Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.5K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በELMIS ፕሮጀክት ላይ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ክስ መመስረቱን ፖሊስ አስታወቀ
++++++++++++++++

ጋዜጣ- ፕላስ- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ(ELMIS) ፕሮጀክት ላይ የተፈጸመ ከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ አጣርቶ መዝገቡን ለፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ልኮ ክስ መመስረቱን አስታወቀ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (Ethiopian Labor market information system (ELMIS)) ፕሮጀክት ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠረውን የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ብርሀኑ አለቃ አስገዶም እና በግብረ-አበሮቹ ላይ ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ በማጠናቀቅ ለፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ልኮ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።

ብርሃኑ አለቃ አስግዶም እና ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች፣ የሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶችና ሌሎች ግለሰቦችን ጨምሮ 13 ሰዎች በዚህ ወንጀል ተሳትፈዋል። ተጠርጣሪዎቹ የተሰጣቸውን የመንግሥት ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ፕሮጀክቱን ከአሠራር ውጭ በማንቀሳቀስ ከጅምሩ የሲስተሙ የጥራት ደረጃ በተገቢው ሳይረጋገጥ ሥራ እንዲጀምር ማድረጋቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል።

ብርሃኑ አለቃ አስግዶም በቂ ሥልጠና ላልወሰዱ ለ81 ሺህ 236 ግለሰቦች ሕገ-ወጥ የሙያ ብቃት ምዘና ሰርተፍኬት በሲስተም እንዲሰጣቸው ያስደረገ ሲሆን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኛ ላልሆኑና ተቋሙ ከማያውቃቸው ሦስት ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ልዩ የሲስተም አስተዳዳሪ መብት በመስጠት ዜጎች ያልሰለጠኑበትን ሐሰተኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንዲያገኙ ማድረጉን በምርመራ ተደርሶበታል።

ለዚህ የወንጀል ድርጊት ሁለት ሐሰተኛ የባንክ ሒሳብ ደብተሮች እንዲከፈቱ በማድረግ በዚህ ሕገ-ወጥ መንገድ አጠቃላይ 1 ቢሊየን 13 ሚሊየን 609 ሺህ 241ብር ከ93 ሣንቲም መሰብሰቡ በምርመራ ተረጋግጧል።

የወንጀሉ ፍሬ የሆነ በባንክ ሂሳብ ውስጥ ይገኝ የነበረ 249 ሚሊዮን ብር የታገደ ሲሆን ወንጀለኞቹ በረቀቀ ዘዴ ገንዘቡን ወደ የክሪፕቶከረንሲ በመቀየር ያስቀመጡትን 965 ሺህ 508 ዶላር ከፍተኛ ጥበብ በተሞላበትና በቴክኖሎጂ በታገዘ ምርመራ በፍርድ ቤት በማሳገድ ወደ ብሄራዊ ባንክ እንዲገባ ተደርጓል።

ተጠርጣሪዎቹ የውጭ ምንዛሪ ሳያስገቡ የታገዱ ኤጀንሲዎችን እግድ ያለአግባብ በማንሳት 10 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ እና 64,500 ዜጎችን በሐሰተኛ ቪዛ ሰነድ ወደ ጆርዳንና ወደ ሌሎች የዓረብ ሀገራት በመላክ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ፖሊስ ባደረገው የተጠናከረ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከልና ከብሄራዊ ባንክ ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ምርመራ በተጠርጣሪው ስም በለሚ ኩራ፣ በቦሌና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የተገዙ ከ55 ሚሊዮን እስከ 68 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 6 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች፣ በ68 ሚሊዮን ብር የተገዛ አንድ V6 ዘመናዊ መኪና በኤግዚቢትነት እንዲያዙ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዚህ ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ እና ሕጋዊነትን ሽፋን በማድረግ መንግሥት ማግኘት የነበረበትን የውጭ ምንዛሪ ሳያስገቡ በቀሩ ኤጀንሲዎች ላይ እያደረገ ያለውን ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልጆቻቸው ወደ ውጭ ሀገር ሄደው መዳረሻቸው የጠፋባቸው ቤተሰቦችና ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ መረጃ ያላቸው በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ በነፃ የስልክ መስመር (991) እና በሰው አልባ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ (SPS) አማካኝነት ጥቆማ እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በመቅረብ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።
❤7👍3😁2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪን ተቀበሉ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 12ኛው ከፍተኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪን ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት በመቀበላቸውና በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውቀዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹 #Ethiopia #Kenya #TanaForum
👍7❤5
#የድል_ሠራዊት
119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን
👍2