በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና ጥላ ውስጥ በሚገኙ ቤተ-እምነቶች ያሉ ክርስቲያኖች የትንሳኤን በዓል በተስፋ፣ በመስዋዕትነት እና በአዲስ መነሳት መንፈስ በአንድነት ያከብራሉ።
ከሳምንታት የፆም፣ ጥሞና እና ራስን የመመልከት ጊዜ በኋላ ፋሲካ በእውነተኛ አምልኮ፣ መንፈስን አድሶ፣ ቤቶችንም በደስታ ይሞላል። በዘመድ አዝማድ መጠያየቅ እና ማዕድ መካፈልም ፍቅርን ያዳብራል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓመታዊውን የፋሲካ መዐድ ማጋራት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአንድነት ፓርክ በጋራ መታደማቸው ለእውነተኛው የአንድነት መንፈስ ጉልህ ማሳያ ነው።
በዓለ ትንሳኤው በመላው ኢትዮጵያ የእምነት፣ ቤተሰባዊነት እና የመታደስ መንፈስ የሚታይበት ጊዜ ነው። ሁላችንም በዚህ የትንሳኤ መንፈስ ዛሬም፣ ነገም፣ ሰርክ ቤታችንን፣ ልባችንንም ለተቸገሩ ወገኖች እንክፈት! መልካም በዓል።
#PMOEthiopia

❤6👎1🥰1
የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።
የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6/ 2018 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።

❤1
በነጻ የንግድ ቀጣና ውስጥ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የገቢ ግብር ነጻ መብት ተፈቀደ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብዓቶችንና ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች፣ በዘርፉ ያለባቸውን የፋይናንስ ጫና ለማቃለል ሲባል ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ እንቅፋት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፣ የግብዓት አቅርቦት ችግርና የባለሙያ እጥረት በዋነኛነት የሚጠቀሱ መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።
በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል ብሏል።
በዚህም መሠረት ግብዓቶችና ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ፣ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥና ታክስ ውስን በሆነው ካፒታላቸው ላይ የሚያሳድረውን ጫና ማቃለል አስፈላጊ ሆኖ እንደተገኘ አትቷል።
ለዚህም ሲባል አስመጪዎች ግብዓቶችንና ምርቶችን ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ አገር አስገብተው ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ክፍያ የሚፈጽሙበት የነጻ የንግድ ቀጣና አሠራር የተዘረጋ ሲሆን፤ ይህም አስመጪዎች ምርቶችን ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ አስገብተው ገበያ ሲያገኙ ብቻ እንዲከፍሉ የሚያስችል ነው።
እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጣናዎች ባለሀብቶችን የበለጠ የሚስቡ እንዲሆኑ ለማድረግም፣ በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል።
አሠራሩ የአስመጪዎችን ካፒታል በማንቀሳቀስ ረገድ ያለውን ጫና በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፤ ሥርዓቱን የሚያስፈጽሙ ነጻ የንግድ ቀጣናዎችም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተቋቁመው ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል።

4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ከተረጂነት ወደ ትርፍ አምራችነት ተሸጋግረዋል
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ባለፉት ዓመታት በግብርናው መስክ በተከናወኑ ተግባራት ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከተረጂነት ተላቀው ወደ ትርፍ አምራችነት መሸጋገራቸውን የግብርና ሚኒስትር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አዘጋጅነት “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ዴአታ ፍቅር ረጋሳ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ግብርና በዝናብ ጥገኝነት ላይ የተመሠረተ ስለነበረ፤ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።
የግብርናው ዘርፍ ከአምስቱ የኢኮኖሚ ማዕዘናት አንዱ በማድረግ ታሪክ ቀያሪ የሆኑ ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ ተደርገዋል ያሉ ሲሆን፤ ኢኒሼቲቮቹ የምግብ እና ሥነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፤ ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት፤ የወጪ ንግድ አቅም ማሳደግ እና የሥራ ዕድሎችን መፍጠር ዓላማ ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት በእርሻ እና እንስሳት ዘርፍ የተገኘው ውጤት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል ያሉት ሚኒስትር ዴታው፤ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በመሥራት የድርቅ ተጋላጭነትን የመቀነስ እና የመስኖ አውታሮችን በብዛት የመገንባት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሚኒስትር ዴታው ማብራሪያ፤ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በሚል በተከናወነው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ከችግር መላቀቅ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ጥረት በማገዝ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ ይገኛሉ። እነዚህ ስራዎች በዓለም አቀፍ መድረኮች ለኢትዮጵያ እውቅና እያስገኙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በአብዱረዛቅ መሐመድ

😁3❤1
የባሕር በር ጉዳይ የሁሉም ፓርቲዎች የጋራ አቋም ሊሆን ይገባል
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የባሕር በር ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነት የማያሳዩበት ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አዲስ መሀመድ ገለጹ።
ሥራ አስፈጻሚዋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ወደብና የባሕር በር ያላትን ሀገር የመረከብ ፍላጎት በሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋምና የጋራ አጀንዳ ነው፡፡
በአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ፓርቲዎች በጉዳዩ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ጠቁመው፤ የባሕር በር ጉዳይ በፖለቲካ አቋም ምክንያት ልዩነት የማይታይበትና የሁሉም ፓርቲዎች የጋራ አቋም ሊሆን የሚገባው ቀዳሚ ሀገራዊ ጥቅም ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ያጣችበት የታሪክ አጋጣሚ በሕግ ሚዛን ሊታይ እንደሚገባ የገለጹት ወይዘሮ አዲስ፤ የባሕር በሮች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶችና ስምምነቶች ሊመረመሩ የሚችሉበት አግባብ መኖሩን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ መነሻ፣ ማስረጃና የባሕር በሩን ስትጠቀምበት የነበረበትን አግባብ በአግባቡ ካቀረበች፣ በማንኛውም ዓለም አቀፍ የክርክር መድረክ የማሸነፍ ዕድሏ ሰፊ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
መንግሥት አሁን የጀመራቸውን የዲፕሎማሲ አማራጮች አጠናክሮ እንዲቀጥልና በታሪካዊ መብቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራም መክረዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች አርስ በእርስ ጣት ከመቀሳሰር ወጥተው ሀገራዊ ጥቅሞች ዙሪያ መመካከራቸው ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውም ሆነ ለብሔራዊ መግባባት ትልቅ መሠረት እንደሚጥል አስረድተዋል፡፡
በሳሙኤል ወንደሰን

❤8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ያደረጉት ጉብኝት
#ኢትዮጵያ #ቴክኖሎጂ #ላይቤሪያ #አፍሪካ #DigitalTransformation #Liberia #AfricaInnovation

"የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ፓውሎ ራንገልን አግኝቼ፤ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንንና ቀጣይ ትብብሮችን በምናጠናክርባቸው ቁልፍ መስኮች ዙሪያ መክረናል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)