This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ 32 ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 30 ፕሬዚዳንት ጋር ያደረጉት ውይይት‼️
#COP32 #COP32Ethiopia #PMOEthiopia #gazette_plus #Ethiopiadelivers

❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" – 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ
++++++++++++++
"ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓም የሚካሄድ አምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አዘጋጅቷል።
በዚህ ታሪካዊ ስፖርታዊ መርሐግብር ላይ ከ20 ሺህ በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሩጫው ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ዜጎች ሁሉ እንድትሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።
#ሀገራዊ_ምክክር #ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው #የጎዳና_ላይ_ሩጫ #ሐምሌ_5 #ሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን #የምክክር_ሩጫ #EthiopianNationalDialogue #Ethiopia

❤2👍2
በመደመር መንግሥት የኢኮኖሚ ስትራቴጂ የታገዘው የግብርናው ዘርፍ፣ ፈጣን ዕድገትን በማረጋገጥ የሀገራችንን ራስን የመቻል ርዕይ እውን እያደረገ ይገኛል።
የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት እና የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ ዘርፉ ለሌሎች ኢንዱስትሪዎችም የማይናወጥ መሠረት ሆኗል። ይኸው ወሳኝ እመርታ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አማካኝነት በሀገር በቀል መፍትሔዎች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት መለወጥና የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚቻል በተግባር እያሳየን ነው።
በጋራ እናልማ፣ እናምርት፣ እንበልጽግ!
#EthiopiaDelivers
#PMOEthiopia

❤3👎2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን ስራ አሰጀመሩ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ሕዝብ ለዓመታት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረውና ለ30 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የአውሮፕላን ማረፊያ፤ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎና ደረጃው ከፍ ብሎ ተገንብቶ ዛሬ መመረቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
በ2,400 ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ላይ የተገነባው እንደ Q400 እና B737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚያስችል ከፍተኛ ዐቅምም ፈጥሯል።
ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ መጀመሩ የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለአካባቢው እና ለመላው ሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስና የጀመርናቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለምርቃት ለማብቃት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየን እንቀጥላለን ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
#NationalDialogue #ሀገራዊምክክር #ኤርፖርት #airport Ethiopian Airlines

❤4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኳታር መንግሥትና ሕዝብ የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ በማረፋቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ በራሳቸው፣ በመንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ለኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ፣ ለሀገሪቱ መንግሥትና ለወንድም የኳታር ሕዝብ ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከመጀመሪያው ሒጅራ ጀምሮ የቆየ ታሪካዊ መሠረት እንዳለው ይገልጹ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በአሁኑ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ መሪነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በሞት ለተለዩት መሪ ዕረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

👍6❤2👎2