"የዘንድሮው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተጠናቅቋል"
- የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ ሀርሰዴ የተከበረው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ መጠናቀቁን የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ገለጹ።
አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ የበዓሉን መጠናቀቅ ተከትሎ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በሆረ ፊንፊኔና በሆረ ሀርሰዴ በልዩ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት በመሆን ባህሉን በጠበቀ መልኩ ወደ ስፍራው በማቅናት ፈጣሪውን አመስግኗል። መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በቦታው ተገኝተው በአንድነት ማክበራቸውንም ጠቁመዋል።
የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ በዓል ከመሆን ተሻግሮ ዓለም አቀፍ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።
ወደ ኢሬቻ ማክበሪያ ቦታ ይወስድ የነበረውን አንድ መንገድ ወደ ሦስት ማሳደግ መቻሉ ለዘንድሮው በዓል ልዩ ድባብ እንደሰጠው የገለጹት ከንቲባው፤ በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደር ልማትም በዓሉ ያለምንም መገፋፋት በድምቀት እንዲከበር እንዳስቻለ ገልጸዋል።
በዓሉ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፍ ዜጎች መታደሙን ጠቁመው፤ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዮሐንስ መልካሙ (ከቢሾፍቱ)
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢሬቻ #ሆራ_ሐርሰዴ #ቢሾፍቱ #አባ_ገዳ #ባህል #ኢትዮጵያ #Irreecha #Horafinfinnee #Horaharsadee #Irreecha #Irreechaa #festivity #celebration #holiday #holidayseason

❤5👎1
አዲስ የመንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል
++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- አዲስ የመንግሥት ምሥረታና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይካሄዳል።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ይደነግጋል።
የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ይታወቃል፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ

❤3👍1
ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++
ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማትና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ።