Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.8K subscribers
41.3K photos
346 videos
7 files
5.82K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፤ በተግባር የታነጸበት ስራ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
+++++++++++++

ዛሬ በሞጆ ተገኝተን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና የሚጫወተውንና በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፍያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስመርቀናል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ጣቢያዎችና ዘመናዊ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን፣ የደረቅ ብትን ጭነቶችን በሀገር ውስጥ እንድናሽግ ማስቻሉ፣ የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ ባለፈ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

የማዕከሉን የአሰራር ፍጥነት ለማሳደግ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተተከለው የባቡር ላይ ክሬን ከባቡር መስመር የሚደረገውን የኮንቴነር ዝውውር በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።

ሙሉ አሰራሩ በዘመናዊ ዲጂታል መሰረተ ልማት የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተገልጋዮች ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎትን ያሳልጣል። ይህ ማዕከል ከኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ባሻገር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን የሚያስተሳስረው የ‘ደሱ’ ኮሪደር አካል ሲሆን፤ ይህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ደረጃ ላይ ያላትን ስፍራ የሚያሻሽልና የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስራችንን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ ድል ነው።

#EthiopiaDelivers
❤3
"በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ባደረግነው በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶችና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ተወያይተናል። የውይይትን አስፈላጊነትና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረናል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

🇪🇹 🇮🇷
❤8
ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
‎
‎ውይይታችን በመከላከያና ደኅንነት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው። የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህልና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል።
‎
‎በተጨማሪም ለኮፕ 32 በምናደርገው ዝግጅት ያለንን አጋርነት ጨምሮ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል። በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

‎🇪🇹 🇷🇺
👏10❤7👍3
በኮሪደር መሰረተ ልማት እርጅናዋ የተገፈፈ አዲስ አበባ
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - በአዲስ አበባ ከተማ ከተከናወኑት የኮሪደር ልማቶች ቀደም ሲል የነበሯትን የታሪክና የተፈጥሮ መስህቦች ከዘመናዊ የመስተንግዶና የመዝናኛ አገልግሎቶች ጋር አስተሳስረዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ከተሞችን ውበትና ንፅህና ከመጠበቅ ባሻገር፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን ሳይበላሹ ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል ዘላቂ የቱሪዝም ልማት መሰረት ጥለዋል።

#TourismEthiopia #LandOfOrigins #VisitEthiopia #EthiopianTourism #TravelEthiopia #ExploreEthiopia #EcoTourism #CulturalHeritage #DestinationEthiopia #TourismSector #EthiopiaTravel #AfricanTourism
❤9😁1
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ ይታደማሉ።

#PMOEthiopia