Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.3K photos
346 videos
7 files
5.82K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሕዳሴ ግድብን አንድ ሦስተኛ ኃይል የማመንጭት አቅም ያለው የኮይሻ ግድብ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ ደርሷል
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተገነባ የሚገኘውና የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ የሚጠበቀው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሽብር ባልቻ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለመገናኛ ብዙኃን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ግድቡን በታቀደለት ጊዜ አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

በሦስት ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ አፈጻጸሙ ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

የኮይሻ ግድብን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በከፊል ሥራ ለማስጀመር ግብ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን አንድ ሦስተኛ ያህል ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ግድብ፣ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

የኮይሻ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ፣ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት ከመቀየር ባለፈ ለዘላቂ ልማት ትልቅ ምሰሶ እንደሚሆን ይጠበቃል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኮይሻ_ግድብ #ኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል #የውኃ_ኃይል_ማመንጫ #የሕዳሴ_ግድብ #የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ኢትዮጵያ
8
"በአረንጓዴ ዐሻራ አትርፈናል፤ በቡና አትርፈናል፣ በፍራፍሬ አትርፈናል፤ በሻይ ልናተርፍ ነው፤ የድህነትና የችግር ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ ያ መልኳና ስሟ እየተቀየረ ነው። ያ የሚቀየረው ግን ደክመን ነው፣ ጭቃ ነክተን ሰርተን ነው፤ ማንም ሊሰራልን አይችልም"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከመስከረም እስከ መስከረም መጽሐፍ፣ 8ኛ ቅጽ፣ገጽ 243
1
የህዳሴ ግድብ በሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አይደለም ሲሉ የውሃ ምህንድስና ተመራማሪው ገለጹ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ፡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው ግድብ ጅማሮ መሆኑንና ገና በርካታ ሥራዎች ሊከናወኑ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

የውኃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ ገና መጠቀም ጀመረች እንጂ የማንንም ጥቅም አልነካችም። ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ የሕዳሴ ግድብን በመገንባቷ ምንም ዓይነት ቅሬታ የሚያስነሳባት ጉዳይ እንደሌለም ተናግረዋል።

የዓባይ ወንዝ 45 ሺህ ጊጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል አቅም እንዳለው የጠቆሙት ፕሮፌሰር ይልማ፤ ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ላይ የምታከናውናቸው ሥራዎች የተደበቁ ሳይሆኑ በግልጽ ለሁሉም በሚታይ መልኩ የሰፈሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዓባይ ወንዝ ከኢትዮያ የሚነሳ ሀብቷ ቢሆንም የታችኛውም ሆነ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን በሚጠቅምና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ያስቀመጠችው እውነታ እንደሆነም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን ሕግ የተላለፈችበት ጊዜ እንደሌለ የገለጹት ፕሮፌሰር ይልማ፤ አሁንም ቢሆን ፍትሐዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ወንዙን ለሌሎች አገልግሎቶች የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት አስረድተዋል።

የግብፅ ጩኸት የውኃ መጠን ቀንሶባት ሳይሆን ቀደም ሲል በበላይነት የመጠቀም አሠራሯ እንዳያበቃ ከመስጋት የመነጨ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አክለው ገልጸዋል።

የህዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣፕላስ #ዓባይወንዝ #የሕዳሴግድብ #የውኃምሕንድስና #ኢፕድ #ኢትዮጵያ
11👍2
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም ስምምነት ተፈረመ
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለው ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ተቋሙ በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የሚቋቋም ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት መሆኑን ገልጸዋል።

በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የሚስተዋለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን የሚቀርፍ መሆኑን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብና በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #የቤት_መግዣ_ብድር #ብሔራዊ_ባንክ #IFC #የፋይናንስ_ዘርፍ #የቤት_ልማት #ኢትዮጵያ
6👍3
ኢትዮጵያ የውጪና የገቢ ምርቶቿን ለማቀላጠፍ በ83 ቢሊዮን ብር ወጪ 16 መርከቦችን ልትገዛ ነው
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ አሁን ካሏት 10 መርከቦች በተጨማሪ በ83 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 16 መርከቦችን ለመግዛት አቅዳ የስድስት መርከቦች ግዥ በሂደት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዋና ክፍል ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ኃይለማርያም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ለወጪና ገቢ ምርቶች ከምትጠቀምባቸው 10 መርከቦች በተጨማሪ 16 መርከቦችን ለመግዛት አቅዳለች፡፡

መርከቦቹን በቀጣይ አምስት ዓመታት ለመግዛት የታቀደ ሲሆን፤ ለዚህም 83 ነጥብ1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ገልፀው መርከቦችን በግዥ የኢትዮጵያ የማድረግ ሥራ የተቋሙ የስትራቴጂክ ዕቅዶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም ስድስት መርከቦች ሕጋዊ የግዥ ሥርዓት በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙ መርከቦች ጠቅላላ የመሸከም አቅም ከ25ሺ እስከ 28ሺ ሲሆን፤ የአዳዲሶቹ መጫን አቅም ከቀድሞቹ አንጻር ሲታይ ግዙፍና ከ50ሺ እስከ 63ሺ የመጫን አቅም ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

የመርከቦቹ ግዥ በሀገሪቱ ስትራቴጂክ የሆኑ ግብዓቶችን ጨምሮ በርካታ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እንዲሁም ወደ ውጭ የሚላከውን በቅልጥፍናና በወቅቱ በመላክ የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴን ውጤታማነት ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ በድርጅቱ መርከቦች፣ በስሎትና በኪራይ መርከቦች ብትን ዕቃን ጨምሮ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን ገቢ ዕቃ ለማጓጓዝ ታቅዶ 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን አጓጉዟል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት የመሆን ሕልሟን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረገች መሆኗን የገለጹት አቶ ስንታየሁ፤ ይህን ውጥን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በክፍለዮሐንስ አንበርብር

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት#ጋዜጣፕላስ #መርከብ ግዥ#ገቢና ወጭ ምርቶች#ንግድ #ኢኮኖሚ#ኢትዮጵያ
2😁1