Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአፍሪካ ተወካዮች ስለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ...
++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - በይፋ የተጀመረው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋ እንግዶች የተገኙበት የአፍሪካ ተወካዮች ስለሀገራዊ ምክክሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክቶቻቸውም ሀገራዊ ምክክሩ "በኢትዮጵያውያን የተመራና የኢትዮጵያውያን የሆነ"፣ የአፍሪካ ኅብረትን "አጀንዳ 2063" ራዕይ የሚያሳካና የአፍሪካውያንን ችግር በአፍሪካውያን የመፍታት መርህን በተግባር ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ቺፍ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

የኢትዮጵያን ታሪክ፣ የህዝቦቿን ብዝሃነትና ታታሪነት በመጥቀስ ይህ ህዝብ የሰነቀውን ብሩህ ተስፋ ለማሳካት ደግሞ አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ስኬት ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ በሀገራዊ ምክክር መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት

በዓለም ታሪክ ውስጥ በግጭት የተገነባ ወይም ያተረፈ ሀገር የለም። በፖለቲካ ባህል ውስጥ ልዩነቶች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ቢሆንም፤ ትልቁና መሰረታዊው ስህተት ግን እነዚህን ልዩነቶች በኃይል ለመፍታት መሞከር ነው። ከሁሉ በላይ ልዩነቶችን መፍታት የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ፣ በመነጋገርና በተለያዩ ሰላማዊ መድረኮች መሆኑን ይገባል። ኢትዮጵያም ለዚህ የሚሆኑ በርካታ ባህላዊ የምክክር መንገዶች ያሏት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ

በዚህ ታሪካዊ ስፍራ ተገኝተው የዚህ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ አካል መሆን ለአፍሪካ ህብረት ትልቅ ኩራት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የሂደቱንም ታላቅነት፣ ስፋትና ጥንካሬ በከፍተኛ ሁኔታ አድንቀዋል። የአፍሪካ ህብረት ይህንን ታሪካዊ ክስተት በሙሉ አቅሙ እንደሚደግፍ በማረጋገጥ፣ ይህ የጋራ ጉዞ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን፣ ልማትንና አዎንታዊ ለውጥን ማምጣት እንደምትችል የሚያሳይ ህያው ምስክር መሆኑን አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ የገጠማትን ውስብስብ የፖለቲካ ችግር መፍታት የምትችለው የራሷን ጥንታዊ የዕርቅ እሴቶች በመጠቀምና ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ ፖለቲካዊ መፍትሄ በማምጣት ብቻ መሆኑን ነው። ለዚህ ታሪካዊ ሽግግር ዋነኛው መሻጋሪያ ድልድይ መሆኑና ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

#Ethiopia #AfricanUnion #IGAD #PeaceBuilding #Agenda2063 #AfricanSolutions
3
በሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጸናች ኢትዮጵያ ያላቸውን ጠንካራ አንድነትና የጋራ ኃላፊነት በሚያንጸባርቀው፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር ለታሪካዊው ሀገራዊ ዘመቻ በጋራ በመሰብሰብ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኞችን ይተክላሉ። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓም፤ እርሶም የዚህ ታሪካዊ ንቅናቄ አካል ይሁኑ!

#ተስፋንእንትከል #አረንጓዴዐሻር #PMOEthiopia #GreenLegacy
👍1
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመሥራት ለታቀደው ሀገራዊ መርሐ-ግብር አምስት ቀናት ብቻ መቅረታቸውን በመጠቆም፣ መላው ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያውያን ክንድ ተባብሮ በአንድነት ለሚመዘገበው ታሪካዊ ድል እውን መሆን ዜጎች በቁርጠኝነት ሊነሡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

"በጋራ ተስፋን እንትከል!" በማለት ውድ ኢትዮጵያ ልጆች በቀሪዎቹ ቀናት ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው በዕለቱ በንቃት እንዲሳተፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

#Ethiopia #greenlegacy #plantinghope #greenlegacy onedayplanting
7👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ያደረጉት ቆይታ ክፍል 1 አርብ ምሽት 2:30 ይጠብቁ።#PMOEthiopia
16👍8👎1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንዲሁም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ጋር በመሆን ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል። #PMOEthiopia
👍4
76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ እንዳመለከተው፤ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ሲሆን፤ የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው ተብሏል።

የአፍሪካ የኢኮኖሚ፣የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መዲና የሆነቸው አዲስ አበባ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባኤዎችን አስተናግዳለች፤ ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤን ታስተናግዳለች፡፡

ስብስባው የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂያዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል።

ጉባኤው ኢትዮጵያ በጤናው ዲፕሎማሲ ዘርፍ የምታደርገው አወንታዊ አስተዋዕጾ እንዲሁም በዘርፉ ያላት ልምድ ለማካፈል እድል ያመቻቻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ቀጣና አባል ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች እንደሚሳተፋ መረጃው አመልክቷል።

#Ethiopia #health #WHO #HealthSecurity #RC76 #AddisAbaba #africaunion
1
“ጊዜ አይለፍብን፣ ዘመን አይለፍብን ዕድል ስናገኝ እንጠቀምበት” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ጊዜ አይለፍብን ዘመን አይለፍብን እድል ስናገኝ እንጠቀምበት፤ ልማት እንስራበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህርዳር ከተማ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናልን የመረቁ ሲሆን በምረቃው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጊዜ አይለፍብን፣ ዘመን አይለፍብን ዕድል ስናገኝ እንጠቀምቡት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የባህርዳርን ዕድገት ለማስቀጠል ሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ያስፈልጋሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመጀመሪያ መሠረተ ልማት በተገነባ ቁጥር በርካታ ሰዎች እየመጡ የከተማዋ ገቢ እንዲያድግና ሌላ ልማት እንዲሰራ የከተማዋን የገቢ አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ባህርዳር በገቢ አቅም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከተሞች 7ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ በመሆኑ ይህንን አቅም ለማሻሻል መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለቱሪስቶች፣ ለባለሀብቶች፣ወጥተው ለሚገቡ ሰዎች ምቹ እንዲትሆን መላው የከተማዋ ነዋሪና የክልሉ መንግሥት በቅንጅት በመሥራት ባህርዳር የሚገባትን የገቢ ልክ ማመንጨት እንድትችል ተጨማሪ ሥራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ሁለተኛው መሠረታዊ ጉዳይ ሰላም መሆኑን በአፅንኦት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተጀመረው ሥራ ልማድ እንዲሆን ተደጋጋሚ ልማት እንዲሰራ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ባህር ዳር ከብዙ የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተሞች የሚሻል አቅም ያለት በመሆኑ ይህ አቅሟ በእኛ ትጋት፣ ልፋትና ሥራ ልቆ እንዲታይ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ሰላም ውድ ስጦታ፣ ጊዜ ትልቅ ሀብት፣ ሥራ ትልቅ ፀጋ፣ ትብብር በጋራ መቆምና መልፋት ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልግበት ዘመን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

እንደዛሬው ዘመን የአማራ ክልልም ሆነ ባህርዳር እራሱን በራሱ በተሟላ መንገድ የሚያስተዳድርበት ዘመን አልነበረም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጊዜ እንዳያልፍብን ተባብረን ተግባብተን ሀገራችንን እንለውጥ ሲሉ አስገንዝበዋል።

በክብረአብ በላቸው
++++++++++++++
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #ጋዜጣ-ፕላስ #ኢትዮጵያ #አማራ #ባህርዳር #ኤርፖርት #የአየርትራንስፖርት
4
ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ተቋም የሆነው 'ፈርስት ፖስት' ስለኢትዮጵያ ባሰራጨው ዘገባ ያነሳቸው ዐቢይት ሃሳቦች
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ| ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት የመጪው ዘመን የአፍሪካ ኃያል ሀገር ወደመሆን እየተሸጋገረች ነው ሲል ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት ፖስት ዘግቧል።

ፈርስት ፖስት ሚዲያ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሠራው ወደ ዘጠኝ ደቂቃ በሚጠጋ ትንታኔው ያነሳቸው ዐቢይት ሃሳቦች፤

✍️ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት አስደናቂ የኢኮኖሚ ሽግግር እያደረገች ነው፣

✍️ በኢነርጂ፣ በአቪዬሽን፣ በማዕድንና በዲጂታል ኢኮኖሚ መስኮች በተግባር እየሰራች ነው፣

✍️ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በግንባታ ላይ ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያሰተናግዳል፣

✍️ አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ አህጉር ለሚካሄደው የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ከፍተኛ መነቃቃትን ለመፍጠር ታስቦ የተነደፈ ስትራቴጂካዊ ምሰሶ ነው፣

✍️ ህዳሴ ግድብ ከየትኛውም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ብድር ሳይወሰድበት በኢትዮጵያውያን መገንባቱ፣ አፍሪካውያን የራሳቸውን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀም እንደሚችሉ ያረጋገጠ ትልቅ ማሳያ ነው፣

✍️ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ የቀጣናው የትስስር ማዕከል እየሆነች መምጣቷን አድንቋል

✍️ የወጪ ንግዱን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ ያለው የማዕድን ዘርፍና በሶማሌ ክልል እየተገነባ ያለው ግዙፉ የማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና አለው፣

✍️ የዲጂታል ትስስር በማስፋፋት የ4ጂ እና 5ጂ አገልግሎቶች በበርካታ ከተሞች ተደራሽ ሆኗል

✍️ ከቻይና፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት፣ ከምዕራባውያን አጋሮችና ከአፍሪካ ኢንቨስትመንትን እየሳበች ትገኛለች፣

✍️ ኢትዮጵያ ጎራ ሳትለይ ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር ትብብሯን እያጠናከረች ነው፣

✍️ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች ረገድ አስደማሚ ለውጦችን እያሳየች ነው

✍️ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍትና የካፒታል ገበያ መጀመር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በእጅጉ እንደሚያሳድገው

✍️ ኢትዮጵያ ካላት የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ አኳያ እድልና ፈተናዎች ከፊቷ መሆናቸውን በማንሳት፥ አዲሱን የዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት ብሪክስ አባል መሆኗ ጠቅሷል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት በቀጣናውና የአፍሪካ ኃያል ሀገር መሆን የሚያስችላትንና የአህጉሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚበይንና የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሠራች መሆኗን በዘገባው አመላክቷል።

#Firstpost #Ethiopia #EconomicGrowth #Africa #Ethiopia #EconomicReform #DigitalTransformation #CapitalMarket
1👍1