Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
331 videos
7 files
5.79K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደረግ ይገባል

+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ ፕላስ | በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ የሚያዝያ ወር ከሌሎቹ የበልግ ወራት አንጻር የዝናብ መጠኑም ሆነ ስርጭቱ የሚሰፋበት ወቅት ሲሆን፤ በርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

ከሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የተሻለ እርጥበት መኖሩ የበልግ አብቃይ አካባቢዎች ለሚያከናውኑት የግብርና እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር የተመላከተ ሲሆን፤ አርሶ አደሮች፤ አርብቶ አደሮችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለግብርና ስራ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

በሄለን ወንድምነው

+++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት#ጋዜጣ_ፕላስ #ሜቲዎሮሎጂ #ኢትዮጵያ #የአየር_ትንበያ #ጥንቃቄ
በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ዛሬ መርቀን ከፍተናል። ‎በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው።

የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን አካትቷል። በተጨማሪም ተቋሙ ለድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ የመስጠት አቅምን በመገንባት ረገድ እንደ ማገር ሆኖ ያገለግላል።

‎ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍2
"ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
+++++++++++++

የከተማችንን እድሳት ለማፋጠንና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል።

በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል።

የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል።

‎የእውነተኛ ልማት ማዕከል ማህበረሰቡ ላይ መሆን አለበት! ይህ ፕሮጀክት ከላቀ የስፖርት አገልግሎት ባለፈ፣ በልማቱ ምክንያት ለተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ አቅም የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆችን እንዲሁም 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ ይዟል።

በአንዴ 300 መኪናዎችን የሚይዝ ባለ ሁለት ወለል የምድር ቤት መኪና ማቆሚያ ያለውና ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር የተሳሰረው ይህ ፓርክ፤ ንፁህና ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የጀመርነውን ቁርጠኝነት ጉልህ ማሳያ ነው። ‎

ታላቋን ኢትዮጵያ ማለም ብቻ ሳይሆን በተግባር እንገነባታለን!

#አዲስ_ስፖርት_ፓርክ #ታላቋ_ኢትዮጵያ #የጀግኖች_ታሪክ #የከተማ_እድሳት #በተግባር
2😁1