Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል
+++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ትናንት የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በስኬት ተጠናቅቋል ። በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና የድኅረ ምርጫ ሥራዎች በአግባቡ ተከናውነዋል።

የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች ምዝገባ፣ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የመመዝገብ እንዲሁም ለሌሎችም አካላት ፈቃድ የመስጠት የቅድመ ምርጫ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ የተጠናቀቁ ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሒደት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አስረድተዋል።

እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ማለዳ 12:00 ክፍት ተደርገው ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል። የሲቪክ ማኅበራትም በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ታዝበዋል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) ታዛቢዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ሲታዘቡ ውለዋል።

በብዙ አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ከተጠናቀቀበት ሰዓት ጀምሮ ድምጾች የተቆጠሩ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጡ ዘግይቶ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ቆጠራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቆጠራው እንደተጠናቀቀ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል። ከድምጽ አሰጣጥና ከቆጠራ ጋር በተገናኘ የሚመጡ ጥቆማዎችን በማጣራት ቦርዱ በሕግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል።

በአብዱረዛቅ መሐመድ

#Ethiopianelection2026 #GeneralElection #EthiopiaVotes #NEBE #AfricanUnion #IGAD
6
በብስክሌት “ሜትር ታክሲ”
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የታክሲ ሰልፉ ረዥም ነው። ስንት ሰዓት ነው ወረፋ የሚደርሰኝ? ታክሲ ባገኝ ደግሞ መንገዱ ይዘጋጋል። በሰዓቴ ሥራ ቦታ መገኘት ይኖርብኛል። ታዲያ ምን ይሻለኛል? ብሎ ለሚጨነቅ ሰው ጭንቀቱን የሚጋራና የሚያቃልል ችግር ፈቺ ስታርትአፕ ተፈጥሯል። ከወጪ አንፃር ገንዘብ ቆጣቢ ጤናም ለመጠበቅ የሚያስችል፤ እንግልትን የሚቀንስ ብስክሌትን በመጠቀም አዲስ ሥራ ይዘን መጥተናል ያሉ ወጣቶች ዘመን ኢኮኖሚ አነጋግራቸዋለች። ወጣቶቹ ስለ ፈጠራ ሥራቸው ያብራራሉ ።

እንደ ሜትር ታክሲ አገልግሎት ብስክሌትን በማጋራት ትራንስፖርትን ማቀላጠፍ ይቻላል ብለው የተነሱ ወጣቶች ዳይናሚክ የተሰኘ አክሲዮን ማኅበር መሠረቱ። ድርጅታቸው መሥራት ካሰባቸው ሥራዎች አንዱ የትራንስፖርት ዘርፍ ነውና አንድ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ መሥራት አለብን በሚል ሐሳብ “ፔዳል ፍላይ” የሚል ስያሜ አውጥተው ወደ ትራንስፖርት ዘርፍ ተቀላቀሉ።https://press.et/
7👍3
56ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

✍️ የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉበት ተግዳሮቶች እየተላቀቀና የኢኮኖሚው መሰረቶችም እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡

ማዕቀፉ በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲያስችልና በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ታሳቢዎች ላይ በመመስረት የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

✍️ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ

የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2019 የፌዴራል መንግስት በጀት የአስር አመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው የ2019-2021 የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና የፊሲካል ማዕቀፍን መሰረት በማድረግ፣ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና አላማዎች እንዲሁም በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግስትን የፋይናንስ አቅምና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

በዚሁ መሰረትም ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
3
የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት በጀት ከሁለት ትሪሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ተወሰነ
+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ| የፌዴራል መንግስት የ2019  በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሁለት ነጥብ ሦስት ትሪሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሰለፈ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት  የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ረቂቅ በጀቱ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና አላማዎች፣ በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግስትን የፋይናንስ አቅምና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተገልጿል።

መስከረም ሰይፉ
++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus
3