Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.7K subscribers
41.3K photos
346 videos
7 files
5.82K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"በአረንጓዴ ዐሻራ አትርፈናል፤ በቡና አትርፈናል፣ በፍራፍሬ አትርፈናል፤ በሻይ ልናተርፍ ነው፤ የድህነትና የችግር ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ ያ መልኳና ስሟ እየተቀየረ ነው። ያ የሚቀየረው ግን ደክመን ነው፣ ጭቃ ነክተን ሰርተን ነው፤ ማንም ሊሰራልን አይችልም"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከመስከረም እስከ መስከረም መጽሐፍ፣ 8ኛ ቅጽ፣ገጽ 243
1
የህዳሴ ግድብ በሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አይደለም ሲሉ የውሃ ምህንድስና ተመራማሪው ገለጹ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ፡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው ግድብ ጅማሮ መሆኑንና ገና በርካታ ሥራዎች ሊከናወኑ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

የውኃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ ገና መጠቀም ጀመረች እንጂ የማንንም ጥቅም አልነካችም። ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ የሕዳሴ ግድብን በመገንባቷ ምንም ዓይነት ቅሬታ የሚያስነሳባት ጉዳይ እንደሌለም ተናግረዋል።

የዓባይ ወንዝ 45 ሺህ ጊጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል አቅም እንዳለው የጠቆሙት ፕሮፌሰር ይልማ፤ ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ላይ የምታከናውናቸው ሥራዎች የተደበቁ ሳይሆኑ በግልጽ ለሁሉም በሚታይ መልኩ የሰፈሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዓባይ ወንዝ ከኢትዮያ የሚነሳ ሀብቷ ቢሆንም የታችኛውም ሆነ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን በሚጠቅምና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ያስቀመጠችው እውነታ እንደሆነም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን ሕግ የተላለፈችበት ጊዜ እንደሌለ የገለጹት ፕሮፌሰር ይልማ፤ አሁንም ቢሆን ፍትሐዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ወንዙን ለሌሎች አገልግሎቶች የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት አስረድተዋል።

የግብፅ ጩኸት የውኃ መጠን ቀንሶባት ሳይሆን ቀደም ሲል በበላይነት የመጠቀም አሠራሯ እንዳያበቃ ከመስጋት የመነጨ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አክለው ገልጸዋል።

የህዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣፕላስ #ዓባይወንዝ #የሕዳሴግድብ #የውኃምሕንድስና #ኢፕድ #ኢትዮጵያ
11👍2
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም ስምምነት ተፈረመ
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለው ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ተቋሙ በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የሚቋቋም ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት መሆኑን ገልጸዋል።

በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የሚስተዋለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን የሚቀርፍ መሆኑን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብና በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #የቤት_መግዣ_ብድር #ብሔራዊ_ባንክ #IFC #የፋይናንስ_ዘርፍ #የቤት_ልማት #ኢትዮጵያ
6👍3
ኢትዮጵያ የውጪና የገቢ ምርቶቿን ለማቀላጠፍ በ83 ቢሊዮን ብር ወጪ 16 መርከቦችን ልትገዛ ነው
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ አሁን ካሏት 10 መርከቦች በተጨማሪ በ83 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 16 መርከቦችን ለመግዛት አቅዳ የስድስት መርከቦች ግዥ በሂደት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዋና ክፍል ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ኃይለማርያም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ለወጪና ገቢ ምርቶች ከምትጠቀምባቸው 10 መርከቦች በተጨማሪ 16 መርከቦችን ለመግዛት አቅዳለች፡፡

መርከቦቹን በቀጣይ አምስት ዓመታት ለመግዛት የታቀደ ሲሆን፤ ለዚህም 83 ነጥብ1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ገልፀው መርከቦችን በግዥ የኢትዮጵያ የማድረግ ሥራ የተቋሙ የስትራቴጂክ ዕቅዶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም ስድስት መርከቦች ሕጋዊ የግዥ ሥርዓት በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙ መርከቦች ጠቅላላ የመሸከም አቅም ከ25ሺ እስከ 28ሺ ሲሆን፤ የአዳዲሶቹ መጫን አቅም ከቀድሞቹ አንጻር ሲታይ ግዙፍና ከ50ሺ እስከ 63ሺ የመጫን አቅም ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

የመርከቦቹ ግዥ በሀገሪቱ ስትራቴጂክ የሆኑ ግብዓቶችን ጨምሮ በርካታ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እንዲሁም ወደ ውጭ የሚላከውን በቅልጥፍናና በወቅቱ በመላክ የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴን ውጤታማነት ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ በድርጅቱ መርከቦች፣ በስሎትና በኪራይ መርከቦች ብትን ዕቃን ጨምሮ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን ገቢ ዕቃ ለማጓጓዝ ታቅዶ 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን አጓጉዟል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት የመሆን ሕልሟን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረገች መሆኗን የገለጹት አቶ ስንታየሁ፤ ይህን ውጥን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በክፍለዮሐንስ አንበርብር

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት#ጋዜጣፕላስ #መርከብ ግዥ#ገቢና ወጭ ምርቶች#ንግድ #ኢኮኖሚ#ኢትዮጵያ
6😁1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የማንሠራራት ቀንን (ጳጉሜ 2ን) አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት
++++++++++++

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል።

ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።

#EthiopiaDelivers
👍64
"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፤ በተግባር የታነጸበት ስራ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
+++++++++++++

ዛሬ በሞጆ ተገኝተን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና የሚጫወተውንና በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፍያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስመርቀናል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ጣቢያዎችና ዘመናዊ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን፣ የደረቅ ብትን ጭነቶችን በሀገር ውስጥ እንድናሽግ ማስቻሉ፣ የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ ባለፈ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

የማዕከሉን የአሰራር ፍጥነት ለማሳደግ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተተከለው የባቡር ላይ ክሬን ከባቡር መስመር የሚደረገውን የኮንቴነር ዝውውር በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።

ሙሉ አሰራሩ በዘመናዊ ዲጂታል መሰረተ ልማት የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተገልጋዮች ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎትን ያሳልጣል። ይህ ማዕከል ከኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ባሻገር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን የሚያስተሳስረው የ‘ደሱ’ ኮሪደር አካል ሲሆን፤ ይህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ደረጃ ላይ ያላትን ስፍራ የሚያሻሽልና የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስራችንን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ ድል ነው።

#EthiopiaDelivers
2
"በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ባደረግነው በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶችና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ተወያይተናል። የውይይትን አስፈላጊነትና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረናል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

🇪🇹 🇮🇷
3