Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
337 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"‎የአራዳ ፓርክ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ስራችን ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******

የአራዳ ፓርክ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ስራችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት አዲሱን የአራዳ ፓርክ መርቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፣ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን መቻሉን ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየተገነባች መሆኑን አስታውቀዋል።

መንግሥት በየቀኑ ይህንን ተስፋ ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
#ጋዜጣ_ፕላስ #አራዳፓርክ #EthiopiaDelivers
👍43😁1
ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጎብኝቻለው።

‎ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው።

‎በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ ነው። ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልም ፈጥሯል።

‎በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሃገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም ፈጥሯል።

በኢንደስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
10🔥5
በአፍሪካ የመጀመሪያው የከተሞች ማውንቴን ባይክ ዓለም አቀፍ ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
2
የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረትና የሚጨበጥ ውጤት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

‎በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው። ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል።

ይኸውም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት አመታት ከ2,800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፤ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርት ከ4.85 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በማዳን ተረጋግጧል።

ኤክስፖው ከመላው የሀገሪቱ የተወጣጡ ንቁ አምራቾችን እና ስታርትአፖችን በጨመረ ዐቅም በአንድነት አሰባስቧል።

‎በጋራ በመሆን ይህንን ጠንካራ መነቃቃት በማስቀጠል፣ ለሚመጣው ትውልድ ጸኑ፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እንገነባለን።

‎ታላቅ የነበርን ይበልጥም ታላቅ እንሆናለን!

#EthiopiaDelivers #MadeInEthiopia
1