Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ
++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ጉብኝትና ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

#ጋዜጣ_ፕላስ #PMOEthiopia #diplomacy #bilateral #Burundi #ETH
4👏4
የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው አካል በሆነው በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየም ጉብኝት አድርገዋል። በታላቁ ቤተ-መንግስት ጣሪያ ስር የተገናኙት ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት፤ በአፍሪካውያን የተጻፈውን ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ በጋራ ዘክረዋል! #PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ታድመዋል። በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃና ኢነርጂ፣ በግብርና ፣ በንግድ ፣ በዲጂታል መታወቅያ እና በቱሪዝም ዘርፎች የተፈረሙት እነዚህ ሁሉን አቀፍ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ ናቸው። እነዚህ የመግባቢያ ስምምነቶች የሁለቱን ሀገራት ሰፊ አቅም በመደመር ወደ ብልጽግና ለምናደርገው የጋራ ጉዞ መሠረት የሚጥሉ ናቸው።

#PMOEthiopia
👍1👎1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቡሩንዲ ፕሬዝደንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን ከሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝታቸው በኋላ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሸኝተዋቸዋል።
#PMOEthiopia
1