Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.4K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተመሠረተ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መመስረቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የፊዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደሩ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ይሆናል ተብሏል።

የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና አስፈጻሚዎች፤
✅ አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ

✅ ⁠ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ ወ/ሥላሴ - የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ

✅ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ - የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ

✅ ⁠አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ - የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ

✅ ⁠ዶክተር ሽሻይ አማረ - የመቐለ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።

ለሚያከናውኗቸው ሁሉም እንቅስቃሴዎች የፌዴራል መንግሥቱ መመሪያ፣ አቅጣጫ፣ ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የኢፌዴሪ መንግሥት የትግራይ ክልልን የሚያጸና ውሳኔ ወስኗል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
👍7❤5
ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶን ክብረወሰን ሰብሮ ሲያሸንፍ አንቺንአሉ ደሴም ድሏን ደግማለች
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ያላቸውን ድል አድራጊነት እና ልዩ አቅም በድጋሚ ባሰመሰከሩበት የ2026 የቤጂንግ ማራቶን ውድድር፤ የፓሪስ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ በበላይነት አጠናቋል።

የ35 ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ የቀድሞውን የውድድሩን ክብረ ወሰን በአራት ደቂቃዎች በማሻሻል ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።

አትሌቱ በአውሮፓውያኑ 2023 በሻንጋይ ማራቶን በኬንያዊው ፊሊሞን ኪፕቹምባ ተይዞ የነበረውን የ2:05:35 ሰዓት በመስበር በቻይና በማራቶን ውድድር የተመዘገበ የምንጊዜም ፈጣኑ ሰዓት ባለቤት መሆን ችሏል።

በውድድሩ አትሌት ታምራት ቶላ ለአንደኛ ደረጃ የተዘጋጀውን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፤ የቦታውን ክብረወሰን በመስበሩ ተጨማሪ 60 ሺህ የቻይና ዩዋን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 59 ሺህ ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል።

በሌላ በኩል በሴቶች በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በማጠናቀቅ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የቤጂንግ ማራቶን አሸናፊ በመሆን የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆናኗን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ! #BeijingMarathon  #Ethiopian #Athletics #World #Champions
👍6❤1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጋር በትግርኛ ቋንቋ ያደረጉትን ቆይታ ነገ ምሽት 2:30 ይጠብቁን!
🔥7👍5❤4😁1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኬንያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ልማት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች ክብር በሚሰጥበት የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት ለመታደም ኤልዶሬት፣ ኬንያ ገብተዋል። #የመደመር_መንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
❤9
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"ዛሬ በኤልዶሬት፣ ኬንያ በተከበረው የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘትና ንግግር በማድረግ፤ ለሀገራቸው ነጻነት ለታገሉና ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ታላቅ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ያለኝን ታላቅ ክብር ገልጫለሁ። ለጀግንነታቸውና ትተውት ላለፉት ዐሻራ የላቀ ክብር አለኝ!

የኬንያ የጀግንነት እና የመስዋዕትነት ታሪክ፤ ከሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመከላከል በአንድነት ከቆሙበት ከኢትዮጵያ የአድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። እነዚህ የጋራ ታሪኮቻችን ነጻነት በስጦታ የተገኘ ሳይሆን በጀግንነት፣ በአንድነት እና በመስዋዕትነት የተረጋገጠ መሆኑን ያስገነዝቡናል።

ታሪካችን የተሳሰረ እንደመሆኑ ሁሉ የወደፊት እጣ ፈንታችንም እንዲሁ የተሳሰረ ሊሆን ይገባል። በመደመር መንፈስ፤ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለህዝቦቻችን ሰፊ እድሎችን እና የጋራ ብልጽግናን ለመፍጠር በንጹህ ሀይል፣ በመንገድ ትስስር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በንግድ ዘርፎች ያለንን ነባር ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ይኖርብናል።

ዛሬ ክብር ለተቸራቸው ጀግኖች ሁሉ፣ ላቅ ያለ አክብሮቴን አቀርባለሁ። መልካም የማሹጃ (የጀግኖች) ቀን!"
👍6
በደቡብ ወሎ ዞን- የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍና ሀገር ለማፍረስ የሚላላኩ ጠላቶችን የሚያወግዝ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ፤ በቃሉ ወረዳ ደጋን ከተማ፤ ቦረና መካነሰላም ፣ በሐይቅ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ታሪካዊ ጠላቶችና ተልዕኮ ተሸካሚ የሀገር ውስጥ ባንዳዎችን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሠልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

በሰልፉ ላይ የተገኙ ነዋሪዎች የሀገርን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት እንደሚያግዙ ገልጸዋል።

ሠልፈኞቹ "የሀገራችንን ሰላም ለማወክ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ኀይሎችን በጽኑ እናወግዛለን!" የሚሉ እና ሌሎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የሀገርን ሰላም ማደፍረስ እና ከውጭ ኀይሎች ጋር በመተባበር ሀገርን ለማዳከም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደሚቃወሙ እና ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመቆም አጋርነታቸውን እንደሚሰጡ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
❤2🕊1