችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር ተልዕኮውን በድል አጠናቆ ወደ ቀድሞው መደበኛው ስራው እስኪመለስ ድረስ ህዝባችን እስከ ህይወት መስዕዋትነት ከጀግናው መከላከያችን ጎን ለመቆም የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኦነግ ሸኔን በመጠራረግ ህዝቦች፣በወንድማማችነት፡በዕኩልነት፡በፍቅርና በሰላም ሚኖሩባትን ኢትዮጵያና ኦሮሚያ እናስቀጥላለን በለዋል።

ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ባጋጠመን የቴክኒክ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ባጋጠመን የቴክኒክ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
በቴክኒክ ችግር የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የቴክኒክ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የማይካድራ ሲቪል ሰዎች ጭፍጨፋ የግፍና ጭካኔ ወንጀል ነው:: ጭፍጨፋው በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን መካሄዱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አረጋግጧል
****************
(ኢፕድ)
ኮሚሽኑ ለኢፕድ በላከው መግለጫ በማይካድራ የተጎዱትን ማቋቋም እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል ብሏል::
በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል (crimes against humanity) እና የጦር ወንጀል (war crime) ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ስለሆነ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡
በቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡ ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን በአገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል፡፡
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹በማይካድራ ከተማ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል፤ ስለ ወደፊት በሰላም አብሮ መኖርም ተስፋ ይሰጣል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹የተጐዱ ሰዎችን እና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና ከመጠገን በተጨማሪ፤ በዚህ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ገለፁ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ዛሬ ሮም ጣሊያን ገብቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ አቅርበዋል።
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ደመቀ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ሁለቱ ሃገራት ረጅም ዘመን የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ወደ ተሻለ የትብብር ከፍታ ለማድረስ ጠንክረው እንደሚሰሩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የኢትዮጵያና የቻይና የንግድ ግንኙነት 26 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ
****************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት 50 ዓመታት የኢትዮጵያ እና የቻይና የንግድ ግንኙነት 26 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ቻይና የኢትዮጵያ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በልማት የነበራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያሰቆጠረ መሆኑ ሚኒስቴሩ ጠቅሶ፣ እ.ኤ. አ. ከ2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ መጠን በ26 በመቶ አድጓል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራ ከምትልካቸው ምርቶች የኢትዮጵያ ቡና እና አበባ በቻይና ገበያ ውስጥ በሰፊው ተወዳጅ ናቸው፡፡ የሰሊጥ ምርትም በቻይና አንድ አሥረኛ ድርሻ አለው፡፡
በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው ከሚገኙ ቻይና ኩባንያዎች ከአንድ ሺህ 500 በላይ ፕሮጀክቶች አንድ ነጥብ 153 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ አጠቃላይ ኢንቨስትመንት 60 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሰራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡
ቻይናና ኢትዮጵያ በአምባሳደሮች ደረጃ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ 50ኛ ዓመትን እያከበሩ ባለበት በዚህ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ጠንካራ የንግድ፣ የኢንቨስትምንት፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትስስር ፈጥረዋል ፡፡
በወንድማገኝ አሸብር

የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ተገለጸ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን እንዳጠናቀቀ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን መግለፃቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን እንዳጠናቀቀ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን መግለፃቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑም ተገልጿል።
ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናው አቅርቧል።
"በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ፣ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን" ጥሪ ቀርቧል።
************
(ኢ.ፕ.ድ)
መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑም ተገልጿል።
ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናው አቅርቧል።
"በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ፣ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን" ጥሪ ቀርቧል።
በሰበታ ከተማ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሰበታ ከተማ 04 ቀበሌ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ ጉዳት ሳያደርስ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ፡፡
ፈንጂው መሀመድ ረጃ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የተገኘ መሆኑን የሰበታ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
መስጂድ አቅራቢያ ላይ መጠመዱ በተቋሙና በምዕመናን ላይ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የተፈፀመ መሆኑን የቀበሌው አስተዳደርና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ተሬሳ ገልፀዋል፡፡
እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ፤ ይሁንና በህብረተሰቡ ጥቆማ ጉዳት ሳያደርስ መክሸፉን ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጥቆማ ሲደርሰው በፍጥነት ወደ አካባቢው በማምራት የማክሸፍ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
ህብረተሰቡ አካባቢውን ከጥፋት ኃይሎች በንቃት እንዲጠብቅና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲታዘብ ጥቆማ እንዲያደርሰው የከተማው ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ
********
(ኢ.ፕ.ድ)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ብራሰልስ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል።
ኮሚሽነሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለህብረቱ ስትራቴጂያዊ አጋር ሃገር መሆንዋን የጠቀሱት፤ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ንፁሃን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥበት መንገድ ለማመቻቸት በመንግሥት የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።
አቶ ደመቀ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአለምአቀፍ የሰብዓዊ ህግ ተፈፃሚ ለማድረግ ነባራዊ ሁኔታውን በማጥናት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የሚደረግበትን አግባብ አስረድተዋል።
ንፁሃን ዜጎች ለከፋ ቀውስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሲል የምክትል ጠቅላይ ሚኒ