Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.8K subscribers
41.4K photos
346 videos
7 files
5.82K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#የመደመር_መንግሥት

"በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም!"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia
❤4👍2😁2
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
+++++++++++++++++++

#ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

በቆይታቸው መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ። በልማት ዘርፎች የልምድ ልውውጥ ማድረግና ቁልፍ ተቋማትንና ልማቶችን እንደሚጎበኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
#የመደመር_መንግሥት #Ethiopia  #Nigeria #NigeriaEthiopiaRelations #Diplomacy #AddisAbaba
❤1
በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ
++++++++++++++

#ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት አሃድ በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፤ ኮሚሽኑ ከህዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ በማቋቋም ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ አድርጓል።

መንግስት በትግራይ ክልል ከፍተኛ ሃብት በመመደብ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም በርካታ ስራዎችን ቢያከናውንም ህገወጡ የሕወሓት ቡድን በፕሪቶሪያው ስምምንት የፈረመውን ትጥቅ የማስፈታት ስምምነት በማፍረስ ወደ ተሃድሶ ማዕከል ለመግባት ፈቃደኛ የነበሩ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና እንዳይወስዱ ሲያደናቅፍ መቆየቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ወጣቶችን አስገድድዶ በማፈስ ለሌላ ጦርነት ሲያዘጋጅ እንደነበርም ነው የገለጹት።

በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ መንግስት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የመልሶ ማቋቋም መርሃ ግብሩ እንዳይቋረጥ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለሚመጡ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ መደበኛ ሕይወት ለማስገባት መንግስት አሁንም በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል የሰላም መንገድን መርጠው ወደ ፌደራል መንግስት የሚመጡ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም በትግራይ ክልል የቀደሞ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት አሀድ እያስረከቡ ወደ የተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡም ጥሪ አቅርበዋል።

ለዚህም መንግስት በርካታ ሃብት መድቦ ዜጎችን ወደ መደበኛ ሕይወት ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተቋቋመ ሲሆን፤ በግጭት ውስጥ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ በዘላቂነት መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው።

#የመደመር_መንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ጋዜጣፕላስ
❤4👏3
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፅድቋል። የተሰየሙት የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በይፋ የቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
#የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርበዋል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ አፅድቋል።

ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለመሀላ ፈጽመዋል።

#የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #Ethiopia #Medemer