Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ አመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማና ውይይት ተደርጓል። #PMOEthiopia
🤔2
አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።

አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፤ በአፍሪካ ህብረትና በተባባሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን መሠራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011ዓ.ም ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይም ልዩ አማካሪም ነበሩ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአምባሳደር ቆንጂት ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል።
2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
++++++++++++++++

ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።

አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል፣ ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው። ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን። ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለመላ ኢትዮጵያውያን መጽናናት እመኛለሁ ብለዋል ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ።
4👏1
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9)እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደርን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን ለአንድ ዓመት ሹመታቸውን አራዝመዋል፡፡ #PMOEthiopia
7🤔2
ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ
++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ጉብኝትና ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

#ጋዜጣ_ፕላስ #PMOEthiopia #diplomacy #bilateral #Burundi #ETH
4👏4
የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው አካል በሆነው በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየም ጉብኝት አድርገዋል። በታላቁ ቤተ-መንግስት ጣሪያ ስር የተገናኙት ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት፤ በአፍሪካውያን የተጻፈውን ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ በጋራ ዘክረዋል! #PMOEthiopia