Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.8K subscribers
41.3K photos
346 videos
7 files
5.82K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ ይታደማሉ።

#PMOEthiopia
"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር
+++++++++

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል።

ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።

በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ።
በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም
👍8👎7❤4😁2👏1
የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል
+++++++++++++++++

በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ  አዳነች አቤቤ፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ብፁዓን አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ታድመዋል።

የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ነው። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።
#Meskel #Demera #MeskelSquare #EthiopianHeritage #Ethiopia
❤6👍1
የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት
+++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚተገበረው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት፣ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነትና የኢኮኖሚ አጋርነት የሚያጎለብትና ድንበር ተሻጋሪ የመሰረተ ልማት ውጥንን እውን አድርጓል።

ፕሮጀክቱ ነዳጅ ለማጓጓዝ የሚወስደውን ጊዜ በመቀነስ የሎጂስቲክስ ቅልጥፍናን የሚያፋጥን ነው። የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ አጋርነት ይተገበራል።

ከአንድ ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን የመያዝና የማስተላለፍ አቅምም ይኖረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ እና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ በተገኙበት ፕሮጀክቱ ይፋ ተደርጓል። ኢትዮጵያ የያዘችው ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ እምቅ አቅሞችን ወደ ተግባር እየቀየረች ትገኛለች

የመሠረተ ልማት ትስስር እንዲሁም የኢነርጂ ዲፕሎማሲ በተለይም በታዳሽ ኃይል አቅርቦት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ለሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኬንያና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን በተግባር እያጠናከረች ትገኛለች።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሀገር ውስጥ ብርሃን ከመሆን አልፎ ለቀጣናው ሀገራት የሚተርፍ ንጹህ የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማመንጨት የምሥራቅ አፍሪካን የኢንዱስትሪ መነቃቃት የሚያግዝ ትልቅ የልማት ሞተር ሆኗል።
#Ethiopia #CouncilOfMinisters #EthiopianGovernment #PolicyDecisions #AddisAbaba