Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.8K subscribers
41.4K photos
346 videos
7 files
5.82K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Photo
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት

ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክልል መንግሥታት በይፋ ርክክብ የተደረገበትን መርሃ ግብር ዛሬ ተከታትያለሁ።
‎
‎ይህ የሰነድ ርክክብ ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚያስመዘግብ ሲሆን የኢትዮጵያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎች አካታች በሆነ ውይይት፣ በሰላማዊ ምክክርና በራሳችን ሀገር በቀል የመፍትሔ አምጭ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

#ትልቅሀገር፣ #ትልቅህዝብ ፤ #ታላቅርዕይ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
❤2🍾1
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
❤1
"የዘንድሮው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተጠናቅቋል"
- የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ ሀርሰዴ የተከበረው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ መጠናቀቁን የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ገለጹ።

አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ የበዓሉን መጠናቀቅ ተከትሎ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በሆረ ፊንፊኔና በሆረ ሀርሰዴ በልዩ ሁኔታ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት በመሆን ባህሉን በጠበቀ መልኩ ወደ ስፍራው በማቅናት ፈጣሪውን አመስግኗል። መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በቦታው ተገኝተው በአንድነት ማክበራቸውንም ጠቁመዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ በዓል ከመሆን ተሻግሮ ዓለም አቀፍ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

ወደ ኢሬቻ ማክበሪያ ቦታ ይወስድ የነበረውን አንድ መንገድ ወደ ሦስት ማሳደግ መቻሉ ለዘንድሮው በዓል ልዩ ድባብ እንደሰጠው የገለጹት ከንቲባው፤ በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደር ልማትም በዓሉ ያለምንም መገፋፋት በድምቀት እንዲከበር እንዳስቻለ ገልጸዋል።

በዓሉ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፍ ዜጎች መታደሙን ጠቁመው፤ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዮሐንስ መልካሙ (ከቢሾፍቱ)

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢሬቻ #ሆራ_ሐርሰዴ #ቢሾፍቱ #አባ_ገዳ #ባህል #ኢትዮጵያ #Irreecha #Horafinfinnee #Horaharsadee #Irreecha #Irreechaa #festivity #celebration #holiday #holidayseason
❤4