Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አበባየሁ ደሳለኝ ትባላለች፤ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ከልጇ ጋር
+++++++++++

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ከሚያስመርቃቸው 6ሺህ 417 ተማሪዎች መካከል 2 ሺህ 646 ሴቶች ናቸው። 377 የሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች መሆናቸው በምረቃው ስነስርዓት ላይ ተገልጿል።
3
16 A+ ያስመዝገበው የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዓመቱ ኮኮብ ዘለቀ መንግስቴ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት ካሰመረቃቸው ከአንድ ሺህ 817 ተማሪዎችን መካከል የሰርቬይ ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ተማሪው ዘለቀ መንግስቴ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 817 ተማሪዎችን በአደዋ ድል መታሰቢያ አስመርቋል።

ተመራቂ ዘለቀ መንግስቴ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከወሰዳቸው 58 ኮርሶች 16 A+ በማስመዝገብ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

​ዘለቀ ባለትዳና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፤ ለስኬቱ የቤተሰቦቹ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሶ፤ በተለይም የባለቤቱ የዕለት ተዕለት ድጋፍ ለውጤቱ መሳካት ትልቅ እገዛ ማድረጉን ገልጿል፡፡

በየዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከአካዳሚክ ትምህርት ባለፈ ብዙ ጥሩ ነገሮችን መማሩን የሚናገረው ዘለቀ፤ በቀጣይም በተማረበት የሞያ ዘርፍ ሀገሩን በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ንጉሥ ታደሰ (ዶ/ር) በምረቃው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት የህይወት ዘመን ጉዞ መሆኑን በመገንዘብ ምሩቃን ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ሀገራቸውን እንዲሁም ህዝባቸውን በታታሪነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች፣ በጥናትና ምርምር በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች የሀገሪቱን የፐብሊክ ሴክተር ተቋማዊ አቅም ግንባታ እያጠናከረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በአማን ረሺድ

#ጋዜጣ_ፕላስ #ፕብሊክየኒቨርሲቲ #ተማሪምርቃት #ኢትዮጵያ #EthiopiaDelivers #gazetteplus #graduation
6👍5
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የተመረቀው የእንጦጦ-ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በፎቶ
16😁3