Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
337 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኮፕ32 አስተናጋጅ እንደሆነ ሀገር፤

ኢትዮጵያ ‎ብሔራዊ ኮሚቴ በይፋ በማቋቋም ዝግጅቷን ቀደም ብላ ጀምራለች። ይህን ሂደት በግልጽ ግብና በላቀ ምልከታ ለመምራት ቁልፍ አመራር መድበናል። ይህን ተከትሎ የኮፕ ፕሬዝደንት መዋቅር የተቀናጀና የላቀ ውጤት የሚያስገኙ የቅድሚያ ተግባራቱን ጀምሯል።

ዛሬ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበረን ስብሰባ፤ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ የእስካሁን ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ሁሉም ጥረቶቻችን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተዳሷል።

በመድረኩ ከግምገማ ባሻገር የጋራ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠንበታል። ትኩረታችን ግልጽ ነው፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልህቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው።

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
4
ሆርሙዝ ወሽመጥ ለንግድ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ክፍት መሆኑን ኢራን አስታወቀች
++++++++++++++

በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺ አስታውቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገፃቸው እንዳሰታወቁት በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል ንግድ መርከቦች እንዲያልፉ ሙሉ ለሙሉ ክፍት ተደርጓል ብለዋል።

​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሸመጥን መተላለፊያ ሙሉ በሙሉ ለንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑንና ለጉዞ ዝግጁ በማድረጓ አመሰግናለሁ ብለዋል።

ይህም ርምጃ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቅናሽ ማሳየቱንና ለንግድና ለቀጠናው መረጋጋት ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል።

በአረቡ ሙህየ

#የሆርሙዝ_ወሽመጥ #ኢራን #የንግድ_መርከብ #መካከለኛው_ምስራቅ #HormuzStrait #GlobalTrade
👍63
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
5
እንደ ሀገር ትኩረት ሰጥተን እየሰራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ስራችን ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል።

የተገኘው ጅምር ውጤት፤ ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን እውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍62👎1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ መርሃግብር አካል የሆነውን የሀሮ ደንዲ ሎጅን ዛሬ በይፋ መርቀዋል። የደንዲ ሐይቅን ቁልቁል የሚመለከተው የሥነ-ምህዳር ቱሪዝም ልማት፣ ኢትዮጵያ ለከፍተኛ እና ዘላቂ የቱሪዝም ዘርፍ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
‎ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ያለመችውን ዳር እንደምታደርስ ህያው ምስክር ነው!

‎ሀገራችን ተፈጥሯዊ ውበቷን ካልተቆጠበ ጥረት ጋር በማቀናጀት፣ የራሷን መጻኢ ዕድል በራሷ የመገንባት ዐቅም እንዳላት በድጋሚ በተግባር ያረጋገጠችበት ስኬት ነው።

#VisitEthiopia #EthiopiaDelivers #PMOEthiopia
13👎2
ዛሬ ጠዋት የአውሮፓ ኅብረት የአለምአቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላን አግኝቼ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር ተወያይተናል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
3