ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለዒድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
አስተላልፈዋል።
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!
ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።
እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።
ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።
የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።
የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ።
የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል።
የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።
ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።
ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።
ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።
የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም

❤4👍2
በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ መደበኛ ስራ እንደማይኖር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።
በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።
በዚህም መሠረት፤
✍️ ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣
✍️ ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤
✍️ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
✍️ የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይይዙና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።
#ምርጫ #ኢትዮጵያ Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ #gazette_plus

😁2
"ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን"
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++
#ጋዜጣ-ፕላስ | ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በበሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከማለዳ ጀምሮ በመውጣት በሰልፍ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል። ይህም የሚሻውን ለመምረጥ መካሪ እንደማያስፈልገው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
እኔ ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ህዝብ በቁርጠኝነት የሚሻውን ወስኖ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመረጠ በኋላ የተመረጡት ሰዎች በዚያ ልክ ታምነው እጃቸውና ልባቸው ንጹህ ሆኖ ደከመን ታከተን ሳይሉ ሰርተው የሀገር ታሪክ ለመቀየርና የህዝቡን ውለታ ለመክፈል ዝግጁነታቸው ምን ያክል ነው የሚለው ነው ሲሉ ተናግረዋል"
በምርጫው ሂደት ያሸነፉ በታማኝነት ማገልገል የተሸነፉ ደግሞ ውጤቱን በጸጋ ሊቀበሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት@ጋዜጣ-ፕላስ#በምርጫብቻ#ዲሞክራሲ#ምርጫ2018#ኢትዮጵያ#አርባምንጭ #EthiopianElection 2026#ዐቢይ አሕመድ

❤7👍2🥱2
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ድምፃቸውን ሰጡ
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ⵏ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕርዳር ምርጫ ክልል ህዳሴ ምርጫ ጣቢያ(02-1) በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎችም በ164 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
በአማን ረሺድ

❤8
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ትናንት የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በስኬት ተጠናቅቋል ። በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና የድኅረ ምርጫ ሥራዎች በአግባቡ ተከናውነዋል።
የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች ምዝገባ፣ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የመመዝገብ እንዲሁም ለሌሎችም አካላት ፈቃድ የመስጠት የቅድመ ምርጫ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ የተጠናቀቁ ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሒደት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አስረድተዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ማለዳ 12:00 ክፍት ተደርገው ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል። የሲቪክ ማኅበራትም በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ታዝበዋል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) ታዛቢዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ሲታዘቡ ውለዋል።
በብዙ አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ከተጠናቀቀበት ሰዓት ጀምሮ ድምጾች የተቆጠሩ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጡ ዘግይቶ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ቆጠራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቆጠራው እንደተጠናቀቀ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል። ከድምጽ አሰጣጥና ከቆጠራ ጋር በተገናኘ የሚመጡ ጥቆማዎችን በማጣራት ቦርዱ በሕግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል።
በአብዱረዛቅ መሐመድ
#Ethiopianelection2026 #GeneralElection #EthiopiaVotes #NEBE #AfricanUnion #IGAD

❤6