Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ብልጽግና፣ ኦፌኮ፣ኢዜማ፣ አብን፣ እና ኢዴፓ ውይይት ሊያካሂዱ ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

ብልጽግና፣ ኦፌኮ፣ኢዜማ፣ አብን፣ እና ኢዴፓ የሚሳተፉበት ውይይት ሊካሄድ ነው።

የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጥናት ተቋም የፊታችን ሀሙስ (የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም) በተለያየ የፖለቲካ አቋማቸው በሚታወቁ የፓርቲ አመራሮችና አባላት መካከል በዴሞክራሲያዊ ሽግግር፣ በሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ውይይት ሊያካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከተቋሙ ባገኘው መረጃ አረጋግጧል።
ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ህትመት እና ቁሳቁሶችን ግዥ ማጠናቀቁን አስታወቀ
*****************************************************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ህትመት እና ቁሳቁሶችን ግዥ አጠናቆ ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ መጋዘን አስገብቶ ያጠናቀቀ ሲሆን የቁሳቁስ ድልድል ስራን በቅርቡ ይጀምራል፡፡

ምንጭ ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂው ካሜሮናዊው ተማሪ ቫይረሱን ይዤ ወደ አገሬ አልመለስም አለ
*^**************
(ኢ.ፕ.ድ)

የ 21 ዓመቱ ካሜሮናዊ ኬም ሴኑ ፓቬል በቻይናዋ ጂንግዙ ግዛት ተማሪ ሲሆን በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ በኋላ "ተሽሎሃል ወደ አገርህ ተመለስ እንኳን ቢሉኝ አልመለስም" ብሏል። ምክንያቱ ደግሞ ቫይረሱን ወደ አፍሪካ ይዞ ላለመግባት ነው።

'' ምንም ነገር ቢፈጠር ይህን በሽታ ወደ አፍሪካ ይዤ መመለስ አልፈልግም'' ያለው በዩኒቨርሲቲ ዶርምተሪ ውስጥ የ 14 ቀናት ክትትል በሚደረግለት ወቅት ነው።

በመጀመሪያ ከባድ ትኩሳትና ደረቅ ሳል አጣድፎት ነበር፤ በመቀጠል ግን ፈሳሽ ከአፍንጫው መውጣት ጀመረ። ምልክቶቹን ካስተዋለ በኋላ በልጅነት ታሰቃየው የነበረችው ወባው እንደተነሳችበት አስቦም ነበር። ነገር ግን ያላሰበውና ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው ኮሮናቫይረስ ሆኖ ተገኘ።

'' ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ስሄድ የምሞትበት ሰአት እንደተቃረበ አስብ ነበር። በቃ መሞቴ ነው እያልኩ ለራሴ ነግሬው ነበር'' ብሏል።

ኬም ሴኑ ፓቬል አሁን በለይቶ ማቆያ ውስጥ 13ኛ ቀኑን ይዟል፤ በአንድ የቻይና ሆስፒታል ውስጥ። ህክምናው በተለይም የኤችአይቪ ታማሚዎችን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውሉ መድሃኒቶችን በብዛት ይጠቀማል።

ከሁለት ሳምንታት ተከታታይ ህክምና በኋላ እየተሻለው መጥቷል። በሲቲ ስካን በተደረገለት ምርመራም ቫይረሱ ከሰውነቱ እንደጠፋ ምልክቶች ታይተዋል።

ፓቬል በገዳዩ ኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሲሆን ሙሉ የህክምናው ሙሉ ወጪ በቻይናዋ ግዛት ተሸፍኗል።

'' ትምህርቴን ሳልጨርስ ወደ አገር ቤት መመለስ አልፈልግም። ወደ ካሜሩን የምምለስበት ምንም ምክንያት የለኝም፤ ሙሉ የሆስፒታል ወጪዬ በቻይና መንግስት ተሸፍኖልኛል''ብሏል።

ምንጭ- ቢቢ ሲ
በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በእንስሳትና ሰብል ላይ ጉዳት አደረሰ
~~~~~~~~~~~~~~~
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ በቋሪት እየሱስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዳሞት ተራራ በተባለ ጎጥ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በቤቶች፣በእንስሳት በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን የአካባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የካቲት 11/2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በሰብሎች ላይ ማለትም ሽምብራና ጓያ እንዲሁም በውሃገብ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ሙላቴ ደሳለው ገልፀው፤ በቤቶች እና በእንስሳት ላይም ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

በእለቱ ከጣለው በረዶ ጋር አሳ አብሮ ወርዷል ሲሉ ነዋሪዎች በጠቆሙን መረጃ መሰረት እኛም በቦታው ተገኝተን እንደተመለከትነው በቁጥር ከስድሰት ያላነሱ መጠናቸው መለስተኛ የሆኑ አሳዎችን ተመልክተኛል፡፡

አሳዎች በሰዎች የመጡ እንዳይሆኑ ብለን ስንጠይቅ በዚያ ሰዓት ማንም ያመጣል ተብሎ አይታሰብም በእርግጠኝነት ከበረዶ ጋር የወረደ ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪ አቶ ላቀው እጅጉ ተናግረዋል፡፡

ዘገባዉ፡- የቋሪት ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው
ከ7 አስከ 10ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶች በዲቪዲ ለገበያ ሊቀርቡ ነው
*********
(ኢ.ፕ.ድ)

ስኮላር ኢ ፐብሊሸር የተባለ የግል ማህበር ከ7ኛ እስከ 10ኛ ያሉ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶችን በዲቪዲ አምርቶ ኢ ፋኖስ በተባለ የምርት መጠሪያ በገበያ ላይ ሊያሰራጭ መሆኑን አስታውቋል።

ዲቪዲዮዎቹ የትምህርት መስጫ፣ የማጠቃለያና የጥያቄና መልስ ክፍል ፣የማጠቀሻ መፅሀፈት ፣ ላብራቶሪና ጭብጥ ሀሳቦችን በቪድዮና በምስል ያቀርባሉ ሲሉ የማህበሩ አመራሮች ለጋዜጠኞች
ዛሬ ሀሙስ የካቲት 12 ለጋዜጠኞች በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።

ዲቪዲዎችም በትምህርት ቤቶችችና በትምህርት መሳሪያ መሸጫ ቤቶች በኩል የሚከፋፈሉ ሲሆን የአንድ ዲቪዲ ዋጋም 98 ብር እንደሆነ ገልፀዋል።

ማህበሩ ከ11ኛ እስከ 10ኛ ያሉ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶችን በዲቪዲ ለማሰራጨት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ከኬጂ አስከ ስድስተኛ ያሉ እንግሊዘኛ፣የአማረኛ ቋንቋና የአካባቢ ሳይንስ ትምህርቶችን ተረቶችን ፣ጨዋታዎችን ጭምር ከመልቲሚድያ መልክ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
በዳግም ከበደ
ከአዲስ አበባ የተነሳው የአደዋ ተጓዥ ቡድን ዛሬ ደሴ ደርሷል። ቡድኑም በደሴ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ይህ አቀባበልና ጉብኝት በድርጅታችን ካሜራ ማን ዳኜ አበራ እንዲህ ተዘግቧል።
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ
*****************************
(ኢ.ፕ.ድ)

ነገ ዓርብ የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ፣
• በኢትዮ ፕላስቲክ፣ በየነገው ሰው ት/ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣

እንዲሁም ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ስዓት ድረስ፣
• በፍሊንት ስቶን ሪል እስቴት፣ በአትሌቶች መንደር፣ በለገጣፎ ሰብስቴሽን ፊት ለፊት እና አካባቢዎቻቸው፣

በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት