Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
331 videos
7 files
5.79K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"በሀገር ውስጥ መድኃኒትን የማምረት አቅም ወደ 44 በመቶ አድጓል”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በሀገር ውስጥ መድኃኒትን የማምረት አቅም ወደ 44 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባውን እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀውን የምርምር ማዕከል መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ እንደ መኪና እና አውሮፕላን ያሉ ቴክኖሎጂዎች ባይኖሩ ሀገር ልትቀጥል ትችላላች።

ምግብ፣ ልብስ እና መድኃኒት ግን የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች በመሆናቸው በእነዚህ ዘርፎች ራስን አለመቻል የሀገርን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከት አስገንዝበዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ በወቅቱ ያስከተለው ተግዳሮት እና መድኃኒት ከውጭ ለማግኘት የነበረው አዳጋች ሁኔታ፣ ኢትዮጵያ በእነዚህ ሦስት ቁልፍ ዘርፎች ራሷን ለመቻል ቁርጠኛ አቋም እንድትይዝ ትልቅ መነሳሳት መፍጠሩን አስታውቀዋል።

በባለፉት ጥቂት ዓመታት በመድኃኒት ምርት ዘርፍ ለውጥ መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሀገር ውስጥ የሚመረተው መድኃኒት ከ8 በመቶ ወደ 44 በመቶ ማደጉን ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚመረቁ አዳዲስ ፋብሪካዎች ደግሞ ይህንን አቅም ከ50 እስከ 55 በመቶ እንደሚያደርሱት ጠቁመዋል።

አዲሱ የምርምር ማዕከል በላቀ የላብራቶሪ ምርምር የኢትዮጵያን የመድኃኒትና የክትባት ማምረት አቅም እንደሚያሳድገው እና ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በዘርፉ ያቀደችውን ራስን የመቻል ግብ ለማሳካት ትልቅ መሠረት እንደሚሆን አመላክተዋል።

የምርምር ማዕከሉ ያለው የቴክኖሎጂ ብቃት፣ የሰው ኃይል መነሳሳት እና የተቋሙ ውበት ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸው፣ ምርምሮች ወደ ገበያ ወጥተው የዜጎችን ሕይወት እንዲታደጉ አደራ ብለዋል።

በሄለን ወንድምነው

++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ጤና #ራስን_መቻል #ሉዓላዊነት
2
"በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በአዲስ ስፖርት ፓርክ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

#የጀግኖቻችን_ታሪክ #OlympicLegacy #የኢትዮጵያ_ጀግኖች #ChampionsPark #አዲስ_ስፖርት_ፓርክ
#NextGenerationAthletes
8