ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተላለፈ መልዕክት
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ለስግብግቡ ጁንታ ግፍ እስትንፋሱ፣ ጭካኔ ነፍሱ ነው። ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ሽራሮን ሲቆጣጠር፣ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታሥረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን አግኝቷል። ጭካኔው ልብ ሰባሪ ነበር።
ዓላማው ኢትዮጵያን መስበር ነው።
አላወቁም ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን።
ዓላማው ሠራዊታችንንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል ርምጃ ማነሣሣት ነው።
አላወቁም ልበ ሰፊ ሕዝብና ሠራዊት እንዳለን።
በየቦታው ስንደርስ ከዚህ የከፋ ጭካኔና ግፍ ሊገጥመን ይችላል። ይህ ግን ለዚህ ጁንታ የመጨረሻው ነው። ጥንቃቄያችን 'ሙት ይዞን እንዳይሞት' ነው። መፍጠን አለብን፤ የተረፉትን ለመታደግና ግፍ የተፈጸመባቸውንም ለዓለም ለማጋለጥ።
የምዕራቡን የትግራይ ክልል ቀጣና ነጻ ወጥቷል። በዚያ ቀጣና ሠራዊቱ ሰብዓዊ ርዳታና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ነጻ ባወጣቸው አካባቢዎች ሕዝቡን እየመገበ፣ እያከመና እየተንከባከበ ነው።

የከሀዲው የህወሓት ቡድን መሪዎች ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።
በዚህም መሰረት፦
1. ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
3. አቶ አባይ ፀሃዬ
4. ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አፅበሃ አረጋዊ
7. አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ
መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣
የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና
አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል።

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስም ዝርዝር
***********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እነማን ናቸው?
1. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ
3. አቶ አባይ ጸሀዬ
4. አምባሳደር ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አጽብሃ አረጋዊ
7. አቶ ታደሰ ሀይሌ
8. ዶ/ር መብራቱ መለስ
9. ወ/ሮ ለምለም ሀድጉ
10. አቶ ገ/እግዚአብሄር አርኣያ
11. አቶ ሀለፎም ግደይ
12. አቶ ሀዱሽ አዛነው
13. ወ/ሮ መብራት ገ/ጊዮርጊስ
14. ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሄር
15. ወ/ሪት ልዕልቲ ጸጋዬ
16. ወ/ሮ ማሚት ተስፋይ
17. ወ/ሮ ማና አብርሃ
18. አቶ ካላዩ ገ/ህይወት
19. አቶ ጌዲዮን ሀ/ስላሴ
20. መ/ር በርሄ ዝግታ
21. አቶ ታደለ አሰፋ
22. አቶ ነጋ አሰፋ
23. ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴ
24. ወ/ሮ ሽሻይ ሀ/ሰላሴ
25. ወ/ሮ አልማዝ አርኣያ
26. ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ
27. ወ/ሮ አስቴር አማረ
28. አቶ አለምሰገድ ወረታ
29. ዶ/ር አድሃና ሃይለ
30. አቶ ኪሮስ ወ/ሚካኤል
31. አቶ ሹምዬ ገብሬ
32. አቶ ካሳ ጉግሳ
33. ወ/ሮ አበራሽ አድማሱ
34. አቶ ዮሀንስ በቀለ
35. አቶ ዳኘው በለጠ
36. ወ/ሮ ፅዋሃብ ታደሰ
37. አቶ ዊንታ ተክሉ እና
38. አቶ ግርማይ ሻዲ ናቸው፡፡
(ምንጭ፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት )

በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ መወሰኑን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ እንዳለው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን ዓላማ ወደ ጎን በመተው ለሌላ እኩይ ተግባር የመረጡዋቸውን በመመልመል፣ ለተቋም ጥበቃ የተሰጣቸውን የጦር መሳሪያ በማስታጠቅና በማሰማራት በህዝብና በመንግስት ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተደርሶባቸዋል ፡፡
ካለፈው ዓመት ጀምሮ ኤጀንሲዎቹ ባንኮችንና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉና ሲያዘርፉ ቆይተዋል። በዚህም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብና ንብረት ዘርፈዋል፤ እንዲዘረፍም አድርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቱን እንዲጠብቁበት የታጠቁትን በርካታ የጦር መሳሪያ ይዘው እንደጠፉም ተረጋግጧል። እነዚህ ከተልዕኮአቸው ውጭ እንደሚንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ይህም አልበቃ ብሏቸው አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በጁንታው የህዋሃት ወንበዴ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባትና የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ በህብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ መሆኑ ተደርሶበታል ብሏል ፖሊስ ።
ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተገለፀው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፦
1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ
2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ
6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ
7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ
8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
10. ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ
11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ
14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
ለሀገርና ለዜጎች ሰላምና ደህንነት ሲባል ስራቸውን እንዲያቆሙ የተወሰነና እስከአሁን ባለው አገር የማተራመስና ህገ-ወጥ ስራቸው በህግ የሚጠየቁ መሆኑን እየገለጽን ስማቸው ከላይ የተገለፀው የጥበቃ ተቋማት በአስቸኳይ ስራቸውን አቁመው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት እንዲያደርጉ እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት አካል ከነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ምንም ዓይነት ቅጥር እንዳይፈፅም የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስማቸው በተገለፀው የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ስር ተቀጥረው ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ሰራተኞችን በተመለከተ ማስተካከያ እስኪወሰድ የጥበቃ ስራቸውን አጠናክረው እንዲሰሩ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

የአብረኸት እንባ
👉150 ጥይት ተስጥቶኝ አንድም ጥይት ሳልተኩስ ነው እጄን የሰጠሁት፤
ምክንያቱም በዚህ ውጊያ አላምንበትም
********************
(ኢ ፕ ድ)
አብረኸት የጁንታው ታጣቂ የነበረችና እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ከሰጡ ውስጥ አንዷ ነች። ገና የ21 አመት ወጣት ናት፡፡ ወጣቷ በ2011 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠና ወስዳለች፡፡ የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት አባል ሁና ነገሌ ቦረና ተመድባም ግዳጇን እየተወጣች ሳለ በጠና ታማ ከውትድርናው ዓለም ተሰናብታ ወደ ቤተሰቦቿ መመለሷን በስፍራው ተገኝቶ ላነጋገራት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅይ ዘጋቢ ገልጻለች።
የአብረኸት ህመም መጥናት ከምትወደው መከላከያ ቢለያትም ከጁንታው ዕይታ ግን መሰወር አልቻለችም። በጠላ ንግድ የሚተዳደሩትን እናቷን እያገዘች ኑሮን ብትቀጥልም፤ የጁንታው አባላት የአብረኸትን ወታደርነት ያውቁ ነበርና የጁንታውን ታጣቂ እንድትቀላቀል በእናቷ በኩል ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ጁንታው የአብረኸትን እናት ሌት ተቀን በማስፈራራታቸው ልጃቸውን ሳይወዱ በግድ ለታጣቂው አስረከቡ፤ አብረኸትም ቤተሰቦቼን ለአደጋ ከማጋልጥ በሚል ታጣቂውን ተቀላቀለች።
“ሌላ ስራ በቀላሉ ማግኘት ስላልቻልኩና ጫናውና ማስፈራሪያው ሲበዛብኝ ታጣቂውን ተቀላቀልኩ። የቤተሰቡ አባላት ሰባት ነን ፤ አባቴ በህይወት የለም፡፡ እናቴ ብቻዋን ነው ጠላ ሽጣ ያሳደገችኝ፡፡ እሷን ለማገዝ ስልም ነው ወደዚህ የገባሁት” ስትልም ነው የታጣቂው አባል የሆነችበትን አጋጣሚ የምታስታውሰው።
አብረኸት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እየወሰዱት ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ላይ እጇን የሰጠችው አንድም ጥይት ሳትተኩስ መሆኑን ትናገራለች፤ “150 ጥይት ተስጥቶኝ አንድም ጥይት ሳልተኩስ ነው እጄን የሰጠሁኝ። ምክንያቱም በዚህ ውጊያ አላምንበትም። እየሞተ ያለውም የደሀው ልጅ ነው። እጄን ከሰጠሁ በሁዋላም ቢሆን ሶስት ቀን ሙሉ የሰራዊቱ አባላት ከሚበሉትና ከሚጠጡት እያካፈሉኝ ቆይቻለሁ።
በትግራይ ክልል በየአካባቢው ያለው ወጣት ተገዶ ወደ ግዳጅ እንዲገባ ተደርጓል የምትለው ወጣቷ፤ ስልጠና የሚሰጠውም የይድረስ ይድረስ መሆኑን አልሸሸገችም፤ “ለአጭር ጊዜ ክላሽ እንዴት እንደሚፈታና እንደሚገጠም፣ ኢላማ እንዴት እንደሚመታ አሳይተው ብቻ ነው ወደ ጦርነት የሚማግዷቸው፡፡ ይህ ደግሞ የህወሓት አመራሮች ለትግራይ እናቶችም ሆነ ወጣቶች ደንታ እንደሌላቸውና የራሳቸውን የስልጣን ጥም ለማርካት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ያሳያል” ነው ያለችው፤ አብረኸት፡፡
“የህወሓት አመራሮች፤ የትግራይን ህዝብ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እንደሚጠላው፣ የትም ሄደው በሰላም መኖር እንደማይችሉ አድርገው ወጣቱንንም ሆነ ህጻናትን ጭምር ይሰብካሉ። ሁሉም የትግራይ ህዝብ የዚህ አይነት አስተሳብ ስላለውና ህወሓትን ስለሚፈራ የሚሉትን ለማድረግ ይገደዳል። ይህ ሰላም የማይወድ ድርጅት ውጤት ለማያመጣ ነገር ወጣቱን እያስፈጀ ነው” ብላላች፤ አብረኸት።
የህወሓት ጁንታ ወጣቱን መስዋዕት የሚያስከፍሉት የማይሆን ነገር እየሞሉት፣ እያስገደዱትና፣ በገንዘብም እያታለለሉት ጭምር መሆኑን አብረኸት ትናገራለች።
የትግራይ ህዝብ መከላከያን እንዲወጋ አይፈልግም፤ ምክንያቱም መካላከያ የትግራይ ህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለህብረተሰቡ ትምህርት ቤት እየሰራ፣ ጤና ጣቢያ እየገነባ የኖረ ወገን ነው፤ የምትለው አብረኸት፤ “ወርቅ ለአበደረ ጠጠር እንዲሉ እኛን አታለው እንደ ቤተሰብ የምናየውን መከላከያ ሰራዊትን እንድንወጋ አድርገውናል” ያለችው በከፍተኛ ጸጸት ውስጥ ሆና ነው።
“የህወሓት ቡድን እንደሚለው መከላከያ እኛን ቢጠላን ኖሮ እንዴት ትግራይን ይጠብቃታል” ስትልም ትጠይቃለች። “እኛ ምንግዜም ኢትዮጵያዊ ነን፤ አጸያፊ ስራ እስካልሰራን ድረስ ህዝቡ ዝም ብሎ አይጠላንም፡፡ በመሆኑም የትግራይ ወጣቶች ዓላማ የሌለው ጦርነት ውስጥ መግባት የለባቸውም። ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን በመስጠት በሰላም መኖር ይኖርባቸዋል” ስትል ሀሳቧን ቋጭታለች።
በጌትነት ምህረቴ

"በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ በተሠማሩ ሥርዓት አልበኞች፣ በተንኮልና በሤራ በተሞሉ የሕወሐት ቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑ ማንም ሰው ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
**************
(ኢ ፕ ድ)
"በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ በተሠማሩ ሥርዓት አልበኞች፣ በተንኮልና በሤራ በተሞሉ የሕወሐት ቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑ ማንም ሰው ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም" ሰል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
ሕወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መለየት
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ሕገ ወጥ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ ያረጋግጣል:: ነገር ግን ይህ ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ አጥብቆ ያወግዛል፡፡
በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ በተሠማሩ ሥርዓት አልበኞች፣ በተንኮልና በሤራ በተሞሉ የሕወሐት ቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑ ማንም ሰው ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም፡፡
በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ ሳይቀር የከፋ በደል የሚፈጽመውን ይህን የሕወሐት ጁንታ የወንጀል ሰንሰለት ለማስቆም የፌዴራሉ መንግሥት ቆርጦ ተነሥቷል፡፡
በዚህ ሕግ የማስከበር ዘመቻ የትግራይ ሕዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ለኢትዮጵያ ያለን ራእይ በብዝኃነት የሚኮሩ ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት የሚኖሩባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን ነው። በዚህ ሕዝባችን ላይ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር እንዲደርስ አንፈልግም። ይሄንን የሚያደርጉትንም አንታገሥም።
ኅዳር 9 ቀን 2013
አዲስ አበባ

የሕወሐት ጁንታ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ ነው።
***********
(ኢ ፕ ድ)
የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው ጁንታ፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቀሌ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮችን አፍርሷቸዋል።
የተማመነባቸው ከባድ ምሽጎቹ ፈራርሰው፣ በሽሬ መንገድ የደረሰበት ሽንፈት ያንገበገበው ጁንታ፣ በሽሬና በአኩስም መካከል የሚገኘውን አስፓልት በግሬደር ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታል።
የሕወሐት ጁንታው እስከዛሬ ከፈጸማቸው ወንጀሎች በተጨማሪ ባወደማቸው መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ይጠይቅባቸዋል።
ምንጭ: የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

የማይካድራው ጭፍጨፋ የዓይን እማኝ
******************
(ኢ ፐ ድ)
መላ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፤ ከንፈሩ ደርቋል። ለሁለት ቀናት ምግብ አላገኘም። ድንጋጤ አለቀቀውም። ከማይካድራ ግድያ አምልጦ ሁመራ ከተማ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በር ላይ ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ማሚን።
የደቡብ ክልል የቴፒ ተወላጅ ነው፤ አገር ሰላም ብሎ በማይካድራ ልብስ እየነገደ መኖር ከጀመረ 13 ዓመት ሆኖታል። በዚች ከተማ ይህን ያህል ሲኖር የከፋ አይደለም፤ ቀለል ያለ ችግርም አጋጥሞት አያውቅም። በሚኖርባትና ህይወቱን ለማሻሻል በሚደክምባት ከተማ ቤትና ንብረትም አፍርቷል።
ከሰባት ቀናት በፊት ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በማይካድራ ከተማ በአማራና በሌሎች ብሄሮች ተወላጆች ላይ ያልታሰበ፣ አስደንጋጭና ዘግናኝ ግድያ ሲፈጸም በዓይኑ ተመልክቷል ፤ እሱም ከዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አምልጦ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ወደ ዋለችው ሁመራ ከተማ መምጣቱን ይናገራል።
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች በአማራና በሌሎች ብሄሮች የፈጸሙት ግፍና ግድያ በጣም የሚያስደነግጥ ያልታሰበ ነበር የሚለው ወጣቱ፤ በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ በምንኖር ንጹሐን ሰዎች ላይ በትግራይ ሚሊሻዎችና ልዩ ኃይሎች ዘግናኝ ጥቃት ይደርስብናል ብለን አስበንም አልመንም አናውቅም። ግን የጭካኔያቸው ጭካኔ በከተማዋ በሚኖሩ አማራን ጨምሮ በሌሎች ብሄሮች ዘግናኝ ድርጊት ፈጸሙ ይላል።
“መጀመሪያ ላይ ጥቃቱን የጀመሩት በወልቃይት አማራዎች ላይ መሆኑን የሚገልጸው ወጣት ዳንኤል ንጹሐን ሰዎችን በየመንገዱ እየደበደቡ፤ በሳንጃ አንገታቸውን እየቀሉ ሲገሏቸው ተመልክቻለሁ። ሰው ሮጦ እንዳያመልጥ እንኳን መንገዱ በሚሊሻ ተከቧል። ሩጠው ለማምለጥ የሚሞክሩትን በጭካኔ በጥይት እየመቱ ገድሏቸዋል” ብሏል ።
በአይኔ ሰው ሲገደል አይቻላሁ። እኔም የዳንኤል ቤት የትኛው ነው እያሉ ሲጠይቁ ሰምቼ ሩጬ ማምለጥ ችያለሁ የሚለው ወጣቱ፤ በዚህ ቀውጢ ስዓት እሱም ሆነ ብዙ በርካታ ሰዎች እየሮጡ ጫካ ባይገቡና ባያመልጡ ኖሮ በማይካድራ ከተማ በግፍ እንደተገደሉት ንጹሐን ሰዎች ሁሉ የእሱም ዕጣ ፋንታ በህወሓት አሸባሪ ቡድን ይገደል እንደነበር ነግሮናል።
ሰዎች ሲገደሉ በዓይኑ ማየቱን የሚገልጸው ወጣት ዳንኤል ሁለቱ ከድብደባው ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ሁለቱ ደግሞ በሳንጃ አንገታቸውን ተወገተው አስፓልት ላይ ሲወድቁ እግሬ አውጪኝ ብሎ ከአካባቢው ተሰውሮ ጫካ መግባቱን ንግሮናል። ሰው በጭካኔ እየተገደለ ባየሁበት ከተማ ለመኖር አልጓጓም ያለው ወጣቱ ከሁመራ ወደ ጎንደር ከዚያም ወደ ትውልድ አገሩ ቴፒ ለመሄድ መወሰኑን ገልጾልናል።
ወጣት ዳንኤል፤ በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ የህወሓት ጸንፈኛ ቡድንን ያልደገፈ የሚደርስበት ጫና እንግልት ከፍተኛ መሆኑን ይናገራል። ለትግራይ ልማት የሚሆን ገንዘብ አዋጣ ሲሉኝ 100.00 ብር አዋጣሁ። ሁለተኛ ዙርም ለውጊያ አዋጣ አሉኝ ። እኔም ውጊያውን ስለማላምንበት ብር የለኝም አልኳቸው። ለካስ ያላዋጣነው ሰዎች የቀበሌው የህወሓት ተላላኪዎች የስም ዝርዝራችንን ይዘው ኑሯል፤ጊዜ ጠብቀው የበቀል ጭካኔያቸውን አወረዱብን።
በየመኖሪያ ቤታችን እየዞሩ እስከ ወዲያኛው ሊያስናብቱን እየገሰገሱ መጡ። እግዜአብሄር አትርፎኝ ይኸው ሁመራ ከተማ አግኝተኸኛል” ሲል የጭካኔያቸው ጥግና የበቀል ዕርምጃቸው ከባድ መሆኑን ገልጾታል።
ማይካድራ ከተማ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከትግራይ ቴሌቪዥንና ከወያኔ ድምፅ ቴሌቪዥን በስተቀር ሌሎች የቴሌዥን ጣቢያዎችን ማየት ወንጀል ነው የሚለው ወጣቱ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ዋልታ፣ ፋና ቴሌቪዥንና ሌሎች ህወሓት የሚጠላቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ማየት ፈጽሞ የተከለከለና የሚያስቀጣ ነው። ሲያይ የተገኘም ካለ በህይወቱ የፈረደ ሰው ብቻ ነው ይላል።
ማይካድራ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል ማይካድራ ለምን አትምለስም የሚል ጥያቄ አቅርበንለት የወጣቱ ምልሽ ሌላ አካባቢ ሊስትሮም ቢሆን ሠርቼ መኖርን እመርጣሉሁ እንጂ ሁለተኛ ትግራይ ክልል አልኖርም። ምክንያቱም ያየሁት የጭካኔ አገዳዳል ለሌት በህልሜ ይመጣብኛል። ዘግናኝ ነው። ይህን እያስብኩ እዚያ ከተማ መኖር አልፈልግም። ህይወቴ ተመሰቃቅሏል ሲልም ያየው የጭካን ተግባር የቱን ያህል እንደጎዳው፣ ከቃላቶቹ በላይ ሁኔታውን ሲያስታውስ የሚሰማው ስሜት ይናገራል።
በጌትነት ምህረቴ
አዲስ ዘመን ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም

ከሀዲው ጁንታ ቤተ ክርስቲያኖች ውስጥ በመጠለል ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እየተኮሰ መሆኑን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ከሀዲው ጁንታ ቤተ ክርስቲያኖች ውስጥ በመጠለል ከቤተ ክርስቲያን ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እየተኮሰ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።
የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታምዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከሀዲው የህወሓት ጁንታ ከፍተኛ የሆነ ሽንፈት ስለደረሰበት እና አብዛኛውን ግዛቱን እየተነጠቀ ስለሆነ ወደ ጥፋት ተልዕኮ እየገባ ነው።
እንደ ጠቅላይ ኢታምዦር ሹሙ ገለጻ፤ የጁንታው ታጣቂዎች ቤተ ክርስቲያኖች ውስጥ በመጠለል ከቤተ ክርስቲያን ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እየተኮሱ ነው፡፡ ኮማንድ ፖስቶቹንና ተተኳሾቹን ቤተክርስቲያን ላይ አድርጓል።
የመከላከያ ሰራዊቱም ይሄንን በመገንዘብ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዘራፊው ጁንታ በግሬደርና በዶዘር ታግዞ በከፍተኛ ሃብት የተሰራውን የአስፓልት መንገድ እየቆረጠ እና ድልድይ እያፈረሰ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ለመግታት ሙከራ እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት ጄኔራል ብርሃኑ፤ ለአብነት ያህልም በጨርጨር ግንባር ሶስት ድልድዮችን ማፍረሱን አስታውቀዋል።
በወንድወሰን ሽመልስ

በምዕራብ ወለጋ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሰራ ስራ 142 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሰራ ስራ 142 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ እንደተወሰደ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ በምዕራብ ወለጋ በጉሊሶ ዞን በአርሶ አደሩ ላይ ከተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ወዲህ የኦሮሚያ ፖሊስ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ቀጥለዋል።
በቅርቡም 142 በሚሆኑ የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገለጸው፤ 48 አባላት እጅ የሰጡ ሲሆን 64 የሚሆኑት ደግሞ ከህብረተሰቡ ውስጥ ቢቀላቀሉም እየተያዙ እንዳለም ተናግረዋል፡፡
እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ፤ ከሁለት ሳምንት ወዲህ በቅንጅት በተሰራው ስራ ይህንን ቡድን ከኦሮሚያ ለማፅዳት ጫካ ላለው ኦነግ ሸኔ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 1 ሺህ 341 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለውል። ከነዚህ ውስጥ 104 የሚሆኑት የከሀዲው ህወሓት አባላት ናቸው፡፡
ቦንብን ጨምሮ 57 የጦር መሳሪያዎች ከ681 ጥይቶች ጋር መያዛቸውንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
አሁን ባለው ተጨባች ሁኔታ ኦነግ ሸኔ እና ከሃዲው የህወሓት ቡድን ለአንድ አላማ የሚሰሩ የጥፋት ሀይሎች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ኮሚሽነር መርዳሳ ማናገራቸውን የኦሮሚያ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል፡፡
በሀይማኖት ከበደ

ገቢዎች ሚኒስቴር በአራት ወራት ውስጥ ከ107 ነጥብ 8 ቢለዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት ለመሰብሰብ ካደቀው 104 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ 107 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ17.3 ቢሊየን ብር እድገት ማሳየቱን ጠቅሰው የህግ ተገዢነት ደረጃ መሻሻል፣ የተቋሙ ሰራተኛና አመራሮች ቁርጠኝነት መጨመር እና የገቢው መሰረትን ለማስፋት የተደረጉ ጥረቶች ገቢው እንዲጨምር ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል ናቸው።
እንደ አቶ ላቀ ገለጻ፤ የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችም በአራት ወራት መጠናከራቸውን ለገቢ አሰባሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው፡፡
ህግን ለማስከበር ከተከናወኑ ተግብራት መካከል የኮንትሮባንድ ክትትል አንዱ ሲሆን በወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የተገኘ መሆኑን አስታውቀዋል።
የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አካላት፣ የጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ባለቤት ያልተገኘላቸው ህንጻዎች 100 መድረሳቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፣ በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች፣ ታጥረው የሚገኙ መሬቶች እና የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ እየተደረገ ባለው ዳሰሳ እስካሁን 100 ህንጻዎች ባለቤት አልተገኘላቸውም።
እንደ ኢቢሲ.ዘገባ፤ ከዚህም በተጨማሪ ታጥሮ የተቀመጠ ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ባለቤት ሳይገኝለት ቀርቷል።
በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ወጣቶች በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንደሚደግፉ እና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚ ልዩ ዞን፣ አዳማ ከተማና የምስራቅ ባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ በራያ አላማጣ አካባቢ ለተሰማራው መከላከያ ሰራዊት 196 የእርድ ሰንጋና 230 ፍየሎች ድጋፍ አደረጉ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ራያ ቆቦ፡- በአዲስ አበበ ዙሪያ የኦሮሚ ልዩ ዞን ፣ የአዳማ ከተማና የምስራቅ ባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ በራያ አላማጣ አካባቢ ህግን ለማስከበር ለተሰማራው መከላከያ ሰራዊት 196 የእርድ ሰንጋና 230 ፍየሎችን በግንባር ተገኝተው ለሰራዊቱ አስረክበዋል፡፡
አቶ አብዱልጀሊል አብዱሮ የአዳማ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ በርክብክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ ከሀዲው የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሰራዊትና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ያነገበውን ሀገር የማፍረስ ዓላማ ለማኮላሸት መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር ርምጃ የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ይደግፋል፡፡
የጁንታው አበላት ሀገርን ለማፍረስ ሲል የፈጸማቸውን የሽብር ተግባራት የክልሉ ህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ እንዳወገዘ ገልጸዋል፡፡
ህዝቡ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም ድጋፉን እያሳየ እንደሚገኝ በመግለጽም ከተጠቀሱት ውስን የኦሮሚያ አካባቢዎች የተሰበሰበው ድጋፍ የሞራል ስንቅ ይሁን በሚል ይዘን መጥተናል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት ከፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚ ልዩ ዞንና ከአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የተሰባሰቡ 196 የዕርድ ሰንጋዎች እና ከምስራቅ ባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ 230 ፍየሎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለሠራዊቱ አስረክበዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ህዝብ መንግስት ተገዶ የገባበትን ህግ የማስከበር ርምጃ እንደሚደግፍና ከመከላካያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚቆም ገልጸዋል፤ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አቶ አብዱልጀሊል ገልጸዋል፡፡
የራያ አላማጣና አካባቢው ግንባር አመራር አባል ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን በበኩላቸው በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ተወካዮች ረዥም መንገድ ተጉዘው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ያደረጉትን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሰራዊቱ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ህዝቡ ከሰራዊቱ እኩል መቆጣቱ ለሀገሩና ለሰራዊቱ ያለውን ፍቅር፣ ክብርና ተቆርቋሪነት የሚያሳይ ነው፡፡
ለሰራዊቱ ድጋፍ በማድረግና ደጀን በመሆን ኦፕሬሽኑ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ የሚደረገው ርብርብ የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡
ሰራዊቱ ህዝብን በማቀፍ በተሰማራባቸው ህግን የማስከበር ዘመቻዎቹ ሁሉ ውጤታማ እንደሆነና በሚቀጥሉት ቀናትም ሌሎች ድሎች እንደሚሰሙ ተናግረዋል፡፡
አንድ ተዋጊ ምንም አይነት ዘመናዊ መሳሪያ ቢታጠቅ የህዝብ ድጋፍ ከሌለው ውጤታማ አይሆንም ያሉት ጀነራሉ እስከ አሁን የተገኙት ድሎችም የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ውጤቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ይህ ከሀዲ ቡድን ተደምስሶ ወይም በቁጥጥር ስር ውሎ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰላሟን ታገኛለች ብለዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅ ሰሙ ማሞ ፣ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንሳይ መኮንን ተገኝተው እንግዶቹን ተቀብለዋል፡፡ ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በኢያሱ መሰለ

ኢትዮ-ቴሌኮም ለሀገር መከላከያ የገቢ ማሰባሰቢያ የአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ ቁጥር ይፋ አደረገ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮ-ቴሌኮም ለሀገር መከላከያ የገቢ ማሰባሰቢያ የአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ ቁጥር ይፋ አደረገ።
ኩባንያው በዛሬው እለት ይፋ ያደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የአጭር የጽሁፍ መልዕክት ቁጥርም 6800 መሆኑን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው ወደ 6800 የፈለገውን የገንዘብ መጠን በማስገባት በመላክ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን ክብር እና አጋርነት ማሳየት እንደሚችልም ኩባንያው ግልጽ አድርጓል።

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦምብ እና ሌሎች የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
******
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ ኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገ አሰሳ 19 ቦምብ፣ 55 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 21 ሽጉጦች፣ 2 ኤስ ኬ ኤስ ጠመንጃ፣ 3 ቺኮዝ፣ 1 ብሬን፣ 6 ቺቺ ጠመንጃ እና ሌሎች ጠመንጃዎች በአጠቃላይ 113 የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
በተጨማሪም 309 የሽጉጥ እና 4829 ዓይነታቸው የተለያየ ጥይቶች ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግሯል።
በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ትራኮን ሪልስቴት አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 64ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር መያዙንና ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ከኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተያዘውን ጨምሮ ከኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ 37 የእጅ ቦምብ፣ 1 ብሬን፣ 5 የጦር ሜዳ መነጽር፣ 18 የሬዲዮ መገናኛ ቁሳቁሶች፣ 589 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 350 ሽጉጦች፣ 46 የተለያዩ ጠመንጃዎች በአጠቃላይ 1023 የተለያዩ ዓይነት የጦር መሣሪያዎች ከ10 ሺህ 404 መሰል ጥይቶች ጋር በብርበራ እና በፍተሻ መያዙን ገልጿል።
738 የተለያዩ የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳት በፍተሻው ወቅት መገኘታቸውንም ጠቅሷል።
በተለያዩ ቦታዎች ተጥለው የተገኙ 7 የእጅ ቦምብ፣ 5 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 1 ተቀጣጣይ ፈንጂ፣ 3 ሽጉጥ፣ 2 የተለያዩ ጠመንጃዎች ከመሰል 841 ጥይቶቻቸው ጋር በኅብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውንም አመልክቷል።
የጥፋት ኃይሎች ለአዲስ አበባ ከተማ የደገሱላትን ሽብርና እልቂት ለመቀልበስ የሚከናወነው ጠንካራ ሕግን የማስከበር ተግባር በኅብረተሰቡ የዕለት ተዕለት መረጃ ሰጪነት እየታገዘ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የሻለቃው ትውስታ- ከሸሸቢት እስከ ዓዲ ዳዕሮ
*************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲነብሪ አካባቢ ታንኮች እዚህም እዚያ ተፈነጣጥረው ቆመው ግዳጃቸውን ለመፈጸም በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ የሽብርተኛውን የህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች ለመደምሰስ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ከእነዚህ ታንኮች መካከል የአንዷ ሹፌር ሻለቃ ባሻ በየነ ይባላል፡፡
ሻለቃ ባሻ የሰሜን ዕዝ ስምንተኛ መካናይዝድ አባል ነው፡፡ እሱም ሆነ ጓዶቹ ቀን የአርሶ አደሩን ምርት ለመሰብሰብ አጨዳ ላይ ውለውና በተግባራቸው ረክተው ደክሟቸው አገር ሰላም ብለው በተኙበት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የትግራይ ልዩ ሀይል ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ ነው ከእንቅልፋቸው የነቁት ።
በወቅቱም የከበባቸው የጽንፈኛው የህወሓት ሀይል መትተው መመለስ መቻላቸውን ሻለቃ በሻ ያስታወሳሉ። ይህ አሳዘኝ ክስትት በተከሰተ ማግሰት የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች የሻለቃ አመራራቸው በስሩ የሚገኙ ሁሉም የሠራዊት አባላት መሳሪያውን ወደ መጋዘን አስገቡ በማለት ትዕዛዝ ማስተላለፉን ያስታውሳሉ።
በተቃራኒው የእሱን ትዕዛዙን ሊያስተባብር ወደ ሠራዊቱ የመጣው ኮነሬል ዳኘው ጦሩ መሳሪያውን ወደ መጋዘን እንዳያስገባ ይልቁኑ በየምሽጉ ሆኖ ራሱን እንዲከላከልና ሁኔታዎችን በጥብቅ እንዲከታተል አደረጉ ፤የጁንታው ቡድን ተላላኪ የሆነው ሻለቃ ትዕዛዙ ሊፈጸም አለመቻሉን ለትግራይ ልዩ ሀይል መረጃ በመስጠቱ በማግስቱ ከቀኑ 5፤ከ30 ላይ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የትግራይ ልዩ ሀይል የሦስተኛ ሻለቃ ካምፕ ውስጥ በሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የተጠናከረ ጥቃት ከፈቱ።
በዚህ ጊዜም በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩ የጽንፈኛው ቡድን ተላላኪዎች ጦሩ ከተከፈተበት ጥቃት እንዳይከላከል ሲያዘናጉ ቆይተው ሠራዊቱ ለመከላከል ከግቢ እንደወጣ የሻለቃ አመራሮች ፣ኦፕሬተሮችና የመድፍ አስተኳሽ፣ የታንክ ሹፌሮች ወደ ትግራይ ልዩ ሀይል ተቀላቀሉ ።
በወቅቱ የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት ቁጥር 225 ቢሆንም በብረት ለበስ ብርታት ጽንፈኛው ኃይል በሠራዊቱ ላይ የሰራውን ቀለበት ሰብረው ሊወጡ መቻላቸውን ይናገራሉ። ከረፋዱ 5 ሰዓት በተጀመረው ውጊያም ከቀኑ10 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ጽንፈኛውን ሀይል በብቃት መክተው መልሰዋል። በተለይ መድፈኛ ሻለቃዋን ለማፈን ያደረገው ጥረት በጀግናው ሰራዊት ተጋድሎ የመድፎቹን መርፌ ማውጣት በመቻሉ ጽንፈኛው ሀይል መድፎቹን ጉትቶ ይዞ እንዳይሄድ አድርገዋል።
የእኛ ካምፕ ከአዲሃገራይ 7 ኪሎ ሜትር ይርቃል የሚሉት ሻለቃ ባሻ ፣አዲሃገራይ ወደ ሚገኘው የክፍለ ጦር ማዘዣቸው ጽንፈኛውን ሀይል እየተከላከሉ መሄዳቸውን ጠቅሰው፤ከዚያም ሀይል ጦሩ በማህይንጻ አድርጎ ጓል ባድሜ አቋርጦ ወደ ኤርትራ ሸሸቢት ወደ ምትባል ስፍራ ማፈግፈጋቸውን ነው የነገሩን ።
ከሁለት ቀናት ራስን የመከላከልና አድካሚ የእግር ጉዞ በኋላም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ከ25 ደቂቃ አካባቢ ኤርትራ ሸሸቢት የምትባል ስፍራ ደርሰዋል ። በዚያም የኤርትራ ህዝብ በሸሸቢት ትምህርት ቤት የቁርስ ግብዣ እንዳደረገላቸው ገልጸውልናል።
ከ”36 ሰዓት በኋላ ነው በሸሸቢት ውሃ የቀረበልንና ምግብ ያገኘነው። በኮዳ ከያዝናት ውሃ በክዳኗ ፉት እያልንና ለሁለት ቀናት ምግብ ሳንበላ የጽንፈኛውን ቡድን ያልተመጣጠነ ጥቃት እየመከትን ኤርትራ ደረስን”ብለዋል።
ግዳጁን ከበድ የሚያደርገው ከውስጣችን ጓዶቻችን ብለን ስናምናቸው የነበሩ የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች ከጎናችን ሆነው የእኛን ጓዶች መግደላቸውና መውጋታቸው ነው የሚሉት ሻለቃ ባሻ ፤እነዚህ ካህዲዎች የታንክ ሹፌሮችን ሳይቀር ገድለውብን ፤በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ግፍ እንደሆነ አመልክተዋል።
አብረህ በልተህ፣ አብረህ ጠጥተህ ይህን አይነት ግፍ መፈጸም በኢትዮጵያ ባህል ያልተለመደ ነው። እኔን ጨምሮ ሌሎች ጓዶቻችን ከ1991ዓ.ም ጀምሮ ለትግራይ ህዝብ ከምናገኘው ደመወዝ እያዋጣን ትምህርት ቤት፤ጤና ጣቢያ፣መንገድ ሰርተናል። ለህዝብ ጋሻ በሆነው መካላከያ ሠራዊት የዚህ አይነት ክህደት ሲፈጸም በጣም ያማል፤ ያበሳጫልና፣ ያናድዳል፤ያሳዝናልም ብሏል።
በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የነበሩ የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች ፣ የሌላ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ ጓዶቻቸውን በጥይትና በሳንጃ ሲመቱና ሲያርዱ በአይኔ አይቻለሁ፡ እኛም የአጸፋ እርምጃ የወሰድንባቸው አሉ፣ ክህደቱ በሠራዊቱ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝብም ጭምር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም ድርጊት ሠራዊቱን በጣም አስቆጭቶት በሞራልና በወኔ ጽንፈኛውን ሀይል በመደምሰስ ድል በድል እየተቀናጀ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ድባቅ እየተመታ ነው ብለዋል ።
በጌትነት ምህረቴ
አዲስ ዘመን ህዳር 11/2013

የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የፈጸመው 27 ዓመታት የቆየበትን ስልጣን ዳግም ለመያዝ አስቦ መሆኑን በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፀሃፊ አስታወቁ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸም ወደ ግጭት የገባው የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር በኃይል በማስወገድ ላለፉት 27 ዓመታት በአገሪቱ ይዞት ወደነበረው ስልጣን ለመመለስ በማሰብ መሆኑን በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፀሃፊ ሚስተር ቲቦር ናጊ አስታወቁ፡፡
ምክትል ፀሃፊው ሚስተር ቲቦር ናጊ ለጋዜጠኞች በቴሌ ኮንፈረንስ እንደገለፁት፤ የህወሓት ቡድን ወደ ጥቃት የገባው የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን በማስወገድ ላለፉት 27 ዓመታት በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ የነበራቸውን የበላይነት ለማስመለስና ወደ ሥልጣን ለመውጣት ያሰቡት ነው።
የህወሓት ቡድን የተከተለው ስልት ተቃራኒ ነገር እንዳስከተለበት የጠቀሱት ቲቦር ናጊ፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያዊያን በሚያስገርም ብሄራዊ ቁጭት ጠቅላይ ሚንስትሩን በመደገፍ እንደ አገር ያሰባሰበ ሆኗል ነው ያሉት።
የአገሪቱ ሕገ መንግስትም ራስን በራስ የማስተዳደርን መብት የሚደነግግ መሆኑን አስታውሰው፤ ቡድኑ የቀሰቀሰው ግጭት ከዚህ በተቀራኒ የስጣን ጥምን ለማርካት ታስቦ የሚደረግ ስለመሆኑም አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትም ሕግን ለማስከበር እየወሰደ ባለው እርምጃ ንፁሃን እንዳይጎዱ ትልቅ ትኩረት መስጠቱንም ጠቁመውል፡፡ በዚህ ህግን የማስከበር እርምጃ ንጹሃን እንዳይጎዱም ከለላ መደረጉ የአሜሪካም ፍላጎት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ መንግስትም ይህን በተግባር ለማዋል ቁርጠኛ ስለመሆኑና ንጹሃንን ለመታደግ ፅኑ ፍላጎት እንዳለው ሚስተር ቲቦር ናጊ አብራርተዋል፡፡
የትግራይ ህዝበ እንደጠላት አለመታየቱንና ፀቡም ከቡድኑ ጋር መሆኑን የጠቀሱት ቲቦር ናጊ፤ ይልቁንም አገሪቱ በግዛቷ ውስጥ የሚገኝ ቡድን የፈጠረውን ሀከት ለማረጋጋት እየተወሰደ የሚገኝ እርምጃ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ አብራርተዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም ሌሊት ጥቃት በመፈጸም ብዙዎችን ዘግናኝ በሆነ መልኩ እንደገደለና የተቀሩትን አፍኖ እንደወሰደ ይታወሳል። ይሄንን ተከትሎ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ጁንታው ከፍተኛ ኪሰራ እየደረሰበት በመሆኑ እንደ ማይካድራ ባሉ ከተሞች በንጹሀን ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ይታወሳል፤ በዚህም አሜሪካን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዳወገዙት ይታወቃል።

ሰበር ዜና!
አዲግራት ከተማ ከህወሓት ጁንታ ነጻ ወጣች
******************
(ኢ ፕ ድ)
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአዲግራት ከተማን ዛሬ ከህወሃት ጁንታ ሃይል ነጻ አወጣ።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ጠዋት የህወሃት ጁንታ ሃይልን ድል አድርጎ የአዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዳወጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ አስታወቀ።
የመከላከያ ሠራዊታችን በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ነው።

“የሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት እርቃናቸውን እንዲሆኑ ተደርገዋል፤ ተገድለዋል ፤ ታፍነው ተወስደዋል”
- ሻለቃ አምሳሉ ደመቀ ከጥቃቱ ያመለጡ የሰራዊቱ አባል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከሀዲው የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ያደረሱትን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ከእነሱ ጋር አልተባበርም ያሉትን
መግደላቸውንና የተቀረውን ማፈናቸውን ሌሎችን ደግሞ እርቃናቸውን ማባረራቸውን ከጥቃቱ ያመለጠው ሻለቃ አምሳሉ ደመቀ አስታወቀ።
የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አባል የሆነው ሻለቃ አምሳሉ ደመቀ ከመከላከያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ እንደተናገረው፤ የክፍለ ጦሩ አመራሮች ከከሀዲው የህወሓት ጁንታ ጋር በነበራቸው ሚስጥራዊ ግንኙነት አስቀድመው ለዋርድያ መጠበቂያ ብቻ አንድ መሳሪያ በማስቀረት ሌላው መስሪያ ወደ ግምጃ ቤት እንዲገባ አድርገዋል።
በመቀጠልም የባንዳው ተላላኪ በሆነው የክፍለ ጦሩ አዛዥ ትዕዛዝ ገቢ የተደረገው መሳሪያ በከሀዲው ህወሓት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት መፈጸሙን የገለጸው ሻለቃ አምሳሉ፤ ሰራዊቱም ያልጠበቀው ክህደት ሲያጋጥመው ወደ መሳሪያ ግምጃ ቤት ቢያቀናም በታጣቂዎቹ ተኩስ እንደተከፈተበትና ግድያ እንደተፈጸመበት ተናግሯል።
ከሃዲው የህወሓት ቡድን መሳሪያ የሚቀመጥበትን ቦታ ተቆጣጥረው ከዘረፉና መግደል የፈለጉትን ከገደሉ በኋላ የተረፈውን ሰራዊት ልብሱን አስወልቀው እርቃኑን በማድረግ ወደ አዳራሽ አስገብተው እንዳፈኗቸው ጠቁመዋል።
ሻለቃ አምሳሉ ደመቀ እንደገለፁት፣ ከሀዲው ቡድን በዕለቱ ከግድያ ለተረፉት የሰራዊቱ አባላት ያቀረበው አማራጭ አብሮ ለ20 ዓመት ከኖረና ለ20 ዓመት የትግራይን ህዝብ ላገለገለ ሰራዊት የማይገባው ነበር ያለው ሻለቃ አምሳሉ፤ “ከእኛ ጋር ወግኑ አሊያም በህይወታችሁ ፍረዱ የሚል አማራጭ እንዳቀረቡላቸው አስታውቀዋል።
የከሀዲው ህወሓት ታጣቂዎች በክተት በታንከኛ፣ በመድፈኛ፣ በአየር መቃወሚያና በከባድ መሳሪያ ስልጣናዎችን እየወሰዱ እንደሆነ በመረዳታቸው ይህን ተግባር አግባብ እንዳልሆነ ሰራዊቱ ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበር ያስታወሰው ሻለቃው፤ የክፈለ ጦሩ አዛዥ “ከፈለጉ ሌላም ይታጠቁ የክልሉ ሥራ ነው” በሚል ያለመቀበል ሁኔታዎች እንደነበር ገልጿል።
በተለይ የአራተኛ ሜካናይዝ ክፍለ ጦር ኃላፊ ከሰራዊቱ በተቃራኒ የመቆምና ሃሳብን ያለመቀበል፤ እኔ የምላችሁን ብቻ ሥሩ የሚል ትዕዛዛት ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሷል።
“የክፍለ ጦሩ አመራር ለውጡን ባለመቀበል ወደ ብሔርተኝነት አሳተሳሰብ ያዘነበለ ስለነበር ሠራዊቱን አስመትተውታል” ያለው ሻለቃ አምሳሉ፤ ቀን ቀን ካንገት በላይ ሲያወሩ ይውላሉ፤ ማታ መቀሌ ሄደው ሲያሴሩ እንደነበር አስታውቋል።
https://www.press.et/Ama/?p=42137