ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በአንድ የታሪክ ገጽ ብቻ ተወስኖ ለመግለጽ መሞከር የሀገሪቱን ትልቅነት፣ የዘመናት ጥልቅ ጥበብና የሕዝቧን ሁለገብ ማንነት ካለመገንዘብ ይመነጫል።
ኢትዮጵያ ሺህ ዓመታትን በብዙ መልክ ያሳለፈች፤ ውጣ ውረዶችንም በትውልዶች ቅብብሎሽ የተሻገረች፤ የሥልጣኔ ከፍታዎችን የገለጠች፣ ነፃነቷን ጠብቃም የዛሬው ትውልድ እጅ የደረሰች ሀገር ናት። በውስጧም ብዙ ባሕሎች፣ ቋንቋዎች፣ እምነቶችና ማንነቶች በአንድ የሀገር ማንነት ውስጥ ተሳስረው የሚኖሩባት ናት።
ይህ መልከ ብዙ እና ጥልቅ ታሪክ ደግሞ መገለጫና መከሰቻውም ብዙ ነው። በአክሱም ግዙፍ ሐውልቶች፣ በላሊበላ የውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ በጎንደር ቤተ-መንግሥታት፣ በሐረር ጀጎል ግንብ፣ በጢያ ትክል ድንጋዮች እንዲሁም በኦሞና በአዋሽ ሸለቆዎች የሰው ልጅ ጥንታዊ ታሪክ ውስጥ ሆኖ ዛሬም በግልጽ ራሱን የሚገልጽ ሕያው ምስክር ነው።
በዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ (በሚዳሰስም በማያዳሰስም) የተመዘገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶችም ይህን ታሪካዊ ጥልቀት ያረጋግጣሉ። ዩኔስኮ በኢትዮጵያ በርካታ ቅርሶችን የዓለም ቅርስ አድርጎ መመዝገቡም የዚህ አስረጂ ነው። ምክንያቱም ይህ የሚያሳየው፣ ሀገሪቱ ለዓለም ሥልጣኔ፣ ለሥነ-ሕንጻ፣ ለባሕልና ለሰው ልጅ ታሪክ ያላትን አበርክቶ ነው።
ነገር ግን ትናንት ታላቅ ነበርን ማለት፣ የዛሬን ታላቅነት ማረጋገጫ አይሆንም። ለምሳሌ፣ ቅርስ የሚከበረው በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን፤ ትርጉሙን ለአዲስ ትውልድ በማስተላለፍ....
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት_https://gw.press.et/am-digital-content/share/am-stories/4zwzpj4ph7hj2vq6pzm7xreqdd

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል። #PMOEthiopia
👍9❤4
❤2👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማማ
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰር የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ በስምምነነቱ መሰረት ቦይንግ 777-8 እና ቦይንግ 777 ኤፍ የተባሉ አውሮፕላኖችን ይገዛል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ አውሮፕላኖቹ ከ2033 እስከ 2035 ባለው ጊዜ እንረከባለን። በተለይም ሁለቱ በጣም ዘመናዊ ናቸው ብለዋል።
በተጨማሪም በ2027 እና 2028 ለርክክብ የሚደርሱ ሁለት ተጨማሪ የቦይንግ 777 የጭነት አውሮፕላኖች ግዢ እንደሚፈጸም ጠቅሰው፣ ከተሳፋሪ አውሮፕላንነት ወደ ጭነት የተቀየሩ 4 ተጨማሪ ቦይንግ 777 ካርጎ አውሮፕላኖችን እንደሚረከብ ተናግረዋል።
የካርጎ አገልግሎቱ ከአጠቃላይ ገቢው ወደ 23 በመቶ የሚሸፍን መሆኑን የጠቆሙት ተጨማሪ የጭነት አውሮፕላኖችን በመጨመር ዘርፉን ለማስፋፋት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በቦይንግ የንግድ ሽያጭና ማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ብራድ ማክሙለን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 777-8 የካርጎ አውሮፕላን በማዘዝ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ በመሆኑ ዕውቅና እንሰጣለን ብለዋል።
ስምንት 777-8 የካርጎ አውሮፕላኖችን እና ሁለት 777 የካርጎ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ የአውሮፕላን ስብስቡን እያሳደገና የአገልግሎት አድማሱን በአፍሪካ እያሰፋ ይገኛል።
በዳግማዊት አበበ

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የሶማሌ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔ አቶ ሙስጠፌ መሃመድን በድጋሚ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አርድጎ መርጧል፡፡
ኢስማኢል ኡስማንን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሰይሟል።
የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ሙበሽር ዱበድን ዋና አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል። እንዲሁም ኢንጂነር ሐናን አብዱ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው በምክር ቤቱ ተሰይመዋል።
የሶማሊ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤውን በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል። #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

❤5👍1
ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋ እንዲዘጋ ወሰነች
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ መወሰኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መንግሥት 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታ ከኢትዮጵያ እንዲወጡም ወስኗል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በቪየና የዲፕሎማሲ ስምምነትን ጥሰዋል የተባሉ አስር ኤርትራውያን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ኢትዮጵያን እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቷዋል።
ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የጠብ አጫሪነት እና የትንኮሳ ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት በአስመራ፣ ኤርትራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት መወሰኑን የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመለክታል።