Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
332 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ይፋ አደረገ
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመካካለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነትና አለመረጋጋት በሀገራችን የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት የሚከተላቸውን አቅጣጫዎች በተመለከተ ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን የሚከታተል፣ እርምጃ የሚወስድና የነዳጅ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፍች የሚለይ ልዩ ክፍል መቋቋሙንም ይፋ አድርገዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነትና አለመረጋጋት በሀገራችን የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።

በጦርነቱ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጦርነቱ በፊት የአንድ በርሜል ነጭ ናፍጣ ዋጋ 80 ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 230 ዶላር መድረሱን ቤንዚንም ከ70 ወደ 150 ዶላር ማሻቀቡን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የነበራት የረጅም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል በጦርነቱ ምክንያት መስተጓጎሉንና አቅራቢ ሀገራቱ ምርቱን ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን አስታውሰዋል።

በዚህም ምክንያት በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን ጠቅሰዋል።

በጦርነቱና አለመረጋጋቱ ምክንያትም በነጭ ናፍጣ ላይ የነበረው የቀን አቅርቦት ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4 ነጥብብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለቱን ጠቁመዋል።

የተለያዩ ሀገራት ያጋጠማቸውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ተከትሎ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እቀባዎችን እያደረጉ መሆኑን ገልጸው፥ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው መርህ ግን ከህዝቡ ጋር በመተባበር ችግሩን በጋራ ለመሻገር መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግሥት የተፈጠረውን የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይገቱ ነዳጅን ከተጓዳኝ ገበያ ስለሚገዛና የዓለም የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት በሦስት እጥፍ ዋጋ እየገዛ ለማቅረብ መገደዱን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም፣ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በነጭ ናፍጣ ላይ በአንድ ሊትር 95 ብር፣ በቤንዚን ላይ ደግሞ 42 ብር ድጎማ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

እስካሁን 262 ቢሊዮን ብር ገደማ ድጎማ ማድረጉን በማንሳት የተደረገ ሲሆን፣ በየወሩም ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለድጎማ እየተመደበ መሆኑ ጠቅሰዋል።

ያጋጠመው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በሀገርና በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና እንዳያሳድርና በፍትሐዊነት ለመምራት መንግሥት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቅድሚያ አሰጣጥ ውሳኔ ማሳለፉን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሠረት

1. ነዳጅ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በማደያ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው

2. ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች በቀጥታ ፣

3. ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ፣

4. የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች

5. ግብርናን የሚያዘምኑ ትራክተሮች፣

6. የከተማና ሀገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች

7. እንዲሁም በናፍጣ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቅድሚያ እንዲያገኙ የሚያደርግ የቅድሚያ የነዳጅ አጠቃቀም አሠራር የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ውጭ የሚደረግ የነዳጅ ስርጭት ተገቢ ባለመሆኑ እርምጃ ይወሰዳል ያሉት ሚኒስትር፥ ይህንን ውሳኔ በአግባቡ ለማስፈጸም በቅንጅት እንደሚሠራም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል መንግሥት የፌደራልና የክልል ተቋማትን ያካተተና ስርጭቱን 24/7 የሚከታተል የሁኔታዎች ልዩ የመከታተያ ክፍል ማቋቋሙን ይፋ አድርገዋል።

ልዩ የመከታተያ ክፍሉ በማዕከል የሚመራ ሲሆን የነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭትና አጠቃቀምን የሚከታተል፣ ውሳኔዎችን የሚየቀርብና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የሚለይ መሆኑን ተናግረዋል።

በነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ዙሪያ ሕገ-ወጥ ድርጊት የፈጸሙ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ 658 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከ720 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተይዞ ለመንግሥት ገቢ ሆኗል ብለዋል።

ከህብረተሰቡ የሚከጠበቁ ተግባራትን ይፋ ያደረጉ ሲሆን በዚህም መሠረት፦

1) ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀም፣

2) የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ስልትን መከተል፣

3) የእግር ጉዞ ባህልን ማጎልበት

4) አላስፈላጊ የጉዞ ፕሮግራሞችን መሰረዝና ማቆም

5) የሕዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም

6) በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ረገድ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።
3
የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ህንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13.1 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርሟል።

በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው። የውጭ ምንዛሬ ተመን ሊበራላይዜሽንና የባንክና ቴሌኮም ዘርፎችን ለንግድ ማህበረሰቡ ክፍት ማድረግ የመሳሰሉ ቆራጥ እርምጃዎች ግልጽና ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መፍጠራቸውን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ይህም በዘመናዊ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አማካኝነት ለዓለም አቀፍ ገበያ ምቹ መዳረሻን ፈጥሯል።

‎ይህ ዕድገት በሁሉም ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በግልጽ እየታየ የሚገኝ ሲሆን፤ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የተንተራሰው የሀገራችንን የታዳሽ ኃይል ሀብትን በመጠቀም በሶላር ምርትና በሃይድሮጅን ፕሮጀክቶች ላይ የተገኘው እመርታ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የማዕድን ዘርፍ ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራበት ይገኛል።

የኢንዱስትሪ ዕድገታችን አዲስ በሚገነቡት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እየተፋጠነ ሲሆን፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በልህቀት እየተመራ ይገኛል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስርና በባህላዊ ቅርሶቻችን የታጀበችው ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ሆናለች።

ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለላቀ አጋርነት እንጋብዛለን፤ ኢትዮጵያ ከነበረው እጅጉን በተሻለ ለንግድ ዝግጁ ናት!

#InvestInEthiopia #EthiopiaDelivers
#PMOEthiopia
5
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች
2👎2👏1
ስምንት ዓመታት፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር ወደ ዘመናዊ እና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚ

#EthiopiaDelivers #PMOEthiopia
3🔥1😢1
ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

ባለፉት የሪፎርም ዓመታት ሕገ መንግሥታዊነትን ለማረጋገጥ፣ የመብቶችን ጥበቃ ለማስፋትና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚያስችሉ ሰፋፊ የሕግና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተደረጉ ሲሆን በዚህ ሒደት ከተለዩት ቁልፍ ሕጎች መካከል አንዱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት የሕግ መድብሉ ነው።

የ1954 የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው።

#EthiopiaDelivers #PMOEthiopia
የአማራ ክልል ምክር ቤት 1ሺህ 224 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ

++++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛው ዙር 5ኛ ዓመት 9ኛው መደበኛ ጉባኤ ለ1 ሺህ 224 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ ፍትህ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) የይቅርታ አሰጣጡን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የይቅርታ ቦርዱ ካቀረባቸው 1 ሺህ 463 ታራሚዎች መካከል መስፈርቱን ሙሉ በሙሉ አሟልተው የተገኙ 1 ሺህ 224 ታራሚዎች ከእስር እንዲፈቱ ምክር ቤቱ ወስኗል።

ታራሚዎቹ ይቅርታ የተደረገላቸው በእስር ቆይታቸው የታረሙ በመሆናቸው በመረጋገጡ፣ ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንደሚችሉ በመታመኑ እና አንድ ሶስተኛ ወይም ሁለት ሶስተኛ የሚሆነውን የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው እንደሆነ ተልጧል።

በሴቶችና በሕፃናት ላይ የመድፈር ወንጀል የፈጸሙ፣ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው፤ እርቅ ያልፈጸሙና ካሳ ያልከፈሉ ታራሚዎች በይቅርታው አለመካተታቸውን ኃላፊው አብራርተዋል።

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፊርማ አማካኝነት አስፈላጊው ደብዳቤ ተጽፎላቸው በቅርቡ ከእስር እንደሚለቀቁ ተገልጿል።

በሙሉጌታ ምህረት

++++++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት# ጋዜጣ-ፕላስ# አማራ ክልል# ፍትህ# ታራሚዎች#ይቅርታ#
2👍1
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
4👍1
በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደረግ ይገባል

+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ ፕላስ | በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ የሚያዝያ ወር ከሌሎቹ የበልግ ወራት አንጻር የዝናብ መጠኑም ሆነ ስርጭቱ የሚሰፋበት ወቅት ሲሆን፤ በርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

ከሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የተሻለ እርጥበት መኖሩ የበልግ አብቃይ አካባቢዎች ለሚያከናውኑት የግብርና እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር የተመላከተ ሲሆን፤ አርሶ አደሮች፤ አርብቶ አደሮችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለግብርና ስራ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

በሄለን ወንድምነው

+++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት#ጋዜጣ_ፕላስ #ሜቲዎሮሎጂ #ኢትዮጵያ #የአየር_ትንበያ #ጥንቃቄ
በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ዛሬ መርቀን ከፍተናል። ‎በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው።

የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን አካትቷል። በተጨማሪም ተቋሙ ለድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ የመስጠት አቅምን በመገንባት ረገድ እንደ ማገር ሆኖ ያገለግላል።

‎ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍3