መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል። ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለፁት፣ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ለመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፤ ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽንና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነው።
በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለበተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል።
ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው። ሥራው መረጃዎች ተሰብስበው፣ ተቀናብረውና ተተንትነው ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዙ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ጠንካራ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎችና የመረጃ ማዕከላት መረብ ላይ ጭምር የተመሰረተ ነው።
ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳትና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምርና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
#የመደመርመንግሥት #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #Ethiopia #Tigray #Mekelle #peace

❤5
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት ተቋማት አመራሮችን ሾመዋል።
በዚህም መሠረት፤
✅ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ- የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
✅ ዶ/ር ታምራት በየነ- የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
✅ አቶ ብርሃኑ ፌይሳ- የመንግሥት ረዳት ተጣሪ
✅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ- የመንግሥት ረዳት ተጣሪ
✅ ዶ/ር መሐመድ አንድሪስ- በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ረዳት አስተባባሪ
✅ ወ/ሪት ፈዲላ አባቢያ- በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዲጂታል ሚዲያ አስተባባሪ
✅ አቶ ተስፋዬ ይግዛው- በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ረዳት አስተባባሪ
#የመደመር_መንግሥት #ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #PMOEthiopia

❤8
የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተመሠረተ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መመስረቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የፊዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደሩ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ይሆናል ተብሏል።
የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና አስፈጻሚዎች፤
✅ አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ
✅ ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ ወ/ሥላሴ - የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ
✅ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ - የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ
✅ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ - የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ
✅ ዶክተር ሽሻይ አማረ - የመቐለ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።
ለሚያከናውኗቸው ሁሉም እንቅስቃሴዎች የፌዴራል መንግሥቱ መመሪያ፣ አቅጣጫ፣ ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የኢፌዴሪ መንግሥት የትግራይ ክልልን የሚያጸና ውሳኔ ወስኗል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

👍7❤5
ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶን ክብረወሰን ሰብሮ ሲያሸንፍ አንቺንአሉ ደሴም ድሏን ደግማለች
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ያላቸውን ድል አድራጊነት እና ልዩ አቅም በድጋሚ ባሰመሰከሩበት የ2026 የቤጂንግ ማራቶን ውድድር፤ የፓሪስ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ በበላይነት አጠናቋል።
የ35 ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ የቀድሞውን የውድድሩን ክብረ ወሰን በአራት ደቂቃዎች በማሻሻል ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።
አትሌቱ በአውሮፓውያኑ 2023 በሻንጋይ ማራቶን በኬንያዊው ፊሊሞን ኪፕቹምባ ተይዞ የነበረውን የ2:05:35 ሰዓት በመስበር በቻይና በማራቶን ውድድር የተመዘገበ የምንጊዜም ፈጣኑ ሰዓት ባለቤት መሆን ችሏል።
በውድድሩ አትሌት ታምራት ቶላ ለአንደኛ ደረጃ የተዘጋጀውን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፤ የቦታውን ክብረወሰን በመስበሩ ተጨማሪ 60 ሺህ የቻይና ዩዋን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 59 ሺህ ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል።
በሌላ በኩል በሴቶች በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በማጠናቀቅ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የቤጂንግ ማራቶን አሸናፊ በመሆን የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆናኗን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ! #BeijingMarathon #Ethiopian #Athletics #World #Champions

👍6❤1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጋር በትግርኛ ቋንቋ ያደረጉትን ቆይታ ነገ ምሽት 2:30 ይጠብቁን!
🔥7👍5❤4😁1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኬንያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ልማት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች ክብር በሚሰጥበት የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት ለመታደም ኤልዶሬት፣ ኬንያ ገብተዋል። #የመደመር_መንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
❤9
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
"ዛሬ በኤልዶሬት፣ ኬንያ በተከበረው የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘትና ንግግር በማድረግ፤ ለሀገራቸው ነጻነት ለታገሉና ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ታላቅ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ያለኝን ታላቅ ክብር ገልጫለሁ። ለጀግንነታቸውና ትተውት ላለፉት ዐሻራ የላቀ ክብር አለኝ!
የኬንያ የጀግንነት እና የመስዋዕትነት ታሪክ፤ ከሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመከላከል በአንድነት ከቆሙበት ከኢትዮጵያ የአድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። እነዚህ የጋራ ታሪኮቻችን ነጻነት በስጦታ የተገኘ ሳይሆን በጀግንነት፣ በአንድነት እና በመስዋዕትነት የተረጋገጠ መሆኑን ያስገነዝቡናል።
ታሪካችን የተሳሰረ እንደመሆኑ ሁሉ የወደፊት እጣ ፈንታችንም እንዲሁ የተሳሰረ ሊሆን ይገባል። በመደመር መንፈስ፤ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለህዝቦቻችን ሰፊ እድሎችን እና የጋራ ብልጽግናን ለመፍጠር በንጹህ ሀይል፣ በመንገድ ትስስር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በንግድ ዘርፎች ያለንን ነባር ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ይኖርብናል።
ዛሬ ክብር ለተቸራቸው ጀግኖች ሁሉ፣ ላቅ ያለ አክብሮቴን አቀርባለሁ። መልካም የማሹጃ (የጀግኖች) ቀን!"

👍6