Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
337 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"የትምህርት ስርዓቱ ከአቋራጭ መንገድ ተላቆ በብቃት ላይ እንዲመሰረት እየተሰራ ነው"
- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
++++++++++++++
#ጋዜጣ-ፕላስ | በትምህርት ዘርፉ በአቋራጭ ዲግሪ የማግኘት የተሳሳተ አመለካከትን በመለወጥ በትክክለኛ እውቀትና ጥረት ላይ የተመሰረተ ትውልድ ለመገንባት ቁርጠኛ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ።

የ100 ቀናት የመንግስት የስራ አፈጻጸም ግምገማን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ቀደም ባሉት ዓመታት የትምህርት ጥራትና የዘርፉ ታማኝነት በእጅጉ ተጎድቶ ቆይቷል።

ትምህርት በአቋራጭ የሚገኝ ተደርጎ መወሰዱ ያልተማሩ ሰዎችን በወረቀት ብቻ ተምረዋል ለማለት የሚያስገድድ መጥፎ ውጤት አስከትሎ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር የትምህርት ቤቶችና የዩኒቨርሲቲዎች ፈተና ጥብቅ እንዲሆን በማድረግ ተማሪዎች ውጤት ማግኘት የሚችሉት ሰርተውና አጥንተው ብቻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ስርአት መዘርጋቱን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ዲግሪ ሲሰጡ ግለሰቡ በዘርፉ በቂ እውቀት እንዳለው ማረጋገጫ መሆን እንዳለበት የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ የውሸት ዲግሪ ማተም የህብረተሰቡን መሰረት ያናጋል ብለዋል።

በፈተናዎች ላይ የተደረገው ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሪያ ላይ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም አሁን ላይ ተማሪዎች ወደ ጥናት ቤተሰቦች ደግሞ ልጆቻቸውን ወደ ማበረታታት መመለሳቸውን ጠቁመዋል።

የተማሪዎችን ተሳትፎና የትምህርት አቀባበልን ለማሳደግ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም የሚደርግላቸው ተማሪዎች ቁጥር ወደ 8 ሚሊዮን ማደጉንም ገልጸዋል።

ከለውጡ በፊት 4 ሺህ አካባቢ የነበረው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ወደ 34 ሺህ ማደጉን አስታውቀዋል።

በዚህ ዓመትም ምንም አይነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በሌለባቸው 626 ወረዳዎች ውስጥ 1 ሺህ 452 አዳዲስ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት አዲስ ኢኒሼቲቭ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን አመላክተዋል።

ይህም ከተማና ገጠር ሳይለይ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ልጅ እኩል የትምህርት ዕድልን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
👍3
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬርን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀበሉ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል።

የሁለቱ መሪዎች ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነቶችና የወል የትብብር መስኮችን በማጠናከር ላይ እንደሚያጠነጥን ይጠበቃል። ጉብኝቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባባ መግግባባታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈትቤት ገልጿል። #PMOEthiopia
👍1
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
2
ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ጋር ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል።

የሁለቱን ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥነ ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብርና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
3👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡ ግዙፍ ፋብሪካዎችን መረቁ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂንና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል።

በዛሬው ዕለት የተመረቁ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅንና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርቧሉ።

የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂና የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
#EthiopiaDelivers #PMOEthiopia #solarenergy #greenenergy #ታዳሽኃይል
👍31