Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
👍91🔥1🥱1
የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ ስኬት...
++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ኤክስፖርት 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት የያዘችውን ዕቅድ ማሳካቷን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ፡፡

በባለፈው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ተችሎ ነበር። ይህን ቁጥር አመት ባልሞላ ጊዜ ማሻሻል የተቻለው መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቡናውን ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስራዎች ተከናውነዋል።

በተለይም ለቡና ምርት ጥራት ትኩረት መደረጉ ለዕቅድ ስኬት ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

#ከማምረትበላይ #BeyondProduction #EthiopiaDelivers #PMOEthiopia
የገበታ ለሀገር ትሩፋቶች....

📌 የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት

📌 የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም

📌 የሃላላ ኬላ ሪዞርት

📌 የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ
#አረንጓዴዐሻራ በአርባምንጭ - ተስፋን እንትከል

#GreenLegacy #Arbaminch
1
"ኩሪፍቱ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

‎በአርባ ምንጭ ከተማ በ52,000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈውን የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ ዛሬ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል! ብለዋል።

‎ይህ ታላቅ ፕሮጀክት 53 ቅንጡ ቪላዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰል ኢንቨስትመንቶች የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

‎የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ መሰል ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሰማሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
#EthiopiaDelivers #InvestInEthiopia
2
ኢትዮጵያ የኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ እኤአ በ2035 መቶ በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።

በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ዳቢ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ በ2035 መቶ በመቶ የኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።

የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽነትን ለማሳካት ሁለት ዋና ዋና ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ አንደኛው ከዋናው የኃይል ማሰራጫ መስመር ኤሌክትሪክን ማዳረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው ከዋናው መስመር ርቀው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሶላር (የፀሐይ) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተጠቃሚ ማድረግ ነው ብለዋል።

የሶላር ኃይል ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በየአካባቢያቸው የመሰረተ ልማት ዕድገት እየተስፋፋ ሲመጣ ዘላቂና አስተማማኝ ወደ ሆነው ዋናው መስመር የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚሸጋገሩም ተናግረዋል።

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የኃይ አቅርቦት ተደራሽነት ለማረጋገጥ 18 ቢሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ መስፍን፤ አስፈላጊውን በጀት ከመንግሥት፣ ከግሉ ዘርፍና ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የማሰባሰብ ሥራውን ለማከናወን አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመታት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በተከናወኑ ተግባራት የሀገሪቱን አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሽፋን 65 በመቶ ማድረስ መቻሉንም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ዳቢ ገልጸዋል።

በክብረአብ በላቸው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #የኤሌክትሪክ_ሽፋን #መሰረተ_ልማት #ታዳሽ_ኃይል
1