Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያ አምስት የባሕር በሮች እንዲኖሯት እንደሚሠራ ነእፓ አስታወቀ
+++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሀገሪቱ ያሏትን ሀብቶች በሰጥቶ መቀበል መርህ በመጠቀም ኢትዮጵያ አምስት የባሕር በሮች እንዲኖሯት ስትራቴጂ ነድፎ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

ፓርቲው ይህን ያለው 7ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ባከበረበትና ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ያዘጋጀውን የቃል ኪዳን ሰነድ (ማኒፌስቶ) ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

የፓርቲው የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ነቢሃ መሐመድ ሰነዱ በቀረበበት ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በርካታ ሀብቶች ያሏት በመሆኑ፣ እነዚህን መሠረት በማድረግና በሰጥቶ መቀበል መርህ አምስት የባሕር በሮች እንዲኖሯት ለማድረግ ፓርቲው በትኩረት ይሠራል።

ኃላፊዋ አክለውም፤ ከባሕር በር በተጨማሪ ሀገሪቱ ያሏትን የውኃ ሀብቶች በአግባቡ መጠቀም እንድትችል ፓርቲው ስትራቴጂ መንደፉን አስረድተዋል።

የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖረው ግንኙነት ሰላማዊ፣ ሚዛናዊና ባለብዙ ወገን እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑንም አመላክተዋል።

ነእፓ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም መሠረት ያደረጉ ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚሰጥ ያነሱት ነቢሃ፤ በተጨማሪም በቀጣናው ያሉ ጂኦ-ፖለቲካዊ ችግሮችን በመፍታት ለጋራ ተጠቃሚነት እንደሚሠራ አብራርተዋል።

ይፋ የተደረገው የፓርቲው የቃል ኪዳን ሰነድ በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች የተደራጀ ሲሆን፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮችንና የውጭ ግንኙነትን በዝርዝር የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ነእፓ #ምርጫ #የባሕር_በር #ፖለቲካ #ማኒፌስቶ
👍7🤣42🤔2
“ከተሞች የሀገር መኳያ እና የአብሮነት ቤተሙከራዎች ናቸው”

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ከተሞች የሀገር መኳያ፣ የስልጣኔ መስታወት እና የአብሮነት ቤተ-ሙከራዎች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተሞች በአዲስ ምናብ በሚል ርዕሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ የከተማ ልማት የለውጥ ሥራዎችን በተመለከተ ከቃና ቴሌቭዥን ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ቆይታ እንዳሉት፣ ቀደም ሲል ከተሞችን እንደ ስጋትና ነዋሪዎቻቸውን እንደ ወላዋይ የመመልከት የተሳሳተ ዝንባሌ ተቀይሮ፣ አሁን ላይ ከተሞች የሀገር ዕድገት መለኪያና የስልጣኔ መስታወት ተደርገው በትኩረት እየተሠራባቸው ነው፡፡

ከተሞች የሀገር "እጅና አእምሮ" የሆኑና ግማሹ የሀገር ኢኮኖሚ የሚንቀሳቀስባቸው በመሆኑ፣ ከተማን ያገለለ የብልጽግና ጉዞ ሊሳካ እንደማይችል አስረድተዋል።

ከተሞች ለዘመናዊ ፈጠራ፣ ለውጥና ቀልጣፋ አሠራር መገኛ ከመሆናቸው ባለፈ፣ የአንድ ሀገር ስልጣኔና ዕድገት የሚለካው በከተሞቿ ውበትና ስልጣኔ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ከተማ ከተለያየ አካባቢ የመጡ ዜጎች በቋንቋ፣ በባህልና በሃይማኖት ሳይገደቡ በጋራ የሚኖሩባትና አብሮነት በተግባር የሚታይባት ስፍራ በመሆኗ፣ ሀገርን ለመገንባት እንደ ትልቅ መነሻ እንደምትወሰድም አክለዋል።

የከተማ ነዋሪ ለለውጥ ዝግጁ፣ ጥሮ ግሮ ለመለወጥ የሚተጋና ችግር ፈቺ በመሆኑ፣ መንግሥት የከተማውን ነዋሪ እንደ ዋና ማኅበራዊ መሠረት በመውሰድ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

ከተሞች የሀገር መኳያ መገለጫ በመሆናቸው፣ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞችን ውብ በማድረግ የሀገርን ክብርና ውበት ከፍ ለማድረግ የተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
4
"የኮሪደር ልማት በርካታ በሥራ የተፈተኑ ኢንጂነሮችን ፈጥሯል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር በሥራ የተፈተኑ በርካታ ወጣት ኢንጂነሮችን በተግባር ማፍራት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

የኮሪደር ልማቱ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ግቦችን የያዘ መሆኑን ያነሱት ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ፕሮጀክቱ ወጣቶች ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከሚያገኙት በላይ የተግባር እውቀት እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ የአዲስ አበባን ኮሪደር ከሠሩ በኋላ፣ በክልል ከተሞች ላይ መቶ በመቶ የራሳቸውን ዲዛይን በማውጣት ሠርተው ለማጠናቀቅ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸውም አብራርተዋል።

የኮሪደር ልማቱ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከገቢ ምንጭነት በተጨማሪ፣ የዕውቀትና የክህሎት ማዳበሪያ እንዲሁም የኢኖቬሽንና ፈጠራ ማጎልበቻ መሆኑን አክለው አስረድተዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ኮሪደር_ልማት #ኢንጂነሪንግ #አዲስ_አበባ #ወጣቶች #gazetteplus
5
ከውበት አንጻር ሲታይ፣ ከተማ የሥነ-ውበት ተምሳሌት ናት። ከተሞች የአንድን ሀገር ገጽታ ይገልጻሉ። ውብ የሆነችውን አዲስ አበባን የተመለከተ ሰው፣ ስለ ኢትዮጵያ ሲያስብ ሁልጊዜ ያ ምስል በአዕምሮው ውስጥ ታትሞ ይቀራል።#PMOEthiopia
4👍2🔥2
በፅኑ መሠረት ላይ እየተገነባ ያለው ዘመናዊ ከተሜነት እና ክትመት ለትውልድ የተሻለ ኑሮ እና ለሀገር ብልጽግና መሰረት ነው
- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
+++++++++++++

ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለው መጠነ ሰፊ የከተሞችና የኮሪደር ልማት ሥራ የአገሪቱን ገጽታ ከመለወጥ ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተወሰደ ታሪካዊ እርምጃ ነው።

ከተሞች ለረዥም ዘመናት ተቆራኝቷቸው የነበረውን የጉስቁልና መልክ ከመቀየር አኳያ እና ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ማራኪ ሆነው እንዲደራጁ ማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ እና የሰው ሀይል በማደራጀት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ተችሏል።

በተለይም በአዲስ አበባ እና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉት የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ የከተማ ማደስ፣ አካባቢዎችን የማስዋብ ስራዎች፣ በመልሶ ማልማት የታሪካዊ ቦታዎች እና የቅርስ ጥገናዎች ማካሄድ እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች በጉልህ ተጠቃሾች ናቸው።

በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች ማህበረሰቡ በንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የተሻሻለ መንገድ፣ ደረጃውን የጠበቀ የጤና አጠባበቅ ስርዓት፣ ጥራት ያለው ትምህርት እና የሀይል አቅርቦት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ የተሰሩት ቅንጅታዊ ስራዎች ውጤታማ እና መንግስት ከህብረተሰቡ ይነሱ የነበሩትን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በተጨባጭ ያሳዩ ናቸው።

በሌላም በኩል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በርካታ የልማት ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከተማን የማስዋብ ስራ በስፋት ከተሰራባቸው መካከል አንዱ እና ዋነኛ ተጠቃሽ ሆኖ ይገኛል።

በተለይ ለኮሪደር ልማት እና ከተማ ማደስ ስራዎች የተሰጠው ትኩረት በኢትዮጵያ ታላላቅ ከተሞች ብቻ ሳይሆን በ78 ከተሞች ነው የተተገበረው።

የኮሪደር ልማቱ በሀገሪቷ የሚገኙትን ከተሞች ኃላ ቀር የኑሮ ስርዓት በመቀየር ዘመናዊነትን የተላበሰ የአኗኗር ስልት እንዲፈጠር ከማስቻሉም ባሻገር በአየር ንብረት ጥበቃ፣ በአመለካከት ለውጥ፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ምቹ የኑሮ አካባቢን ከመፍጠር፣ በቱሪስት መስህብነት እና ጤናማ ማህበረሰብ እንዲኖር ከማስቻል አኳያ የራሱን ትሩፋት ያበረከተ ነው።

በዚህም የዜጎችን ጥሩ የመኖር ተስፋን ያለመለመ ከመሆን አልፎ የኩራት ምንጭ ለመሆን የበቃ ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሌሎች ሀገራት ዜጎችም አድናቆት እና ምስክርነት በእጅጉ የጎላ ለመሆን በቅቷል።

የቅርስ ጥገናዎች ላይ ታሪካዊ እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የተደረገው መልሶ ማልማት ወይም እድሳት በተጠና ሁኔታ ለትውልድ ማስተላለፍ በሚያስችል እና የከተሞችን ውበት በማጉላት የቱሪዝም መስህብነታቸውን እንዲጨምሩ ያስቻለ ለመሆን አስችሏል።

በዚህም በርካታ ቱሪስቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የቆይታ ጊዜያቸውን በማራዘም ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ማግኛ መንገድ የሚሆንበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

እነዚህን የብልጽግና ትሩፋቶች አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚጠይቅ ነው የሚሆነው።

የኢትዮጵያን አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌትነት እና ርዕዩዋን ለማሳካትም የዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ከእስካሁኑ የትብብር መንፈስ በላቀ ሁኔታ አስተዋጽኦ በማበርከት የኢትዮጵያን ቀጣይ የስኬት መንገድ ዕውን ለማድረግ መረባረብ የሚገባ ይሆናል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የጀመረችው የከተማነት ብልጽግና ጉዞ መጪውን ትውልድ ታሳቢ በማድረግ ጭምር የተከናወነ ሲሆን መንግሥት የዲጂታል ቴክኖሎጂንና ዘመናዊ አሰራርን በማጣመር፣ ከተሞቻችን የቱሪስት እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከመሆን አልፈው ለነዋሪዎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ማዕከል፣ ምቹ እና የኩራት ምንጭ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል።
4
“ንጹህ ከባቢ ላይ መኖር በገንዘብ የማንለካቸውን የጤና ትሩፋቶች የሚያስገኝ ነገር ነው፡፡” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

#PMOEthiopia
3
በማኅበራዊ ሚዲያ ከሚተላለፉ ይዘቶች 25 በመቶ ያህሉ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች ናቸው

+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ ፕላስ | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በናሙና ከመረመራቸው የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች መካከል 25 በመቶ ያህሉ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች መሆናቸውን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት፤ ከየካቲት 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2018 ዓ.ም ድረስ ከፍተኛ ተከታይ ባላቸው እና ከፍተኛ ይዘቶች በሚሰራጭባቸው የፌስቡክ፣ የቲክቶክ፣ የቴሌግራም፣ የኤክስ እና የዩቲዩብ ገጾች ላይ ክትትል ተደርጓል።

በናሙናነት ከተመረመሩ 32 ሺህ ይዘቶች ውስጥ ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ይዘት ያላቸው እንደሆኑ ማረጋገጡን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች የተሰበሰቡ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ይዘቶችን በሳይንሳዊ መንገድ የመተንተን እና የመተርጎም ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ባለሥልጣኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሯ አመልክተዋል።

በሄለን ወንድምነው

++++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት@ጋዜጣ-ፕላስ#መገናኛ_ብዙኃን_ባለሥልጣን#የጥላቻ_ንግግር#ሐሰተኛ_መረጃ #ኢትዮጵያ#
3
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
5
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል
2👍1