Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ በአርባምንጭ - ተስፋን እንትከል

#GreenLegacy #Arbaminch
1
"ኩሪፍቱ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

‎በአርባ ምንጭ ከተማ በ52,000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈውን የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ ዛሬ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል! ብለዋል።

‎ይህ ታላቅ ፕሮጀክት 53 ቅንጡ ቪላዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰል ኢንቨስትመንቶች የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

‎የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ መሰል ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሰማሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
#EthiopiaDelivers #InvestInEthiopia
2
ኢትዮጵያ የኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ እኤአ በ2035 መቶ በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።

በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ዳቢ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ በ2035 መቶ በመቶ የኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።

የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽነትን ለማሳካት ሁለት ዋና ዋና ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ አንደኛው ከዋናው የኃይል ማሰራጫ መስመር ኤሌክትሪክን ማዳረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው ከዋናው መስመር ርቀው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሶላር (የፀሐይ) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተጠቃሚ ማድረግ ነው ብለዋል።

የሶላር ኃይል ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በየአካባቢያቸው የመሰረተ ልማት ዕድገት እየተስፋፋ ሲመጣ ዘላቂና አስተማማኝ ወደ ሆነው ዋናው መስመር የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚሸጋገሩም ተናግረዋል።

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የኃይ አቅርቦት ተደራሽነት ለማረጋገጥ 18 ቢሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ መስፍን፤ አስፈላጊውን በጀት ከመንግሥት፣ ከግሉ ዘርፍና ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የማሰባሰብ ሥራውን ለማከናወን አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመታት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በተከናወኑ ተግባራት የሀገሪቱን አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሽፋን 65 በመቶ ማድረስ መቻሉንም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ዳቢ ገልጸዋል።

በክብረአብ በላቸው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #የኤሌክትሪክ_ሽፋን #መሰረተ_ልማት #ታዳሽ_ኃይል
1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ‎በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ የጎበኙት የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ በፎቶ‼️
#EthiopiaDelivers #InvestInEthiopia
4😁1
ከወጪ ንግድ ከ10 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
+++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ│በ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ከ10 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማት ጋር የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በግምገማ መድረኩላይ የተገኙት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በሀገሪቱ የውጭ ንግድ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ስኬት ተመዝግቧል።

በበጀት ዓመቱ ከወጪ ንግድ 10 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት በተሰራው ስራ ዕቅዱን መቶ በመቶ ማሳካት ተችሏል።

ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዋና መሥሪያ ቤትና በተጠሪ ተቋማት አማካኝነት በተከናወኑ የተቀናጁ የሪፎርም ሥራዎች፣ የወጪ ምርቶች ጥራትን በማረጋገጥና በተዘረጉ ዘመናዊ አሠራሮች መሆኑን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የንግድ ፈቃድ፣ ምዝገባና ዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ፣ ከ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑት አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

በታደሠ ብናልፈው

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #ጋዜጣ_ፕላስ #የወጪ #ገቢ #ንግድ #ንግድናቀጠናዊትስስር #ኢትዮጵያ
1😁1
በአዲስ አበባ 543 ትምህርት ቤቶች የ6ኛ ክፍል ፈተና ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችለዋል- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ⵏበከተማው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ 768 ትምህርት ቤቶች መካከል 543 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት 50 በመቶ እንዲሆን ወስኗል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናውን ከወሰዱት ከ97 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል። 543 ትምህርት ቤቶችም የ6ኛ ክፍል ፈተና ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችለዋል።

የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተማሪዎች 50 በመቶ እንዲሁም 45 በመቶ ለአካል ጉዳተኞች መወሰኑን ተናግረዋል።

በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በቀንና በማታ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከ85 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸው፤ በዘንድሮው ፈተና ሁለት ተማሪዎች 98 አማካይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

459 ተማሪዎች 95 እና ከዚያ በላይ አማካይ ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው፤አምስት ሺህ 559 የሚሆኑት ከ90 በላይ አማካይ ያስመዘገቡ ናቸው ብለዋል።

አጠቃላይ ውጤቱ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በሁለት ነጥብ አራት በመቶ እድገት ማሳየቱንም ገልጸው፣ ከዛሬ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦላይን መመልከት የሚችሉ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++++
#Gazetteplus #ጋዜጣፕላስ #AddisAbaba #AddisAbabaEducation #Grade6Exam
👍3
ኢትዮጵያ 33 ሚሊየን ቶን ስንዴ በዓመት እያመረተች ትገኛለች
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - "በአፍሪካ ትልቋ የስንዴ አምራች ሀገር ግብጽ ነበረች፤ በአመት 9.7 ሚሊዮን ቶን ታመርት ነበር። ኢትዮጵያ ከዚህ በጣም ያነሰ ነበር የምታመርተው። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከ33 ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴ ማምረት ችላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከ33 ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴ ማምረት ችላለች።

ይህም ቀዳሚ አምራች የነበረችውን ግብጽን በ3 እጥፍ መብለጥ ያስቻለን ትልቅ ድል ነው ብለዋል።

በስንዴ ዕርዳታ ጥገኝነት ስትታወቅ የነበረችው ሀገር፣ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት የምግብ ሉዓላዊነቷን አረጋግጣ ወደ ስንዴ ላኪነት መሸጋገሯ የኢኮኖሚ "ሉዓላዊነት ማሳያ ነው።

#Ethiopia #Wheat #AfricaNo1 #WheatProduction #AgriculturalTransformation #Rising
6😁6