“ጊዜ አይለፍብን፣ ዘመን አይለፍብን ዕድል ስናገኝ እንጠቀምበት” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ጊዜ አይለፍብን ዘመን አይለፍብን እድል ስናገኝ እንጠቀምበት፤ ልማት እንስራበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህርዳር ከተማ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናልን የመረቁ ሲሆን በምረቃው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጊዜ አይለፍብን፣ ዘመን አይለፍብን ዕድል ስናገኝ እንጠቀምቡት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የባህርዳርን ዕድገት ለማስቀጠል ሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ያስፈልጋሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመጀመሪያ መሠረተ ልማት በተገነባ ቁጥር በርካታ ሰዎች እየመጡ የከተማዋ ገቢ እንዲያድግና ሌላ ልማት እንዲሰራ የከተማዋን የገቢ አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ባህርዳር በገቢ አቅም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከተሞች 7ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ በመሆኑ ይህንን አቅም ለማሻሻል መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ለቱሪስቶች፣ ለባለሀብቶች፣ወጥተው ለሚገቡ ሰዎች ምቹ እንዲትሆን መላው የከተማዋ ነዋሪና የክልሉ መንግሥት በቅንጅት በመሥራት ባህርዳር የሚገባትን የገቢ ልክ ማመንጨት እንድትችል ተጨማሪ ሥራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ሁለተኛው መሠረታዊ ጉዳይ ሰላም መሆኑን በአፅንኦት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተጀመረው ሥራ ልማድ እንዲሆን ተደጋጋሚ ልማት እንዲሰራ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ባህር ዳር ከብዙ የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተሞች የሚሻል አቅም ያለት በመሆኑ ይህ አቅሟ በእኛ ትጋት፣ ልፋትና ሥራ ልቆ እንዲታይ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ሰላም ውድ ስጦታ፣ ጊዜ ትልቅ ሀብት፣ ሥራ ትልቅ ፀጋ፣ ትብብር በጋራ መቆምና መልፋት ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልግበት ዘመን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።
እንደዛሬው ዘመን የአማራ ክልልም ሆነ ባህርዳር እራሱን በራሱ በተሟላ መንገድ የሚያስተዳድርበት ዘመን አልነበረም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጊዜ እንዳያልፍብን ተባብረን ተግባብተን ሀገራችንን እንለውጥ ሲሉ አስገንዝበዋል።
በክብረአብ በላቸው
++++++++++++++
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #ጋዜጣ-ፕላስ #ኢትዮጵያ #አማራ #ባህርዳር #ኤርፖርት #የአየርትራንስፖርት

❤4
ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ተቋም የሆነው 'ፈርስት ፖስት' ስለኢትዮጵያ ባሰራጨው ዘገባ ያነሳቸው ዐቢይት ሃሳቦች
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ| ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት የመጪው ዘመን የአፍሪካ ኃያል ሀገር ወደመሆን እየተሸጋገረች ነው ሲል ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት ፖስት ዘግቧል።
ፈርስት ፖስት ሚዲያ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሠራው ወደ ዘጠኝ ደቂቃ በሚጠጋ ትንታኔው ያነሳቸው ዐቢይት ሃሳቦች፤
✍️ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት አስደናቂ የኢኮኖሚ ሽግግር እያደረገች ነው፣
✍️ በኢነርጂ፣ በአቪዬሽን፣ በማዕድንና በዲጂታል ኢኮኖሚ መስኮች በተግባር እየሰራች ነው፣
✍️ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በግንባታ ላይ ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያሰተናግዳል፣
✍️ አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ አህጉር ለሚካሄደው የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ከፍተኛ መነቃቃትን ለመፍጠር ታስቦ የተነደፈ ስትራቴጂካዊ ምሰሶ ነው፣
✍️ ህዳሴ ግድብ ከየትኛውም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ብድር ሳይወሰድበት በኢትዮጵያውያን መገንባቱ፣ አፍሪካውያን የራሳቸውን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀም እንደሚችሉ ያረጋገጠ ትልቅ ማሳያ ነው፣
✍️ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ የቀጣናው የትስስር ማዕከል እየሆነች መምጣቷን አድንቋል
✍️ የወጪ ንግዱን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ ያለው የማዕድን ዘርፍና በሶማሌ ክልል እየተገነባ ያለው ግዙፉ የማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና አለው፣
✍️ የዲጂታል ትስስር በማስፋፋት የ4ጂ እና 5ጂ አገልግሎቶች በበርካታ ከተሞች ተደራሽ ሆኗል
✍️ ከቻይና፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት፣ ከምዕራባውያን አጋሮችና ከአፍሪካ ኢንቨስትመንትን እየሳበች ትገኛለች፣
✍️ ኢትዮጵያ ጎራ ሳትለይ ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር ትብብሯን እያጠናከረች ነው፣
✍️ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች ረገድ አስደማሚ ለውጦችን እያሳየች ነው
✍️ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍትና የካፒታል ገበያ መጀመር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በእጅጉ እንደሚያሳድገው
✍️ ኢትዮጵያ ካላት የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ አኳያ እድልና ፈተናዎች ከፊቷ መሆናቸውን በማንሳት፥ አዲሱን የዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት ብሪክስ አባል መሆኗ ጠቅሷል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት በቀጣናውና የአፍሪካ ኃያል ሀገር መሆን የሚያስችላትንና የአህጉሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚበይንና የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሠራች መሆኗን በዘገባው አመላክቷል።
#Firstpost #Ethiopia #EconomicGrowth #Africa #Ethiopia #EconomicReform #DigitalTransformation #CapitalMarket

❤1👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ጋር በነበራቸው ቆይታ፤
✅ የአሮሞ ህዝብ የኢኮኖሚ ፣የማንነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን በግልጽ አስቀምጦ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሊተዳደሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር በዚህች ሀገር ውስጥ መረጋገጥ የሚችልበትን መንገድ ለመቀየስ መስዋዕትነትን ከፍሏል፣
'✅ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የቆዬ ነው። ይህ ትግል በአንድ ቦታ፣ በአንድ አካባቢ የተጀመረና እዚያው የቆመ አይደለም፣
✅ የአሮሞ ትግል ድል የራቀው የአመራር ትግል ነው፤ ትልቅ ሃሳብ አሸናፊ ሃሳብ ይዞ የሚነሳ አመራር አለመኖር ነው፣
✅ የአሮሞ ህዝብ በዘመናት ታሪኩ በማንኛውም ጊዜ ከሥርዓቱ መበላሸት ውጭ በኢትዮጵያ ላይ ተቃውሞ አያውቅም፤ ጥያቄው ሁልጊዜ ከሥርዓቱ እንጅ ከሀገሪቱ አይደለም፣

😁5👍2