ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበትን ምርጫ አካሂደዋል - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት እንዲሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህመድ አሊ ገለፁ።
ሊቀመንበሩ ባወጡት መግለጫ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን አድናቆት ገለፀው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየውን ሙያዊ ብቃት እና ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በታማኝነት፣ ሰላማዊ እና ግልጽነት ባለው የምርጫ ሂደቶችን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑንም በመግለጫቸው ገልጸዋል።
ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት በአብላጫ ድምፅ ላሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ውስጥ ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ የምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ያለውን ጽኑ አቋም መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia #AfricanUnion #AU #Election2026

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም- ከማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት እስከ ማዕድን ዘርፍ ዕድገት
+++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ ተካሂዷል።
በጉባኤው ላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችና ያመጧቸው ተፅዕኖዎች ታይተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በጉባኤው በሰጡት ማብራሪያ ፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱን ገልጸዋል።
ይህም የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ነፃ በማድረግ፣ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲን በማዘመን፣ ለዘላቂና አካታች ዕድገት ጠንካራ መሠረት ለመጣል የፋይናንስ ዘርፉን በማጠናከር የተገኘ መሆኑን አብራርተዋል።
በተመሳሳይ የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሐና ብርሃኑ፣ የማዕድን ዘርፍ ከነበረበት ደካማ አፈጻጸም በመላቀቅ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አንዱ መሆን የቻለበትን ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አቅርበዋል።
በቁርጠኛ ማሻሻያዎች፣ በገበያ መልሶ ማዋቀርና እሴትን መጨመር በሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶች በመታገዝ ዘርፉ ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢን እያስገኘ፣ የገቢ ምርቶችን ጥገኝነት እየቀነሰ እና ለኢንዱስትሪ ልማት አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ኢንጂነር ሐና አመላክተዋል።
በወርቅ፣ በወሳኝ ማዕድናት፣ በነዳጅና በማዳበሪያ ምርት ላይ እየተስፋፋ በመጣው የኢንቨስትመንት ለውጦች፣ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረችው ትገኛለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ በገዘፈ ርዕይና አፈጻጸም ድምር ውጤት እንደሚያስገኙ ህያው ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል።
#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers

👍3❤2
ለዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ 8 አጀንዳዎች ይፋ ሆኑ
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለዋናው የምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ 8 አጀንዳዎችን ይፋ አደረገ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ ግልጽ በሆነ ሥርዓትን በተከተለ መንገድ 8 ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎችን ለይቷል።
በኮሚሽኑ የተለዩት 8 አጀንዳዎች እያንዳንዳቸው በስራቸው ዝርዝር ንዑስ ጉዳዮችን አካተዋል ብለዋል።
በዚህ መሠረት
1.የሀገር ግንባታ
2.የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ የፖለቲካ ውክልና የምርጫ ሥርአት ጉዳዮች
3.የፌድራል ከተሞች አዲስአበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ
4.የሃይማኖት ጉዳዮች
5.የተቋማት ግንባታ የህግ የበላይነትና የሰብአዊ መብቶች
6.ማህበራዊና ኢኮኖሚ እንዲሁም የአርሶአደር እና አርብቶ አደር ጉዳዮች
7.ሙስና እና መልካም አስተዳደር
8.ሰላም ግንባታ
አጀንዳዎቹ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ በሚካሄደው ጉባዔ ላይ የሚመከርባቸው ናቸው፡፡
በማርቆስ በላይ

❤3
አበባየሁ ደሳለኝ ትባላለች፤ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ከልጇ ጋር
+++++++++++
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ከሚያስመርቃቸው 6ሺህ 417 ተማሪዎች መካከል 2 ሺህ 646 ሴቶች ናቸው። 377 የሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች መሆናቸው በምረቃው ስነስርዓት ላይ ተገልጿል።

16 A+ ያስመዝገበው የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዓመቱ ኮኮብ ዘለቀ መንግስቴ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት ካሰመረቃቸው ከአንድ ሺህ 817 ተማሪዎችን መካከል የሰርቬይ ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ተማሪው ዘለቀ መንግስቴ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 817 ተማሪዎችን በአደዋ ድል መታሰቢያ አስመርቋል።
ተመራቂ ዘለቀ መንግስቴ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከወሰዳቸው 58 ኮርሶች 16 A+ በማስመዝገብ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ዘለቀ ባለትዳና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፤ ለስኬቱ የቤተሰቦቹ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሶ፤ በተለይም የባለቤቱ የዕለት ተዕለት ድጋፍ ለውጤቱ መሳካት ትልቅ እገዛ ማድረጉን ገልጿል፡፡
በየዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከአካዳሚክ ትምህርት ባለፈ ብዙ ጥሩ ነገሮችን መማሩን የሚናገረው ዘለቀ፤ በቀጣይም በተማረበት የሞያ ዘርፍ ሀገሩን በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ንጉሥ ታደሰ (ዶ/ር) በምረቃው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት የህይወት ዘመን ጉዞ መሆኑን በመገንዘብ ምሩቃን ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ሀገራቸውን እንዲሁም ህዝባቸውን በታታሪነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች፣ በጥናትና ምርምር በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች የሀገሪቱን የፐብሊክ ሴክተር ተቋማዊ አቅም ግንባታ እያጠናከረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በአማን ረሺድ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ፕብሊክየኒቨርሲቲ #ተማሪምርቃት #ኢትዮጵያ #EthiopiaDelivers #gazetteplus #graduation

❤6👍5