Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መረሐግብር የችግኝ ተከላ በቢሾፍቱ ሲያስጀምሩ
#GreenLegacy #ቢሾፍቱ_ኤርፖርት #AfricaRising #አረንጓዴዐሻራ #water
"የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታ አትችሉም ለሚሉን እንደምንችል የምናሳይበት ፕሮጀክት ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | እየተገነባ ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማሪፊያ ፕሮጀክት አትችሉም ለሚሉን እንደምንችል፣ የአፍሪካን አቅም ለዓለም የምናሳይበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ፕሮጀክቱ ሲታሰብ ጀምሮ በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከ8ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታን በጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የማሰብ፣ የማቀድና የመስራት አቅም ለአለም የሚያሳይ ግዙፍ ስራ ነው ብለዋል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም እንደነበሩትና በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚዘገዩት ፕሮጀክቶች ሳይሆን በከፍተኛ ክትትል የሚመራ፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቅ እንደሆነም ገልጸዋል።

በፕሮጀክቱ ጅማሮ ላይ ብዙዎች አትችሉም፣ ገንዘቡም አይገኝም፣ ስራውን መምራት አይሆንላችሁም፣ ለምን ታስባላችሁ የሚል የተስፋ ማስቆረጥ ምልከታ እንደነበራቸው አስታውሰው፤ እኛ ግን እንችላለን፣ ይገባናል የሚመጥነን ፕሮጀክት ነው ብለን በተግባር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የኤርፖርቱ ግንባታ በትልቅነቱ፣ በሚመደብለት ሃብትና በአጠቃላይ በሚያንቀሳቅሰው ማሽነሪ በአፍሪካ ደረጃ ትልቁ ፕሮጀክት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በግንባታው ሂደት የሚገጥሙ በርካታ ፈተናዎችን በመፍታት ፕሮጀክቱን ማሳካት እንደሚቻል በተግባር እየታየ ይገኛል ብለዋል።

በልማቱ ምክንያት የተነሱ የአካባቢው አርሶ አደሮች የቤት ግንባታና የቢዝነስ ተቋማት መደራጀታቸውንና በፕሮጀክቱ ምክንያት የሚጎዳ አርሶ አደር እንደማይኖርና ሙሉ በሙሉ ህይወታቸው እንደሚሻሻል አረጋግጠዋል።

በፕሮጀክቱ ከ8 ሺህ በላይ ሠራተኞች እንደሚገኙና እስከ 4 ሺህ የሚጠጉ ማሽነሪዎችና መኪናዎች እንደሚንቀሳቀሱ ጠቅሰው፣ ለማሽኖቹና ለመኪናዎች አገልግሎት በቀን ከ650 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል።

በብዙ ሀገራት ብሎም በኢትዮጵያ የሥራ ሐሳብና ሀብት ቢኖርም፤ የፕሮጀክት አመራር ችግር ስላለ ፕሮጀክቶች መቼ ተጀምረው መቼ እንደሚጠናቀቁና እንዴት ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው በቂ ግንዛቤ አለመኖሩን ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ በረከት ነው፤ ለልጆቻችንም ትልቅ መሰረት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በተባበረ ክንድ የኢትዮጵያን ድህነት ለመስበር፣ የበለጸገችና ያደገች ኢትዮጵያን በጋራ ለማየት በጋራ እንዲቆምና እንዲተባባር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአማን ረሺድ እና በሀብታሙ በውቀት

#ቢሾፍቱ_ኤርፖርት #ሜጋ_ፕሮጀክት #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #አፍሪካ #BishoftuAirport #AfricanExcellence #Infrastructure #AfricaRising
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስጀመሩ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዚህ ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠን፣ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን።

ዜጎች ‎ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራቸውን እንዲያኖሩም ጥሪ አቅርበዋል።
9👏1😁1🏆1
ኢጋድ ለምርጫው ስኬታማነት ቀዳሚውን ሚና ለተወጡ ኢትዮጵያውያን ዕውቅና ሰጠ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፣ በአብላጫ ድምፅ ላገኘው ብልጽግና ፓርቲና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

በመልዕክቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን በሙያዊ ብቃትና በቁርጠኝነት በመምራቱና የምርጫው በስኬት መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደርና ለሕገ-መንግስታዊ ሥርዓት ያላትን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ መሆኑንም ጠቁሟል።

ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁን ለኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላለፈው ኢጋድ፣ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ውይይትን ለማስፋፋት፣ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት ለምታደርገው ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ገልጿል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትብብርን፣ ውህደትን፣ ሰላምን እና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

በጋዜጣ ፕላስ ሪፖርተር

#ጋዜጣፕላስ #ኢጋድ #ምርጫ2018 #IGAD #Ethiopia #EthiopianElection2026 #Democracy #NEBE #GazettePlus
2
ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበትን ምርጫ አካሂደዋል - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት እንዲሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህመድ አሊ ገለፁ።

ሊቀመንበሩ ባወጡት መግለጫ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን አድናቆት ገለፀው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየውን ሙያዊ ብቃት እና ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በታማኝነት፣ ሰላማዊ እና ግልጽነት ባለው የምርጫ ሂደቶችን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑንም በመግለጫቸው ገልጸዋል።

ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት በአብላጫ ድምፅ ላሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ውስጥ ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ የምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ያለውን ጽኑ አቋም መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia #AfricanUnion #AU #Election2026
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም- ከማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት እስከ ማዕድን ዘርፍ ዕድገት
+++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ ተካሂዷል።

በጉባኤው ላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችና ያመጧቸው ተፅዕኖዎች ታይተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በጉባኤው በሰጡት ማብራሪያ ፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱን ገልጸዋል።

ይህም የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ነፃ በማድረግ፣ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲን በማዘመን፣ ለዘላቂና አካታች ዕድገት ጠንካራ መሠረት ለመጣል የፋይናንስ ዘርፉን በማጠናከር የተገኘ መሆኑን አብራርተዋል።

በተመሳሳይ የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሐና ብርሃኑ፣ የማዕድን ዘርፍ ከነበረበት ደካማ አፈጻጸም በመላቀቅ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አንዱ መሆን የቻለበትን ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አቅርበዋል።

‎ በቁርጠኛ ማሻሻያዎች፣ በገበያ መልሶ ማዋቀርና እሴትን መጨመር በሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶች በመታገዝ ዘርፉ ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢን እያስገኘ፣ የገቢ ምርቶችን ጥገኝነት እየቀነሰ እና ለኢንዱስትሪ ልማት አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ኢንጂነር ሐና አመላክተዋል።

‎በወርቅ፣ በወሳኝ ማዕድናት፣ በነዳጅና በማዳበሪያ ምርት ላይ እየተስፋፋ በመጣው የኢንቨስትመንት ለውጦች፣ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረችው ትገኛለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ በገዘፈ ርዕይና አፈጻጸም ድምር ውጤት እንደሚያስገኙ ህያው ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል።

#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
👍32
ለዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ 8 አጀንዳዎች ይፋ ሆኑ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለዋናው የምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ 8 አጀንዳዎችን ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ ግልጽ በሆነ ሥርዓትን በተከተለ መንገድ 8 ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎችን ለይቷል።

በኮሚሽኑ የተለዩት 8 አጀንዳዎች እያንዳንዳቸው በስራቸው ዝርዝር ንዑስ ጉዳዮችን አካተዋል ብለዋል።

በዚህ መሠረት

1.የሀገር ግንባታ

2.የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ የፖለቲካ ውክልና የምርጫ ሥርአት ጉዳዮች

3.የፌድራል ከተሞች አዲስአበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ

4.የሃይማኖት ጉዳዮች

5.የተቋማት ግንባታ የህግ የበላይነትና የሰብአዊ መብቶች

6.ማህበራዊና ኢኮኖሚ እንዲሁም የአርሶአደር እና አርብቶ አደር ጉዳዮች

7.ሙስና እና መልካም አስተዳደር

8.ሰላም ግንባታ

አጀንዳዎቹ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ በሚካሄደው ጉባዔ ላይ የሚመከርባቸው ናቸው፡፡

በማርቆስ በላይ
3