Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
337 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬርን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀበሉ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል።

የሁለቱ መሪዎች ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነቶችና የወል የትብብር መስኮችን በማጠናከር ላይ እንደሚያጠነጥን ይጠበቃል። ጉብኝቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባባ መግግባባታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈትቤት ገልጿል። #PMOEthiopia
👍1
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
2
ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ጋር ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል።

የሁለቱን ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥነ ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብርና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
3👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡ ግዙፍ ፋብሪካዎችን መረቁ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂንና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል።

በዛሬው ዕለት የተመረቁ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅንና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርቧሉ።

የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂና የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
#EthiopiaDelivers #PMOEthiopia #solarenergy #greenenergy #ታዳሽኃይል
👍31
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሞዛምቢኩ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ደማቅ አቀባበል አደረጉ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሞዛምቢክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

‎የፕሬዝደንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። #PMOEthiopia #Mozambique #diplomacy #ዲፕሎማሲ #redsea #Tradein
👍71
ሚኒስቴሩ ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የሚውሉ 92 የኤሌክትሪክ ገልባጭ መኪኖችን ስራ አስጀመረ
+++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 92 የኤሌክትሪክ ገልባጭ መኪኖችን ስራ አስጀምሯል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ መኪኖች የመተካት ስራ በከፍተኛ ፍጥነት እያከናወነች ነው፡፡

ይህም ሀገሪቱ ከነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ ለዘላቂ ልማትና ለታዳሽ ኃይል የሰጠችውን የላቀ ትኩረት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስና የዜጎችን የትራንስፖርት ወጪ ለመቆጠብ ጭምር እየሰራች እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

አዲስ የገቡት የኤሌክትሪክ ገልባጭ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እንደሚውሉ ገልጸዋል፡፡

መኪኖቹ ከቀረጥ ነጻ የገቡ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው÷ ሲሲሲሲ የተሰኘ የቻይና ካምፓኒ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
5